የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አሥራአንደኛ ዓመት ቁጥር ፴፯ አዲስ ኣበባ- ግንቦት ፲፰ ቀን ፲፱፻ኝ ፤ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፬፻፵፱ / ፲፱፻፲፯ ዓ.ም የሕዝብ ቆጠራ ኮሚሽንን እንደገና ለማቋቋም የወጣ አዋጅ ገጽ ፫ሺ፩፻፪ አዋጅ ቁጥር ፬፻፵፱ / ፲፱፻፵፯ የሕዝብ ቆጠራ ኮሚሽንን እንደገና ለማቋቋም የወጣ አዋጅ የሕዝብ ቆጠራ ውጤት የሕዝቡን ኑሮ ለማሻሻል ለሚደረገው ሕገ መንግሥታዊ አደረጃጀትና ለፖለቲካዊ | the constitutional organization and preparation of the ሥርዓቱ ዝግጅት አስፈላጊ ስለሆነ ፣ ትክክለኛውን የሕዝብ ብዛት ማወቅ በሀገር አቀፍ በተወሰነ አስተዳደር ለሚደረጉ ምርጫዎች አፈጻጸም አስተማማኝ መሠረት በመሆኑ ፣ የተግባሩን አስፈላጊነት ፣ ስፋት እና ውስብስብነት በማገናዘብ የሕዝብ ቆጠራ ኮሚሽን እንደሚቋቋም በሕገ | provision on the establishment of a commission , in መንግሥቱ የተደነገገውን በሥራ ላይ ለማዋል ዝርዝር ሕግ | consideration of the necessity , extensiveness and ማውጣት አስፈላጊ በመሆኑ ፣ ቆጠራ ኮሚሽንን ለማቋቋም ቀደም ሲል የወጣው አዋጅ ቁጥር ፩፻፫ / ፲፱፻፵፩ በተግባር ሲታይ የሥራ | proclamation No. 180/1999 was found to be creating ድግግሞሽን የሚፈጥር ሆኖ በመገኘቱ ፣ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፩፻፫ እና አንቀጽ መሠረት ከዚህ እንደሚከተለው ታውጇል ፡፡ ፩ . አጭር ርዕስ አዋጅ " የሕዝብ ቆጠራ ኮሚሽንን እንደገና ለማቋቋም የወጣ አዋጅ ቁጥር ፬፻፵፱ / ፲፱፻፲፯ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ፡፡ ያንዱ ቀጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖ.ሣ.ቁ ዥ : ፩ ፪ / ኮሚሽኑ ተጠሪነቱ ለምክር ቤቱ ይሆናል ) ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፯ ግንቦት ፲፰ ቀን ፲፱፻፵፯ ዓ.ም Federal Negarit Gazeta - No . 37 26 May , 2005 -- Page 3103 ፪ . ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ፡ ፩ / “ የሕዝብ ቆጠራ ” ወይም ቆጠራ ማለት በሀገር በተወሰነ አስተዳደር እርከን ስለሚገኘው ጠቅላላ የሕዝብ ብዛት ፣ የጾታ ፣ የዕድሜ ፣ የጋብቻ ፣ የትምህርት ደረጃ ፣ የሰው ኃይል ፣ የሥራ ዓይነት ፣ የሥራ መስክ ፣ የልደት ፣ የሞት ፣ የፍልሰትና ሌሎች ተመሳሳይ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መረጃዎችን የመሰብሰብ ፣ የማጠናቀር ፣ የመገምገምና የማሰራጨት ተግባር ነው ፣ ፪ / “ የቆጠራ ካርታ ሥራ ” ማለት ማንኛውም ሰው ሳይቆጠር እንዳይቀር እንደዚሁም ከአንድ ጊዜ በላይ እንዳይቆጠር ለማድረግ የቆጠራው ክንዋኔ ከመጀመሩ በፊት የቆጠራ ቦታና የመቆጣጠሪያ ቦታ ካርታዎች ማዘጋጀት ነው ፣ ፫ / “ ምክር ቤት ” ማለት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ተወካዮች ምክር ቤት ነው ፣ ፬ / “ ሰው ማለት የተፈጥር ሰው ወይም የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው ” ፭ / “ ባለሥልጣን ” ማለት የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ባለሥልጣን ነው ፣ ስለመቋቋም የሕዝብ ቆጠራ ኮሚሽን ( ከዚህ በኋላ “ ኮሚሽኑ ” እየተባለ የሚጠራ ) በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ፣ ዓላማዎች የኮሚሽኑ ዓላማ ለአስተዳደራዊ ጉዳዮችና ለምርጫዎች ፣ ለዕቅድ ዝግጅት ፣ ለዕቅድ አፈጻጸም ፣ ክትትልና ግምገማ እንዲሁም ለምርምር የሚጠቅሙ የሚመለከቱ መረጃዎችን በቆጠራ መሰብሰብ ፣ ማጠናቀር ፣ መገምገምና ማሰራጨት ፣ ይሆናል ። ፭ / የኮሚሽኑ አወቃቀር ፩ / በሕገ - መንግሥቱ አንቀጽ ፩፻፪ ንዑስ አንቀጽ ፪ በተደነገገው መሠረት የኮሚሽኑ አባላት በጠቅላይ “ ሚኒስትሩ አቅራቢነት በምክር ቤቱ ይሾማሉ ፣ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፯ ግንቦት ፲፰ ቀን ፲፱፻፵፯ ዓ.ም Federal Negarit Gazeta - No . 37 26 May , 2005 -- Pag 3104 የኮሚሽኑ ሰብሳቢ የሚሆነው አባል የሚኒስትር ወይም ከዚያ በላይ ደረጃ ያለው የፌዴራል መንግሥት ሹም ሆኖ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት በምክር ቤቱ ተለይቶ ይሰየማል ፣ የባለሥልጣኑ መሥሪያ ቤት የኮሚሽኑ ጽሕፈት ቤት ሆኖ ያገለግላል ፡፡ ባለሥልጣኑ ለሕዝብ ቆጠራ ጉዳይ ብቻ ተጠሪነቱ ለኮሚሽኑ ይሆናል ፣ ፬ / የባለሥልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ የኮሚሽኑ አባለና ዋና ፀሐፊ ሆኖ ይሠራል ፡፡ 3 የኮሚሽኑ አባላት ስብጥር ኮሚሽኑ ለሕዝብ ቆጠራ ጉዳይ አግባብነት ካላቸው የፌዴራል ሚኒስቴር ሚኒስትሮች ፣ ከምርጫ ቦርድ ፣ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ፣ ከዘጠኙ ክለቦች ፣ ከአዲስ አበባና ከድሬዳዋ መስተዳድሮች የተውጣጡ አባላት ይኖሩታል ፣ የኮሚሽኑ ሥልጣንና ተግባር ኮሚሽኑ፡ ፩ / የሕዝብ ቆጠራ እንዲካሄድ በማድረግ የአገሪቱ የሕዝብ ብዛት በአገር አቀፍ ፣ በክልል ፣ በዞን ፣ በወረዳ ፣ በከተማ እንዲሁም በከተማና በገጠር ቀበሌዎች ተለይቶ በጾታና በዕድሜ እንዲዘጋጅ ያደርጋል ፣ ፪ / የቆጠራ ካርታ ሥራ የሕዝብ ቆጠራን በሚመለከት መመሪያ ያወጣል ፣ አፈጻጸማቸውን ይከታተላል ፣ ስለቆጠራ ፫ / ስለቆጠራ ካርታ ምንነት ሕዝቡን ያሳውቃል ፣ በሚያወጣው በወረዳና አስፈላጊ ሆነው በሚያገኛቸው ተጨማሪ የአስተዳደር እርከኖች ደረጃ ሌሎች ኮሚሽኖችን በቆጠራ ማካሄጃ ወቅት ያቋቁማል ፣ እንዲሁም ሥልጣንና ተግባራቸውን የአባላቱን አሰያየምና የስብሰባ ሥነ - ሥርዓታቸውን ይወስናል ፣ ፭ / ከፌዴሬሽን ምክር ቤት በሚቀርበው የብሔረሰቦች ዝርዝር መሠረት እና በሕዝብ ቆጠራ አማካኝነት የብሔረሰቦች እንዲታወቅ ያደርጋል ፣ ፮ / በየክልሉ በሚገኙት ዞኖች ፣ ወረዳዎች ፣ ከተማዎች እና የከተማና የገጠር ቀበሌዎች ውስጥ ያለው የእያንዳንዱ ብሔረሰብ የሕዝብ ቁጥር በጾታና በዕድሜ ተከፋፍሎ በገጠርና በከተማ ተለይቶ እንዲዘጋጅ ያደርጋል ፣ * ብራል ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፯ ግንቦት ፲፰ ቀን ፲፱፻፵፯ ዓ.ም Federal Negarit Gazeta - No . 37 26 May , 2005 -- Page ፯ / በዚህ አዋጅ መሠረት በሚካሄደው አፈፃፀም ሂደት በስፋቱና በዓይነቱ የቆጠራውን ውጤት ሊያዛባ የሚችል ግድፈት ስለመከሰቱ መረጃ ካገኘ ለምክር በማሳወቅ ውጤቱን ይሠርዛል ፣ እንደገና ቆጠራ እንዲካሄድ የቆጠራ ውጤቶችን ያረጋግጣል ፣ ለምክር ቤቱ ያቀርባል እንዲሁም ሲቀበለው ለሕዝብ በይፋ እንዲለጽና በተለያዩ መንገዶችም እንዲሰራጭ ያደርጋል ፣ ፱ / የሕዝብ ቆጠራ በጀት ለመክር ቤቱ ያስፈቅዳል ፣ በትክክል በሥራ ላይ መዋሉን ያረጋግጣል ፣ ፲ / ስለ ሥራ አፈፃፀሙ በየጊዜው ለምክር ቤቱ ሪፖርት ያቀርባል ፡፡ ፮ . የኮሚሽኑ ስብሰባ ፩ / ኮሚሽኑ ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ ይሰበስባል ፣ ፪ / ከኮሚሽኑ አባላት ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑ በስብሰባ ላይ ሲገኙ ምልዓተ - ጉባዔ ይሆናል ፣ ፫ / የኮሚሽኑ ወሳኔዎች በድምጽ ብልጫ ይሰጣሉ ፣ ሆኖም ድምጽ እኩል ለእኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው ወሳኝ ድምጽ ይኖረዋል ፬ / የዚህ አንቀጽ ሌሎች ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው ፣ ኮሚሽኑ የራሱን የስብሰባ ሥነ - ሥርዓት ደንብ ሊያወጣ ይችላል ፡፡ ፱ . የኮሚሽኑ ስብሳቢ ሥልጣንና ተግባር የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ፣ ፩ / ኮሚሽኑን ስብሰባ ይጠራል ፣ ፪ / የኮሚሽኑ ውሳኔዎች በሥራ ላይ መዋላቸውን ያረጋግጣል ፣ የሕዝብ ቆጠራ ሥራን በሚመለከት የኮሚሽኑን ጽሕፈት ቤት የሥራ እንቅስቃሴ በበላይነት ይቆጣጠራል ፡፡ ፲ የኮሚሽኑ ጽሕፈት ቤት ሥልጣንና ተግባር የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ጽሕፈት ቤቱ ይኖሩታል የቆጠራ ካርታ ሥራ የማከናወን ፣ ም ል ሌሎች ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፯ ግንቦት ፲፰ ቀን ፲፱፻፵፯ ዓ.ም Federal Negarit Gazeta - No . 37 26 May , 2005 -Pag 3106 ፪ / የቆጠራ ዕቅድ አዘጋጅቶ ለኮሚሽኑ የማቅረብ ፣ ፫ / የቆጠራ ሥራ የማካሄድ ፣ ለዚሁም አፈፃፀም በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፯ ( ፴ መሠረት የሚቋቋሙትን ኮሚሽኖች እንቅስቃሴ የመምራት የማስተባበርና የመቆጣጠር ፣ ፬ / ለቆጠራ አፈፃፀም የሚያስፈልጉ መጠይቆች መመሪያዎችና ልዩ እንዲሁም ቁሳቁሶች የማዘጋጀትና የማሠራጨት ፣ ፩ / ሕዝብን የሚመለከቱ መረጃዎችን ለመሰብሰብ ያላቸውን ሰነዶችና መዛግብት የመመርመር ፣ ምርመራውንም ለማከናወን ተገቢ በሆነ ጊዜ ወደ ማንኛውም ሰው ቤት ወይም ቅጥር ግቢ የመግባት ፣ ለቆጠራ አፈፃፀም የሚያስፈልገውን የሰው ኃይል የማሰልጠን ፣ ፯ / በዚህ አዋጅ በአንቀጽ ፯ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እና ፪ ) መሠረት የቆጠራ ካርታ ሥራ ወይም ቆጠራ ለማካሄድ በተወሰነው ጊዜ ውስጥ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ለመንግሥት በማንኛውም የመንግሥት ሠራተኞች ንብረትና አገልግሎት የመጠቀም ፣ የተሰበሰበውን ማደራጀት መተንተንና ሪፖርቱን አዘጋጅቶ እንዲወድቅ ለኮሚሽኑ የማቅረብ ፣ በየጊዜው የሚደረገውን አፈፃፀም የመገምገም እንዳስፈላጊነቱም የአሠራር ማሻሻያ ጥናቶች እንዲካሄዱ የማድረግ ፣ ፲ / በኮሚሽኑ በሚሰጠው መመሪያ መሠረት አግባብ ያላቸውን ተግባሮች የማከናወን ፡፡ ፲፩ . በጀ ት ኮሚሽኑ ፣ ፩ / በምክር ቤቱ በሚጸድቀው መሠረት ለቆጠራ የካፒታል በጀት ከመንግሥት ይመደብለታል ማካሄጃ ከውጭ ይችላል ፡፡ ፲፪ ግዴ ታ ፩ / ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ለቆጠራው ሥራ የመተባበር ግዴታ አለበት ፣ ዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፯ ግንቦት ፲፰ ቀን ፲፱፻፵፯ ዓ.ም Federal Negarit Gazeta - No . 37 26 May , 2005 -Page በዚህ አዋጅ መሠረት ለቆጠራ መረጃ እንዲሰጥ የተጠየቀ መንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ከኮሚሽኑ ጽሕፈት ቤት የተሰጠውን መታወቂያ ለሚያሳይ መረጃ ሰብሳቢ ወይም ተቆጣጣሪ ትክክለኛውን መረጃ የመስጠት ግዴታ አለበት፡ ፫ / ማንኛውም የቤት ወይም የቅጥር ግቢ ባለንብረት ባለይዞታ ወይም ጠባቂ ከኮሚሽኑ ጽሕፈት ቤት የተሰጠውን መታወቂያ ለሚያሳይ የቆጠራ መረጃ ሰብሳቢ ወይም ተቆጣጣሪ ወደተባለው ንብረት እንዲገባ የመፍቀድ ግዴታ አለበት ። ፲፫ የመረዎች ምሥጢራዊነት በፍርድ ቤት በማስረጃነት እንዲያቀርብ ካልታዘዘ በስተቀር የኮሚሽኑ ጽሕፈት ቤት የሰበሰባቸውን ያልተጠቃለሉ መረጃዎች በምሥጢር ይጠብቃል ፡፡ ፲፬ . ቅ ጣ ት በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ መሠረት የበለጠ ቅጣት የሚስከትል ካልሆነ በስተቀር ማንኛውም ሰውን ፩ / የቆጠራ መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ ያልሆነ እንደሆነ በሚደርስ እሥራት ይቀጣል ፡፡ ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘው የሕግ ሰውነት መብት የተሰጠው ድርጅት ሲሆን ከብር ፪ ሺህ ሁለት ሺህ ብር ) በማይበልጥ ገንዘብ ይቀጣል ፣ ፪ / ይህንኑ በሚመለከት ሀሰተኛ መረጃ የሰጠ ወይም በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፬ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) መሠረት ወደተመለከተው ንብረት ገብቶ የቆጠራ መረጃ የማግኘት ሥራን ያሰናከለ እንደሆነ ጥፋተኛ ሆኖ ሲገኝ እስከ አንድ ዓመት በሚደርስ እሥራት ይቀጣል ፡፡ ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘው በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው ድርጅት ሲሆን ከብር ፭ ሺህ ( አምስት ሺህ ብር ) በማይበልጥ ገንዘብ ይቀጣል ። ፲፭ . የተሻሩ እና ተፈጻሚ የማይሆኑ ሕጎች ፩ / የሕዝብ ቆጠራ ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፪ / ይህን አዋጅ የሚቃረን ማናቸውም ሌላ ሕግ ፣ ደንብ ፣ መመሪያ ወይም የአሠራር ልምድ በዚህ በተመለከቱ ተፈፃሚነት አይኖረውም ፡፡ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፯ ግንቦት ፲፰ ቀን ፲፱፻፵፯ ዓ.ም Federal Negarit Gazeta - No . 37 26 May , 2005 - Page ፲፯ . ዲንብና መመሪያ የማውጣት ሥልጣን ኮሚሽኑ ይህን አዋጅ ለማስፈጸም የሚያስፈልጉትን ደንቦችና መመሪያዎች ለማውጣት ይችላል ፡፡ ፲፯ . የመብትና ግዴታዎች መተላለፍ በአዋጅ ቁጥር ፩፻፯ / ፲፱፻፲፩ መሠረት ተቋቁሟ የነበረው የሕዝብ ቆጠራ ኮሚሽን ጽ / ቤት መብትና ግዴታዎች ለባለሥልጣኑ ተላልፈዋል ፡፡ ፲፰ . አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከግቦት ፲፰ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓ.ም ጀምሮ የፀና ይሆናል ፡፡ አዲስ አበባ ግንቦት ፲፰ ቀን ፲፱፻፵፯ ዓ.ም ግርማ ወልደጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት