የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ነጋሪት ጋዜጣ አምስተኛ ዓመት ቁጥር ፴፭ አዲስ አበባ- የካቲት ፳፭ ቀን ፲፱፻፲፩ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፩፻፷፬ / ፲፱፻፲፩ ዓ.ም ከኔዘርላንድ መንግሥት ጋር ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋትና ዋስትና ለመስጠት የተደረገው ስምምነት ማጽደቂያ ገጽ ፩ሺህ፲፪ አዋጅ ቁጥር ፩፻፷፬ / ፲፱፻፲፩ ከኔዘርላንድ መንግሥት ጋር ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋትና ዋስትና ለመስጠት የተደረገውን ስምምነት ለማጽደቅ የወጣ አዋጅ በኔዘርላንድ መንግሥትና በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት መካከል ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት እና ዋስትና ለመስጠት ነሐሴ ፲፭ ቀን ፲፱፻፲ ዓም : አዲስ አበባ ላይ ስምምነት የተፈረመ ስለሆነ ፡ ስምምነቱ በሚገባ ሥራ ላይ የሚውለው በተዋዋዮቹ ሀገሮች ሕጐች መሠረት ስምምነቱን ህጋዊ ለማድረግ መሟላት የሚገባቸው ህገ መንግሥታዊ ሥርዓቶች መፈጸማቸውን የሚያረጋግጡ ሰነዶች ልውውጥ ከተደረገበት ከሁለተኛው ወር የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ እንደሚሆን በስምምነቱ ውስጥ የተገለፀ ስለሆነ ፣ ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የካቲት፳፭ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓ • ም • ባደረገው ስብሰባ ያጸደቀው ስለሆነ ፡ በሕገመንግሥቱ አንቀጽ ፶፭ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እና ( ፲፪ ) መሠረት ከዚህ እንደሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ ከኔዘርላንድ መንግሥት ጋር ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋትና ዋስትና ለመስጠት የተደረገው ስምምነት ማጽደቂያ አዋጅቁጥር ፩፻፷፬ / ፲፱፻፲፩ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ያንዱ ዋጋ ብር 2:30 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ : ዥሺ፩ ገጽ፩ሺህ፲፫ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፭ የካቲት ፳፭ ቀን ፲፱፻፶፩ ዓ • ም • ፪ ስምምነቱ ስለመጽደቁ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በኔዘርላንድ መንግሥት መካከል ኢንቨስትመንትን ለማስፋ ፋትና ዋስትና ለመስጠት ነሐሴ ፲፭ ቀን ፲፱፻፲ ዓም : አዲስ አበባ ላይ የተፈረመው ስምምነት ጸድቋል ። ፫ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ባለሥልጣን ኃላፊነት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ባለሥልጣን ስምምነቱ በሥራ ላይ እንዲውል ለማድረግ በዚህ አዋጅ ሥልጣን ተሰጥቶታል ። ፬ • አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከየካቲት ፳፭ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓ.ም. ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ የካቲት ፳፭ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓም : ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ