×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
ደንብ ቁጥር 6/1988 የጉምሩክ ቀረጥ ማስከፈያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት (ማሻሻያ) ደንብ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሁለተኛ ዓመት ቁጥር ፳፯ አዲስ አበባ ሰኔ ፳፯ ቀን ፲፱፻፲፰ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ ደንብ ቁጥር ፮ ፲፬፻፰፰ ዓ • ም • የጉምሩክ ቀረጥ ማስከፈያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ( ማሻሻያ ) ገጽ ፻፲፭ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፮ ፲፱፻ T ፰ የጉምሩክ ቀረጥ ማስከፈያ ደንብን ለማሻሻል የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ ፲፱የጡ፯ አንቀጽ ፭ እና በዓለም አቀፍ | ters pursuant to Article 5 of the Definition of Powers and የተዋሀደ የሸቀጦች አሰያየምና አመዳደብ ሥርዓት ኮንቬንሽን | Duties of the Executive Organs of the Federal Democratic ማጽደቂያ አዋጅ ቁጥር ፳፯ ፲፱፻ዥ፭ አንቀጽ ፬ መሠረት ይህን | Republic of Ethiopia Proclamation No.4 / 1995 and Article 4 ደንብ አውጥቷል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ « የጉምሩክ ቀረጥ ማስከፈያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት | 1 Short Title ( ማሻሻያ ) ደንብ ቁጥር ፮ ፲፱፻ T ፰ » ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ማሻሻያ ከጉምሩክ ቀረጥ ማስከፈያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፳፪ ፲፱፻፱፭ ( እንደተሻሻለ ) ጋር ተያይዞ የሚገኘው የጉምሩክ | 2. Amendment የዕቃ ቀረጥ ሥርዓትና ተመን ሁለተኛ መደብ እንደሚከተለው ተሻሽሏል ፡ ፩ . ኣንቀጽ ( ፪ ) ( ለ ) ተሰርዞ በሚከተለው አዲስ አንቀጽ ( ፪ ) ( ለ ) ተተክቷል ፡ « ለ ) ከውጭ አገር የሚመለሱ ዜጐችና በተራድኦ ስምምነት የሚመጡ የውጭ ዜጐች ( ፩ ) በውጭ አገር የኢትዮጵያ የዲፕሎማቲክ ሚሲዮን አገልግለው ወይም ለሌላ የመንግሥት ሥራ : ለትምህርት ፡ ለግል ሥራ ፡ በስደት ወይም ለተለያዩ ጉዳዮች ውጭ አገር ቆይተው የሚመለሱ ወይም መንግሥት በሚያደርገው ልዩ ጥሪ መሠረት የሚ ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፱ሺ፩ ገጽ ፻፲፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፯ ሰኔ ፳፯ ቀን ፲፱፻፷፰ ዓም መጡ ኢትዮጵያውያን የፌዴራል መንግሥት የገቢዎች ቦርድ በሚያወጣው መመሪያ በተመለከተው ዝርዝር መሠረት የግል መገልገያ ዕቃዎቻቸውን ከቀረጥ ነጻ ማስገባት ይችላሉ ። ( ፪ ) የኢትዮጵያ መንግሥት ከልዩ ልዩ መንግሥታትና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ወይም ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በሚያደ ርገው የተራድኦ ስምምነት መሠረት የሚመጡ የውጭ አገር ዜጐች የፌዴራል መንግሥት የገቢዎች ቦርድ በሚያወጣው መመሪያ በተመለከተው ዝርዝር መሠረት የግል መገልገያ ዕቃዎቻቸውን ከቀረጥ ነጻ ማስገባት ይችላሉ ። » ፪ አንቀጽ ለ ( ፬ ) ተሰርዞ በሚከተለው ኣዲስ ኣንቀጽ ለ ( ፬ ) ተተክቷል ፡ « ፬ • የኢትዮጵያ መንግሥት መሥሪያ ቤቶችና መንግሥታዊ ያልሆኑ የእርዳታ ድርጅቶች ስለሚያስመጧቸው | 2. Article B ( 4 ) is hereby deleted and replaced by the following ( ሀ ) የኢትዮጵያ መንግሥት መሥሪያ ቤቶች እና መንግ ሥታዊ ያልሆኑ የእርዳታ ድርጅቶች የሚያስመጧ ቸውን የልማት መሣሪያዎችና ዕቃዎች የኢትዮጵያ ኢንቬስትመንት ባለሥልጣን ፡ አግባብ ካለው የፌዴራል መሥሪያ ቤት ወይም የክልል መስተ ዳድር ቢሮ ከሚቀርብለት የፕሮጀክት ሰነድ ኣንጻር መርምሮ፡ ከፕሮጀክቱ ጋር የሚዛመዱ እና በኢንቬስ ትመንት ሕግ መሠረት ከቀረጥ ነጻ ሆነው ሊገቡ የሚችሉ የልማት መሣሪያዎችና ዕቃዎች መሆና ቸውን ሲያረጋግጥ ከቀረጥ ነጻ ሆነው መግባት ይችላሉ ። ( ለ ) ከዚህ በላይ በንዑስ አንቀጽ ( ሀ ) የተመለከቱት መሥሪያ ቤቶችና ድርጅቶች የሚያስመጧቸው ሌሎች ዕቃዎች በታሪፍ ደንቡ በተመለከተው መሠረት ቀረጥ ይክፈልባቸዋል ። ( ሐ ) በአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኮሚሽን ጥሪ መሠረት መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ የእርዳታ ድርጅቶች ለድንገተኛ አደጋ በሚያስገ ቡአቸው የምግብ ምርቶች ፡ የሕክምና መሣሪ ያዎች እና ሌሎች ተመሳሳይ አቅርቦቶች ላይ ሊከፈል የሚገባውን ቀረጥ ኮሚሽኑ በጀት በማስ | 3. The following new sub - Article 10is added aftersub - Article ፈቀድ እየያዘ ይከፍላል ። » - ከንዑስ አንቀጽ ፬ ቀጥሎ የሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ ፲ ተጨምሯል ፡ « ፲ ልዩ ሥልጣን ( ሀ ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ባለሥልጣን ፡ በዚህ ደንብ መሠረት የኢትዮጵያ መንግሥት መሥሪያ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ የእርዳታ ድርጅቶች የሚያስመጧቸው የልማት መሣሪያ ዎችና እቃዎች ከፕሮጀክቶቹ ጋር የሚዛመዱ መሆና ቸውን ፕሮጀክቱ የሚመለከታቸው የፌዴራል መሥሪያ ቤቶችና የክልል መስተዳድር ቢሮዎች የሚያቀርቡለትን ሰነድ መርምሮ በማረጋገጥ ፡ ነጻ መብቱን አፈጻጸም የማመቻቸት ኃላፊነት ተሰጥቶታል ። ( ለ ) በመንግሥታዊ መሥሪያ ቤቶች እና መንግሥታዊ ባልሆኑ የእርዳታ ድርጅቶች የሚካሄዱ ፕሮጀክ በተመለከተ ከክልል መስተዳድሮች የሚቀርቡ መረጃዎች ይዘት ምን ሊሆን እንደሚገባ ባለሥልጣኑ መመሪያ ያወጣል ። » ገጽ ፻፲፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፯ ሰኔ ፳፯ ቀን ፲፱፻፷፰ ዓም ፫ • ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ ይህ ደንብ ከሐምሌ ፩ ቀን ፲፱፻፷፰ ዓ.ም. ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ሰኔ ፳፯ ቀን ፲፱፻፶፰ ዓም መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?