ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አምስተኛ ዓመት ቁጥር ፲፯ አዲስ አበባ ኅዳር ፳፱ ቀን ፲፱፻፲፩ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፩፻፵ / ፲፱፻፶፩ ዓ.ም ለእርሻ ምርምርና ሥልጠና ፕሮጀክት ከፊል ማስፈጸሚያ ከዓለምአቀፍ የልማትማኅበር ብድር ለማግኘት የተፈረመው የብድር ስምምነት ማጽደቂያ ገጽ ፬፻፲፫ አዋጅ ቁጥር ፩፻፮ / ፲፱፻፶፩ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በዓለምአቀፍ የልማት ማኅበር መካከል የተደረገውን የብድር ስምምነት ለማጽደቅ የወጣ አዋጅ ለእርሻ ምርምርና ሥልጠና ፕሮጀክት ከፊል ማስፈጸሚያ የሚውል መጠኑ ኤስዲአር ፴፬ሚሊዮን፭፻ሺህ ( አርባ አራት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ኤስዲአር የሆነ ገንዘብ የሚያስ ገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በዓለምአቀፍ የልማት ማኅበር መካከል እኤአ ኦገስት ፯ ቀን ፲፱፻፶፰ በዋሽንግተን ዲሲ የተፈረመ በመሆኑ ፤ መሠረታዊ የኢኮኖሚ ዓለምአቀፍ ውሎች ተፈጻሚ ከመሆ ናቸው በፊት መጽደቅ ስላለባቸው ፣ ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኅዳር ፳፬ ቀን ፲፱፻፵፩ ዓም . ባደረገው ስብሰባ ያጸደቀው ስለሆነ ፤ በሕገመንግሥቱ አንቀጽ ፲፭ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እና ( ፲፱ መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ ለእርሻ ምርምርና ሥልጠና ፕሮጀክት ከፊል ማስፈጸሚያ ከዓለምአቀፍ የልማት ማኅበር ብድር ለማግኘት የተፈረመው የብድር ስምምነትማጽደቂያ አዋጅቁጥር ፩፻፵ ፲፱፻፵፩ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ያንዱ ዋጋ 2.30 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁር ገጽ ፱፻፲፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፭ ኅዳር ፳፱ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓ.ም. ፪ . ትርጓሜ በዚህ አዋጅ ውስጥ “ የብድር ስምምነት ” ማለት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በዓለምአቀፍ የልማት ማኅበር መካከል እ.ኤ.አ ኦገስት ፯ ቀን ፲፱፻፶፰ በዋሽንግተን ዲሲ- የተፈረመው ቁጥር ፫ሺህ፲፪ የብድር ስምምነት ነው ። ፫ የገንዘብ ሚኒስትር ሥልጣን የገንዘብ ሚኒስትሩ በብድር ስምምነቱ የተገኘውን ኤስዲአር ፬ሚሊዮን፭፻ሺህ ( አርባ አራት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ኤስዲአር ) በብድር ስምምነቱ በተመለከቱት ሁኔታዎች መሠረት በሥራ ላይ እንዲውል ለማድረግ በዚህ አዋጅ ሥልጣን ተሰጥቶታል ። ፩ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከኅዳር ፳፱ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓ.ም. ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ኅዳር ፳፬ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓ.ም. ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ