የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አሥረኛ ዓመት ቁጥር ፪ አዲስ አበባ የካቲት ፳፪ ፲፱፻፲፮ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፲፯ ፲፱፻፲፮ ዓም “ የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ድርጅት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ደንብ ገጽ ፪ሺ፭፻፴፬ የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ድርጅት ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎትን ኮርፖሬሽንን በድርጅትነት እንደገና ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፤ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢፌዲሪፑብሊክ የሕግ አስፈጻ ሚውን አካል ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር | Hence . This Regulation is issued by the Coouncil of Ministers ፬ / ፲፱፻ T ፯ አንቀጽ ፭ እና በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ | pursuant to article 5 of the Definition ofPowers and Duties of ቁጥር ፳፭ / ፲፱፻፫፬ አንቀጽ ፵፯ ፩ / ሀ መሠረት ይህንን ደንብ | the Executive Organs of the Federal Democratic Republic of አውጥቷል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ድርጅት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር፲፯ ፲፱፻፲፮ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ መቋቋም ፩ የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ድርጅት ( ከዚህ በኋላ “ ድርጅት ” እየተባለ የሚጠራ ) የመንግሥት የልማት ድርጅት ሆኖ በዚህ ደንብ ተቋቁሟል ። ፪ • ድርጅቱ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ / ፲፱፻፳፬ መሠረት ይተዳደራል ። ፫ . ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን የድርጅቱ ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ይሆናል ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ • ሸሺ፩ የ እ ንብረት በላይ በዕዳ ተጠያቂ | 7 . Liability ገጽ ፪ሺ፭፻፲ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵ የካቲት ፳፪ ቀን ፲፱፻፲፮ ዓ • ም • ዋና መሥሪያ ቤት የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ ይሆናል ። እንደአስ ፈላጊነቱም በማናቸውም ሥፍራ ቅርንጫፍ ሊኖረው ይችላል ። ፭ ዓላማ ድርጅቱ የተቋቋመባቸው ዓላማዎች የሚከተሉት ናቸው ። ፩ የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎትን በኪራይ መስጠት ፣ ፪ የእርሻ መሣሪያዎች የጥገና አገልግሎት በክፍያ መስጠት ፣ ፫ የእርሻ መሣሪያዎችንና መለዋወጫዎችን ከአገር ውስጥ እና ከውጭ ገዝቶ ለሽያጭ ማቅረብ ፣ ፬ . የእርሻ መሣሪያዎችንና ተቀጽላዎችን በኪራይ ለተጠቃ ሚዎች መስጠት ፣ ፭ የምርትና የግብርና ግብአቶችን የማጓጓዝ አገልግሎት በኪራይ መስጠት ፣ የግብርና ቴክኖሎጂ የሽግግር ማዕከል ሆኖ በማገልገል ዘመናዊ የእርሻ መሣሪያዎችን አጠቃቀም እንዲለመድ ማድረጋ ፣ ፯ የእርሻ መሣሪያዎች አያያዝና አጠቃቀም ሥልጠናና የምክር አገልግሎት በክፍያ መስጠት ፣ ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ የሆኑ ሥራዎችን ማካሄድ ። ፮ ካፒታል ለድርጅቱ የተፈቀደለት ካፒታል ብር ፳ሚሊዮን ፭፻፳ሺ፰ ፻፷፩ ከ፳፯ ሃያ ሚሊዮን አምስት መቶ ሰማንያ ሺህ ስምንት መቶ ስልሳ ኣንድ ከሃያ ሰባት ሣንቲም ሲሆን ከዚህ ውስጥ ብር ፲፩ሚሊዮን ፪፻፰፱ሺ ፪፻፩ ከ፳፯ አሥራ አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ሺህ ሁለት መቶ አንድ ከሃያ ሰባት ሣንቲም በዓይነትና በጥሬ ገንዘብ ተከፍሏል ። ፯ : ኃላፊነት ድርጅቱ ካለው ጠቅላላ አይሆንም ። ፰ ድርጅቱ የሚቆይበት ጊዜ ድርጅቱ ላልተወሰነ ጊዜ ይቆያል ። ፱ መብትና ግዴታን ስለማስተላለፍ በአዋጅ ቁጥር ፫፻፴፯ / ፲፱፻፳፱ የተቋቋመው የግብርና ሜካናይ ዜሽን አገልግሎት ኮርፖሬሽን መብትና ግዴታ በዚህ ደንብ ለድርጅቱ ተላልፋል ። ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ ይህ ደንብ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ የካቲት ፳፪ ቀን ፲፱፻፲፮ ዓም : መለስ ዜናዊ የኢትዮኣያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ