አምሳ ሦስተኛ ዓመት ቁጥር ፯
ነ ጋ ሪ ት
የአንዱ ዋጋ
ማ ው ጫ
የ ሽ ግ ግ ር
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፳፮ ፲፱፻፹፮ አንዳንድ የመንግሥት ልማት ድርጅቶችን ለማፍረስ የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ
„ ጽ ፲፮
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፳፮ ፲፱፻፹፮ አንዳንድ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ለማፍረስ የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ
በ ኢ ት ዮ ጵ ያ የ ሽ ግ ግ ር መ ን ግ ሥ ት የተወካዮች ምክር ቤት ተጠባባቂነት የወጣ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የጠቅላይ ሚኒስትርንና የሚኒ ስትሮች ምክር ቤትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣ አዋጅ ቁጥር ፪ ፲፱፻፹፫ አንቀጽ ፬፪ እና በመንግሥት የል ማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ ፲፱፻፹፬ አንቀጽ ፵፯ ፩ ሐ መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ።
፩. አጭር ርእስ
ይህ ደንብ « አንዳንድ የመንግሥት ልማት ድርጅቶችን ለማፍረስ የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፳፮ ፲፱፻፹፯ » ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ።
መ ፍ ረ ስ
የሚከተሉት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች በዚህ ደንብ ፈርሰዋል ፤
፩. በደንብ ቁጥር ፶፱ ፲፱፻፸ ተቋቁሞ የነበረው የኢት ዮጵያ ቡና ገበያ ኮርፖሬሽን ፤
፪. የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ኮፖሬሽን በመባል ይታወቅ የነበረው ድርጅት ´
፫. የአዋሽ እርሻ ልማት ኮርፖሬሽን በመባል ይታወቅ የነበረው ድርጅት ፤
፬. የእንስሳት ልማትና ሥጋ ኮርፖሬሽን በመባል ይታ ወቅ የነበረው ድርጅት ፤
አዲስ አበባ ኅዳር ፲ ቀን ፲፱፻፹፮ ዓ. ም.
ጋ ዜ ጣ
የፖስታ ሣጥን ቍ ፹ሺ፩ (80,001)