×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
አዋጅ ቁጥር ፫፻፳፬/፲፱፻፶፭ የፍትህ አካላት ባለሙያዎች የሥልጣን ማዕከልን ማቋቋሚያ አዋጅ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ዘጠነኛ ዓመት ቁጥር ፳፬ አዲስ አበባጳጉሜ ፪ ቀን ፲፱፻፶፭ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፫፻፳፬ / ፲፱፻፶፭ ዓም የፍትህ አካላት ባለሙያዎች የሥልጠና ማዕከልን ማቋቋሚያ ገጽ ፪ሺ፫፻፰ አዋጅ ቁጥር ፫፻፳፬ / ፲፱፻፲፭ የፍትህ አካላት ባለሙያዎች የሥልጠና ማዕከልን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ በዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ውስጥ ዳኝነት ሕገ መንግ ሥታዊ ሥርዓቱን የመጠበቅና የመገንባት የማይተካ ሚና ስለሚጫ ወትና ከሙያተኞቹ ከፍተኛ ሙያዊ ክህሎትና ሥነ ምግባር | Judiciary plays an irreplaceable role and requires highest የሚጠይቅ ስለሆነ፡ ለዚህም በበቂ ሁኔታ የሠለጠኑ ሙያተኞችን | professional standard and integrity , so that it is necessary to ማፍራት አስፈላጊ በመሆኑ፡ በፍትሕ ሥርዓቱ ውስጥ ዳኞችን ፣ ዓቃብያነ ሕግንና ሌሎች ሙያተኞችን ለማብቃት ባለማቋረጥ የሚያድግና ተከታታይነት | organize a sustainable and continuous training of system , ያለው የሥልጠና ሥርዓት ማደራጀት አስፈላጊ በመሆኑ ፣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት ከዚህ የሚከተለው ታውጇል ። | Ethiopia , it is hereby proclaimed as follows . ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የፍትህ አካላት ባለሙያዎች የሥልጠናማዕከልን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፫፻፳፬ / ፲፱፻፲፭ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ : ዥሺ፩ ገጸ ፪ሺ፫፻፳፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፱ ጳጉሜ ፪ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓም ፪ . ትርጓሜ ፩ . “ የፍትህ አካላት ” ማለት በዋነኛነት ፍርድ ቤቶችንና የዐቃቤ ሕግ መሥሪያ ቤቶችን ሆኖ እንደአግባብነቱ ከፍትህ ሥራ ጋር የተያያዘ ሥራ የሚሠሩ ሌሎች አካላትን ሊጨምር ይችላል ። ፪ . “ የፍትህ አካላት ባለሞያዎች ” ማለት በዋናነት ዳኞች ፣ ዐቃብያን ሕግ ፣ ሬጅስትራሮችን ፣ ተከላካይ ጠበቆችን ሆኖ እንደአስፈላጊነቱ በፍትህ አካላት ውስጥ የሚሠሩ ሌሎች ሙያተኞችን ሊጨምር ይችላል ። • መቋቋም ፩ የፍትህ አካላት የሥልጠና ማዕከል ከዚህ በኋላ ማዕከሉ እየተባለ የሚጠራ የሕግ ሰውነት ያለው የፌዴራል መሥሪያ ቤት በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ። ፪ . የማዕከሉ ተጠሪነት ለፌዴራል ጠቅላይ ፍ / ቤት ይሆናል ። ዋና መሥሪያ ቤት የማዕከሉ ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ ሆኖ በማናቸውም ሥፍራ ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤት ሊኖረው ይችላል ። ዓ ላ ማ የሥልጠና ማዕከሉ ዓላማ ፩ የዳኝነት ሥርዓቱ ከፍተኛ ሙያዊ ብቃትና ሥነ ምግባር እንዲሁም ሕዝባዊ አመኔታና ተቆርቋሪነት ያላቸውና ለሕገ - መንግሥታዊ ሥርዓቱ መከበር በጽናት በሚቆሙ ሙያተኞች የተገነባ እንዲሆን ማስቻል ፣ በሕግ የበላይነት ፣ በግልጽነትና ተጠያቂነት መርሆዎች ላይ የተመሠረተ ፣ የተቀናጀና ወጥነት ያለው የፍትህ አሰጣጥ ሥርዓትን ማምጣት ፣ ፫ ፍትኃዊ ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ የፍትህ ሥርዓት ለማስፈን የሚያስችል በቀጣይነት የሚያድግና ተከታታይነት ያለው ሥልጠና ማካሄድ ይሆናል ። ሥልጣንና ተግባር ማዕከሉ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ፣ ፩ በፌዴራልና በክልል የፍትህ አካላት ውስጥ በዳኝነት ፣ በዓቃቤ ሕግነት፡ በተከላካይ ጠበቃነት ወይም በሬጅስት ራርነትና በሌሎች ከፍትህ ሥርዓቱ ጋር ተዛማጅነት ባላቸው ሙያዎች ውስጥ ሥርዓቱን ለሚቀላቀሉ የሕግ ባለሙያዎች ሥልጠናዎችን መስጠት ፣ ፪ • በፌዴራልና በክልል የፍትህ አካላት ውስጥ በሥራ ላይ ለሚገኙ ዳኞች ፣ ዓቃብያነ ሕግ ፣ ተከላካይ ጠበቆች ፣ ሬጅስትራር እና ሌሎች በፍትህ ሥርዓቱ ውስጥ ለሚገኙ ባለሙያዎች የሙያ ብቃታቸውን ከፍ ለማድረግ በሚች ሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ቀጣይነት ያላቸው የሥራ ላይ ሥልጠናዎች መስጠት ፣ ፤ በፍትህ ሥርዓቱ ውስጥ የሚታዩ የተዘበራረቁ የፍትህ አሰጣጥ አሠራሮች ተስተካክለው ወጥነት እንዲኖራ ቸውና ደረጃቸውን የጠበቁ የፍትህ አሰጣጥ ሥርዓቶች በሁሉም ቦታ እውን እንዲሆኑ ተገቢውን ምርምርና ጥናት በማካሄድ የውሳኔ ሃሣብ ማመንጨት ፣ ፬ በራሱ ወይም ከሌሎች የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ የትምህርት ፣ የሥልጠናና የምርምር ተቋማት ጋር በመቀ ናጀት ለፍትህ ሥርዓቱ መጠናከር አስተዋጽኦ በሚኖ ራቸው የሕግና የፍትህ ጉዳዮች ላይ መምከርና የማሻሻያ ሃሣቦችን ማመንጨት ፣ ፭ አስፈላጊዎቹን የሥልጠና ማቴሪያሎች ማሰባሰብ ፣ ማዘጋጀት ፣ ማሠራጨት ፣ ፮ ሌሎች የማዕከሉን ዓላማና ግብ መሠረት ያደረጉ ተዛማጅ ተግባራትን ማከናወን ። የን .. ገጽ ፪ሺ፫፻፳፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፬ ጳጉሜ ፪ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓ.ም. ፯- የማዕከሉ አቋም ማዕከሉ ፣ ፩ . የሥልጠና ካውንስል ኣንድ ዳይሬክተር ፫ . ሁለት ምክትል ዳይሬክተሮች እና ሌሎች ለሥራው አስፈላጊ የሆኑ ሠራተኞች ይኖሩታል ። ፰ የሥልጠና ካውንስሉ አካላት ካውንስሉ የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል ፣ ፩ . የፌዴራል ጠቅላይ ፍ / ቤት ፕሬዚዳንት • የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት ፕሬዚዳንት .... ፫ • የፍትህ ሚኒስትር ፬ . የአቅም ግንባታ ሚኒስትር ፭ የክልሎች ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ፕሬዚዳንቶች ከመካከላቸው የሚወክሏቸው አምስት ፕሬዚዳንቶች ፮ የሥልጠና ማዕከሉ ዳይሬክተር ........... አባልና ጸሐፊ የካውንስሉ ሥልጣንና ተግባር ካውንስሉ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ፣ ፩ የማዕከሉን እንቅስቃሴ በበላይነት ይመራል ፣ ያስተባ ብራል ፣ ይቆጣጠራል ፣ የማዕከሉን ዕቅድና የሥራ መርሐ ግብሮች ይገመግማል ፣ ያጸድቃል ፣ አስፈላጊ በጀት እንዲፈቀድ ለመንግሥት ያቀርባል ፣ ፫ ሥልጠናን ኣስመልክቶ በሚቀርቡ የፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ይወስናል ፣ ፬ . የማዕከሉን ወቅታዊና ዓመታዊ ሪፖርት ያጸድቃል ፣ የማዕከሉን ዓላማ ለማስፈጸም የሚረዱ ድጋፎችንና ስጦታዎችን በሚመለከት አጠቃላይ መመሪያዎችን ይሰጣል ፣ የተቋሙን ድርጅታዊ መዋቅር ፣ የሥራ መመሪያና የሠራ ተኞች የአገልግሎት ሁኔታ ይወስናል ፣ ፯ ሌሎች በዳይሬክተሩ ጉዳዮችን መርምሮ ይወስናል ። ፲ የካውንስሉ ስብሰባ ፩- ካውንስሉ ቢያንስ በሩብ ዓመት አንድ ጊዜ ይሰበስባል ፣ ፪ አስቸኳይ ስብሰባ መጥራት አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ የማዕከሉ ካውንስል ሰብሳቢ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል ፣ ፫ የካውንስሉ ምልዓተ የሚኖረው ከአባላት ከ፵ % + ፩ ሲገኙ ብቻ ነው ፣ ፬ • ማናቸውም ውሳኔ የሚያልፈው ስብሰባ ላይ ከተገኙ የካውንስሉ አባላት ከግማሽ በላይ ድምዕ ሲደገፍ ብቻ ነው ። ሆኖም ድምዕ እኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው ወሳኝ ድምዕ ይኖረዋል ። ፲፩ . የማዕከሉ ዳይሬክተር አሰያየም ፣ ሥልጣንና ተግባር ፣ ፩ . የማዕከሉ ዳይሬክተር በካውንስሉ ሰብሳቢ ኣቅራቢነት በካውንስሉ ይሾማል፡ • ዳይሬክተሩ የማዕከሉ ኃላፊ በመሆን ከካውንስሉ በሚሰጠው መመሪያ መሠረት የማዕከሉን ሥራ ይመራል ፣ ያስተባብራል ፣ ፫ . በዚህ አንቀጽ በንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) የተመለከተው ኣጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ዳይሬክተሩ የሚከ ተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ፣ ( ሀ ) የማዕከሉን የአጭር ፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ዕቅድ ፣ መርሃ ግብርና በጀት አዘጋጅቶ ለካውንስሉ ያቀርባል ፣ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል ፣ ( ለ ) ለማዕከሉ በተፈቀደለት በጀትና የሥራ ፕሮግራም መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል ፣ ሂሣብ ያንቀሳ ገጽ ፪ሺ፫፻፷፱ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፬ ጳጉሜ ፪ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓ.ም. ( ሐ ) የማዕከሉን የሥራ አፈጻጸምና የሂሣብ ሪፖርት አዘጋጅቶ ለካውንስሉ ያቀርባል፡ ( መ ) ለማዕከሉ አስፈላጊ የሆኑ ሠራተኞች ይቀጥራል፡ ያስተዳድራል፡ ( ሠ ) ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች ሁሉ ማዕካለን ይወክላል ፤ ( ረ ) የካውንስሉን ውሳኔዎች ያስፈጽማል፡ ( ሰ ) ሌሎች በካውንስሉ የሚሰጡትን ሥራዎች ያካና ፲፪- የማዕከሉ ም ዳይሬክተሮች ፩ . የማዕከሉ ምክትል ዳይሬክተሮች በዳይሬክተሩ አቅራ ቢነት በካውንስሉ ይሾማሉ፡ ይ- ምክትል ዳይሬክተሮች በዳይሬክተሩ ተለይቶ የሚሰጣ ቸውን ሥራ ይሠራሉ፡ ፫ ዳይሬክተሩ በሚሰጠው ውክልና መሠረትም ዳይሬክተሩ ሳይኖር የሱን ሥራ ተክተው ይሠራሉ ። 11. በ ጀ ት የማዕከሉ በጀት ከሚከተሉት ምንጮች የሚገኝ ይሆናል ፣ ፩ በመንግሥት ከሚመደብ በጀት፡ ፪ : ማዕከሉ ሊያመነጭ ከሚችለው ገቢና ፣ ፫ ከሌሎች ምንጮች ከሚገኝ ገንዘብ ። 10 • የሂሣብ መዛግብት ፩ ማዕከሉ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሣብ መዛግብት ይይዛል፡ ፪ ) የማዕከሉ የሂሣብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በዋናው ኦዲተር ወይም እርሱ በሚሰይመው ኦዲተር በየዓመቱ ይመረመራሉ፡ ፲፭ ደንብ የማውጣት ሥልጣን የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይህንን አዋጅ በሥራ ላይ ደንቦች ለማውጣት ሥልጣን ይኖረዋል ። ፲፮ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ጀምሮ የጸና ይሆናል ። ከወጣበት ቀን አዲስ አበባ ጳጉሜ ፬ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓም ግርማ ወልደጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?