የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አሥራ አንደኛ ዓመት ቁጥር ፩ አዲስ አበባ መስከረም ፲ ቀን ፲፱፻፳፯ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ( ቻርተር ) ቁጥር ፩፻፲፩ / ፲፱፻፵፯ ዓም • የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማቋቋሚያ ደንብ ገጽ ፪ሺ፰፻፲፭ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ( ቻርተር ) ቁጥር ፩፻፲፩ / ፲፱፻፲፯ የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲን ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ( ቻርተር የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፷፯ አንቀጽ ፭ እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርት አዋጅ ቁጥር ፫፻፵፩ / ፲፱፻፲፭ አንቀጽ ፰ መሠረት ይህን | pursuant to Article 5 of Definitions of Powers and Duties of ደንብ ( ቻርተር አውጥቷል ። ክፍል አንድ ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ቻርተር “ የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማቋቋሚያ የሚኒስ የ ትሮች ምክር ቤት ደንብ ( ቻርተር ቁጥር ፩፻፲፩ / ፲፱፻፲፯ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ በዚህ ቻርተር ውስጥ ፡ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያ | 2 . Definitions ሰጠው ካልሆነ በስተቀር ፣ ፩ ) “ አዋጅ ” ማለት የከፍተኛ ትምህርት አዋጅ ቁጥር ፫፻፶፩ / ፲፱፻፶፭ ነው ። ፪ ክልል ” ማለት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሕገመንግሥት አንቀጽ ፵፯ ፩፯ ) የተጠቀሰው ክልል ፫ ) “ መንግሥት ” ፡ “ ሚኒስቴር ” ፡ “ ሚኒስትር ” ፣ “ ቦርድ ” “ ሴኔት ” ፣ “ የአካዳሚክ ሠራተኛ ” ፣ “ ፈንድ ” ፡ “ ድርጅት ” ፣ “ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ” የሚሉ ቃላት በአዋጅ የተሰጣቸው ትርጉም ይኖራ ያንዱ ዋጋ 4.40 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፰ሺ፩ ፬ ) ለፈንዱ ዓላማ መሳካት የሚያስፋ ገጽ ፪ሺ፱፻፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፩ መስከረም ፲ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓም : ፳፬ • የድርጅቱ የፋይናንስ መግለጫና የሥራ እንቅስቃሴን ስለማ | 24. Submission of Enterprise and Activity Report of the የድርጅቱ የፋይናንስ መግለጫና የሥራእንቅስቃሴ የድርጅቱ የበጀት ዓመት ካለቀበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት የ፫ ወራት ጊዜ ውስጥ በሚመለከተው የድርጅቱ አካል ለቦርዱ መቅረብ አለበት ። ፳፭ ስለ ፈንድ መቋቋም ዓላማና የገቢ ምንጩ በአዋጁ የተገለጸው የዩኒቨርሲቲው ፈንድ በዚህ ደንብ ተቋቁሟል ። ፳፮ የፈንዱ አካላት ፩ ) ፈንዱ ፣ ( ሀ ) የፈንዱ አስተዳደር ቦርድና ( ከዚህ በኋላ ቦርድ ተብሎ የሚጠራ ) ( ለ ) ሴክሬታሪያት ይኖረዋል ። ፪ ) ቦርዱ ተጠሪነቱ ለዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ይሆናል ። ፳ : የፈንዱ ቦርድ አባላት ፩ ) ቦርዱ በዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት የሚሰየሙ አባላት ይኖሩታል ። ፪ ) የቦርዱ የሥራ ዘመን ሁለት ዓመት ይሆናል ። ፫ ) የቦርዱ አባላት በማናቸው ሁኔታ ሥራቸውን መሥራት | 28. Duties and Responsibilities of the Fund Board ካልቻሉ በምትካቸው አዲስ አባል ይሰየማል ። ፳፰ የፈንዱ ቦርድ ሥልጣንና ተግባር ቦርዱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባር ይኖሩታል ፣ ፩ ) የፈንዱ ዓላማዎችን ሥራ ላይ መዋሉን ይቆጣጠራል ለአፈጸጸማቸው አስፈላጊውን መመሪያ ያወጣል ፣ ፪ ) ከልዩ ልዩ የፈንዱ ምንጮች የተገኙ ገቢዎች በተገቢ ሁኔታ ሥራ ላይ መዋላቸውን በተመለከተ በሴክሬታ ሪያቱ የሚቀርብለትን ሪፖርት መርምሮ ያጸድቃል ፣ ፫ ) የፈንዱ ገቢዎች በየጊዜው መሰብሰባቸውን ያረጋ ሌሎችተግባራትን ያከናውናል ። ፳፱ • የፈንዱ ቦርድ ስብሰባዎች የቦርዱ ስብሰባዎች የሚካሄዱበት ሁኔታና የድምጽ አሰጣጡ ሥነ ሥርዓት ቦርዱ በሚያወጣውየውስጥ ደንብ ይወሰናል ። ፴ የአስፈጻሚ ሴክሬታሪያቱ ሥልጣንና ተግባር አስፈጻሚ ሴክሬታሪያቱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባር ይኖሩታል ። ፩ ) ዓመታዊ በጀት ፣ የሥራ እንቅስቃሴና የሂሣብ መግለጫ ሪፖርቶችን ለፈንዱ ቦርዱ አቅርቦ ያጸድቃል ፣ ፪ ) በፈንዱ ድጋፍ የሚካሄዱ ፕሮጀክቶችን ይመረምራል ፣ በቦርዱ መመሪያ መሠረት የፕሮጀክቶቹን የሥራ ማስኬጃ ገንዘብ ይፈቅዳል ፣ ፫ ) ለፈንዱ ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ሊሆኑ የሚችሉ ሁኔታ ዎችን ያጠናል ፣ ፬ ) የቦርዱን የሥራ መዛግብት ፣ ዘገባዎችና የስብሰባ ቃለ ጉባዔዎችን ይይዛል ፣ የቦርዱ ውሣኔዎችን በትክክል መፈጸማቸውን ያረጋግጣል ፣ ፭ ) በፈንድ ቦርዱ የሚሰጡ ሌሎች ሥራዎችን ያከናውናል ። ፴፩ የፈንዱ ሴክሬታሪያት ዳይሬክተር ሥልጣንና ተግባር የፈንዱ ሴክሬታሪያት ዳይሬክተር ፈንዱን በሚመለከት ጉዳዮች ተጠሪነቱ ለቦርዱ ሆኖ በዚህ ደንብ አንቀጽ ፴ የተመለከቱትን የሴክሬታሪያቱን ሥልጣንና ተግባርሥራላይ ያውላል ። ገጽ ፪ሺ፬፻፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፩ መስከረም ፲ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓም : ክፍል ስድስት ስለ ልዩ ልዩ ሁኔታዎች ፴፪ ተፈጻሚነት ስለማይኖራቸው ሕጎች ይህን ቻርተር የሚቃረኑ ደንቦችና መመሪያዎች ተፈጻሚነት አይኖራቸውም ። ፴፫ : የመብትና ግዴታ መተላለፍ አርባምንጭ በመባል የሚታወቀው ዩኒቨርሲቲ በዚህ ቻርተር ከመቋቋሙ በፊት ያለው መብትና የነበረበት ግዴታ በዚህ ቻርተር ለዩኒቨርሲቲው ተላልፋል ። ፴፬ • ቻርተሩ የሚጸናበት ጊዜ ይህ ቻርተር በነጋሪት ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ መስከረም ፲ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓም መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ገጽ ፪ሺ፰፻፲፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፩ መስከረም ፲ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓም : ክፍል ሁለት የዩኒቨርሲቲው መቋቋም ፫ መቋቋምና ተጠሪነት ፩ ) አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ( ከዚህ በኋላ “ ዩኒቨርሲቲ ” [ 3. Establishment and Accountability ተብሎ የሚጠራ ) ራሱን የቻለና የሕግ ሰውነት ያለው ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ሆኖ በዚህ ቻርተር ተቋቁሟል ። ፪ ዩኒቨርሲቲው በሥሩ የሚከተሉት ተቋማት ፣ ፋካል ቲዎች እና ትምህርት ቤቶች ይኖሩታል ፣ ሀ ) ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ፣ ለ ) ምህንድስና ፋኩልቲ ፣ ሐ ) ሳይንስ ፋኩልቲ ፣ መ ) የማኅበራዊ ሣይንስ ፣ ሁማኒቲስና ቢዝነስ ፋኩልቲ፡ ሠ ) የድህረ ምረቃ ትምህርት ቤት ፣ ረ ) ወደፊት በቦርዱና በሚኒስቴሩ የሚቋቋሙ ሌሎች ፋኩልቲዎች ፣ ኮሌጆችና ተቋማት ፣ ፫ ዩኒቨርሲቲው ተጠሪነቱ ለትምህርት ሚኒስቴር ይሆናል ። ዩኒቨርሲቲው የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል ። ፩ ) ሀገሪቱን በተለያዩ ሙያዎች ሊያገለግል የሚችል የሰለጠነ የሰው ኃይል በብዛትና በጥራት ማፍራት ፣ ፪ ) የዘር ፣ የሃይማኖት ፣ የፆታ ፣ የፖለቲካና የመሳሰሉት ልዩነቶች የማይደረግበት የከፍተኛ ትምህርት አገል ግሎት መስጠት ፣ ፫ ) ችግር ፈቺ የሆነና የሀገሪቱን እምቅ ሃብት ሥራ ላይ ለማዋል የሚያስችል ትምህርታዊና ተቋማዊ ሥርዓት መዘርጋት እና ጥናትና ምርምር ማድረግ ፣ ፬ ) ከሀገሪቱእናከክልሉፍላጎትእናዕድገት ጋር የተጣጣመ የከፍተኛ ትምህርት እና የኅብረተሰብ አገልግሎት መስጠት ፣ ፭ ) የዩኒቨርሲቲውን ተጠያቂነት የሚያረጋግጥ ሥርዓት መዘርጋት ፣ ፮ ) በአስተዳደር ውሳኔ አሰጣጥ ላይ የሚመለከተውን ሁሉ ተሳትፎ ማረጋገጥ ፣ የአሳታፊነት ባህልን መፍጠርና ማሣደግ ፣ ፯ ) በሰዎች መካከል መከባበር ፣ መቻቻልና አብሮ የመኖር ባህል እንዲጎለብትና እንዲሰርጽ ማድረግ ፣ ፭ ሥልጣንና ተግባር ዩኒቨርሲቲው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ። ፩ ) ፋኩልቲዎች ፣ ኮሌጆችና ሌሎች የትምህርትና የምርምር ተቋሞች አቋቁሞ የቅድመ ምረቃና የድህረ ምረቃ ፕሮግራም ሥራ ማካሄድ ፣ ፪ ) የምስክር ወረቀት ፣ ዲፕሎማና ዲግሪ እንዲሁም ሌሎች የተለያዩ የአካዳሚክ ሽልማቶችን መስጠት እንዲሁም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ ሰዎች የአካዳሚክ ሜዳይ ሽልማትና ማዕረግ መስጠት ፣ ፫ ) ለሀገር ዕድገት ቅድሚያ በሚሰጥባቸው መስኮች ላይ ጥናትና ምርምር ማድረግ ፣ ፬ ) ሴሚናሮች ፣ ዓውደ ጥናቶችና ሲምፖዚየሞችን ማዘጋ ጀትና ማካሄድ ፣ ፭ ) በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ፣ የምርምር ተቋሞችና ተመሳሳይ ዓላማ ካላቸው አካላት ጋር ግንኙነት መመሥረት ፣ ፮ ) የማማከር ፣ የሥልጠናና ሌሎች አገልግሎቶች ለኅብረ ተሰቡ ፣ ለክልል መስተዳድሮችና ለፌዴራል መንግሥት በአግባቡ መስጠት ፣ * እርምር ፕሮግ ገጽ ፪ሺ፰፻፵፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋቁጣ ቁጥር ፩ መስረከም ፲ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓም ፯ ) የትምህርት መጽሔቶችና ማቋቋምና ማሰራጨት ፣ ፰ ) የማንኛውንም ንብረት ባለቤት የመሆን ፣ ፱ ) ከሦስተኛ ወገን ጋር ውል መፈራረም ፣ ፲ በሥሙ የመክሰስና የመከሰስ ፣ ፲፩ ) ለሚሰጠው አገልግሎት ተገቢ ክፍያ የማስከፈል ፣ ፲፪ የገቢ ፈንድ እና የገቢ ማመንጫ ድርጅት ማቋቋም ማስተዳደር ፣ ፲፫ የዩኒቨርሲቲውን ዓላማ ለማስፈጸም አስፈላጊ የሆኑ ሌሎች ተግባራትን ማከናወን ። ፮ : ነጻነትና ተጠያቂነት በቦርዱ የውስጥ ደንቦችና በሌሎች ህጎች የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ዩኒቨርሲቲው በተለይ በሚከተሉት ላይ ተጠያቂነት ላይ ይኖረዋል ። ( ሀ ) የሲቪል ሰርቪስ መርሆዎችን መሠረት በማድረግ የተቋሙ ሠራተኞች አስተዳደር ፣ ቅጥር ፣ ዕድገት ፣ እገዳና ሌሎች ጉዳዮችን መፈጸም ፣ ( ለ ) የኢትዮጵያን የፋይናንስ አስተዳደር ህግ በመን ተራስ በፋይናንስ አስተዳደር ፣ በውስጡላሉ አካላት በጀት የማከፋፈልና በአግባቡ የመጠቀም ፣ ( ሐ ) የሀገሪቱን እና የዓለም አቀፍ ደረጃዎችን በጠበቀ መልኩሥርዓተትምህርት የመገምገምናየማሻሻል ፣ ( መ ) የግልጽነትና ተጠያቂነት የተከተለ የምርምር ስትራቴጂ መንደፍና የማስፈጸም ፣ ( ሠ ) የሲቪል ሰርቪስ መርሆዎችን በመመርኮዝ የውስጥ አደረጃጀትን የመወሰን ፣ ( ረ ) የትምህርት ፣ የምርምርና የኅብረተሰብ አገልግሎት ኃላፊነቱን ለመወጣት ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የትብብር ግንኙነት መፍጠር ፣ ( ሰ ) የገቢ ማመንጫ ድርጅትን ማቋቋምና ገቢዎቹን መጠቀም ፣ ፪ በህግ በሌላ ሁኔታ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ዩኒቨር ሲቲው ዕውነት ለመሻት ፣ ዕውቀትን ለማበልጸግ እንዲሁም ውጤቱን ለማሰራጨት የመማር ማስተማር እና ምርምር ነፃነት ይኖረዋል ። ፫ ) የዩኒቨርሲቲው ተጠያቂነት በተለይ ፣ ( ሀ ) የሚያካሂዷቸው የትምህርትና ራሞች ከሀገር ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች የተገኙ መሆናቸውን ፣ ( ላ ) ለመንግሥት ፕሮግራሞች ቅድሚያ መስጠቱንና ከሀገራዊ ሁኔታዎች ጋር የተገናዘቡ መሆናቸውን ፣ ( ሐ ) አጠቃላይ አሠራሩ በግልጽነትና በአሳታፊነት ላይ የተመሠረቱ መሆኑን ፣ ( መ ) የበጀትና ሀብት አደላደሉና አጠቃቀሙ ወጪ ቆጣቢና ለሕዝብኃላፊነትን የሚያረጋግጥ መሆኑን ፣ ( ሠ ) የመማር ፣ ማስተማርና የምርምር ሥራዎች ተቋማዊ ሆነው በግልጽ የሚከናወኑ መሆናቸውን ፣ ( ረ ዩኒቨርሲቲውና የተቋሙ ማኅበረሰብ በሚያስመዘ ግቡት የጥራትና ተገቢነት ደረጃ ውጤት የሚለኩ መሆኑን ፣ ( ሰ ) ማንኛውም በማስተማር ፣ በመመራመር በማስተዳ ደርና በመምራት ኃላፊነት ላይ ያለ የተቋሙ ባልደረባ በተናጠልም ሆነ በጋራ ለተጠሪው አካልና ለኅብረተሰብ ተጠያቂነት ያለው መሆኑን ፣ በማረጋገጥ ላይ የተመሠረተ ይሆናል ። ፯ . የመረጃ ልውውጥ ፩ ) ቦርዱ በሚያወጣው የመረጃ ልውውጥ ሥርዓት መመሪያ መሠረት ከግል ተቋማት ፣ ከመንግሥታዊ ተቋማት እና ከሌሎች አካላት ጋር የመረጃ ልውውጥ ያደርጋል ። ገጽ ፪ሺ፰፻፲፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፩ መስከረም ፲ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓም : ፪ ) ዩኒቨርሲቲው ማንኛውም ከትምህርት ጋር የተያያዘ ምርምር የሚሰራ ሠራተኛ ወይም ተማሪ ጥያቄ ሲያቀር ብለት መረጃ ይሰጣል ወይም መረጃ እንዲያገኝ ያደርጋል ። ፫ ) የምርምርና ጥናት ጽሑፎች ለዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ፣ ተመራማሪዎችና ሌሎች ተጠቃሚዎች በሙሉ እንዲ ደርሱ የሚደረጉ መሆን አለባቸው ። ጥናትና ምርምር ፩ ) የጥናትና ምርምር ሥራ ለማከናወን አስፈላጊ ሆኖ የተገኘው አደረጃጀት በዩኒቨርሲቲው የውስጥ ደንብና የአስተዳደር መዋቅር የሚወሰን ሆኖ የሚከተሉት መስፈ ርቶች ይኖሩታል ። ( ሀ ) የዩኒቨርሲቲው የምርምር ተግባራት በአካዳሚክና ምርምር ምክትል ፕሬዚዳንት ይመራል ። ( ለ ) ዩኒቨርሲቲው ኣስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው የምርምር ተቋማት ሊከፍት ይችላል ። ( ሐ ) ዩኒቨርሲቲው ለሚያከናውነው ምርምርና ጥናት በቂ ገንዘብ ማፈላለግ ፣ መመደብና በሥራ ላይ ማዋል ይኖርበታል ። ( መ ) ዩኒቨርሲቲው የምርምር ሥራን የሚሰሩ ተመራማሪ ዎችና የምርምር ረዳቶች በግል ወይም በጋራ ቅጥር ሊቀጥር ይችላል ። ( ሠ ) ዩኒቨርሲቲው የሚያካሂዳቸው ምርምሮች አግባ ብነት ካላቸው ከሌሎች ተቋማት ጋር በትብብር ሊሆን ይችላል ። የዩኒቨርሲቲው የጥናትና ምርምር ርዕስ አመራረጥ ፣ የበጀት አጠቃቀምና የሀብት አያያዝ ፣ እንዲሁም የምርምር አፈጻጸም የግልጽነትና ተጠያቂነት መርሆ ዎችን የተከተለ ይሆናል ። ክፍል ሦስት ስለ ዩኒቨርሲቲው የሥራ አስፈጻሚ አካላት ፱ : ስለዩኒቨርሲቲው ቦርድ ፩ ) የዩኒቨርሲቲው ቦርድ በሚኒስቴሩ የሚሰየም ሰብሳቢ ይኖረዋል ። ፪ ) ቦርዱ የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል ። የትምህርት ሚኒስቴር የፌደራል መንግሥት ተወካይ ( አንድ ) ( ሐ ) የክልል መንግሥት ተወካዮች ( አራት ) ( መ ) ታዋቂ ግለሰብ ( ሠ ) ሌሎች በቦርዱ የሚሰየሙ አባላት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት አባል እና ጸሐፊ ፫ ) በቦርዱ የሚሰየሙ አባላ ልማት አስተዋጽኦ ያደረጉ የዩኒቨርሲቲው አገልግሎት ተጠቃሚዎች መሆን አለባቸው ። ፬ ) ቦርዱ በአዋጁ የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ። ፲ የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ሴኔቱ ተጠሪነቱ ለፕሬዚዳንቱ ሆኖ የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል ። ፩ ) የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፪ ) የዩኒቨርሲቲው ም / ፕሬዚዳንቶች ፫ ) አካዳሚክ ፕሮግራም ኃላፊ ፬ ) የፋካልቲ ፣ የኢንስቲትዩት ፣ የት / ቤቶችና ኮሌጆች ዲኖችም ፭ “ የሕዝብና ውጭ ግንኙነት ኃላፊ ፮ ) የዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር ፯ ) የዩኒቨርሲቲው የቤተመጻሕፍት ኃላፊ ፰ ) የተማሪዎች ዲን ፀ ) የአካዳሚክ ሠራተኞች ሁለት ተወካዮች ፬ ) ሁለት የተማሪዎች ተወካዮች ገጽ ፪ሺ፰፻፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፩ መስከረም ፲ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓም ፲፩ ) የዩኒቨርሲቲው የሴቶች ጉዳይ ተወካይ ፲፪ የምርምርና ህትመት ኃላፊ ፲፫ ቦርዱ የሚሰይማቸው አግባብነት ያላቸው ሌሎችኃላፊዎች ፲፩ . የሴኔቱ ሥልጣንና ተግባር በአዋጁ የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ ሴኔቱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ፣ ፩ ) በቦርዱ የሚወጡ አ c ቃላይ መመሪያዎችን ተግባራዊ ማድረግ ፣ ፪ ) የተማሪዎች አቀባበልን ፣ የትምህርት ደረጃ አወሳሰንን የዲሲፕሊን ጉዳዮችንና ምረቃን የሚመለከቱ መመዘኛ መስፈርቶችን ማውጣት ፣ በዚህ ላይ የሚቀርቡ ቅሬታ ዎችን መመርመር ፣ ፫ ) አጠቃላይ የፈተና አሰጣጥና ደረጃዎች አቅጣጫዎችን መወሰን ፣ ፬ ) በህግና በቦርዱ የሚወጡ ፖሊሲዎችን መሠረት በማድረግ በተለይ በተማሪዎች አስተዳደር ፣ የዩኒቨር ሲቲው የትምህርት ነክ ጉዳዮች ፡ የትምህርት ኃላፊዎች የምርጫ ሥነ - ሥርዓት ፣ የአካዳሚክ ሠራተኞች ቅጥር ፣ ዕድገት ፣ ጥቅማ ጥቅም ፣ ዲሲፕሊን ፣ ደመወዝ በሚመ ለከት መመሪያማውጣት ፣ ፭ ) የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ እንዲሰጥ ለቦርዱ ሀሳብ ማቅረብ ፣ ፮ የረዳትና የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግን መስጠት ፣ ፯ ) የአካዳሚክ ሠራተኞችን ቅጥር መመርመርናማጽደቅ፡ ፰ ) የራሱን የስብሰባ ሥነ - ሥርዓት መወሰን ፣ ፱ ) ፕሬዚዳንቱ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው የሚጠራው ስብሰባ እንደተጠበቀ ሆኖ በየሩብ ዓመቱ ቢያንስ አንድ ጊዜ መሰብሰብ ፣ ፲ ) ተግባሩን ለሌሎች የዩኒቨርሲቲው አካላትና ቋሚ ወይም ጊዜያዊ ኮሚቴዎች ማስተላለፍ ፣ ፲፩ ) በቦርዱ የሚሰጡትን ሌሎች ተግባሮች ማከናወን ። ፲፪ ስለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንትና ም / ፕሬዚዳንቶች ፩ ) የዩኒቨርሲቲው ዕጩፕሬዚዳንት ሆነውየሚቀርቡ ሰዎች የተመሰከረለት የአካዳሚክና አስተዳደር እንዲሁም መልካም ሥነ ምግባር ሊኖራቸው ይገባል ። ፪ ዩኒቨርሲቲው ለፕሬዚዳንቱ ተጠሪ የሆኑሦስትም / ፕሬዚ ዳንቶች ይኖሩታል ። ፫ ) የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንትና ም / ፕሬዚዳንቶች የሥራ ዘመን አምስት ዓመት ይሆናል ' ። ፬ ) የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት በአዋጁ የተመለከቱት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ። ፲፫ የዩኒቨርሲቲው የምክትል ፕሬዚዳንቶች ሥልጣንና ተግባር ፩ ) የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክና ምርምር ም / ፕሬዚዳንት ፣ ( ሠ ) የዩኒቨርሲቲውን ሥልጣንና ተግባር በተመለከተ የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዚዳንት ያማክራል ፣ ይረዳል ፣ ( ለ ) በቦርዱና በሴኔቱ የተላለፉ ውሳኔዎችና መመሪ ያዎች በሥራ ላይ በማዋል ለእርሱ ተጠሪ የሆኑ ክፍሎችን ይመራል ፣ ይቆጣጠራል ፣ ( ሐ ) የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት በማይኖርበት ጊዜ ተተክቶዩኒቨርሲቲውን ይመራል ፣ ያስተባብራል ፣ ( መ ) የትምህርት ማዕከላትን እንደፋኩልቲ ፣ ኮሌጅ ፣ ተቋም ፣ ትምህርት ቤት እና ተከታታይ ትምህርት ክፍሎችን ሥራ ያቅዳል ፣ ይመራል ፣ በበላይነት ይቆጣጠራል ፣ ( ሠ ) የምርምር እና ጥናት እንቅስቃሴዎችን ያቅዳል ፣ ይመራል ፣ በበላይነት ይቆጣጠራል ፣ ( ረ የዩኒቨርሲቲውን መጽሐፍት ቤት ፣ ሬጅስትራር ጽሕፈት ቤትና ሌሎች በሥሩ ያሉትን ክፍሎች ይመራል ፣ በበላይነት ይቆጣጠራል ፣ ገጽ ፪ሺ፱፻ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፩ መስከረም ፲ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓም : ( ሰ ) ብሔራዊና ዓለምአቀፍ ግንኙነቶችንና ትብብሮችን ያፈላልጋል ፣ አፈጻጸማቸውን ይከታተላል ፣ ( ሸ ) በሥራ ያሉ ክፍሎችን የሥራ አፈጻጸም ፣ በጀት ክፍፍልና አጠቃቀም እንዲሁም ሌሎችእንቅስቃሴ በተመለከተ ለፕሬዚዳንት ያቀርባል ፣ ( ቀ ) በቦርዱ ፣ በሴኔቱና በፕሬዚዳንቱ የሚሰጡትን ሌሎች ተመሳሳይ ተግባራት ያከናውናል ። ፪ ) የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር ም / ፕሬዚዳንት ፣ ( ሀ ) የዩኒቨርሲቲውን ሥልጣንና ተግባር በተመለከተ የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዚዳንት ያማክራል ይረዳል ፣ ( ለ ) ለእርሱ ተጠሪ የሆኑ የዩኒቨርሲቲው ክፍሎችን ይመራል ፣ ይቆጣጠራል ፣ ( ሐ ) የተማሪዎች አገልግሎትን ፣ የአስተዳደርና የፋይ ናንስ ሥራ ያቅዳል ፣ ይመራል ይቆጣጠራል ፣ ( መ ) በቦርድና በሴኔቱ የተሰጡ ውሳኔዎችንና መመሪያ ዎችን ተግባራዊ ያደርጋል ፣ ( ሠ ) የተቋሙን አስተዳደርና ማኔጅመንት አቅም ለማሻሻል ከብሔራዊና ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ግንኙነት ይፈጥራል ፣ ተግባራዊነቱን ይከታተላል ፣ ( ረ ) የሥራ አፈጻጸም ፣ የበጀት አመዳደብና አጠቃቀም እንዲሁም የሌሎች እንቅስቃሴዎችን ሪፖርት ለፕ ሬዚዳንቱ ያቀርባል ፣ ( ሰ ) በቦርዱ ፣ በሴኔቱና በፕሬዚዳንቱ የሚሰጡትን ሌሎች ተመሳሳይ ተግባራት ያከናውናል ። ፫ ) የዩኒቨርሲቲው የቢዝነስና ልማት ም / ፕሬዚዳንት ፣ ( ሀ ) የዩኒቨርሲቲውን ሥልጣንና ተግባር በተመለከተ የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዚዳንት ያማክራል ፣ ይረዳል ፣ ( ለ ) ለእርሱ ተጠሪ የሆኑ የዩኒቨርሲቲውን ክፍሎች ይመራል ፣ ይቆጣጠራል ፣ ( ሐ ) በቦርድና በሴኔቱ የተላለፉ ውሳኔዎችና መመሪ ያዎች በሥራ ላይ መዋላቸውን ይከታተላል ፣ ( መ ) የገቢ ማመንጫ ድርጅቶችንና የዩኒቨርሲቲውን የቢዝነስ ክፍሎች በተመለከተያቅዳል ፣ ይመራል ፣ ይቆጣጠራል ፣ የሥራ ባህልን ያጎለብታል ፣ ( ሠ ) በዩኒቨርሲቲው አዳዲስ የቢዝነስ ሀሳቦችንና ልማትን ያቅዳል ፣ ይመራል ፣ ይቆጣጠራል ፣ ( ረ ) የዩኒቨርሲቲውን አዳዲስ የልማትና የማስፋፋት የካፒታል ኢንቨስትመንቶችን ያቅዳል ፣ ያስተዳ ድራል ፣ ( ሰ ) ከሌሎች ድርጅቶች ጋር የተገናኙና እርሱን የሚመ ለከቱ ስምምነቶችና ፕሮጀክቶችን አፈጻጸም ይመራል ፣ ይጠቆጣጠራል ፣ ( ሸ ) ብሔራዊና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶችንና ትብብ ሮችን ያፈላልጋል ፣ አፈጸጸማቸውን ይከታተላል ፣ ( ቀ ) በሥሩ የሚገኙትን አካላት የሥራ አፈጻጸሙን ፣ የበጀት ድልድልና አጠቃቀምን በተመለከተ ሪፖርት ያቀርባል ፣ ( 0 ) የቢዝነስና የስትራቴጂክ ዕቅድ በማዘጋጀት ያቀርባል ፣ ( ረ ) ሌሎች ከቦርድ ፣ ከሴኔቱና ከፕሬዚዳንቱ የሚሰ ጡትን ተግባራት ያከናውናል ። ፲፬ • የአካዳሚክ ኮሚሽን ፩ ) እያንዳንዱ ፋኩልቲ ኮሌጅ ኢንስቲትዩት እና ትምህርት ቤት ለዲኑ ተጠሪ የሆነ የራሱ አካዳሚክ ኮሚሽን ይኖረዋል ። ፪ ) የአካዳሚክ ኮሚሽኑ የሚከተሉት ኣባላት ይኖሩታል ፣ ( ሀ ) የፋኩልቲ ፣ ኮሌጅ ፣ ኢንስቲትዩት ወይም ትምህርት ቤት ዲን ( ሸ ) የራሱን የመ . ገጽ ፪ሺ፱፻፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፩ መስከረም ፲ ቀን ፲፱፻፲፯ ዓም ( ለ ) የፋኩልቲ ፣ ኮሌጅ ፣ ት / ቤት ወይም ኢንስቲትዩት ምክትል ዲኖች ካሉ ( ሐ ) የትምህርት ክፍሎችኃላፊዎች ( መ ) አንድ የተማሪዎች ተወካይ ( ሠ ) በአካዳሚክ ሠራተኞች ጠቅላላ ጉባዔ የተመረጠ አንድ የመምህራን ተወካይ ( ረ የፋኩልቲው የተከታታይ ትምህርት አስተባባሪ ( ሰ ) በኮሚሽኑ የሚመደቡ አግባብነት ያላቸውኃላፊዎች ፫ ) የዩኒቨርሲቲው ሴኔት የሚያወጣው መመሪያ እንደተ ጠበቀ ሆኖ የአካዳሚክ ኮሚሽኑ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ፣ ( ሀ ) የፋካልቲውን ፣ የኮሌጁን ፣ የተቋሙን ወይም የትም ህርት ቤቱን ዕቅድ ያዘጋጃል ፣ በጀት በማዘጋጀት ይደለድላል ፣ ቀልጣፋ አፈጻጸሙን ይከታተላል ፣ ( ለ ) የሥልጠናና የትምህርት መርሀግብሮችን ሥርዓተ ትምህርቶች አዘጋጅቶ በሚመለከተው አካል ያስጸ ድቃል ፣ ( ሐ ) በሴኔቱ መመሪያ መሠረት የተማሪዎችን ትምህ ርትና ሥነ ምግባር የተመለከቱ ዝርዝር መስፈር ቶችን ይወስናል ፣ ( መ ) ከትምህርት ጋር የተያያዙ ሽልማቶችንና የክብር ዲግሪ እንዲሰጥ ለሴኔቱ ሀሳብ ያቀርባል ( ሠ ) የሌክቸረር ፣ ረዳት ሌክቸረር ፣ ረዳት ምሩቅና ቴክኒክ ረዳቶችን ዕድገት በሴኔቱ የውስጥ መተዳ ደሪያ ደንብ መሠረት መርምሮ ይወስናል ፣ ( ረ ) የተባባሪና ረዳት ፕሮፌሰርነት ማዕረግ እንዲሰጥ ለሴኔቱ አቅርቦ ያፀድቃል ፣ ( ሰ ) የአካዳሚክ ሠራተኞች ቅጥርን ይመረምራል ፣ የነፃ ትምህርት ዕድልና የምርምርና ሰባቲካል እረፍ ቶችን ያጸድቃል ፣ ሥነ ሥርዓትና የውስጥ ደንብ ይወስናል ፣ ( ቀ ) ከሴኔቱ እና ከፕሬዚዳንቱ የሚሰጡትን ሌሎች ተመሳሳይ ተግባራትን ያከናውናል ። ፲፭ የትምህርት ክፍል ጉባዔ ፩ ) እያንዳንዱ የትምህርት ክፍል የራሱ ጉባዔ ይኖረዋል ። ፪ ) የትምህርት ክፍል ጉባዔ በትምህርት ክፍሉ ኃላፊ የሚመራም ሆነ ሁሉንም የሙሉ ጊዜ መምህራንን ያካትታል ። ፫ ) የትምህርት ክፍል ጉባዔ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፣ ( ሀ ) ተፈላጊ በሆኑና ሰርቲፊኬት ወይም ዲግሪ የሚያሰጡ መርሃግብሮችን ለአካዳሚክ ኮሚሽኑ ያቀርባል ፣ ሲፈቀድ ያስፈጽማል ፣ ( ለ ) የትምህርት ክፍሉን ዓመታዊ ዕቅድ በጀትና ሪፖርት ያዘጋጃል ፣ ይመዘግባል ፣ ( ሐ ) የትምህርት ክፍሉን የሰውኃይልናፋይናንስ ይከታ ( መ ) የመምህራንና የተማሪዎችን ግምገማና ክትትል ያከናውናል ፣ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ይመረ ( ሠ ) ፈተናዎችንና የአካዳሚክ ግምገማ ሥርዓትን ደረጃ ያወጣል ፣ ይከታተላል ፣ ( ረ ) የማስተማሪያ ጽሑፎችን አመራረጥና ዝግጅት ይወስናል ፣ የመምህራንን የሥራ ጫና ይወስናል ፣ ( ሰ ) በሥርዓተ ትምህርትና በመማር ማስተማር ሥርዓት ማሻሻያዎችና ፈጠራዎችእንዲጎለብቱሁኔታዎችን ያመቻቻል ፣ ገጽ ፪ሺ፱፻፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፩ መስከረም ፲ ፲፱፻፵፯ ዓም ( ሸ ) የተማሪዎችን ውጤት ያጸድቃል ፣ ( ቀ ) ሌሎች በፋካልቲውና በዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት የሚሰጡ ተግባራትን ያከናውናል ። ፲፮ ስለዩኒቨርሲቲው ልዩ ልዩ ክፍሎች የውስጥ ሥልጣን ፩ ) በዚህ ቻርተር አንቀጽ ፪ ንዑስ አንቀጽ ፪ ሥር የተዘረ ዘሩት እና ሌሎች የዩኒቨርሲቲው አካላት አደረጃጀት ቦርዱ ባጸደቀው መዋቅር መሠረት ይወሰናል ። ፪ ) እያንዳንዱፋኩልቲ ፣ ተቋም ፣ ትምህርት ቤት ወይም / እና ኮሌጅ የበጀት ማዕከል ደረጃ ሊኖረው ይችላል ፣ ፫ ) እያንዳንዱ የበጀት ማዕከል የራሱን ዕቅድና በጀት ማዘጋጀት ፣ የበጀት እና ሀብት አጠቃቀምን መወሰንና ሪፖርት ማዘጋጀት ይኖርበታል ። ፲፯ . የማኔጅመንት አመራር አሰያየም በዩኒቨርሲቲው አካላት ውስጥ ያሉ አካላትን ለመምራት የሚታጭ ሰው በተለይ የሚከተሉትን ማሟላት አለበት ። ( ሠ ) የማኔጅመንት የአስተዳደርና የአመራር ብቃት ያለው ፣ ( ለ ) በዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ፣ የምርምርና የኅብረተሰብ አገልግሎት ውስጥ ብቁ ተሳትፎ ያለው ፣ ( ሐ ) ሥራዎቹ ውጤትያሳዩና መልካም ሥነ ምግባርያለው ፣ ( መ ) ዲሞክራሲያዊ እሴቶችን የመተግበርና የማስረጽ ዝግጁ ነትና ቁርጠኝነት ያለው ፣ ክፍል አራት ስለ ዩኒቨርሲቲው ሠራተኞችና ተማሪዎች ፲፰ የዩኒቨርሲቲው ሠራተኞች ፩ ) ዩኒቨርሲቲው በአዋጁ የተመለከቱት ሠራተኞች ይኖሩታል ። ፪ ) ዩኒቨርሲቲው ከሌላ መንግሥታዊ ወይም የግል ተቋም ሠራተኛን በጋራ ቅጥር መቅጠር ይችላል ። ፫ ) የጋራ ቅጥሩ በሁለቱ ተቋማት መካከል በሚደረግ ውለታና በግለሰቡ ስምምነት መሠረት ተግባራዊ ይሆናል ፬ ) በጋራ የተቀጠረው ባለሙያእንደቋሚመምህር የሚታይ ሆኖ በሕጉ የተመለከቱት ግዴታና መብቶች ይኖሩታል ። ፭ ) የዩኒቨርሲቲው ሠራተኞች መብትና ግዴታ በአዋጁ የተመለከተው ይሆናል ። ፲፱ : ስለተማሪዎች መቀበያ መመዘኛ ፩ ) በሌሎች ህጎች ስለመቀበያ መመዘኛ የተደነገገው እንደ ተጠበቀ ሆኖ ዩኒቨርሲቲው ፣ ( ሀ ) ተገቢውን መመዘኛ ላሟሉ ኢትዮጵያውያን ያለምንም ልዩነት ክፍት ይሆናል ፣ ( ለ ) የኢትዮጵያ የሁለተኛ ደረጃ የመዘጋጃ ትምህርት ወይም ሚኒስቴሩ በሰጠው ግምት አቻ ደረጃ ያለው የውጭ ሀገርሁለተኛደረጃን ያጠናቀቀእና በዩኒቨር ሲቲው የተሰጠውን የመግቢያ መመዘኛ ያሟላ ተማሪን ለቅድመ ምረቃ መርሀ ግብር ትምህርት ይቀበላል ፣ ( ሐ ) የዲፕሎማ ( ፲፪ ፥ ፪ እና ፲ + ፫ ) ደረጃ ያላቸው ተማሪ ዎችን በአድቫንስድ ተማሪነት በቅድመ ምረቃ ይቀበላል ፣ ( መ ) የከፍተኛ ትምህርት የቅድመ ምረቃ ትምህርት ያጠናቀቀና በዩኒቨርሲቲው የተወሰኑ መመዘኛ ዎችን ያሟላ ተማሪን ለድህረ ምረቃ መርሃ ግብር ትምህርት ይቀበላል ፣ ( ሠ ) ለሴቶች ፣ ለታዳጊ ክልል ብሔረሰብ እንዲሁም ለጎልማሣ ወይም ልምድ ላላቸው ተማሪዎች የተለየ አቀባበል ሥርዓት ሊወሰን ይችላል ። ፪ ዩኒቨርሲቲው የሚቀበለው ተማሪ በወጪ መጋራት መርህ መሠረት ያለበትን ግዴታ የሚያሟላ መሆን አለበት ። ገጽ ፪ሺ፱፻፫ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፩ መስከረም ፲ቀን ፲፱፻፵፯ ዓ.ም ፫ ዩኒቨርሲቲው የተማሪውን ችሎታ እና የዕውቀት ደረጃ እንዲሁም ክህሎት ለመገምገም የሚያስችል መመዘኛ ያዘጋጃል ። ፬ ) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ፫መሠረትየሚሰጥመመዘኛ ለተማሪው በተሰጠው ትምህርት ወይም ሥልጠና ይዘት ላይ የተመሠረተ ተከታታይ ምዘና መሆን አለበት ፣ ፭ ) መመዘኛው የሚሰጥበት መንገድ በቃል ፣ በጽሑፍ ፣ በተግባርና ሌሎች ሴኔቱ በሚወስንባቸው መንገዶች ሊሆን ይችላል ። ፮ ) የምዘና ውጤቶች እና የፈተና ወረቀቶችን ለተማሪው መመለስ ወይም በግልጽ ማሳወቅ አለበት ። ክፍል አምስት ስለድርጅትና ፈንድ ፳ ስለ ድርጅቱ መቋቋምና አካላቱ ተጠሪነቱ ለዩኒቨርሲቲው የቢዝነስና ልማት ምክትል ፕሬዚ ዳንት የሆነ የሚከተሉት አካላት ያሉት የዩኒቨርሲቲው ድርጅት ተቋቁሟል ። ( ሀ ) የምክር አገልግሎት ( ለ ) የምርት አገልግሎት ( ሐ ) የፕሮጀክት አገልግሎት ( መ ) የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎት ( ሠ ) ወደፊት የሚቋቋሙ ሌሎች አገልግሎቶች ፳፩ . የገቢ ምንጭ በአዋጁ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ፣ ፩ ) ይህ ቻርተር ሥራ ላይ ከመዋሉ በፊት ከዩኒቨርሲቲው የገቢ ምንጭ አካላት የተገኙ ገቢዎች የድርጅቱ የገቢ ምንጭ ይሆናሉ ። ፪ ) ቻርተሩ ሥራ ላይ ከመዋሉ በፊት የነበሩ የዩኒቨርሲቲው የገቢ ማመንጫ አካላት በድርጅቱ ሥር ይሆናሉ ። ፳፪ : የድርጅቱ ሥልጣንና ተግባራት ፈቃድ ማግኘትን የመሳሰሉ በሕግ የተደነገጉ ሁኔታዎች | 22. Powers and Duties of the Enterprise እንደተጠበቁ ሆነው ድርጅቱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ። ፩ ) የማማከር አገልግሎት መስጠት ፣ ፪ ለረጅም ወይም ለአጭር ጊዜ ምርቶችን መጓጓዣና የግንባታ መሣሪያዎችን ማከራየት ፣ ፫ ) የግንባታ መሣሪያዎች ማምረትና መሸጥ ወይም ማከራየት ፣ ፬ ) በቴክኖሎጂ የላቁ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎችን ማምረት ፣ ፭ ) የቤተ ሙከራ አገልግሎት መስጠት ፣ ፮ ) የጥናት ሞዴሎችንና ሙከራዎችን ማከናወን ፣ በውሃ ሀብት አስተዳደር መሰል አገልግሎቶችን መርዳት ፣ ፰ ) የግብርና ውጤቶችን ማቅረብ ፣ ፱ ) የእንጨትና የብረት ውጤቶችን ማምረትና ማቅረብ ፣ ፲ የግንባታ ሥራዎችን መቆጣጠር ፣ ፲፩ ) ጥናቶችን ፣ ንድፍ ሥራዎችን እና የፕሮጀክት ሰነዶችን ማዘጋጀትና ኣስተያየት መስጠት ፣ ፲፪ ) የኢንተርኔት ካፌና የኮምፒውተር አገልግሎት መስጠት ፣ ፲፫ ) የመጽሐፍትና የህትመት ሙያዊ አገልግሎት መስጠት ፣ ፲፬ ) የንብረቶች ባለቤት መሆን ፣ ፳፫ • የድርጅቱ አስተዳደር የድርጅቱ አጠቃላይ አስተዳደር ድርጅቱን ፣ አካላቱን የሚመሩሰዎች የሚመረጡበትእናየሚተዳደሩበት የድርጅቱ መዋቅር ፣ የካፒታሉና ሌሎች አግባብነት ያላቸው ጉዳዮች በቦርዱ ይወሰናሉ ።