አምሳ ሦስተኛ ዓመት ቍጥር ፲፰
የ ኢ ት ዮ ጵ ያ የ ሽ ግ ግ ር
የአንዱ ዋጋ
ነ ጋ ሪ ት
ጋ ዜ ጣ
ማ ው ጫ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻ a ፯ ፲፱፻፹፮ የወተት ልማት ድርጅት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ
ገጽ ፴፱
በ ኢ ት ዮ ጵ ያ የ ሽ ግ ግ ር መ ን ግ ሥ ት የተወካዮች ምክር ቤት ተጠባባቂነት የወጣ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፴፯፲፱፻፹፮ የወተት ልማት ድርጅትን ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የጠቅላይ ሚኒስትርንና የሚ ኒስትሮች ምክር ቤትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወ ጣው አዋጅ ቁጥር ፪፲፱፻፹፫ አንቀጽ ፬፪ እና በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ ፲፱፻፹፬ አንቀጽ ፵፯ (፩) (ሀ) መሠረት ይህንን ደንብ አውጥቷል ።
፩. አጭር ርዕስ
ይህ ደንብ « የወተት ልማት ድርጅት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፴፯ ፲፱፻፹፮ » ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ።
፪. መቋቋም
፩. የወተት ልማት ድርጅት (ከዚህ በኋላ « ድርጅት » እየተባለ የሚጠራ) የመንግሥት የልማት ድርጅት ሆኖ በዚህ ደንብ ተቋቁሟል ።
፪. ድርጅቱ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ ፲፱፻፹፬ መሠረት ይተዳደራል ።
አዲስ አበባ ኅዳር ፲ ቀን ፲፱፻፹፮ ዓ ም.
፫. ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን
በመንግሥት የሚሰየም አካል የድርጅቱ ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ይሆናል ።
የፖስታ ሣጥን ቍ ፹ሺ፩ (80,001)