በሚያገለግልበት ወቅት ተረኛ በነበረ .
የሰ / መ / ቁ 17680
ጥቅምት 24 ቀን 1999 ዓ.ም.
ዳኞች 1. አቶ ከማል በድሪ
2. አቶ ፍስሐ ወርቅነህ
3. አቶ አብዱልቃድር መሐመድ
4. አቶ መስፍን እቁበዮናስ
5. ወ / ት ሒሩት መለሠ
አመልካች ሰባተኛው ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን
መልስ ሰጭ፡ አቶ በየነ ሞላው
ፍ ር ድ
ጉዳዩ ለዚህ ችሎት የቀረበው መልስ ሰጭ በአመልካች ቤተክርስቲያን በዘበኛነት
ቀን የድርጅቱ ንብረት ተዘርፏል በሚል አመልካች
መልስ ሰጭን ከስራ ካሰናበተ በኋላ መልስ ሰጭ ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት
ባቀረቡት ክስ ፍርድ ቤቱ ስንብቱ ሕጋዊ ነው በማለት የሰጠውን ውሣኔ ጉዳዩ በይግባኝ
የቀረበለት ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመሻር የሰጠው
ውሣኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት
የተፈጸመበት ነው በማለት አመልካች የሰበር አቤቱታ በማቅረቡ ነው :: ጉዳዩ ለሰበር ችሎት
እንዲቀርብ በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት አመልካችና መልስ ሰጭ ክርክራቸውን ለችሎት
በጽሁፍ አቅርበዋል ፡፡
ችሎቱም መልስ ሰጭ ወደ ስራው እንዲመለስ የተወሰነው በአግባቡ ነው ? ወይስ
አይደለም ? የሚለውን ነጥብ መሠረት በማድረግ ጉዳዩን መርምሯል ፡፡
የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ስንብቱ ሕጋዊ ነው በማለት መልስ ሰጭ
ያቀረቡትን ክስ ውድቅ በማድረግ የወሰነው
ተረኛ በነበሩ ቀን የአሰሪው ንብረት የጠፋ
መሆኑ በማስረጃ የተረጋገጠ ነው ፤ ተረኛ በነበሩ ቀን የአሰሪ ንብረት ለመጥፋቱ መልስ ሰጭ
ተጠያቂ ናቸው በማለት ነው :: ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ
ከሥራ እንዲያ ባ ou
ራተኛው ጥፋት ምክንያት በአሠሪው ንብረት ላይ የሚደርሰው ቤት በበኩሉ የፌዴሪል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ የሻረው አመልካች መልስ ሰጭ ተረኛ በነበሩበት ሚያዝያ 30 ቀን 1994 ዓም . ቀን ጠፋብን ሲል ግንቦት 1 ቀን 1994 ዓ.ም. ለፖሊስ ያመለከተው ብር 670 ብቻ ነው ፤ ሌሎቹ ጠፉት የተባሉትን ንብረቶች በሚመለከት ለፖሊስ ሪፖርት የተደረገው ግንቦት 7 ቀን 1994 ዓ.ም. ነው ፤ የአመልካች ምስክሮች የሚያስረዱት ጠፋ ስለተባለው ጥሬ ገንዘብ እንጅ ስለሌሎች ንብረቶች አይደለም ፤ ይህ ደግሞ ከሥራ የሚያሰናብት ስለመሆኑ ፍርድ ቤቱ አላመነም በሚል ነው ::
በመሠረቱ ጉዳዩ የሚታይበት የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 42/85 አንቀጽ 27 / 1 / በ / በአሰሪው ንብረት ወይም ከድርጅቱ ሥራ ጋር በቀጥታ ግንነት ባለው ማናቸውም ንብረት ላይ ሆነ ብሎ ወይም በቸልተኝነት ጉዳት ማድረስ ያለማስጠንቀቂያ ጥፋት ከፍተኛ መሆን የለበትም ፡፡ ሠራተኛው በአሠሪው ንብረት ላይ ለሚደርስ ጉዳይ
ተጠያቂ ከሆነ የንብረቱ ግምት ከፍተኛ ሆነም አልሆነ አሠሪው ሠራተኛውን በተጠቀሰው
ድንጋጌ በሕጋዊ መንገድ ከሥራ ሊያሰናብት ይችላል ።
በዚህ ጉዳይ መልስ ሰጭ ተረኛ በነበሩበት ቀን የአሰሪው ንብረት የሆነ ብር 670.00
የጠፋ ስለመሆኑ የቀረቡት ምስክሮች ያስረዱ መሆኑን የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤቱም
አምኖበታል ፡፡ ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ስንብቱ ሕጋዊ
ነው በማለት የሰጠውን ውሣኔ የሻረው ይህ በምስክሮች የተረጋገጠው ፍሬ ነገር ሰራተኛን
ከሥራ ለማሰናበት በቂ አይደለም በሚል ነው ። ሆኖም ይህ በማስረጃ የተረጋገጠ ፍሬ ነገር
ከላይ በተመለከተው መሠረት መልስ ሰጭን በሕጋዊ መንገድ ከሥራ ለማሰናበት የሚያበቃ
ምክንያት መሆኑን መረዳት ይቻላል ፡፡ በመሆኑም ይህ ችሎት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት
መሠረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበትና
መታረም የሚገባው
አግኝቶታል ፡፡
ው ሣ ኔ
አመልካች
መልስ ሰጭን ከሥራ ያሰናበተው
ተወስኗል ።
የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት በመ / ቁ 28627 ኅዳር ለ 2 ቀን 1997 ዓ.ም. የሰጠው
ው ተሽሮ የፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በመ / ቁ 06540 ጥር 03 ቀን
1996 ዓ.ም. የሰጠው ውጭ ጸንቷል ።
- አመልካችና መልስ ሰጭ በዚህ ችሎት ያወጡትን ወጭና የደረሰባቸውን ኪሣራ
የየራሳቸውን ይቻሉ ፡፡
መዝገቡ ተዘግቷል ።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ፡፡
You must login to view the entire document.