×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
የደህንነት፣ የኢሚግሬሽንና የስደተኞች ጉዳይ ባለሥልጣን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፮/፲፱፻፹፯

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አንደኛ ዓመት ቁጥር ፮ አዲስ አበባ ነሐሴ ፲፰ ቀን ፲፱፻ዥ ፤ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፮ / ፲፱፻፫፯ ዓም የደህንነት ፡ የኢሚግሬሽንና የስደተኞች ጉዳይ ባለሥልጣን ማቋቋሚያ አዋጅ . . . . . . . . . . . . . . ገጽ ፰ አዋጅ ቁጥር ፮ ፲፱፻ዥ፯ የደህንነት ፡ የኢሚግሬሽንና የስደተኞች ጉዳይ ባለሥልጣን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ - የደህንነት ፣ የኢሚግሬሽንና የስደተኞችን ጉዳይ ባለሥልጣን | ማቋቋም በማስፈለጉ ፣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ኣዋጅ “ የደህንነት ፣ የኢሚግሬሽንና የስደተኞች ጉዳይ ባለሥልጣን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፮ iሀየጊ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . መቋቋም ፩ . የደህንነት ፣ የኢሚግሬሽንና የስደተኞች ጉዳይ ባለሥልጣን ( ከዚህ በኋላ “ ባለሥልጣን ” ተብሎ የሚጠራ ) ራሱን የቻለ የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤት ሆኖ በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ። ፪ . ባለሥልጣኑ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሆናል ። ፫ . የባለሥልጣኑ ዋና መሥሪያ ቤት የባለሥልጣኑ ዋና መሥሪያ ቤት አዲስ አበባ ሆኖ እንደ አስፈላጊነቱ በማናቸውም ሥፍራ ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች ማቋቋም ይችላል ። ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፱ሺ፩ ያንዱ ዋጋ ጽና ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፮ ነሐሴ ፲፰ ቀን ፲፱፻፯ ዓም _ Negarit Gazeta – No . 6 – 24 August 1995 – Page 61 6• የባለሥልጣኑ ዓላማ የባለሥልጣኑ ዓላማ የሃገሪቱንና የሕዝብ ደህንነት ፡ የኢሚግ ሬሽን ፡ የዜግነትና የስደተኞች ፖሊሲዎችና ሕጐችን ማስፈጸም ይሆናል ። ፭ የባለሥልጣኑ ሥልጣንና ተግባር ባለሥልጣኑ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፣ 15 . Powers and Duties of the Authority ፩ . የአገርንና የሕዝብን ደህንነት ጥበቃ ፣ የኢሚግሬሽንና የስደተኞች ጉዳይ ፖሊሲዎች ያዘጋጃል ፣ ተግባራዊ የሚሆኑበትን ስልት ይቀይሳል ፤ ፪ . በሃገር ውስጥና በውጭ አገር የአገርንና የሕዝብን ደህንነት ጥበቃ ሥራ በኃላፊነት ይሠራል ፤ | አግባብ ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ነፃነትና ኢኮኖሚ ላይ የሚጠነሰሰውን ማናቸውንም ሴራ ይከታተላል ፣ ያጣራል ፣ እንደ ሁኔታው አግባብ ላለው ክፍል ያሳውቃል ፤ ፬ . አግባብ ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር የውጭ ሃገር ዜጐች እንዲመዘገቡ ያደርጋል ፣ ወደ አገር ውስጥ እንዲ ገቡና ከአገር እንዲወጡ እንዲሁም በአገር ውስጥ እንዲዘ ዋወሩ ፈቃድ ይሰጣል ፤ ፭ . አግባብ ካላቸው የመስተዳድር አካላት ጋር በመተባበር ጥገኝነትና የኢትዮጵያ ዜግነት እንዲሰጣቸው የሚጠይቁ ሰዎችን ጉዳይ እያጣራ ውሣኔ እንዲያገኙ ያደርጋል ፤ ፮ . ከዲፕሎማቲክ ፓስፖርት በስተቀር ለዜጐች ፓስፖርት ይሰጣል ፣ እንዲሁም ለማንኛውም ሰው የመጓጓዣ ሰነድ ( ቪዛ ) ይሰጣል ፤ ጊ ኣግባብ ካላቸው አካላትና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ስለስደተኞች ጉዳይ ኃላፊ ይሆናል ፤ ፲ . የጦር መሣሪያ ፣ የተኩስ መሣሪያ ወይም ፈንጂ ለመያዝ | ወይም በእነዚሁ ለመጠቀም ፈቃድ ይሰጣል ፣ ፈንጂ ስለሚሸጥበት ሁኔታ ይወስናል ፣ ፈንጂ ለሚሸጡና የጦር ወይም የተኩስ መሣሪያ ለሚያድሱ ፈቃድ ይሰጣል ። ፮ . የባለሥልጣኑ አቋም ባለሥልጣኑ ፣ ፩ . በመንግሥት የሚሾም አንድ ኃላፊ ፤ እና ፪ . አስፈላጊው ሠራተኞች | ይኖሩታል ። ጊ የኃላፊው ሥልጣንና ተግባር ፩ . ኃላፊው የባለሥልጣኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን የባለሥል ጣኑን ሥራዎች ይመራል ፣ ያስተዳድራል ። ፪ . የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ኃላፊው ፤ ሀ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከተውን የባለሥል ጣኑን ሥልጣንና ተግባር ሥራ ላይ ያውላል ፤ ለ ) በፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግ መሠረት የባለሥልጣኑን ሠራተኞች ይቀጥራል ፣ ያስተዳድራል ፤ ገጽ ፳፪ ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፮ ነሐሴ ፲፰ ቀን ፲፱፻ዥ፯ ዓም _ Negarit Gazeta – No . 6 - 24 August 1995 – Page 62 ሐ ) የባለሥልጣኑን የሥራ ፕሮግራምና በጀት ያዘጋጃል ፡ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል ፤ መ ) ለባለሥልጣኑ በተፈቀደለት በጀትና የሥራ ፕሮግራም መሠረት ገንዘብ ወጭ ያደርጋል ፤ ሠ ) ባለሥልጣኑ ከሶስተኛ ወገኖች ጋር በሚያደርጋቸው ግንኙ ነቶች ባለሥልጣኑን ይወክላል ፤ ረ ) ስለ ባለሥልጣኑ የሥራ እንቅስቃሴ ሪፖርት ያቀርባል ። ፫ . ኃላፊው ለባለሥልጣኑ የሥራ ቅልጥፍና በሚያስፈልግ መጠን ሥልጣንና ተግባሩን በከፊል ለባለሥልጣኑ ሌሎች ኃላፊዎችና ሠራተኞች በውክልና ሊያስተላልፍ ይችላል ። ፰ . ውክልና ባለሥልጣኑ ለሥራው አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው ሥልጣኑን ለፌዴራል ወይም ለክልል አስፈጻሚ አካላት በውክልና ሊሰጥ ይችላል ። ፱ . በ ጀ ት የባለሥልጣኑ በጀት በመንግሥት ይመደባል ። ፲ . የሂሣብ መዛግብት ፩ . ባለሥልጣኑ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሣብ መዛግብት ይይዛል ። ፪ . የባለሥልጣኑ የሂሣብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በዋናው ኦዲተር ወይም እርሱ በሚሰይማቸው ኦዲተሮች በየዓመቱ ይመረመራሉ ። ፲፩ . ተፈፃሚነት ስለማይኖራቸው ሕጐች ከዚህ አዋጅ ጋር የሚቃረኑ ወይም በዚህ አዋጅ የተሸፈኑ ጉዳዮችን የሚመለከቱ ማናቸውም ሕጐች ወይም መመሪያዎች ተፈጻሚነት አይኖራቸውም ። ፲፪ . መብትና ግዴታ ስለማስተላለፍ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ( ፭ ) ከተዘረዘሩት ጉዳዮች ጋር የተያያዙ የቀድሞው የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር መብ ና ግዴታዎች በዚህ አዋጅ ለባለሥልጣኑ ተላልፈዋል ። ፲፫ . አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከነሐሴ ፲፰ ቀን ፲፱፻ዥ፯ ዓም ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ነሐሴ ፲፰ ቀን ፲፱፻፯ ዓም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ ።

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?