×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፮ ፲፱፻፶፮ ዓም የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አሥረኛ ዓመት ቁጥር ፲፩ አዲስ ኣበባ - ጥቅምት ፳፯ ቀን ፲፱፻፲፮ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፲፮ / ፲፱፻፶፮ ዓም የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ገጽ ፪ሺ፬፻፵፰ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፲፮ / ፲፱፻፲ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ ፲፱፻፷፯ አንቀጽ ፭ እና የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አዋጅ ቁጥር ፫፻፲፫ / ፲፱፻፵፭ አንቀጽ ፳፬ ( ፪ ) መሠረት የሚኒስትሮች ምክር ቤት | Organs of the Federal Democratic Republic of Ethiopia ይህንን ደንብ አውጥቷል ። ክፍል አንድ አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፲፮ ፲፬፻፲፮ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ በዚህ ደንብ ውስጥ ፣ ፩ . “ ፖሊስ ” ማለት መሠረታዊ የሆነ የፖሊስ ሙያ ሥልጠና ተሰጥቶት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ተቀጥሮ የሚሠራ ነው ። ፪ . “ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ” ማለት የአዲስ ኣበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ነው ። ፫ . “ የከተማ አስተዳደር ” ማለት የአዲስ አበባ ከተማ ኣስተዳደር ነው ። ፬ . “ ኮሚሽነር ” ማለት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ነው ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ : ፰ሺ፩ ገጽ ፪ሺ፬፻፵፱ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፩ ጥቅምት ፳፯ ቀን ፲፱፻፶፮ ዓም ክፍል ሁለት ስለአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን መቋቋም ፩ . የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ከዚህ በኋላ “ ኮሚሽን ” እየተባለ የሚጠራ በዚህ ደንብ ህጋዊ ሰውነት ያለው አካል ተቋቁሟል ። ፪ • ኮሚሽኑ በሕግና በሙያ የሚኖረው ነፃነት እንደተጠበቀ ሆኖ ተጠሪነቱ ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ይሆናል ። ፫ . የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የኮሚሽኑን አደረጃጀት ፣ አሠራር ፣ ሥልጠና ፣ ወንጀል መከላከልና ምርመራ ሥራ የሚመለከቱ የፖሊሲ ፣ የስትራቴጂና የስታንዳርዳይ ዜሽን አቅጣጫዎችን ይወስናል ፣ ተግባራዊነታቸውን ይከታተላል ። የከተማው አስተዳደር የኮሚሽኑን ዕቅድና በጀት ይወስናል ፣ የኮሚሽኑን ስምሪትና የዕለት ተዕለት ሥራ ይከታተላል ። ውክልና ስለመስጠት ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ከተሰጡት ሥልጣንና ተግባሮች መካከል በዚህ ደንብ በዝርዝር የተለዩት ተግባሮች በአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን እንዲከናወኑ ለከተማው አስተ ዳደር ውክልና ተሰጥቷል ። ፭ ዓላማ የኮሚሽኑ ዓላማ በከተማው አስተዳደር ውስጥ የሀገሪቱን ሕገ መንግሥትና ሌሎች ሕጎችን በማክበርና በማስከበር የሕዝብን ተሳትፎ መሠረት በማድረግ ወንጀል በመከላከል የከተማውን ነዋሪዎች ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ ነው ። ፮ . የኮሚሽኑ ሥልጣንና ተግባር ኮሚሽኑ ፣ ፩ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፳፭ ፲፱፻፳፰ ( እንደተሻሻለ ) በአንቀጽ ፬ ለፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከተሰጡት የወንጀል የዳኝነት ሥልጣን ውጭ ባሉ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በሚነሱ ማናቸውም የወንጀል ጉዳዮች የመመርመርና የመከላከል ሥልጣን ይኖረዋል ። ፪ . በአዲስ አበባ ከተማ ቻርተር በአንቀጽ ፴፩ ንዑስ አንቀጽ ፪ መሠረት በአዲስ አበባ ከተማ ነክ ፍርድ ቤት የወንጀል እና የደንብ መተላለፍ የዳኝነት ሥልጣን ሥር ያሉ ጉዳዮችን ይመረምራል ፣ ይከላከላል ። ፫ . የከተማውን ኣስተዳደር ቻርተር በመጣስ አስተዳደሩን አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ማናቸውም እንቅስቃሴዎች ይከላከላል ፣ ፬ • በከተማው አስተዳደር ጥቅሞችና ተቋሞች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ይከላከላል ፣ ፭ የከተማው አስተዳደር ተቋማትን ይጠብቃል ፣ ፮ . ለከተማው አስተዳደር ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጥበቃ ያደርጋል ፣ ፯ . በፌዴራልና በከተማ ነክ ፍርድ ቤቶች የሚሰጠውን ትዕዛዝ ወይም ውሳኔ ይፈጽማል ፣ ፰ የወንጀል ምርመራን በተመለከተ ከፌዴራል ዐቃቤ ሕግና ከከተማ ኣስተዳደር ዐቃቤ ሕግ የሚሰጠውን ትዕዛዝ ይፈጽማል ፣ ፬ . በከተማው ደረጃ ለወንጀል መከላከልና ምርመራ ሥራ የሚረዱ ጥናቶችን ያከናውናል ፣ ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽንና ለከተማው አስተዳደር ያቀርባል ፣ ገጽ ፪ሺ፬፻፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፩ ጥቅምት ፳፯ ቀን ፲፱፻፲፮ ዓ.ም ፲ በኮሚሽኑ ሥልጣን ሥር የሚወድቁ የወንጀል መረጃ ዎችን ያሰባስባል ፣ ያጠናቅራል ፣ ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን እና ለከተማው አስተዳደር ያስተላልፋል ፣ ፲፩ ከጸጥታ አካላት ጋር የመረጃ ልውውጥና የሥራ ቅንጅት ያደርጋል ፣ ፲፪ የከተማውን የትራፊክ እንቅስቃሴ ሥርዓት ያስከብራል ፣ ፲፫ በከተማው በሚደረጉ ሕዝባዊና ሃይማኖታዊ በዓላት ፣ በስፖርትና በመሳሰሉት ዝግጅቶች የጥበቃ አገልግሎት ይሰጣል ፣ ፲፬ ውል ይዋዋላል ፣ በራሱ ስም ይከሳል ፣ ይከሰሳል ፣ ፯ • የኮሚሽኑ አቋም ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ፩ . በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር አቅራቢነት በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር የሚሾም አንድ ኮሚሽነር እና ምክትል ኮሚሽነር ፣ ፪ ኮሚሽነሩን ፣ ምክትል ኮሚሽነሩን እና የመምሪያ ኃላፊዎችን ያቀፈ የሥራ አመራር ጉባዔ ፣ እና ለሥራው አስፈላጊ የሆኑ ሌሎች ሠራተኞች ፣ ይኖረዋል ። ፰ የኮሚሽኑ የሥራ አመራር ጉባዔ የሥራ አመራር ጉባዔ ፣ ፩ . በከተማው ውስጥ ወንጀልን ለመከላከልና ለመመርመር የሚረዱ የፖሊሲና የስትራቴጂ ጥናቶችን በመመርመር ከአስተያየት ጋር ለከተማው ከንቲባ እና ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር እንዲቀርብ ያደርጋል ፣ ፪ የኮሚሽኑን አደረጃጀት ፣ አወቃቀርና አሠራር የሚመ ለከቱ ጥናቶችን ይመረምራል ፣ በጥናቶቹ መሠረት ሊወሰዱ የሚገባቸውን እርምጃዎች ከአስተያየት ጋር ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ያቀርባል ፣ • በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በሚወሰነው የፖሊስ ሥልጠና ስትራቴጂና ስታንዳርድ መሠረት የኮሚሽኑን መሠረታዊ የፖሊስ ሥልጠና ዕቅድ ያዘጋጃል ፣ እንዲጸ ድቅለትም ለከተማው አስተዳደር ያቀርባል ፣ ፬ የኮሚሽኑን ዓመታዊ ዕቅድ ሪፖርትና የሥራ አፈፃፀም ይገመግማል ፣ ከአስተያየት ጋር ለከተማው አስተዳደር ከንቲባ እና ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ያቀርባል ። ፱ . የከተማው አስተዳደር ከንቲባ ሥልጣንና ተግባር የከተማው አስተዳደር ከንቲባ ፩ . የኮሚሽኑን ሥራ በበላይነት ይመራል ፣ ይቆጣጠራል ፣ ፪ በኮሚሽኑ የቀረበለትን ዓመታዊ ዕቅድ ፣ በጀት ፣ ሪፖርትና የሥራ አፈፃፀም በሚመለከት ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የሚሰጠውን አስተያየት በማካተት ተገቢው ውሳኔ እንዲሰጥ ለከተማው ምክር ቤት ያቀርባል ፣ ፫ • የኮሚሽኑ ኣደረጃጀት ፣ የስታንዳርዳይዜሽን ፣ የሥልጠና ጥናቶች በመመርመር ከአስተያየቱ ጋር ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ያቀርባል ፣ ፬ . በከተማው ውስጥ ሕግና ሥርዓትን ለማስከበር ኮሚሽኑ ለሚያደርገው እንቅስቃሴ የከተማው ነዋሪዎች ቅንጅትና ትብብር እንዲጠናከር ያደርጋል ። ገጽ ፪ሺ፬፻፶፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፩ ጥቅምት ፳፯ ቀን ፲፱፻፲፮ ዓም ፲ የኮሚሽነሩ ሥልጣንና ተግባር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽነር ተጠሪነቱ ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ሆኖ የኮሚሽኑን ሥራ በበላይነት ይመራል ፣ ያስተዳድራል ፣ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ኮሚሽነሩ ፣ ሀ ) የኮሚሽኑን ኃላፊዎች እንዲሾሙ ከከተማው አስተዳዳሪ ጋር በመመካከር ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ያቀርባል ፣ ለ ) የኮሚሽኑን የመተዳደሪያ ደንብ ያስፈጽማል ፣ ሐ ) በፖሊስነት ከተቀጠሩት ውጪ ያሉትን የድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች በፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግ መሠረት ይቀጥራል ፣ ያስተዳድራል ፣ መ ) የኮሚሽኑን አደረጃጀት ፣ አወቃቀር ፣ አሠራር ፣ የወንጀል መከላከልና ምርመራ ሥራዎች የሚመ ለከቱ ጥናቶች እንዲከናወኑ ያደርጋል ፣ ሠ ) የኮሚሽኑን የሥራ ዕቅድ እና ረቂቅ በጀት በማዘ ጋጀት ለከተማው አስተዳደር ከንቲባ ያቀርባል ፣ በጀት ሲጸድቅም በሥራ ላይ እንዲውል ያደርጋል ፣ ቀ ) ለኮሚሽኑ በተፈቀደው በጀት መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል ፣ የኦዲትና ኢንስፔክሽን ሥራዎች እንዲሰሩ ያደርጋል ፣ ረ ) የኮሚሽኑን የሥራ አመራር ጉባዔ በሰብሳቢነት ይመራል ፣ ፲፩ የምክትል ኮሚሽነሩ ሥልጣንና ተግባር ምክትል ኮሚሽነሩ፡ የኮሚሽኑን ተግባራት በማቀድ ፣ በማደራጀት ፣ በማስተባበር ኮሚሽነሩን ይረዳል ፣ በኮሚሽኑ መዋቅር መሠረት የሥራ ክፍፍል በማድረግ ከኮሚሽኑ ዘርፎች መካከል ከፊሉን ይከ ታተላል ፣ ሐ ) ኮሚሽነሩ በማይኖሩበት ጊዜ ተክቶት ይሠራል ፣ መ ) በኮሚሽነሩ ተለይተው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል ። ምክትል ኮሚሽነሩ ተጠሪነቱ ለኮሚሽነር ይሆናል ፲፪ በጀት የኮሚሽኑ በጀት በከተማው አስተዳደር ምክር ቤት ይመደባል ። ፲፫ . ስለሂሣብ መዛግብት ፩ ኮሚሽኑ የተሟላና ትክክለኛ የሂሣብ መዛግብት | 13. Books of Accounts ይይዛል ። ፪ የኮሚሽኑ የሂሣብ መዛግብት እና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በዋናው ኦዲተር ወይም በሚሰይማቸው ኦዲተሮች በየዓመቱ ይመረመራል ። ክፍል ሦስት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ፲፬ . የፌዴራል ፖሊስ አዋጅና ደንብ ተፈፃሚ ስለመሆናቸው የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፪፻፲፫ ፲፱፻፷፭ዓም አንቀጽ ፲፭ ፣ ፲፮ ፣ ፲፮ ፣ ፲፰ ፣ ፲፱ ፣ ፳ ፣ ፳፩ ፣ ፳፬ ፣ ፳፭ ፣ ፳፮እና፳፯ላይየተመለከቱድንጋጌዎችእና የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን መተዳደሪያ ደንብ ቁጥር ፳፮ / ፲፱፻፶፭ በኮሚሽኑ ላይ ተፈፃሚነት ይኖራቸዋል ። ገጽ ፪ሺ፬፻፵፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፩ ጥቅምት ፳፯ ቀን ፲፱፻፲፮ ዓም : መመሪያ ስለማውጣት ኮሚሽኑ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ይህን ደንብ ለማስፈፀም መመሪያ ለማውጣት ይችላል ። ደንቡ የሚፀናበት ጊዜ ይህ ደንብ በነጋሪት ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ የፀና ይሆናል ። ኣዲስ ኣበባ ጥቅምት ፳፯ ቀን ፲፱፻፲፮ ዓም መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?