×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 18/1989 ዓም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ሦስተኛ ዓመት ቁጥር ፲፩ አዲስ አበባ ሰኔ ፴ ቀን ፲፱፻፳፱ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፲፫ / ፲፱፻፳፱ ዓ.ም. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ማቋቋሚያ የሚኒስ ትሮች ምክር ቤት ደንብ . ገጽ ፮፻፲፩ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፲፰ ፲፱፻፳፱ ዓም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽንን ለማቋቋም የወጣ ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲ ያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ ኣካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻ዥ፯ አንቀጽ ፭ እና በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ / ፲፱፻፴፬ በአንቀጽ ፵፯ ፩ / ሀ መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፲፰ / ፲፱፻ T ሀ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . መቋቋም ፩ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ( ከዚህ በኋላ “ ኮርፖሬሽኑ ” እየተባለ የሚጠራ ) የመንግሥት የልማት ድርጅት ሆኖ በዚህ ደንብ ተቋቁሟል ። ፪ • ኮርፖሬሽኑ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ / ፲፱፻ዥ፱ መሠረት ይተዳደራል ። ፫ . ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን በመንግሥት የሚሰየም አካል የኮርፖሬሽኑ ተቆጣጣሪ ባለሥ ልጣን ይሆናል ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖ.ሣ.ቁ. ፱ሺ፩ ገጽ ፲፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፶፩ ሰኔ ፴ ቀን ፲፱፻፲፱ ዓም ፬ ዋና መሥሪያ ቤት የኮርፖሬሽኑ ዋና መሥሪያ ቤት አዲስ አበባ ሆኖ ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች እንደአስፈላጊነቱ በማናቸውም ሥፍራ ሊኖረው ይችላል ። የኮርፖሬሽኑ ዓላማ ( በመንግሥት ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ የል ማት ፖሊሲዎችና እቅዶች ላይ በመመርኮዝ ) የኤሌክትሪክ ኃይል ማምረት፡ ማስተላለፍ፡ ማከፋፈል እና መሽጥ፡ በተጨማሪም ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ ሥራዎችን መሥራት ነው ። ፳ ካፒታል ለኮርፖሬሽኑ የተፈቀደለት ካፒታል ብር ቼ ቢሊዮን ፩፻ ሚሊዮን ( ስድስት ቢሊዮን አንድ መቶ ሚሊዮን ብር ሲሆን ከዚህ ውስጥ ብር ፪ ቢሊዮን ፳፻፭ ሚሊዮን ( ሁለት ቢሊዮን ስድስት መቶ ሰባ ሚሊዮን ብር ) በጥሬ ገንዘብና በዓይነት ተከፍሏል ። ፮ ኃላፊነት ኮርፖሬሽኑካለው ጠቅላላ ንብረት በላይ በዕዳ ተጠያቂ አይሆንም ። ፰ ኮርፖሬሽኑ የሚቆይበት ጊዜ ኮርፖሬሽኑ ላልተወሰነ ጊዜ ይቆያል ። ፱ የመብትና ግዴታ መተላለፍ በመንግሥትማስታወቂያ ቁጥር ፪፲፫ / ፲፱፻፴፰ መሠረት ይተዳደር የነበረው የቀድሞው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ መብራትና ኃይል ባለሥልጣን መብትና ግዴታዎች በዚህ ደንብ ለኮርፖሬሽኑ ተላልፋል ። ፲ ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ ይህ ደንብ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ሰኔ ፴ ቀን ፲፱፻፳፬ ዓ.ም. መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?