የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ስድስተኛ ዓመት ቁጥር ፪ አዲስ አበባ ጥቅምት ፲፩ ቀን ፲፱፻፪ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ፲፯ / ፲፱፻፶፪ ዓም • የኢትዮጵያ የእህል ንግድ ድርጅትን እንደገና ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ገጽ ፭ሺ፩ደ፪፩ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፵፯ / ፲፱፪ የኢትዮጵያ የእህል ንግድ ድርጅትን እንደገና ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልሥንና ተግባር ለመወሰን | These Regulations are issued by the Council of Ministes በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፷፯ አንቀጽ ፩ እና በመንግሥት | Pursuant to Article 5 of the Definitions of Power and Duties የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ / ፲፱፻፳፬ አንቀጽ ፯ / ፩ / ( መ ) | of the Executive Organs of the Federal Democratic Republic መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የኢትዮጵያ የእህል ንግድ ድርጅትን ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፲፰ / ፲፱፻፶፪ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ እንደገና መቋቋም ፩ የኢትዮጵያ የእህል ንግድ ድርጅት ከዚህ በኋላ “ ድርጅቱ ” እየተባለ የሚጠራው ከኢትዮጵያ የቅባት እህልና ጥራጥሬ ላኪ ኮርፖሬሽን ጋር ተዋህዶና የመን ግሥት የልማት ድርጅት ሆኖ በዚህ ደንብ እንደገና ተቋቁሟል ። ፪ ድርጅቱ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ / ፲፱፻፳፬ መሠረት ይተዳደራል ። ፫ . ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን በመንግሥት የሚሰየም አካል የድርጅቱ ተቆጣጣሪ ባለሥ ልጣን ይሆናል ። ያንዱ ዋጋ 29 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፰ሺ፩ • ፉትማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ገጽ ፩ሺ፩ IRI ፈዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፪ጥቅምት ፲፩ ቀን ፲፱፻ ዓ.ም ፬ . ዋና መሥሪያ ቤት የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት አዲስ አበባ ሆኖ እንደ አስፈላጊነቱ በማንኛውም ሥፍራ ቅርንጫፍ ሊኖረው ይችላል ። ድርጅቱ የተቋቋመባቸው ዓላማዎች የሚከተሉት ናቸው ፤ ፩ የእህል ምርቶችን ከአገር ውስጥ አምራቾች በመግዛት ለሀገር ውስጥና በዋነኛነት ለውጭ ገበያ ማቅረብ ፤ ፪ የገበሬው የእህል ማምረት ፍላጐት እንዲያድግ አስተ ማማኝ ገበያ የሚያገኝበት ሁኔታ እንዲፈጠር እገዛ ማድረግ ፤ ፫ ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ሥራዎችን መሥራት ፤ ፳ ካፒታል ለድርጅቱ የተፈቀደው ካፒታል ብር ፩፻፲፪ ሚሊዮን ፲፪ሺ ፬፻፶፬ ( አንድ መቶ አሥራ ሁለት ሚሊዮን አሥራ ሁለት ሺ አራት መቶሃምሣአራትብር ሲሆን ፤ ከዚህ ውስጥብር ፩፻፭ ሚሊዮን ፵፯ ሺህ ፻፬ ( አንድ መቶ አምስት ሚሊዮን አርባ ሰባት ሺ ሰባ ዘጠኝ ብር ) በጥሬ ገንዘብ እና በዓይነት ተከፍሏል ። ፯ : ኃላፊነት ድርጅቱ ከአለው ጠቅላላ ንብረት በላይ በዕዳ ተጠያቂ አይሆንም ። ድርጅቱ የሚቆይበት ጊዜ ድርጅቱ ላልተወሰነ ጊዜ ይቆያል ። ፱ የተሻረ ደንብ የኢትዮጵያ የእህል ንግድ ምክር ቤትደንብ ቁጥር ፩፻፬ / ፲፱፻፷፭ በዚህደንብተሽሯል ። ፲ • መብትና ግዴታን ስለማስተላለፍ በደንብ ቁጥር ፩፻፬ / ፲፱፻፷፭ ዓ.ም ተቋቁሞ ዮጵያ እህል ንግድ ድርጅትና የኢትዮጵያ የቅባት እህልና ጥራጥሬ ላኪ ኮርፖሬሽን በመባል ይታወቅ የነበረው ድርጅት መብቶችና ግዴታዎች በዚህ ደንብ ለድርጅቱ ተላልፈዋል ። ፲፩ ደንቡ የሚፀናበት ጊዜ ይህ ደንብ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ጥቅምት ፲፩ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓም መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ