የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ
ስድስተኛ ዓመት ቁጥር ፲፫ አዲስ አበባ ታህሣሥ ፲፪ ቀን ፲፱፻፺፪
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፷፩ ፲፱፻፺፪ ዓም ‥ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፷፩ ፲፱፻፺፪ መቀሌ ዩኒቨርሲቲን ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ ፲፱፻፹፯ አንቀጽ ፭ መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ።
፪ · ትርጓሜ
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ
አጭር ርዕስ
ይህ ደንብ “ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፷፩ ፲፱፻፺፪ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ።
ገጽ ፩ሺ፪፻
ክፍል አንድ
በዚህ ደንብ ውስጥ፡
፩ “ መንግሥት ” ማለት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት ነው፡
፪ “ ቦርድ ” ማለት በዚህ ደንብ አንቀጽ ፮ መሠረት የተቋቋመው የዩኒቨርሲቲው ቦርድ ነው
፫
ያንዱ ዋጋ
“ ጉባዔ ” ማለት በዚህ ደንብ አንቀጽ ፰ መሠረት የተቋቋመው የዩኒቨርሲቲው ጉባዔ ነው
“ የአካዳሚክ ሠራተኛ ” ማለት በማስተማር ወይም በምርምር ተግባር ላይ የተሠማራ ሠራተኛ ነው ፣
| pursuant to Article 5 of the Definitions of Powers and Duties
ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፹ሺ፩