×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
አዋጅ ቁጥር 120/1990 ዓም የሕይወታዊ ሀብት ጥበቃናቲcኣንስቲ ትዩት ማቋቋሚያ አዋጅ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

3 . የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ራላዊ ደመካኒሳ ወ , ma . - ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አራተኛ ዓመት ቁጥር ፵፱ አዲስ አበባ ሰኔ ፲፰ ቀን ፲፱፻1 | | በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ - የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፩፻፳ / ፲፱፻፲ ዓም : የሕይወታዊ ሀብት ጥበቃና ምርምር ኢንስቲትዩት | Institute of Biodiversity Conservation and Research ማቋቋሚያ አዋጅ . . . . . . . . . . . . . ገጽ ፯፻፸፮ አዋጅ ቁጥር ፩፻፳ / ፲፱፻፲ የሕይወታዊ ሀብት ጥበቃና ምርምር ኢንስቲትዩት ለማቋቋም የወጣ አዋጅ ኢትዮጵያ ባላት የተለያየ የመልክዓ ምድር አቀማመጥና የአየር ንብረት ምክንያት ሰፊና የዳበረ የሕይወታዊ ሀብት ስብጥር የሚገኝባትና በዓለም ላይ ይህን መሰል ጸጋ ካላቸው አካባቢዎች አንዷ በመሆኗ ፡ ይህ በዕዕዋት ፡ በእንስሳትና በጥቃቅን ሕዋሳት የሚካተተው | biological potential ; የሕይወታዊ ሀብቷ ለሀገሪቱ የግብርና ፡ የኢንዱስትሪና የጤና ዘርፎች እድገት እንዲሁም ለሌሎች ማኅበራዊና ልማት ነክ ተግባራት ከፍተኛ ድርሻ ያለው መመኪያ የተፈጥሮ ሀብት የአየር ንብረት ለውጥ መከሰት : የድርቅና ምድረ በዳነት መስፋፋት የሕዝብ ቁጥር ከልማት ዕድገት ጋር ባልተመጣጠነ ሁኔታ መጨመር እንዲሁም የሕይወታዊ ሀብት ጥበቃን ያላገናዘቡ የግብርናና የኢንዱስትሪ ቴክኖሎጂዎች ተግባራዊ መሆን ፣ ይህን ሀብት መልሶ ሊተካ በማይቻል ሁኔታ እያጠፉት በመሆናቸው በዚህ የተነሳ በተፈጥሮ ሀብት ላይ የሚደርሰው ጥፋት አሳሳቢ እየሆነ በመምጣቱ ፣ በኢትዮጵያ ያለውን ሕይወታዊ ሀብት በሚገባ ለመቃኘት ፡ ለመሰብሰብ ፡ ጠብቆ በዘላቂነት ለማቆየትና ተመራምሮ ጥቅም ላይ ለማዋል ሁኔታዎችን ማመቻቸት ቅድሚያ ትኩረት ሊሰጣቸው ከሚገባቸው ለልማት አስፈላጊ ከሆኑ ተግባራት አንዱ በመሆኑ ፣ ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ : ዥሺ፩ ገጽ ፯፻፸፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፱ ሰኔ ፲፰ ቀን ፲፱፻፲ ዓም Federal Negarit Gazeta – No . 49 25 June , 1998 - Page 777 በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያ በሕይወታዊ ሀብቷ ላይ | WHEREAS , in line with protecting its sovereign rights ያላትን ሉዓላዊ መብት ከማስከበር ጐን ለጐን ሀብቱ ከዜጐቿ አልፎ ተርፎ በየትኛውም ዓለም ለሚገኝ የሰው ዘር ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ በዓለም አቀፍ ውሎች መሠረት በሚገባ ለመጠበቅ ፣ ለመንከባከብና በአግባቡ ጥቅም ላይ ለማዋል የተስ ማማች በመሆኗ ፤ የሕይወታዊ ሀብትን ጥበቃ ፣ ምርምርና አጠቃቀም በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚያከናውን ፣ የሚመራና የሚያስተባብር አካል ማዋቀር በማስፈለጉ ፣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የሕይወታዊ ሀብት ጥበቃና ምርምር ኢንስቲ | Ethiopia , it is hereby proclaimed as follows : ትዩት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፩፻፳ / ፲፱፻፶ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም ካላሰጠው በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ ፤ ፩ . “ ሕይወታዊ ሀብት ” ማለት በአንድ አካባቢ ውስጥ የዕፅዋት ፣ የእንስሳትና የጥቃቅን ሕዋሳት ዘረመሎችና ዝርያዎችክምችትና ስብጥርእንዲሁም በተደጋጋፊነትና በአንድነት የሚገኙበትን ሥርዓተ መህድር የሚያጠ ቃልል ነው ። ፪ . “ ሥርዓተ መህድር ” ማለት ሕይወት ያላቸው ስብስቦች - - ለመ ሕይወት ከሌላቸው አካላት ጋር በተስተጋብሮት ያለማ ቋረጥ በሚለዋወጥ ሂደት ውስጥ የሚኖሩበት የተፈጥሮ ሥርዓት ነው ፡ ፫ “ ዘረመል ” ማለትተወራራሽ ባህሪያትን የሚያስተላልፍ በማንኛውም ሕይወት ያለው ነገር ውስጥ የሚገኝ የኬሚካል ቅንብር ነው ፤ ፬• ቦታ ጥበቃ ” ማለት በተፈጥሮ የአኗኗር ሁኔታ ውስጥ “ በሚገኙበት አኳኋን እንዳሉ የሚፈጸም የእንስሳት ፣ የዕጽዋትና የጥቃቅን ሕዋሳት አጠባበቅ ነው ፣ ፩ “ ኢዘቦታ ጥበቃ ” ማለት ከተፈጥሮ የአኗኗር ሁኔታ ውጭ በማኖር ወሚካሄድ የእንስሳት ፣ የእጽዋትና የጥቃቅን ሕዋሳት አጠባበቅ ነው ፤ ፮ . “ ሰው ” ማለት ማንኛውም የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ | የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው ። ፫ መቋቋም ፩ የሕይወታዊ ሀብት ጥበቃና ምርምር ኢንስቲትዩት | 3 . Establishment ( ከዚህ በኋላ “ ኢንስቲትዩቱ ” እየተባለ የሚጠራ ) የሕግ ሰውነት ያለው ራሱን የቻለ የፌዴራል መንግሥት አካል ሆኖ በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ። - ፪ ኢንስቲትዩቱ ተጠሪነቱ ለኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ድርጅት ይሆናል ። ገጽ ፯፻ኞቿ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፱ ሰኔ ፲፰ ቀን ፲፱፻፲ ዓም Federal Negarit Gazeta No . 49 25 June , 1998 - Page 778 ፬ . ዋና መሥሪያ ቤት የኢንስቲትዩቱ ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ ሆኖእንደአስ I 4 . Head Office ፈላጊነቱ በማናቸውም ሥፍራ ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤት ሊኖረው ይችላል ። ፭ ዓላማ የኢንስቲትዩቱ ዓላማ የሀገሪቱ ሕይወታዊ ሀብት እንዲጠና ፣ በአግባቡ እንዲጠበቅ ፡ እንዲበለጽግና ለዘላቂ ጠቀሜታ እንዲውል ማድረግና መደረጉን ማረጋገጥ ይሆናል ። ፮ . ሥልጣንና ተግባር ኢንስቲትዩቱ የሚከትሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ፩ የሀገሪቱን የሕይወታዊ ሀብት ጥበቃ ፣ ምርምርና አጠቃቀም የሚመለከቱ የፖሊሲና የሕግ ሀሳቦችን ማመ ንጨትና ሲፈቀዱም ሥራ ላይ ማዋልና መዋላቸውን መከታተል ፤ . . በመላው ሀገሪቱ የሚገኘውን የዕፅዋት ፣ የእንስሳትና የጥቃቅን ሕዋሳት ሀብት ክምችትና ሥርጭት በመቃ ኘትና በማሰስ ለኢዘቦታ ጥበቃ የሚውሉትን መሰብሰብና ለምርምርና ለልማት ሥራዎች ጠቀሜታ እንዲውሉ ማድረግ ፤ ፫ የሀገሪቱን ሕይወታዊ ሀብት ለመጠበቅ የዘቦታና ኢዘቦታ ጥበቃ ዘዴዎችን ሥራ ላይ ማዋል ፣ . የሕይወታዊ ሀብት ጥበቃና ምርምር መርሀ ግብሮች ከፌዴራላዊና ክልላዊ የግብርና ፣ የኢንዱስትሪና የጤና ልማት ስትራቴጂዎችና ዕቅዶች ጋር የሚጣጣሙበትን ስልት መቀየስ ፤ ፭ የሀገሪቱን የሕይወታዊ ሀብት ለማበልጸግ ከሚመለከ ታቸው አካላት ጋር በመተባበር ነባር ዝርያዎችን በሀገር ውስጥ ከአንዱ ክልል ወደሌላው ባሕሪያቸው ሳይለወጥ ባሉበት መልክ ማስተዋወቅ ፣ በተለያዩ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮች ምክንያት የጄኔቲክ ሀብት የተመናመነባ ቸውን አካባቢዎች በማጥናትና በመለየት ቀደም ሲል ከተሰበሰበውና በኢዘቦታ ጥበቃ ከሚገኘው ዘር በመጠቀም መልሶ የመተካት ተግባራትን ማከናወን ፤ ፮ ሀገሪቱን በተጨማሪ የሕይወታዊ ሀብት ለማበልጸግ · እንደአስፈላጊነቱ በዓለም አቀፍደረጃ የሕይወታዊ ሀብት ከውጭ ማስመጣትና ቀደም ሲል ከሀገር የወጡትን ዝርያዎች ተከታትሎ ማስመለስ ፤ ቪ ኢትዮጵያ አባል በመሆን የተቀበለቻቸው የሕይወታዊ ሀብት ጉዳይን የሚመለከቱ ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ፣ ውሎችና ግዴታዎች በተግባር እንዲፈጸሙ ተገቢውን ጥረት ማድረግ ፤ እንዲሁም የሕይወታዊ ሀብትን በሚመ ለከቱ በአገር ውስጥና ዓለምአቀፍ ጉባዔዎች ላይ መሳተፍ ፣ ፰ ለሕይወታዊ ሀብት ጥበቃ ምርምርና ልማት የቴክኒክ | ዕርዳታና ሌላም ድጋፍ ለመስጠት ችሎታና አቅም ካላቸው ማናቸውም ወገኖች ጋር ዓለም አቀፍ ግንኙነት መመስረት ፤ ፱ የሕይወታዊ ሀብት ጥበቃ ፡ ምርምር ፣ እንክብካቤና | አጠቃቀምን በሚመለከትከሚመለከታቸው የፌዴራልና የክልል አካላት ጋር በመተባበር መሥራት ፣ ገጽ ፯፻፻፱ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፱ ሰኔ ፲፰ ቀን ፲፱፻፲ ዓ . ም Federal Negarit Gazeta – No . 49 25 June , 1998 Page 779 ፲ . ብሔራዊ የእንስሳት ቤተመዘክር እና ብሔራዊ ኸርባ ሪየም በማደራጀት ለተመራማሪዎችና ተጠቃሚዎች አገ ልግሎት መስጠት ፡ ፲፩ የሀገሪቱን ሕይወታዊ ሀብት መጠንናሥርጭት ለማወቅ ፣ ለማጥናት ፣ ለመጠበቅ ፡ ለማሻሻል ፣ ለማበልጸግና ለዘላቂ ጥቅም ለማዋል የሚያስችሉ ምርምሮችን ማካሄድ ፤ ፲፪• የሥርዓተ መህድር ጥናትና ምርምር ማካሄድ ፣ የሀገሪቱን የሕይወታዊ ሀብት መጠንና ሥርጭት የሚያራምዱ ወይም የሚያናጉ ክስተቶችን አስቀድሞ በመተንበይ ጤናማ ሁኔታዎችን ለመቀጠልና ችግሩን ለመገደብ የሚ ያስችሉ የፖሊሲ ሀሳቦችን ለሚመለከታቸው አካላት ማቅረብ ፤ ፲፫ ሕይወታዊ ሀብትን በመጠበቅ ፣ በማበልጸግና ለዘላቂ ጥቅም እንዲውሉ በማድረግ ረገድ የኅብረተሰቡን ተሳትፎና ድጋፍማበረታታት ፤ ፲፬• የሕይወታዊ ሀብት አጠባበቅ ፣ ልማትና አጠቃቀም የሚመለከቱ ባሕላዊ አሠራሮችን ማጥናትና ለወደፊት ዕድገት ከሣይንሳዊ አሠራሮች ጋር እንዲጣጣሙ ማድረግ ፣ ፲፭ የሕይወታዊ ሀብት ጥበቃና ምርምርን በሚመለከት ከአህ ጉራዊና ዓለምአቀፍ ተቋማት ጋር በመተባበር ፣ ሀገሪቱ በሕይወታዊ ሀብቷ ላይ ያላትን የሉዓላዊነት መብት ለማረጋገጥና ጥቅሟን ለማስከበር የሚያስችሉ ርምጃ ዎችን አግባብ ባላቸው ዓለምአቀፍ ስምምነቶችና በሀገሪቱ ሕጐች መሠረት መውሰድ ፤ ፲፮ የሀገሪቱ ሕይወታዊ ሀብት መረጃዎች የሚጠበቁበትንና ጥቅም ላይ የሚውሉበትን ሥርዓት መዘርጋት ፤ ፲፯• የሀገሪቱን ሕይወታዊ ሀብት ጥበቃና ምርምር አቅም ለመገንባትና በቂ የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት እንዲሁም ሀብትን በይበልጥ ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያ ስችል የባዮ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም እንዲዳብር አግባብ ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር መሥራት ፤ 9 - ፲፰ በኅብረተሰቡ ዘንድ ስለሕይወታዊ ሀብት ጥበቃ ፣ ልማትና አጠቃቀም ተገቢው እውቀት እንዲሰርጽ ከብዙሃን መገናኛ ዘዴዎችና ከትምህርት ተቋማት ጋር በመተባበር የአሕዝበት ሥራ መሥራት ፤ ፲፬• በሕይወታዊ ሀብት አጠባበቅና አጠቃቀም ረገድ የአማካ ሪነት አገልግሎት መስጠት ፡ ፳ የሕይወታዊ ሀብት ናሙና ለመሰብሰብ ፣ ለማሠራጨት ወደውጭ አገር ለመላክ ፣ ወይም ከውጭ አገር ለማስ መጣት ለሚፈልጉ ፈቃድ መስጠት ፤ ፳፩ ለሚሰጠው አገልግሎት ተገቢውን የአገልግሎት ክፍያ መወሰንና መሰብሰብ ፣ · ፳፪ የንብረት ባለቤት መሆን ፣ ውል መዋዋል ፣ በስሙ መክሰስና መከሰስ ፣ ፳፫ ዓላማውን ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ ሌሎች ተግባሮችን ማከናወን ። . ገጽ ፯፻፲ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፱ ሰኔ ፲፰ ቀን ፲፱፻፶ ዓም Federal Negarit Gazeta – No . 49 25 June , 1998 - Page 780 ፯ . የኢንስቲትዩቱ አቋም ኢንስቲትዩቱ ፡ ፩ . ኣንድ ዋና ሥራ አስኪያጅ ፡ ጀ• አንድ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ እና ፫ አስፈላጊው ሠራተኞች ይኖሩታል ። ፰ የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ድርጅት ቦርድ የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ድርጅት ቦርድ ከዚህ በፊት | በአዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፳፬ የተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪ በሕይወታዊ ሀብት ጥበቃና ምርምር ረገድ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል ፤ ፩ . በዚህ አዋጅ የተመለከቱት የኢንስቲትዩቱ ዓላማዎች - እንዲሁም ሥልጣንና ተግባሮች በሚገባ ሥራ ላይ መዋላቸውን መከታተል ፡ ፪• ኢንስቲትዩቱ የሚያመነጫቸውን የፖሊሲና የሕግ ሃሣቦች መገምገምና ኢንስቲትዩቱ ተጠሪ በሆነበት ድርጅት በኩል ለመንግሥት ማቅረብ ፤ ፫ በኢንስቲትዩቱ የሚካሄዱ የሕይወታዊ ሀብት ጥበቃና ምርምር ፕሮግራሞችን መገምገምና ማጽደቅ ፣ በሥራ ላይ መዋላቸውንም መከታተልና መቆጣጠር ፤ ፬• ለኢንስቲትዩቱ ተግባር አፈጻጸም አመቺ የሆነ ድርጅታዊ መዋቅር ፡ የአሠራር ዘዴና የአስተዳደርደንብ ተጠንቶ በሥራ ላይ እንዲውል ማድረግ ፤ ፭ የኢንስቲትዩቱን ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅና ለዋናው ሥራ አስኪያጅ ተጠሪ የሆኑ ኃላፊዎችን ምደባ ማጽደቅ ፡ ፮ : በዋናው ሥራአስኪያጅየሚቀርበውን የኢንስቲትዩቱን ሪፖርት ማጽደቅ ፡ — ለኢንስቲትዩቱ ዓላማ መሳካት በሚረዱ ሌሎች ጉዳዮች ላይ በመምከር ተገቢውን ውሳኔ መስጠት ። ፬ ስለ ዋናው ሥራ አስኪያጅ ፩ . ዋናው ሥራአስኪያጅ በቦርዱ አቅራቢነት በመንግሥት ይሾማል ፡ ፪ ዋናው ሥራ አስኪያጅ የኢንስቲትዩቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ ከቦርዱና በቦርዱም አማካኝነት ከኢት ዮጵያ ግብርና ምርምር ድርጅት በሚሰጠው አጠቃላይ መመሪያ መሠረት የኢንስቲትዩቱን ሥራዎችይመራል ፣ ያስተዳድራል ፡ ፫ . የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ዋናው ሥራ አስኪያጅ ሀ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፮ የተመለከቱትን የኢንስቲት ዩቱን ሥልጣንና ተግባሮች በሥራ ላይ ያውላል ፤ ለ ) ኢንስቲትዩቱ ተጠሪ ለሆነበት ግብርና ምርምር “ ድርጅት በወጣው መመሪያና አግባብነት ባላቸው ሌሎች ሕጎች ተመሥርቶ የኢንስቲትዩቱን ሠራተኞች ይቀጥራል ፡ ያስተዳድራል ፤ ሐ ) የኢንስቲትዩቱን የሥራ ፕሮግራምና በጀት ያዘጋጃል ፣ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል ፤ ገጽ ፯፻፳፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፱ ሰኔ ፲፰ ቀን ፲፱፻፶ ዓም Federal Negarit Gazeta – No . 49 25 June , 1998 Page 781 መ ) ለኢንስቲትዩቱ በተፈቀደለት በጀትና የሥራ ፕሮግራም መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል ፤ ሠ ) ኢንስቲትዩቱ ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚያደር ጋቸው ግንኙነቶች ሁሉ ኢንስቲትዩቱን ይወክላል ፤ ረ ) የኢንስቲትዩቱን ዓመታዊ ሪፖርት አዘጋጅቶ በኢት ዮጵያ ግብርና ምርምር ድርጅት ዋና ዳይሬክተር በኩል ለቦርዱ ያቀርባል ። ፩ . ዋና ሥራ አስኪያጁ ለኢንስቲትዩቱ የሥራ ቅልጥፍና በሚያስፈልግ መጠን ከሥልጣንና ተግባሩ በከፊል ለኢን ስቲትዩቱ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ፡ ለሌሎች ኃላፊዎችና ሠራተኞች በውክልና ሊያስተላልፍይችላል ። ፲ በጀት · , ፩ . የኢንስቲትዩቱ በጀት ከሚከተሉት ምንጮች የተውጣጣ ይሆናል ፤ ሀ ) ከመንግሥት በጀትና ድጐማ ፡ ለ ) ከኢንስቲትዩቱ ገቢ ፡ እና ሐ ) ከማናቸውም ሌላ ምንጭ ። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ከተጠቀሱት ምንጮች የሚገኘው ገንዘብ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ወይም በሚወክለው ሌላ ባንክ ተቀማጭ ሆኖ በመንግሥት የፋይናንስ ሕግ መሠረት ለኢንስቲትዩቱ ዓላማዎች ማስፈጸሚያ ይውላል ። ፲፩ . የሂሣብ መዛግብት እ ኢንስቲትዩቱ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሣብ መዛግብት ይይዛል ። ፪ የኢንስቲትዩቱ የሂሣብ መዛግብት በዋናው ኦዲተር | l . D00 ወይም እርሱ በሚሰይመው ኦዲተር በየዓመቱ ይመረ ፲፪ የፈቃድ አስፈላጊነት የሕይወታዊ ሀብት ናሙና ለመሰብሰብ ፣ ለማሠራጨት ፣ ወደውጭ አገር ለመላክ ፣ ወይም ከውጭ አገር ለማስመጣት | 12 . Requirement of Pemit የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ከኢንስቲትዩቱ ፈቃድ ማውጣት ይኖርበታል ። ፲፫ ስለ ቅጣት የኢንስቲትዩቱ ፈቃድ ሳይኖረው የሕይወታዊ ሀብት ናሙና የሰበሰበ ፡ ያሰራጨ ፣ ወደውጭ አገር የላከ ፣ ወይም ከውጭ አገር ያስመጣ ማንኛውም ሰው ከአምስት ዓመት እስከ አሥር ዓመት በሚደርስ እስራትና ከአሥራ አምስት ሺህ እስከ ሃያ ሺህ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል ። ፲፬• የመተባበር ግዴታ ማንኛውም ሰው ፣ ወይም ተቋም ወይም ድርጅት ለዚህ አዋጅ አፈጸጸም ከኢንስቲትዩቱ ጋር የመተባበር ግዴታ አለበት ። ፲፭ የመብትና ግዴታዎች መተላለፍ የዕፅዋት ጀኔቲክ ማዕከል እንዲሁም የዱር እንስሳት ጥበቃ ልማትና አጠቃቀም ድርጅት በመባል ይታወቁ የነበሩት ተቋማት መብትና ግዴታዎች በዚህ አዋጅ ለኢንስቲትዩቱ ተላልፈዋል ። ገጽ ፯፻ዥያ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር፱ ሰኔ ፲፰ ቀን ፲፱፻፶ ዓም . Federal Negarit Gazeta No . 49 25 June , 1998 Page 782 ፲፮• ተፈጻሚነት ስለማይኖራቸው ሕጎች ከዚህ አዋጅ ጋር የሚቃረን ማናቸውም ሕግ በዚህ አዋጅ በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት አይኖረውም ። ፲፯ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከሰኔ ፲፰ ቀን ፲፱፻፲ ዓም ጀምሮ የጸና ይሆናል ። | 17 . Effective Date አዲስ አበባ ሰኔ ፲፰ ቀን ፲፱፻፲ ዓ . ም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?