×
Browse Products About Us Login / Sign Up Contact Us አማርኛ
African Law Archive
Logo
የፍርድ ቤት ውሳኔ 16270

      Sorry, pritning is not allowed

የመ / ቁ 16270
ታህሣሥ 17 ቀን 1998 ዓ.ም
ዳኞች፡ መንበረፀሐይ ታደሰ
ኣብዱልቃድር መሐመድ
ሐጉስ ወልዱ
ዳኜ መላኩ
መስፍን ዕቁበዮናስ አመልካች ...
.... አዋሳ እርሻ ልማት ድርጅት ተጠሪ ... አቶ መሓሪ ማታ ከውል ውጪ ያለ ኃላፊነትን በተመለከተ ስለ ካሳ መካስን አወሳሰን የፍ / ብ / ህ / ቁ . 2066 ( 2 ) ፣ 2086 ( 2 ) ፣ 2081 ፣ 2090 ፣ 2091 2102 ( 1 ) እና 2092
የሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከሳሽ የሆነው የአሁን አመልካች መኪናው አድርሷል በተባለው የግጭት አደጋ ለተጎጂው የጉዳት እና መራል ካሳ እንዲሁም የህክምና ወጪ በድምሩ ብር 30.198 እንዲከፍለው በመወሠኑ እና የደቡብ ብሔር ብሔረሠቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔውን ሰማፅናቱ የቀረበ አቤቱታ
ውሳኔ፡ . የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ
ፍርድ ቤት የሠጠው ውሳኔና የሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ፅድቋል ፡፡
1 ኛ . ከውል ውጪ ኃላፊነት በሆነ ጉዳት የደረሰበት ሰው ጉዳቱ የደረሰው
በተከሳሹ መኪና መሆኑን ከማስረዳት ውጪ በባለሀብቱ በኩል ጥፋት
ስለመኖሩ ማረጋገጥ አይጠበቅበትም :: ጥፋት ባይኖርም በኃላፊነት ተጠያቂ የሆነ ሰው ከኃላፊነት ነፃ ለመሆን
ጉዳት የደረሰበትን ሠው ሌላ የወንጀል ድርጊት ለመጥቀስ አይችልም ፡፡ ጉዳዩ በፍ / ብ / ሥ / ሥ / ህ / ቁ . 343 ( 1 ) መሠረት ለመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ
ቤት ተመልሶ ከተላከ ፍርድ ቤቱ በመጀመሪያው ውሳኔ ሳይገደብ * The Afri ካሳውን መጠንካሊያሻሽል ይችላል W.AfricanLawArchive.com
አብዱልቃድር መሐመ ” ,,
የመ / ቁ 16270
ታህሣሥ 17 ቀን 1998 ዓ.ም ደኞች : መንበረፀሐይ ታደሰ
ሐጉስ ወልዱ ዳኜ መላኩ
መስፍን ዕቁበዮናስ አመልካች አዋሳ እርሻ ልማት ድርጅት ነገረፈጅ አቶ ጀማል አህመድ ቀረበ
ተጠሪ ... ኣቶ መሐሪ ማታ ጠበቃ አቶ ተሰማ አበበ ቀረበ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል ፡፡
ፍ ር ድ በዚህ መዝገብ ለሰበር ለቀረበው አቤቱታ መነሻ የሆነው ተከሣሽ የሆነው የአሁኑ አመልካች መኪናው አድርሷል በተሳለው የግጭት አደጋ ምክንያት ለተጉጂው ለአሁኑ ተጠሪ የጉዳት ካሣ ብር 28,800 ፣ የሞራል ካሣ ብር 1000 እና የህክምና ወጪ ብር 308 በጠቅላላው ብር 30,198 እንዲከፍለው መወሰኑ ነው ፡፡
ክርክሩን በመጀመሪያ ደረጃ ያየው የሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍ / ቤት ነው ። ከሣሽ የሆነው የአሁኑ ተጠሪ ሐምሌ 15 ቀን 1987 ዓም ሰሞተር ሣይክል በመጓዝ ላይ እያለ ንብረትነቱ የአዋሳ እርሻ ልማት ድርጅት በሆነ የሰሌዳ ቁጥር 3-00217 መኪና ተገጭቶ አንድ እግሩ በመጉዳቱ ወይም በመቆረጡ ምክንያት ከአደጋው በፊት እየሰራ ያገኝ የነበረው ገቢ መቋረጡን በመግለጽ የመኪናው ባለቤት በሕግ ባለበት ኃላፊነት መሠረት የጉዳት ካሣ ብር 58,600 እንዲከፍለው የሚጠይቅ ክስ ለሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍ / ቤት አቅርቦ ፍ / ቤቱ በኃላፊነቱ ጉዳይም ሆነ በካሣው መጠን ላይ ካከራከረና ማሥረጃ ም ከሰማ በኋላ ጉዳቱን ያደረሰው የተከሣሹ የአዋሳ እርሻ ልማት ድርጅት መኪና መሆኑ ስለተረጋገጠ ለደረሰው ጉዳት በሕግ ኃላፊነት አለበት ፣ በተከሣሹ መኪና ባይገጭ ኖሮ እግሩ ሊቆረጥ አይችልም ነበር ፣ እግሩ ከተቆረጠ ደግሞ ቀደም ሲል ሲሰራ የነበረውን ሥራ ተመልሶ ለመሥራት እንደማይችል ግምት ውስጥ በማስገባት በክሱ የጠየቀውን የጉዳት ካሣ በከፊል በመቀነስ
አደረሰ o
ለደረሰበት ጉዳት ብር 28,800 የሞራል ካሣ ብር 1000
ካሣ ብር 1000 እና ለህክምና ያወጣውን ወጪ ብር 308 በጠቅላላው ብር 30,198 ሊከፍለው ያገባል በማለት ወስኗል ፡፡
የአሁኑ አመልካች የነፍ ከፍተኛ ፍ / ቤት በኃላፊነቲ ጉዳይም ሆነ የካሣውን መጠን በማስመልከት የሰጠውን ውሣኔ በመቃወም ለደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍ / ቤት በመ / ቁ 3144 የይግባኝ አቤቱታ ሊያቀርብ የቻለ ቢሆንም ፍ / ቤቱ የአሁኑ ተጠሪ ቀርቦ መልስ እንዲሰጥበት አድርጉ የይግባችን ክርክር ከሰማ በኋላ በመጨረሻ ግንቦት 19 ቀን 1996 ዓ.ም መርምሮ በሰጠው ውሣኔ ክርክሩን በመጀመሪያ ደረጃ ያየው የዞኑ ከፍተኛ ፍ / ቤት በጉዳዩ ላይ የሰጠው ውሣኔ የሚታይበት ጉድለት የለም በማለት በፍ / ሥ / ሥ / ሕ / ቁ . 348 ( 1 ) መሠረት አጽንቶታል ።
አመልካች የክልሉ ሁለት ፍርድ ቤቶች በጉዳዩ ላይ በተመሣሣይ መንገድ የሰጡት ውሣኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት አለበት በሚል ምክንያት በዚህ መዝገብ ለሰበር አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን እቤቱታው ተመርምሮ ጉዳዩ ለሰበር ችሉት ቀርቦ እንዲታይ በመወሰኑ አመልካች በ 30 / 10 / 96 ዓ.ም ጽፎ ያቀረበው ማመልከቻ ለአሁኑ ተጠሪ ተልኮ ቀርቦ መልስ እንዲሰጥበት ታዞ በጠበቃው አማካኝነት ጥቅምት 5 ቀን 1997 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርቧል ። አመልካች በበኩሉ በተጠሪው
ባተጠሪው ጠበቃ በኩል በጽሑፍ የተሰጠውን መልስ ከተመለከተ በኋላ የመልስ መልስ ጽፎ ከመዝገቡ ጋር እንዲያያዝ አድርጓል ፡፡
ችሉቱም የኃላፊነቱን ጉዳይም ሆነ የካሣውን መጠን ከሕጉ በማገናዘብ መርምሯል ፡፡
በቅድሚያ የኦሁኑ አመልካች በተጠሪው ላይ ለደረሰው ጉዳት በሕግ ኃላፊነት አለበት የለበትም ? ጉዳቱ የደረሰው በተጉጂው ( ተበዳዩን በገዛ ራሱ ጥፋት ነው ለማለት የሚያስችል ምክንያት አለ ወይንስ የለም የሚለው ሲመረመር በፍሬ ነገር ረገድ የአሁኑ ተጠሪ ሞተር ሣይክል እየነዳ በመጓዝ ላይ እያለ ሁለተኛው ተከሣሽ ሲያሽከረክረው በነበረው ንብረትነቱ የአሁኑ አመልካች በሆነው የሰሌዳ ቁጥር 3.00211 መኪና ገጭቶ ከነሞተር ሣይክሉ በመውደቁ ምክንያት በአንድ እግሩ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት የተቆረጠ
መሆኑ ተረጋግጧል ፡፡
የግጭት ኣደጋ ሆኖ ከተገኘ ጉዳዩ ከውል ውጭ ስለሚደርስ ኃላፊነት
የሚመለከት ነው :: የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2081 ( 1 ) የአንድ መኪና ወይም የኣንድ ባለሞተር ተሽከርካሪ ባለቤት የሆነ ሰው አደጋውን ያደረሰው መኪናውን ወይም ባለሞተር ተሽከርካሪውን ለመንዳት ወይም ለማንቀሣቀስ ሳልተፈቀደለት ሰው ቢሆንም እንኳን መኪናው ወደ ባለሞተር ተሽከርካሪሁ ላደረሰው ጉዳት አላፊ የሚሆነው ባለሀብቱ፡ መሆኑን ይደነግጋል ። የአንድ መኪና ወይም ባለሞተር ተሽከርካሪ ባለቤት እጥፊ ሣይሆን ጉዳት ያደረሰው መኪና ወይም ባለሞተር ተሽከርካሪ ባለሀብት በመሆኑ ብቻ ለደረሰው ጉዳት በሕግ እላፊ ይሆናል ፡፡ ተጉጂው ወይም ተበዳዩ ጉዳቱ የደረሰው በተከሣሹ መኪና መሆኑን ከማሥረዳት
በባለሀብቱ ስለመኖሩ ማረጋገጥ አይጠበቅበትም ።
ያደረሰው ባለሀብት ከአላፊነት የሚድንባቸው የሕግ ምክንያቶች ያሉ ሲሆን ከእነዚህም አንዱ ጉዳቱ የደረሰው በተጉጂው ወይም በተበዳዩ ጥፋት ምክንያት እንደሆነ አላፊነት አያመጣም በሚል ሰፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2066 ( 2 ) ላይ የተመለከተው ነው ። ጉዳት ያደረሰው መኪና ባለሃብት ጉዳቱ የደረሰው በተጉጂው ጥፋት ምክንያት ነው የሚል መከላከያ ካለው የማስረዳት ሸክም የራሱ ይሆናል ፡፡ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2086 ( 2 ) ላይ እንደተመለከተው የአንድ መኪና ባለሀብት ጉዳቱ የደረሰው በከፊል ወይም በሙሉ ከተበዳዩ ጥፋት የተነሣ መሆኑን ካላረጋገጠ በቀር በከፊልም ሆነ በሙሉ ከኣላፊነቱ ሊድን አይችልም ፡፡
በቀረበው ጉዳይ የአሁኑ አመልካች ለደረሰው ጉዳት በተበዳዩ በኩል ጥፋት አለ በማለት የሚከራከረው በሁለት ምክንያቶች ሲሆን እንደኛው ተጠሪው የሌላ ድርጅት ሞተር ሣይክል ሰርቆ እየነዳ ሲሄድ ነው የተገጨው በሚል የቀረበ ነው ። የተሰረቀን ሞተር ሣይክል ወይም ሌላ ባለሞተር ተሽከርካሪ በሚነዳ ሰው ላይ ጉዳት ማድረስ በአላፊነት አያስጠይቅም የሚል ሕግ የለም ፡፡ የጉዳቱም መንስኤ ተበዳዩ የተሰረቀ ሞተር ሣይክል ይዞ መገኘቱ ወይም መንዳቱ ሣይሆን የአመልካችን መኪና ሲያሽከረክር የነበረው ሾፌር መንገዱን በማጥበብ ተጠሪው , የሚነዳውን ሞተር ሣይክል . ሊገጨው መቻሉ ነው ፡፡ በመሆኑም አመልካች ተጠሪው የተሰረቀ ሞተር ሣይክል እየነዳ ሲጓዝ ነው የተገጨው በሚል ያቀረበው ክርክር ሕጋዊ መከላከያ ሊሆን አይችልም ፡፡ ሁለተኛው ሞተር ሣይክል ለመንዳት የሚያስችል መንጃ ፈቃድ የለውም
የሚለው ነው ። መንጃ ፈቃድ የሌለው መሆኑ ብቻ ጉዳቱ የደረሰው በእርሱ * The A ጥፉት ነው ለማልት c ኤያስችልም ። መንጻት የሚገባው LY ተፍ c ዘይክሉን እየነዳ
ሲጓዝ የፈፀመው ጥፋት ምንድነው የሚለው ነው ። የአሁኑ አመልካች ደግሞ
ተጠሪው መንጃ ፈቃድ የሌለው መሆኑን የሚገልጽ በቀር በሥር ክርክሩ ወቅት ተጠሪው የፈፀመው ጥፋት መኖሩን እላስረዳም ። መንጃ ፈቃድ ሣይኖረው የሚያሽከረክርን ሰው በመኪና መግጨት በሕግ በአላፊነት ከመጠየቅ ሊያድን ስለማይችል አመልካች በዚህም ረገድ ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት የለውም ። በአጠቃላይ የአሁኑ አመልካች መኪናው ላደረሰው ጉዳት አላፊ ነው ተብሎ በመወሰኑ የተፈፀመ የሕግ ስህተት የለም ።
የካሣውን መጠን በተመለከተም ተጉጂው የእሁኑ ተጠሪ በአመልካች መኪና በተፈፀመው ግጭት የተነሣ አንድ እግሩ የተቆረጠ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በእግሩ መቆረጥ ምክንያት ቀደም ሲል የተሰማራበትን ሥራ ለመቀጠል አልቻለም ፡፡ ከአደጋው በፊት በወር ብር 120 ደመወዝ እየተከፈለው ሲሰራ የነበረ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማሥረጃ ክርክሩን በመጀመሪያ ደረጃ ለሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍ / ቤት መቅረቡን ከተሰጠው ለመረዳት ተችሏል ። የአሁኑ አመልካች ይህንን የሚያፈርስ , ሌላ ተቃራኒ ማሥረጃ አላቀረበም ። ፍ / ቤቱም በተጠሪው በደረሰበት አደጋ ምክንያት ገቢው ሊቋረጥ መቻሉንና ጉዳቱም ዘለቄታ ያለው መሆኑን በመገንዘብና ከአደጋው በፊት በየወሩ ሲያገኝ ነበር የተባለውን ደመወዝ በመነሻነት በመጠቀም በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2102 ( 1 ) መሠረት የጉዳት ካሣውን ልክ በርትዕ በማመዛዘን ወስኗል ። የካሣ አከፋፈልና ልክ የሚወሰነው ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2090 ጀምሮ በተከታታይ በተፃፉ ድንጋጌዎች መሠረት ነው ፡፡ የመጀመሪያው ቁጥር 2090 ( 1 ) በመደቡ በጉዳቱ ምክንያት ተበዳዩ የሚካሠው ለጉዳቱ ተመዛዛኝ የሆነ ኪሣራ በመከፈል እንደሆነ የሚገልጽ ሲሆን ቁጥር 2093 ደግሞ ለደረሰው ጉዳት አላፊ መሆኑ
መሆኑ በሕግ የታወቀው ሰው የሚከፍለው የጉዳት ካሣ እላፊነቱን ያመጣው ጉዳይ በተበዳዩ ላይ ከደረሰው ጉዳት ጋራ እኩል ሆኖ መመዛዝን እንዳለበት የሚደነግግ ነው ። ቀጥሉ ያለው ቁጥር 2092 ሲታይ ለብህደፊት ሊደርስ ይችላል ተብሎ የሚገመተው ጉዳት የተረጋገጠ በሆነ ጊዜ እስኪፈፀም ድረስ ይጠቅ ካሣ ሊከፈል የሚገባ መሆኑን ያስረዳል ፡፡ ከዚህ ሌላ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2 102 ( 1 ) ላይ የሠፈረውን ድንጋጌዎ ” ስንመለከት ስለጉዳቱ ምን ያህል ኪሣራ እንደሚከፈል በትክክል ለመወሰን ያልተቻለ እንደሆነ
የነገሮቲን ሁኔታዎችንና ያደረገውን አመዛዝነው በመገመት የኪሣራሲ l ውን ልክ በርትዕ እንዲወስኑ የሚፈቅድ ነው ::
በዚህ መዝገብ በቀረበው ጉዳይ የጉዳት ካሣሁ መባን ስለመብነት ከላይ W አቶዶች
እለመብዛ ። ድንጋጌች አንፃር
ሺመረመር
በአሁኑ ተጠሪ ላይ በመኪና ግጭት በደረሰው አደጋ ምክንያት አንድ እግሩ ሊቆረጥ መቻሉ ከአደጋው በፊት እየሰራ ሲያገኝ የነበረውን ገቢ ያስቀረት
ብቻ ሣይሆን ወደፊት የሚኖረውን የኢኮኖሚ እድገት እንደሚጐዳው ይገመታል ። በነበረው ሥራ በመቀጠል ወይም በሌላ ሙያ በመሰማራት የራሱን የገቢ ምንጭ ሊያሻሽልና ሊያሣድግ ይችላል ። በደረሰበት አደጋ የአንድ እግሩ መቆረጥ ደግሞ በዚህ የወደፊት እድሉ ላይ ሁሉ ተጽእኖ ያደርጋል ፡፡ ይህ ሁሉ ሲታይ በወቅቱ የ 23 ዓመት እድሜ
ዓመት እድሜ በረው የተባለው የአሁኑ ተጠሪ በዋናው መንቀሣቀሻ በእግሩ ላይ የደረሰው ከፍተኛ ጉዳት እና ይኼው ሳለው የኢኮኖሚ ጥቅም ላይ ያስከተለው ጉዳት ተመዛዝኖ በርትዕ ብር ካሣ እንዲከፈለው
እይታ በዝቷል
በዝቷል ለማለት አይቻልም :: የሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍ / ቤት በመጀመሪያ ቀርቦላት በነበረው ክሥ መነሻ ጉዳዩን መርምሮ የጉዳት ካሣ ብር 16.000 እንዲከፈለው ከወሰነ በኋላ ሰይግባኝ ጉዳዩን የተመለከተው የክልሉ ጠቅላይ ፍ / ቤት የአሁኑ አመልካች መከላከያ መልስ እና ማሥረጃ እቅርቦ ክርክና ማሥረጃ ው ከተጠናቀቀ በኋላ
በፍ / ሥ / ሥ / ሕ / ቁ 343 ( 1 ) ከመለሰለት በኋላ ከሣሹ የአሁኑ ተጠሪ በፍ / ሥ / ሥ / ሕ / ቁ .91 ( 1 ) መሠረት ክሱን እሻሽሉ እንዲቀርብ ተፈቅዶለት በአዲስ መልክ ክርክሩ ተካሂዶ በመጨረሻ የካሣውን በመወሰኑ ተፈጸ'ሟል የምንለው የሕግ ስህተት የለም ፡፡ ጉዳዩ በፍ / ሥ / ሥ / ሕ / ቁ 34 3 ( 1 ) መሠረት ለመጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት ተመልሶ ከተላከ ፍ / ቤቱ በመጀመሪያው ውሣኔ ሣይገደብ የካሣውን መጠን ዝቅ ወደ ከፍ አድርጉ ከመወሰን የሚከለክለው ሕግ የለም ፡፡
በኣጠቃላያ በዚህ ጉዳይ በኃላፊነቱ ጉዳዩም ሆነ በካሣው አወሳሰን ረገድ ተፈጽሟል የሚባል የሕግ ስህተት አልተገኘም ፡፡
ው ሣ ኔ 1. የክልሉ ጠቅላይ ፍ / ቤት ይህንን ጉዳይ በማስመልከት በይ ? መ / ቁ .31 4 4 ,
ግንቦት 19 ቀን 1996 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በፍ / ሥ / ሥ / ሕ / ቁ . · : “ 348 ( 1 ) መሠረት ፀንቷል ፡፡ 2. በዚህ መዝገብ በተደረገው ክርክር ምክንያት የደረሰህ ን ወጪና ኪ'ሃራ ግራቀኙ የየራሣቸውን ቻሉ ፡፡
መዝገቡ ተዘግቷል ፡፡ የመለስ ፡፡
* የማይነካካ rd አይሰካ aw ዳኞች b ፈፎ e W ት ፡፡

You must login to view the entire document.

Enter your email address and password to login.
Please enter a valid email address
Please enter your email address
Please enter your password
Password must be at least 8 characters long
Forgot your password?