የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ነጋሪት ጋዜጣ አምስተኛ ዓመት ቁጥር፳፩ አዲስ አበባ ሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፲፩ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፩፻፭፯ / ፲፱፻፲፩ ዓ.ም. የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች ምዝገባና ቁጥጥር ገጽ ፩ሺ፩፻፲፯ አዋጅ ቁጥር ፩፻፪ / ፲፱፻፲፩ ስለኮንስትራክሽን መሣሪያዎች ምዝገባና ቁጥጥር የወጣ አዋጅ የኮንስትራክሽን ሥራ ዘርፍን ለማጠናከር የሚያስችል ሁኔታዎችን ማመቻቸት በማስፈለጉ ፡ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች ምዝገባና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር ፩፻ሮ፯ / ፲፱፻፲፩ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ በዚህ አዋጅ ውስጥ ፡ ፩ . “ ሚኒስቴር ” ማለት የሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር ፪ . “ የኮንስትራክሽን መሣሪያ ” ማለትሚኒስቴሩ በመመሪያ የሚወስነው ለኮንስትራክሽን ሥራ እንዲያገለግል ሆኖ የተሠራ መሣሪያ ሲሆን በክልል ወይም ለፌዴራል መንግሥት ተጠሪ በሆኑ ከተሞች ትራንስፖርትና መገናኛ ቢሮዎች በአዋጅ ቁጥር ፲፬ / ፳፬ የሚመዘገቡ የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችን አይጨምርም ፡ ፫ . “ የባለቤትነት መታወቂያ ደብተር ” ማለት ለኮንስትራ ክሽን መሣሪያ ባለንብረቶች የሚሰጥ የባለቤትነት ማረጋገጫ ማስረጃ ነው : ፬ . “ መለያ ቁጥር ” ማለት በኮንስትራክሽን መሣሪያዎች ላይ የሚለጠፍ ፊደል ወይም ቁጥር ወይም ሁለቱም ነው ። ያንዱ ዋጋ 2:30 ነጋሪት ጋዜጣ ፖ.ሣቁ ፰ሺ፩ | ገጽ ፩ሺ፩፻፲፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር፳፩ ፲፱፻፷፩ ዓም • የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች ምዝገባና ቁጥጥር ዓላማዎች የሚከተሉት ይሆናሉ፡ ፩ . በመንግሥትና በግል ባለቤትነት የተያዙ የኮንስትራ ክሽን መሣሪያዎችን በዓይነትና በመጠን መዝግቦ ለመያዝ ፡ ፪ የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች ለዋስትና መያዣና ለመሳ ሰሉት አገልግሎቶች የሚውሉበትን ሁኔታዎች ለማመ ቻቸት ። የሚኒስቴሩሥልጣንና ተግባር ሚኒስቴሩ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፣ ለሥራው የሚያስፈልገውን የሰው ኃይልና መሣሪያዎች ያደራጃል ፡ ፪ የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችን ይመዘግባል ፣ የባለቤ ትነት ደብተር ይሰጣል፡ ወደሀገር ውስጥ ሲገቡም ሆነ ሲወጡ ይቆጣጠራል ፡ ፫ ለኮንስትራክሽን መሣሪያዎች መለያ ቁጥር ይሰጣል፡ በመሣሪያዎቹ ላይ መለጠፉንም ይቆጣጠራል ፣ ፬ የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች ለምርመራየሚቀርቡበትን ቦታና ጊዜ ይወስናል ፡ ፭ የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችን ብቃት በመመርመር ማስረጃ ይሰጣል፡ ብቃት የሌላቸውን መሣሪያዎች ሥራ ላይ እንዳይውሉ ይቆጣጠራል ፡ በዚህ አዋጅ በሚወጣ ደንብ በሚወሰነው መሠረት ለሚሰጠው አገልግሎት ዋጋ ያስከፍላል ። ደንብ ወይም መመሪያ የማውጣት ሥልጣን ፩ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም የሚረዳ ደንብ ማውጣት ይችላል ። ፪ ሚኒስቴሩ ይህን አዋጅና በዚህ አዋጅ መሠረት የሚወ መመሪያ ማውጣት ይችላል ። ፮ ቅጣት ይህን አዋጅ የተላለፈማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት አግባብ | 6. Penalties ባለው የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ መሠረት ይቀጣል ። ፯ . የተሻሩ ሕጐች የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣንን እንደገና ማቋቋሚያ ( ማሻሻያ ) ኣዋጅ ቁጥር ፩፻፳፪ / ፲፱፻፷፯ በዚህ አዋጅ ተሽሯል ። አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፵፩ ዓ.ም ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳ ት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅትታተመ