×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
አዋጅ ቁጥር 88/1989 ዓምየኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትአባላት በመራጫቸው አመኔታ በሚያጠብትጊዜ ስለሚወለድእርምጃ የወጣ አዋጅ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ሦስተኛ ዓመት ቁጥር አዲስ አበባ - ሰኔ ፴ ቀን ፲፱፻፳፱ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፳፯ / ፲፱፻፷፬ ዓ . ም . የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በመራጮቻቸው አመኔታ በሚያጡበት ጊዜ ስለሚወሰድ እርምጃ የወጣ አዋጅ . . . . . ገጽ ፮፻፳፭ አዋጅ ቁጥር ፳፰ / ፲፱፻፷፱ ዓም የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በመራፎቻቸው ኣመኔታ በሚያጡበት ጊዜ ስለሚወሰድ እርምጃ - የወጣ አዋጅ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመንግሥት አንቀጽ ፲፬ ንዑስ አንቀጽ ( ፰ ) ማናቸውም የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የመረ ጠው ሕዝብ አመኔታ ባጣ ጊዜ በሕግ መሠረት ከምክር ቤት አባልነቱ እንደሚወገድ ስለሚደነግግ ይህ መሠረታዊ ዲሞክራሲያዊ መርሆ በሥራ ላይ መዋሉ አስፈላጊ በመሆኑ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፭ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውኛል ። ክፍል አንድ ፩ አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ | This Proclamation may be cited as the Loss of የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በመራጮቻቸው አመኔታ በሚያጡበት ጊዜ ስለሚወሰድ እርምጃ የወጣ አዋጅ ቁጥር ተ $ / pጀቴቑ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። የ ትርጓሜ ፩ . በዚህ አዋጅ ውስጥ ' “ ተመራጭ ” ማለት በኢትዮጵያ የምርጫ ቦርድ አስፈጻሚነት በተካሄደ ምርጫ አንድን የምርጫ ክልል ለመወከል የተመረጠና በምርጫ ቦርድ የምስክር ወረቀት የተሰጠው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ነው ያንቶ ዋጋ 160 ነጋሪት ጋዜጣ ' ሣቁ ዥሺ፩ ገጽ ፮፻፳፮ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፫ ሰኔ ፴ ቀን ፲፱፻፷፱ ዓ . ም . Federal Negarit Gazeta - No . 53 7 " July 1997 – Page 626 ፪ . “ የምርጫ ክልል ” ማለት በምርጫው ሕግ መሠረት ፩፻ ሺህ ሕዝብ እና በልዩ ምርጫ ክልል የተወከሉትንም ያካተተ ወረዳ ወይም ወረዳዎችማለት ነው : ፫ “ መራጭ ” ማለት በሕጉ መሠረት አሥራ ስምንት ዓመት የሞላውና በምርጫ ክልሉ ለሁለት ዓመት ወይም በላይ የኖረ ግለሰብ ነው : | “ ወረዳ ” ማለት የክልሉ ምክር ቤት በሚወስነው መሠረት | የተከለለ የአስተዳደር እርከን ነው ። ክፍል ሁለት , መብቶችና ግዴታዎች _ ፫ - መሠረታዊ መብቶች ፩ . ማንኛውም ዜጋ ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት ለሕዝብ ተወካ ዮች ምክር ቤት ተወካዩን የመምረጥ መብት አለው ። ፪ . ማንኛውም ዜጋ ከሌሎች መራጮች ጋር በመሆን የወከለውን ተመራጭ በየጊዜው መመርመር ፡ መገምገምና መመዘን ይችላል ። ማንኛውም ዜጋ ለወከለው ተመራጭ ሲሰጥ የነበረውን ድጋፍ የማቋረጥ ወይም የመቀጠል መብት አለው ። ፬ . ማንኛውም ተመራጭ በመራጮች የሚቀርብለትን ምስጋና ፡ ተግሳጽ ፡ ግምገማ ወይም ሂስ በግልጽና በአደባባይ የማስተጋ ባት ፡ የመቃወምና ሂስ የማድረግ መብት አለው ። ፬ - የመራጮች አመኔታ የሚለካበት ዘዴ አንድ ተመራጭ የመራጮች አመኔታ የለውም ሊባል የሚችለው ፤ ፩ . በተወከለበት የምርጫ ክልል ከሚገኙ መራጮች ከ፲፭ሺህ በላይ የምርጫ ቦርድ በሚያወጣው ደንብ መሠረት የይውረ ድልን ጥያቄ ለምርጫ ቦርድ ሲያቀርቡ ፤ ፪• በተወከለበት የምርጫ ክልል በሚገኙ ፲ ሺህ መራፎች አሳሳቢነት የምርጫ ቦርድ በሚያወጣው ደንብ መሠረት የወረዳ ምክር ቤቶች በአብላጫ ድምጽ ተወካዩ ተመልሶ እንዲጠራ ውሳኔ ያሳለፉ እንደሆነ ፤ ፫ የልዩ ምርጫ ክልል ተወካይን በተመለከተ የምርጫ ቦርድ በሚያወጣው ደንብ መሠረት የመራፎች አመኔታ ማጣቱ ሲረጋገጥ ፣ ፱ . የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመራፎች በሚያሳየው ሥነ ምግባር የወከለውን ሕዝብ በብቃት ሊወክል አልቻለም ብሎ በሁለት ሦስተኛ ድምዕ ሲወስን ይሆናል ። ጅ የሥነ ምግባር መለኪያዎች ፩ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ተገዥነቱ በሕገ | 5 . Standards of Good Conduct መንግሥቱ አንቀጽ ፵፬ ( ፱ ) ( ሐ ) ለሕሊናውም ጭምር በመሆኑ በማናቸውም ረገድ የጸዳና የጠራ መሆን አለበት ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሕዝብን ጉዳይ በሚወያይበትጊዚ ሀቀኛና ግልጽ የመሆን ኃላፊነት አለበት ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሀሰት ማስረጃዎች መፍጠር ፡ መቅጠፍ ፡ ያልተጣሩ ጉዳዮች ወደ ምክር ቤቱ መድረክ ማቅረብና መዋሽት ዋነኞቹ የሥነ ምግባር ብልሹ ነት መግለጫዎች ናቸው ። . በሥነ ምግባር ብልሹነት ላይ የሚወሰዱ እርምጃዎች ፩ . ምክር ቤቱ በሚያቋቁመው ኮሚቴ አማካይነት በሥነ ምግ ባር ብልሹነት የተከሰሰ ተመራጭ ጉዳይ ይጣራል ። ግጽ ፮፻፳፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፫ ሰኔ ፴ ቀን ፲፱፻፰፱ ዓም ጀ አጣሪ ኮሚቴው በሚሰጠው የውሳኔ ሃሳብ ምክር ቤቱ ተወያይቶ ይወስናል ። ፫ ምክር ቤቱ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው የሚከተሉትን እርምጃዎች መውሰድ ይችላል ፤ ሀ ) የሥነ ምግባር ብልሹነት ለተገኘበት ተመራጭ ለሕዝብ ይፋ በሆነ መልኩ የማስጠንቀቂያ ተግሳጽ ሊሰጠው ይችላል ፤ ለ ) የሥነ ምግባር ብልሹነት የተገኘበት ተመራጭ ለተወሰነ ጊዜ ከምክር ቤቱ እንዲታገድ ማድረግ ይችላል ፤ ሐ ) የሥነ ምግባር ብልሹነት የተገኘበት ተመራጭ በዚህ ንዑስ አንቀጽ ( ሀ ) እና ( ለ ) የተደነገጉትን ቅጣቶች ከተቀበለ በኋላ የሥነ ምግባር ብልሹነቱ የቀጠለ እንደ ሆነ ምክር ቤቱ በሁለት ሦስተኛ ድምፅ ከምክር ቤት አባልነቱ ሊሰርዘው ይችላል ። ፬ ) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) የተመለከቱት ተከታታይ የዲስፕሊን እርምጃዎች እንደጥፋቱ ክብደት ቅደም ተከተላቸው ሳይጠበቅ ተፈጻሚ ሊደረጉ ይችላሉ ። ከምክር ቤቱ መወገድ የሚኖረው ውጤት ፩ አንድ ተመራጭ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፪ እና ፭ መሠረት መቀመጫውን ሲያጣ በምርጫ ቦርድ የተሰጠው የተወካይ ነት መታወቂያ ሕጋዊነቱ ያከትማል ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ የምክር ቤት መቀመጫውን ያጣ የቀድሞ ተመራጭ በምርጫ ክልሉ መቀመጫውን ለመሙላት በሚደረገው ምርጫ ተወዳዳሪ ለመሆን ይችላል ። ፫ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) የተጠቀሰው ምርጫ የሚከናወነው የቀድሞው ተመራጭ የምክር ቤት መቀመጫ ውን ካጣበት ቀን ጀምሮ ከ፫ ወራት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ይሆናል ። ፰ አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ _ ይህ አዋጅ ከሰኔ ፴ ቀን ፲፱፻፫፱ ዓም ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ሰኔ ፴ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?