አምሳ ሦስተኛ ዓመት ቁጥር ፶፯
የአንዱ ዋጋ
መ ን ግ ሥ ት
ጋ ዜ ጣ
የ ኢ ት ዮ ጵ ያ የ ሽ ግ ግ ር
ነ ጋ ሪ ት
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፷፮ ፲፱፻፹፮ ዓ.ም. የመኖሪያ ቤቶች ኮንስትራክሽን ድርጅት ማቋቋሚያ የሚኒስ ትሮች ምክር ቤት ደንብ
ገጽ ፫፻፲፫
በ ኢ. ት ዮ ጵ ያ የ ሽ ግ ግ ር መ ን ግ ሥ ት የተወካዮች ምክር ቤት ተጠባባቂነት የወጣ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፷፭ ፲፱፻፹፮ የመኖሪያ ቤቶች ኮንስትራክሽን ድርጅትን ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የጠቅላይ ሚኒስትርንና የሚኒስ ትሮች ምክር ቤትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፪ ፲፱፻፹፫ አንቀጽ ፬፪ እና በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ ፲፱፻፹፬ አንቀጽ ፵፯ ፩ ሀ መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ።
፩. አጭር
ይህ ደንብ « የመኖሪያ ቤቶች ኮንስትራክሽን ድርጅት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፷፭ ፲፱፻፹፮ » ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ።
፩.የመኖሪያ ቤቶች ኮንስትራክሽን ድርጅት | ከዚህ በኋላ « ድርጅት » እየተባለ የሚጠራ የመንግሥት የልማት ድርጅት ሆኖ በዚህ ደንብ ተቋቁሟል ።
፪. ድርጅቱ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ ፲፱፻፹፬ መሠረት ይተዳደራል ።
፫. ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን
በመንግሥት የሚሰየም ኣካል የድርጅቱ ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ይሆናል ።
፬. ዋና መሥሪያ ቤት
የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ ይሆናል ። እንደአስፈላጊነቱም በማናቸውም ሥፍራ ቅርንጫፍ ሊኖረው ይችላል ።
አዲስ አበባ የካቲት ፮ ቀን ፲፱፻፹፮ ዓ.ም.
የፖስታ ጥን ቍ ፹ሺ፩ (80,001)