×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
አዋጅ ቁጥር ፪፻፶፬ ፲፱፻፲፭ የኢሚግሬሽን ኣዋጅ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ መንግሥት አንቀጽ ፵፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተ e 0 የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ዘጠነኛ ዓመት ቁጥር ፳፭ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አዲስ ኣበባ - ሰኔ ፳፮ ቀን ፲፱፻፲፭ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ ነዋጅ ቁጥር ፪፻፶፬ ፲፱፻፲፭ ዓም የኢሚግሬሽን አዋጅ ገጽ ፪ሺ፫፻፲፰ አዋጅ ቁጥር ፪፻፶፬ / ፲፱፻፲፭ የኢሚግሬሽን አዋጅ ከወቅቱ የዕድገት ደረጃ ጋር የተጣጣመና የተሟላ የኢሚግ | comprehensive immigration law which is compatible with the ሬሽን ሕግ ማውጣት በማስፈለጉ ፤ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ ታውጇል ፤ ክፍል አንድ ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የኢሚግሬሽን አዋጅ ቁጥር ፪፻፵፬ ፲፱፻፲፭ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር | 2. Definitions በዚህ አዋጅ ውስጥ ፤ ፩ . “ የውጭ ሀገር ሰው ” ማለት የኢትዮጵያ ዜጋ ያልሆነ ማንኛውም ሰው ነው ፤ ፪ . “ ባለሥልጣን ” ማለት የደህንነት ፤ የኢሚግሬሽንና የስደተኞች ጉዳይ ባለሥልጣን ነው ፤ ፫ . “ ሚኒስቴር ” ማለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው ፤ “ የጉዞ ሰነድ ” ማለት በሚኒስቴሩ ወይም በባለሥልጣኑ ወይም በኢትዮጵያ መንግሥት በታወቀ የውጭ ሀገር መንግሥት ወይም ዓለም አቀፍ ወይም አህጉራዊ ድርጅት የሚሰጥ የተሰጠውን ሰው ማንነትና ዜግነቱን የሚገልጽ ፓስፖርት ወይም ሌላ የጉዞ ሰነድ ነው ፤ ፭ . “ አካለ መጠን ያላደረሰ ” ማለት በኢትዮጵያ የፍትሐ ብሔር ሕግ መሠረት ዕድሜው ለአካለ መጠን ያላደረሰ ሰው ነው ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፱ሺ፩ ፪ሺ፫፻፳፱ ፌዴራል ቁጥር ፪፭ ሰኔ፳፰ቀን፲ምዓም ክፍል ሁለት ወደ ኢትዮጵያ ስለመግባት ፫ መሟላት ስለሚገባቸው ሁኔታዎች ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት የሚፈልግ ማንኛውም የውጭ ሀገር ሰው ፣ ሀ ) የፀና የጉዞ ሰነድ ፤ ለ ) የፀና የመግቢያ ቪዛ ወይም የፀና ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ወይም በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፬ ( ፩ ) የሚሸፈን የውጭ አገር ሰውን የሚመለከት ሲሆን ፤ ከሚኒስቴሩ የተሰጠ መታወቂያ ወረቀት ፤ እና ሐ ) እንደአስፈላጊነቱ የጤና የምስክር ወረቀት ፤ መያዝ ይኖርበታል ። ፪ • የቱሪስት ወይም የትራንዚት ቪዛ ያለው የውጭ ሀገር ሰው በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ከተዘረዘሩት በተጨማሪ ፤ ሀ ) ከኢትዮጵያ ወደ ሌላ ሀገር ለመጓዝ የሚያስችል የጉዞ ቲኬት ፤ እና ለ ) የማያስፈልግ ካልሆነ በቀር ሊሔድበት ወደአሰበው ሀገር የሚያስገባ የፀና የመግቢያ ቪዛና የጤና የምስክር ወረቀት መያዝ ይኖርበታል ፤ ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት የሚፈልግ አካለ መጠን ያላደረሰ የውጭ አገር ሰው ፤ ሀ ) የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ( ሀ ) እና ( ለ ) ድንጋጌ ቢኖርም ፤ አብሮት በሚመጣው ሰው የጉዞ ሰነድላይ ከተመዘገበ ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት ይችላል ፤ ለ ) ብቻውን የሚመጣ ከሆነ በኢትዮጵያ ውስጥ በኃላ ፊነት የሚቀበለው ሰው ያስፈልገዋል ። • የመግቢያ ቪዛ የማይጠየቅበት ሁኔታ በሌላ ሕግ ወይም ኢትዮጵያ አባል በሆነችበት ዓለም አቀፍ ውል የመግቢያ ቪዛ እንደማይጠየቅ የተደነገገ ከሆነ ያለመ ግቢያ ቪዛ ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት ይቻላል ። ፭ የመግቢያ ቪዛ ስለመከልከል ወይም ስለመሠረዝ የመግቢያ ቪዛ አመልካቹ ወይም ያዝ ፤ ፩ ራሱን ችሎ ለመኖር የሚያስችለው ሀብት ከሌለው ወይም ለሀገሪቱ ሸክም ይሆናል ተብሎ ከተገመተ ፤ ፪ • ኣደገኛ ወንጀለኛ መሆኑ ከታወቀ ። ፫ የአደገኛ ዕፅ ሱስ ተገዢ መሆኑ ከተረጋገጠ ፤ ፬ . በአደገኛ ተላላፊ በሽታ መያዙ የሚጠረጠር ከሆነ ፤ ፭ ለኢትዮጵያ ፀጥታ የሚያሰጋ ሆኖ ከተገኘ ፤ የተጭበረበረ መረጃ ያቀረበ እንደሆነ ፤ ወይም ፯ ይህንን አዋጅ ወይም በዚህ አዋጅ መሠረት የወጡትን ደንቦች ተላልፎ ከተገኘ ፤ ሊከለከል ወይም ሊሠረዝ ይችላል ። ክፍል ሦስት ከኢትዮጵያ ስለመውጣት ፮ መሟላት ስለሚገባቸው ሁኔታዎች ከኢትዮጵያ የሚወጣ ማንኛውም ሰው ፤ የፀና የጉዞ ሰነድ ፤ የማያስፈልግ ካልሆነ በቀር ወደሚሄድበት ለመግባት የሚያስችል የመግቢያ ቪዛ ፤ እና ፫ : እንደአስፈላጊነቱ የጤና የምስክር ወረቀት ፤ መያዝ ይኖርበታል ። • ከኢትዮጵያ እንዳይወጡ ስለሚታገዱ ሰዎች ማንኛውምሰው ከኢትጵዮጵያ እንዳይወጣ ሊታገድ የሚችለው በሕግ መሠረት በፍርድ ቤት ሲታዘዝ ብቻ ነው ። ገጽ ፪ሺ፫፻፪ ፌዴራል ቁጥር ፪፭ ሰኔ ፮ ቀን ፲፱ደ፲፭ ዓም ክፍል አራት ከኢትዮጵያ እንዲወጡ ስለሚደረጉ የውጭ ሀገር ሰዎች ፰ ከሀገር ስለማስወጣት ባለሥልጣኑ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፭ በተዘረዘሩት ምክን ያቶች አንድን የውጭ ሀገር ሰው ከሀገር ለማስወጣት ትዕዛዝ ማስተላለፍ ይችላል ፤ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት የሚተላለፍ ትዕዛዝ ከሀገርእንዲወጣ የተወሰነበትን የውጭ ሀገር ሰው ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ የቤተሰብ አባላትንም ይመለከታል ፤ ፫ . ከሀገርእንዲወጣ ትዕዛዝ የተላለፈበትን የውጭ ሀገር ሰው በትዕዛዙ መሠረት ከሀገር እስከሚወጣ ድረስ ባለሥ ልጣኑ በማረፊያ ቤት እንዲቆይ ለማድረግ ይችላል ፤ ፬ • ከሀገር ለማስወጣት የሚተላለፍ ትዕዛዝ የውጭ ሀገሩን ሰው ከሀገር ለማስወጣት ምክንያት የሆነውን ጉዳይ ፤ ከኢትዮጵያ የሚለቅበትን ቀንና የመውጫውን በር መግለጽ ይኖርበታል ፤ ባለሥልጣኑ በማናቸውም ጊዜ የውጭ ሀገሩ ሰው ከሀገር እንዲወጣ የሰጠውን ትዕዛዝ ለመሻር ይችላል ፤ ፮ ከሀገር እንዲወጣ ትዕዛዝ የተላለፈበት የውጭ ሀገር ሰው ወደ ሀገሩ ወይም ሊሄድበት የሚፈልገው ሀገር ለመቀበል ፈቃደኛ ከሆነ ወደ ሌላ ሀገር እንዲሄድ ይደረጋል ፤ ፯ • በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ መሠረት ከሀገር እንዲወጣ በፍርድ ቤት የተወሰነበትን የውጭ አገር ሰው በሚመ ለከት የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ፤ ( ፬ ) እና ( ፮ ) ድንጋጌ ተፈጻሚ ይሆናሉ ። ፱ • በማስወጪያ ትዕዛዝ ላይ ስለሚቀርብ አቤቱታ ፩ ከሀገር ለማስወጣት በባለሥልጣኑ በተሰጠ ትዕዛዝ ላይ ቅሬታ ያለው የውጭ ሀገር ሰው ትዕዛዙ በደረሰው በሦስት የሥራ ቀናት ውስጥ የሚኒስቴሩ ፤ የፍትሕ ሚኒስቴርና የባለሥልጣኑ ተወካዮች በአባልነት ለሚገኙበት ኣቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አቤቱታውን ማቅረብ ይችላል ፤ ፪ • ኮሚቴው የቀረበለትን አቤቱታ በመመርመር የውሳኔ ለባለሥልጣኑ ያቀርባል ባለሥልጣኑም የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል ፤ የኮሚቴው የአሠራር ሥርዓት ባለሥልጣኑ በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል ። ስለ ጉዞ ወጪ ከኢትዮጵያ እንዲወጣ ትዕዛዝ የተላለፈበት የውጭ ሰው ለጉዞው የሚያስፈልገውን ወጪ ራሱ መሸፈን ይኖርበታል ፤ ፪ ከኢትዮጵያ እንዲወጣ ትዕዛዝ የተላለፈበት የውጭ አገር ሰው በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት ወጪውን ለመሽፈን ፈቃደኛ ካልሆነና ንብረት ካለው በሕግ መሠረት ንብረቱ ለወጪው መሸፈኛ ሊውል ይችላል ። ክፍል አምስት ስለጉዞ ሰነዶችና ቪዛዎች ፲፩ ስለጉዞ ሰነዶች ዓይነትና አሰጣጥ በዚህ አዋጅና ይህን አዋጅ ለማስፈጸም በሚወጣ ደንብ መሠረት የሚሰጡ የጉዞ ሰነዶች የሚከተሉት ይሆናሉ ፣ ሀ ) ዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ፣ ለ ) ሰርቪስ ፓስፖርት ፣ ሐ ) መደበኛ ፓስፖርት ፣ መ ) የይለፍ ሰነድ፡ ሠ ) አስቸኳይ የጉዞ ሰነድ ፣ ረ ) የስደተኞች የጉዞ ሰነድ ፣ ሰ ) እንደአስፈላጊነቱ በዚህ አዋጅ መሠረት በሚወጣ ደንብ የሚወሰኑ ሌሎች የጉዞ ሰነዶች ፣ ገጽ ሺ፫፻ኛ§ ሩዴራል ቁጥር ፪፭ ሰኔ ፳፭ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓ • ም • በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ( ሀ ) እና ( ለ ) የተመለ ከቱት የጉዞ ሰነዶች የሚሰጡት በሚኒስቴሩ ይሆናል ፣ ፫ • በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ( ሐ ) እና ( ሰ ) የተመለ ከቱት የጉዞ ሰነዶች የሚሰጡት በባለሥልጣኑ ይሆናል ፣ የጉዞ ሰነዶች የሚሰጡበት ሁኔታ በዚህ አዋጅ መሠረት በሚወጣ ደንብ ይወሰናል ፣ ፲፪ ስለቪዛ ዓይነቶችና አሰጣጥ በዚህ አዋጅና ይህን ለማስፈጸም በሚወጣ ደንብ መሠረት የሚሰጡ ቪዛዎች የሚከተሉት ይሆናሉ ፣ ሀ ) ዲፕሎማቲክ ቪዛ ፣ ለ ልዩ ቪዛ ፣ የሥራ ቪዛ ፣ መ ) የመኖሪያ ቪዛ ፣ የቱሪስት ቢዛ ፣ ረ ) የትራንዚት ቪዛ ፣ ሰ ) የተማሪ ቪዛ ፣ ሸ ) የመውጫ ቪዛ ፣ ቀ ) የደርሶ መልስ ቪዛ ፣ በ ) እንደአስፈላጊነቱ በዚህ አዋጅ መሠረት በሚወጣ ደንብ የሚወሰኑ ሌሎች ቪዛዎች ፣ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ( ሀ ) እና ( ለ ) የተመለ ከቱት ቪዛዎች የሚሰጡት በሚኒስቴሩ ይሆናል ፣ ፫ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ( ሐ ) እና ( በ ) የተመለ ከቱት ቪዛዎች የሚሰጡት በባለሥልጣኑ ይሆናል ፣ ፬ ቪዛዎች የሚሰጡበት ሁኔታ በዚህ አዋጅ መሠረት በሚወጣ ደንብ ይወሰናል ። ክፍል ስድስት የውጭ ሀገር ሰዎችን ስለመመዝገብና ስለመኖሪያ [ ስለምዝገባ ፩ . የሚከተሉት ሰዎች በባለሥልጣኑ መመዝገብ አለባቸው ፣ ሀ ) በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ የውጭ አገር ሰዎች ፣ ለ ) በመኖሪያ ቪዛ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ የውጭ አገር ሰዎች ከገቡበት ቀን ጀምሮ በሰላሳ ቀናት ውስጥ ፣ ሐ ) ከዘጠና ቀናት በላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ለመቆየት በሥራ ወይም በተማሪ ቪዛ የሚገቡ የውጭ አገር ሰዎች ከገቡበት ቀን ጀምሮ በሰላሳ ቀናት ውስጥ ፣ መ ) የዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፬ እንደተጠበቀ ሆኖ ከዘጠና ቀናት በላይ ለመቆየት በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፬ መሠረት ያለቪዛ የሚገቡ ሰዎች ከገቡበት ቀን ጀምሮ በሰላሳ ቀናት ውስጥ ፣ የውጭ አገር ሰው የሚመዘገብበት ሁኔታ በዚህ አዋጅ መሠረት በሚወጣ ደንብ ይወሰናል ። ፲፬ • ምዝገባ ስለማያስፈልጋቸው የውጭ ሀገር ሰዎች ፩ የሚከተሉት የውጭ ሀገር ሰዎች መመዝገብ አያስፈልጋ ሀ ) ተቀማጭነታቸው ኢትዮጵያ ውስጥ የሆኑ ዲፕሎማ ቶችና የዓለም አቀፍ ሲቪል ሠራተኞች እና የነዚሁ ቤተሰብ አባላት ፣ ለ ) በኢትዮጵያ መንግሥት እና በተባበሩት መንግ ሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን በስደተኛነት የታወቀ የውጭ አገር ሰው ፣ ሐ ) በሌላ ሕግ ወይም ኢትዮጵያ ኣባል በሆነችባቸው ዓለም አቀፍ ውሎች መሠረት ከመመዝገብና የመኖሪያ ፈቃድ ከማውጣት ነፃ የተደረጉ የውጭ አገር ሰዎች ፣ ፪ . በዚህ አንቀጽ መሠረት ከምዝገባ ነፃ የተደረጉ ሰዎች ከገቡበት ቀን ጀምሮ በሰላሳ ቀናት ውስጥ አግባብ ካለው አካል መታወቂያ ወረቀት ማውጣት አለባቸው ። ገደብ ሳያልፍ ሥልጣን ላለው ፍርድ ቤት ማቅ ንጽ ፪ሺ፫፻፳፪ ፌዴራል ቁጥር ፻፭ ሰኔ ፳፮ ቀን ፲፱፻፷፭ ዓም ፲፭ የመኖሪያ ፈቃድ ስለማውጣት በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፫ መሠረት የተመዘገበ የውጭ ሀገር ሰው እንደአግባቡ ጊዜያዊ ወይም ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ማውጣት አለበት ፣ ፪ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች በወላጆቻቸው መኖሪያ ፈቃድ ላይ መመዝገብ አለባቸው ፣ ፫ . የመኖሪያ ፈቃድ የሚሰጥበት ሁኔታ በዚህ አዋጅ መሠረት በሚወጣ ደንብ ይወሰናል ። ክፍል ሰባት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ፲፮ ስለኢምግሬሽን ኦፊሰሮች ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡትንና ከኢትዮጵያ የሚወጡትን ሰዎች የሚቆጣጠሩ የኢምግሬሽን ኦፊሰሮች ባለሥልጣኑ ይመድባል ፣ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት የተመደበ የኢምግሬሽን የሚከተሉት ሥልጣኖች ይኖሩታል ፣ ሀ ) ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ወይም ከኢትዮጵያ የሚወጡ መንገደኞችን የጫነ መጓጓዣ ውስጥ ለመግባት ፣ ለ ) የጉዞ ሰነዶችን ፣ ቪዛዎችንና በዚህ አዋጅ ወይም በዚህ አዋጅ መሠረት በሚወጣ ደንብ የተደነገጉ ሌሎች ሰነዶችን ለመመርመር ፣ ሐ ) ይህን አዋጅ ወይም በዚህ አዋጅ መሠረት የወጡ ደንቦችን በመጣስ ፣ ( ፩ ) ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት ወይም ለመውጣት የሚሞክር ማንኛውንም ሰው ፣ ወይም ( ፪ ) በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር ማንኛውንም የውጭ አገር ሰው ፣ መያዝ ፫ . ማንኛውም የኢምግሬሽን ኦፊሰር በዚህ አንቀጽንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) ( ሐ ) መሠረት የያዘውን ሰው በሕግ የተፈቀደው የጊዜ አለበት ። ፲፯ . የአጓጓዥ ኃላፊነት የውጭ ሀገርን ሰው ወደ ኢትዮጵያ ይዞ የሚመጣ የውጭ ሀገር ዜጋው በዚህ አዋጅ በአንቀጽ ፫ የተመለከ ተውን የፈጸመ መሆኑንና በዚህ አዋጅ መሠረት በሚወጣ ደንብ በተወሰነው መግቢያ በር መውረዱን ማረጋገጥ አለበት ፣ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ወይም ከኢትዮጵያ የሚወጡ መንገደኞችን ያሳፈረ የማንኛውምማጓጓዣ ኃላፊ የመንገ ደኞቹን ስም የያዘ ዝርዝር ለሚመለከተው የኢምግሬሽን ኦፊሰር የመስጠት ግዴታ አለበት ፣ ፫ የዚህ አዋጅ አንቀጽ ፳ ( ፩ ) ( ሀ ) እና ( ፪ ) እንደተጠበቁ ሆኖ ፣ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከተውን የተላለፈ አጓጓዥ ያመጣውን የውጭ ሀገር ሰው በራሱ ወጭ እንዲመልስ ይገደዳል ። ፲፰ ከሆቴሎችና የእንግዳ ማረፊያ አገልግሎቶች ስለሚቀርቡ መረጃዎች በቀን ወይም በሌላ ሁኔታ ለውጭ ሀገር ሰዎች ማረፊያ የሚያከራዩ ሆቴሎችና የእንግዳ ማረፊያ አገልግቶች በዚህ አዋጅ መሠረት በሚወጣ ደንብ በሚወሰነው መሠረትከውጭ ሀገር ሰው አስፈላጊውን መረጃ የመቀበል እና ለሚመለከተው አካል የማስተላለፍ ግዴታ አለባቸው ። ገጸ ፪ሺ፫፻፫፫ ፌዴራል ቁጥር ፫ ሰኔ ፳፮ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓ.ም ፲፱ : ስለክፍያ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) እና ( ፫ ) እንደተጠበቁ ሆኖ ፣ ለጉዞ ሰነድ ፣ ለቪዛ ፣ ለምዝገባ ፣ ለመኖሪያ ፈቃድና ለሌሎች አገልግሎቶች የሚጠየቀው ክፍያ በዚህ አዋጅ መሠረት በሚወጣ ደንብ ይወሰናል ፣ ፪ ለዲፕሎማቲክና ለሰርቪስ ፓስፖርቶችእና ቪዛዎች ክፍያ አይጠየቅም ፣ በሕግ ወይም በዓለም አቀፍ ውል በሚወሰነው መሠረት ክፍያ ላይጠየቅ ይችላል ። ስለቅጣት ፩ . በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ የበለጠ ቅጣት የሚያስቀጣ ካልሆነ በቀር ፣ ሀ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፫ ወይም ፮ የተደነገገውን በመተላለፍ ወደ ኢትዮጵያ የገባ ወይም ከኢትዮጵያ ወይም እንደዚህ ያለውን ሰው የረዳ ማኝኛውም ሰው ከሶስት ዓመት ባልበለጠ እሥራት ወይም ከአሥር ሺህ ብር ባልበለጠ መቀጮ ወይም በሁለቱም ይቀጣል ፣ ለ ) የዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፬ እንደተጠበቀ ሆኖ የፀና የመኖሪያ ፈቃድ ሳይኖረው ኢትዮጵያ ውስጥ የኖረ ወይም የመኖሪያ ፈቃድ የሚያስፈልገው መሆኑን እያወቀ የውጭ ሀገር ዜጋ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲቆይ ወይም እንዲኖር የረዳ ማንኛውም ሰው ከሶስት ዓመት ባልበለጠ እሥራት ወይም ከአሥር ሺህ ብር ባልበለጠ መቀጮ ወይም በሁለቱም ይቀጣል ፣ ሐ ) በዚህ አዋጅ ወይም በዚህ አዋጅ መሠረት በሚወጡ ደንቦች የተደነገጉትን በመተላለፍ ሌሎች ጥፋቶችን የፈጸመ ሰው ከአንድ ዓመት ባልበለጠ እሥራት ወይም ከአምስት ሺህ ብር ባልበለጠ የገንዘብ መቀጮ ወይም በሁለቱም ይቀጣል ። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ( ሀ ) ፣ ( ለ ) ወይም ( ሐ ) የተደነገገው ጥፋት በመፈጸም ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘው በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል የሆነ እንደሆነ የገንዘብ መቀጮው መድረሻ አራት እጥፍ ይሆናል ። ደንብ የማውጣት ሥልጣን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም አስፈላጊ የሆኑ ደንቦችን ለማውጣት ይችላል ። የተሻረ ሕግ የጉዞ ሠነዶችና ቪዛዎች አሰጣጥ እንዲሁም ስለውጭ ሀገር ሰዎች ምዝገባ የወጣው አዋጅ ቁጥር ፪፻፸፩ ፲፱፻፳፩ በዚህ አዋጅ ተሽሯል ። የመሸጋገሪያ ድንጋጌ ይህ አዋጅ ከፀናበት ቀን ጀምሮ እስከ አንድ ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ ከኢትዮጵያ ለመውጣት የሚፈልግ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፮ ከተመለከቱት በተጨማሪ የፀና የመውጫ ቪዛ መያዝ ይኖርበታል ። አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከሰኔ ፳፮ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓ.ም ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ሰኔ ፳፮ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓ.ም ግርማ ወልደጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?