የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ዘጠነኛ ዓመት ቁጥር ፳፫ አዲስ አበባ ሰኔ ፳፮ ቀን ፲፱፻፲፭ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፫፻፶፪ ፲፱፻፲፭ ዓም የሱዳን ወደብ አጠቃቀም የፕሮቶኮል ስምምነት ማጽደቂያ ገጽ ፪ሺ፪፻፳፬ አዋጅ ቁጥር ፫፻፶፪ ፲፱፻፲፭ በኢትዮጵያና በሱዳን መንግሥታት መካከል የተደረገውን የሱዳን ወደብ አጠቃቀም የፕሮቶኮል ስምምነት ለማፅደቅ የወጣ አዋጅ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና በሱዳን ሪፐብሊክ መንግሥት መካከል የተደረገው የሱዳን ወደብ | Utilization between the Government of the Fedral De አጠቃቀም የፕሮቶኮል ስምምነት የካቲት ፳፮ ቀን ፲፱፻፲፪ ዓም | mocratic Republic of Ethiopia and the Government of ካርቱም ላይ የተፈረመ ስለሆነ ፣ ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ ፳፮ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓም ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ ፣ በሕግ-- መንግሥቱ አንቀጽ ፶፭ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እና ( ፲፪ ) መሠረት ከዚህ እንደሚከተለው ታውጇል ። አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ የሱዳን ወደብ አጠቃቀም የፕሮቶኮል ስምምነት ማፅደቂያ አዋጅ ቁጥር ፫፻፴፪ / ፲፱፻፲፭ ” ተብሎ | 1 . ሊጠቀስ ይችላል ። ስምምነቱ ስለመፅደቁ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና በሱዳን ሪፐብሊክ መንግሥት መካከል | 2 . የካቲት ፳፮ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓም ካርቱም ላይ የተፈረመው የሱዳን ወደብ አጠቃቀም የፕሮቶኮል ስምምነት ፀድቋል ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፱ሺ፩ ገጽ ፪ሺ፪፻፷፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፫ ሰኔ ፳፰ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓም ስለ አስፈጻሚ አካል ሥልጣን ይህ የፕሮቶኮል ስምምነት በሥራ ላይ እንዲውል የማድረግ ሥልጣን ለንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በዚህ አዋጅ ተሰጥቶታል ። አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከሰኔ ፳፮ቀን ፲፱፻፲፭ ዓም ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ሰኔ ፳፮ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓም ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ