የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ሁለተኛ ዓመት ቁጥር ፲፰ አዲስ አበባ የካቲት፲፬ ቀን ፲፱፻፷፰ _ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፰ ዓ ም የኬሚካል ጦር መሣሪያዎችን ዝግጅት ፡ መመረት ፡ ክምችትና በጥቅም ላይ መዋል ለመከልከልና የተመረቱትንም ለማስ ወገድ የተደረገውን ኮንቬንሽን ለማጽደቅ የወጣ . . . . . . . . . . ገጽ ፻፵፱ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፭ / ፲፱፻ዥ፰ ዓም የኢትዮጵያ የሰላምና የልማት ዓለም አቀፍ ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ . . . . . . . . . . . . . ገጽ ፻፰ አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻ዥ፰ የኬሚካል ጦር መሣሪያዎችን ዝግጅት ፡ መመረት ፡ ክምችትና በጥቅም ላይ መዋል ለመከልከልና የተመረቱትንም ለማስወገድ የተደረገውን ኮንቬንሽን ለማጽደቅ የወጣ አዋጅ የኬሚካል ጦር መሣሪያዎችን ዝግጅት ፡ መመረት ፡ ክምችትና በጥቅም ላይ መዋል ለመከልከልና የተመረቱትንም ለማስወገድ እኤአ ጃንዋሪ ፲፫ ቀን ፲፱፻፶፫ ዓም በፓሪስ የተደረገውን ኮንቬንሽን ከፈረሙት አገሮች ኢትዮጵያ ኣንዷ በመሆኗ ፤ ይህንኑ ኮንቬንሽን የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ | ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የካቲት ፲፬ ቀን ፲፱፻ዥ፰ ዓም ባደረገው ስብሰባ ያጸደቀው ስለሆነ ፤ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) እና ( ፲፪ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ « የኬሚካል ጦር መሣሪያዎችን ዝግጅት መመረት ክምችትና በጥቅም ላይ መዋል ለመከልከልና የተመረቱትንም ለማስወገድ የተደረገውን ኮንቬንሽን ማጽደቂያ የወጣ አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፳፰ » ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፰ሺ፩ ገጽ ፻፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፰ የካቲት ፲፬ ቀን ፲፱፻፻፰ ዓ . ም . Federal Negarit Gazeta No . 18 22ሥ February 1996 Page 160 ፪ ኮንቬንሽኑ ስለመጽደቁ የኬሚካል ጦር መሣሪያዎችን ዝግጅት ፡ መመረት ፡ ክምችትና በጥቅም ላይ መዋል ለመከልከልና የተመረቱትንም ለማስ | ወገድ እ ኤ . አ ጃንዋሪ ፲፫ ቀን ፲፱፻፶፫ ዓም በፓሪስ የተደ ረገው ኮንቬንሽን ጸድቋል ። ፫ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሥልጣን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ኣግባብ ካላቸው የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ጋር በመተባበር ይህን የኬሚካል ጦር መሣሪ | ያዎች ዝግጅት ፡ መመረት ፡ ክምችትና በጥቅም ላይ መዋል ለመከልከልና የተመረቱትንም ለማስወገድ የተደረገውን ኮንቬ ንሽን በሥራ ላይ እንዲውል የማድረግ ሥልጣን በዚህ አዋጅ ተሰጥቶታል ። ፬ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከየካቲት ፲፬ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓ . ም . ጀምሮ የጸና ይሆናል ። ኣዲስ አበባ የካቲት ፲፬ ቀን ፲፱፻T፰ ዓም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፭ / ፲፱፻፷፰ የኢትዮጵያ የሰላምና የልማት ዓለም አቀፍ ኢንስቲትዩትን ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ | ters pursuant to Article 5 of the Definition of Powers and ሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፳፯ ኣንቀጽ ፭ መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የኢትዮጵያ የሰላምና የልማት ዓለም አቀፍ ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ | ቁጥር ፭ / ፲፱፻፷፰ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ በዚህ ደንብ ውስጥ “ ሚኒስቴር ” ማለት የውጭ ጉዳይ | ሚኒስቴር ነው ። ፫ መቋቋም ፩ የኢትዮጵያ የሰላምና የልማት ዓለም አቀፍ ኢንስቲትዩት ( ከዚህ በኋላ “ ኢንስቲትዩቱ ” እየተባለ የሚጠራ ) በሕግ የሰውነት መብት ያለው ራሱን የቻለ ኢንስቲትዩት ሆኖ በዚህ ደንብ ተቋቁሟል ። ፪ ኢንስቲትዩቱ ተጠሪነቱ ለሚኒስቴሩ ይሆናል ። ገጽ ደ፳፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፰ የካቲት ፲፬ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓም . Federal Negarit Gazeta – No . 18 22 February 1996 Page 161 ፩ ዋና መሥሪያ ቤት የኢንስቲትዩቱ ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ ሆኖ በማና ቸውም ሥፍራቅርንጫፍ መሥሪያ ቤት ሊኖረው ይችላል ። | ፭ ዓላማ ኢንስቲትዩቱ የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል ፤ ፩ ኢትዮጵያ በሕገ መንግሥቱ እውን ያደረገችው የሁሉም ዜጐችዲሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶች መከበር ይበልጥ ሥር እንዲሰድ ፣ የተገኘው ሰላምና መረጋጋት ይበልጥ እንዲጐለብትና የኢኮኖሚና የሶሻል እድገት እንዲፋጠን ሀገሪቱ ከዓለም አቀፍ ኅብረተሰብ ጋር የምታደርገውን ትብብርና የምትመሠርተውን ቅንጅት ለማሳካት የሚረዳ ጥናት ፣ ምርምርና ሥልጠናማካሄድ ፤ ፪ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ሀገሮች መካከል በመተማመን ፣ በመከባበር ፣ በጋራ ፍላጐትና ጥቅም ላይ የተመሠረተ ግንኙነት እንዲጠናከር የበኩሉን አስተዋጽኦ ማድረግ ፤ የምርምር ተግባሮችን በማበረታታትና በመርዳት እንዲሁም በማያቋርጥ የሥልጠናፕሮግራም አማካይነት የጽንሰ ሃሳብና ተግባራዊ ድጋፍ በመስጠት የኢትዮጵያንና የአፍሪካ ቀንድ አካባቢን የወደፊት ደኅንነት ፣ መረጋጋት እና የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትን ለማፋጠን የሚያ ስችሉ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ፤ ፩ የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ሀገሮች በክልሉ ዘላቂ ሰላምና ልማት እንዲረጋገጥ ለሚያደርጉት ትግል የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ድጋፍና ትብብር እንዲጠናከርና ከሌሎች ሪጅኖች ጋር በሚደረገው ግንኙነት በጋራ ጥቅም ላይ የተመሠረተ ቅንጅት እንዲፈጠርና እንዲዳብር ማበረ ታታት ። ፮ . ሥልጣንና ተግባር ኢንስቲትዩቱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል | ፩ ከሰላምና ከልማት ጥያቄዎች ጋር የተዛመዱ የፖሊሲ | አማራጭ ጥናቶችን ማካሄድና ማሰራጨት ፤ ፪ ከዲሞክራሲያዊ ተቋማት ግንባታና የሰብዓዊ መብት | መከበር ፣ ከሰላምና ጸጥታ መረጋገጥ ፣ ከውጭ ግንኙነትና ትብብር ፡ እንደዚሁም ከኢኮኖሚና ሶሻል ግንባታ ጋር የተሳሰሩ ፖሊሲዎችና መርሆዎችን አፈጻጸም መገም ገምና አማራጭ የአፈጻጸም ስልቶችን በጥናት ላይ ተመርኩዞ ማቅረብናማሰራጨት ፤ የዲሞክራሲ ባህል እንዲዳብርና ልዩነቶች ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ትግል እንዲካሄድባቸው ፣ የሰብዓዊ መብቶች መከበር ሥር እንዲሰድ ተጠያቂነት ፡ ግልጽነትና የሕዝብ አመኔታያለው የአስተዳደር ሥርዓት እንዲጠናከር ፣ የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ተቋሞችእንዲስ ፋፉና እንዲጠናከሩ የሚያግዝ ጥናት ፣ ምርምርና ሥልጠናማካሄድ ፤ ፩ ከሰላምና ከልማት ጥያቄዎች ጋር የተያያዙ መረጃዎችን መሰብሰብ መተንተንና ለሚመለከታቸው አካላት ማሰራዉት ጅ በብሔራዊና በአካባቢው ደረጃ የሚከሰቱ አለመግባባ ቶችን በሰላማዊ መንገድ በመፍታት ረገድ አስተዋጽኦና ድጋፍ ማድረግ ፤ ፮ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ የሚረዱ በተለይም አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ በማስወገድና ሰላምን በማስፈን ስልቶች ላይ ያተኮሩ የሥልጠና ፕሮግራሞችን ማካሄድ ፤ 1 ) to conduct and disseminate policy - option studies On ገጽ ፻፳፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፰ የካቲት ፲፬ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓ . ም Federal Negarit Gazeta – No . 18 22 February 1996 Page 162 • ሴሚናሮችን ፣ ወርክሾፖችን ፣ ሲምፖዚየሞችን ፣ ጉባዔዎ ችንና የመሳሰሉ የዕውቀትና የልምድ ልውውጥ መድረ ኮችን ማዘጋጀት ፤ ፰ ከመንግሥታዊ ፣ ከዓለም አቀፍና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶችና ተመሳሳይ ዓላማ ካላቸው ተቋሞች ጋር የትብብር ግንኙነት መመሥረት ፤ ፱ የጥናትና የምርምር ውጤቶችን ማሳተምናማሠራጨት ፤ ፲• ዓላማውን ለማስፈጸም የሚረዳ ዕርዳታና ስጦታ መቀበል ፤ ፲፩ ለሚሰጠው አገልግሎት እንደአስፈላጊነቱ የአገልግሎት ዋጋ መወሰንናማስከፈል ፤ ፲፪ የንብረት ባለቤት መሆን ፣ ውል መዋዋል ፣ በስሙ መክሰስና መከሰስ ፤ ፲፫ ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚያስፈልጉ ሌሎች ተግባ ሮችን ማከናወን ። ፯ የኢንስቲትዩቱ አቋም ኢንስቲትዩቱ ፤ ፩ የባለአደራ ቦርድ ( ከዚህ በኋላ “ ቦርዱ ” እየተባለ የሚጠራ ) ፣ ፪ በሚኒስቴሩየሚሾሙ አንድዲሬክተርና ምክትል ዲሬክተር ፣ ፫ አስፈላጊው ሠራተኞች ይኖሩታል ። ፰ የቦርዱ አባላት የቦርዱ ሰብሳቢና አባላት በሚኒስቴሩ ይሰየማሉ ። ፱ የቦርዱ ሥልጣንና ተግባር ቦርዱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ፩ የኢንስቲትዩቱን ሥራዎች በበላይነት ይመራል ፣ ይቆጣ ፪ የኢንስቲትዩቱን የጥናት ፣ የምርምርና የሥልጠና ፕሮግ ራሞች መርምሮ ያጸድቃል ፤ ተግባራዊነታቸውን ይከታ ፫ የኢንስቲትዩቱን ዓመታዊ በጀት ያጸድቃል ፣ ተግባራዊነ ቱንም ይቆጣጠራል ፤ ፩ የኢንስቲትዩቱን የውስጥ ደንቦች ያጸድቃል ፣ ተግባራዊነ ታቸውንም ይከታተላል ፤ ፭ በኢንስቲትዩቱ ዲሬክተር በሚቀርቡለት ሌሎች የፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ይመክራል ፣ ይወስናል ፤ ፮ . የኢንስቲትዩቱን የሥራ አፈጻጸም ይገመግማል ፤ ለሚኒስ | ቴሩም ከአስተያየቱ ጋር ያስተላልፋል ። ፲ የቦርዱ ስብሰባ ፩ ቦርዱ ለሥራው ባስፈለገ መጠን ይሰበሰባል ። ፪ በቦርዱ ስብሰባ ላይ አብዛኞቹ አባላት ከተገኙ ምልዓተ | ጉባዔ ይሆናል ። ፫ የቦርዱ ውሳኔ የሚተላለፈው በስብሰባው በተገኙ አባላት በኣብዛኛው ድምጽ ሲደገፍ ነው ፤ ሆኖም ድምጹ እኩል በእኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው ወሳኝ ድምጽ ይኖረዋል ። ፬ ቦርዱ የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ሊያወጣ ይችላል ። ፭ ለቦርድ አባላት ሊከፈል የሚገባው አበል በቅድሚያ የሚኒስቴሩን ፈቃድ በማግኘት በኢንስቲትዩቱ የውስጥ ደንብ ይወሰናል ። ገጽ ፻፳፫ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፰ የካቲት ፲፬ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓም Federal Negarit Gazeta _ No . 18 22 February 1996 Page 163 ፲፩ . የዲሬክተሩ ሥልጣንና ተግባር ፩ ዲሬክተሩ የኢንስቲትዩቱ ዋና ኣስፈጻሚ ሆኖ ቦርዱ በሚሰጠው ኣጠቃላይ መመሪያ መሠረት የኢንስቲት ዩቱን ሥራዎች ይመራል ፣ ያስተዳድራል ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከተው ኣጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ዲሬክተሩ ፤ ሀ ) በዚህ ደንብ ኣንቀጽ ፭ የተመለከቱትን የኢንስቲት ዩቱን ሥልጣንና ተግባሮች በሥራ ላይ ያውላል ፤ ለ ) የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕጐችን መሠረታዊ ዓላማ በመከተል ቦርዱ የሚያጸድቀውን የውስጥ ደንብ መሠረት በማድረግ የኢንስቲትዩቱን ሠራተኞች ይቀጥራል ፣ ያስተዳድራል ፤ ሐ ) የኢንስቲትዩቱን ፕሮግራሞችና በጀት አዘጋጅቶ ለቦርዱ ያቀርባል ፣ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል ፤ መ ) ለኢንስቲትዩቱ በተፈቀደለት በጀትና የሥራ ፕሮግራም መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል ፤ ሠ ) ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች ሁሉ ኢንስቲትዩቱን ይወክላል ፤ ረ ) የኢንስቲትዩቱን የሥራ አፈጻጸምና የሂሳብ ሪፖርት አዘጋጅቶ ለቦርዱ ያቀርባል ። ዲሬክተሩ ለኢንስቲትዩቱ የሥራ ቅልጥፍና ባስፈለገ መጠን ከሥልጣንና ተግባሩ በከፊል ለምክትል ዲሬክ ተሩና ለኢንስቲትዩቱ ሌሎች ሠራተኞች በውክልና ሊያስ ተላልፍ ይችላል ። ፲፪ በጀት ፩ የኢንስቲትዩቱ በጀት ከሚከተሉት ምንጮች የተውጣጣ ይሆናል ፤ ሀ ) በፌዴራሉ መንግሥት ከሚመደብለት ድጐማ ፤ | 12 . Budget ለ ) ከሚያገኘው ማንኛውም ስጦታና እርዳታ ፤ ሐ ) ከሚሰበስበው የአገልግሎት ክፍያ ፤ እና መ ) ከማናቸውም ሌላ ምንጭ ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከተው ገንዘብ በኢንስቲትዩቱ ስም በሚከፈት የባንክ ሂሳብ ተቀማጭ ሆኖ የኢንስቲትዩቱን ዓላማዎች ለማስፈጸም ወጪ ይሆናል ። ፲፫ የሂሳብ መዛግብት ፩ ኢንስቲትዩቱ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሳብ መዛግብት ይይዛል ። ፪• ለዋናው ኦዲተር በሕግ የተሰጠው ሥልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ ፣ የኢንስቲትዩቱ የሂሣብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች ቦርዱ በሚሰይመው የውጭ ኦዲተር በየዓመቱ ይመረመራሉ ። ፲፬ ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ ይህ ደንብ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ የካቲት ፲፬ ቀን ፲፱፻ዥ፰ ዓም መለስ ዜናዊ የኢትየጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር