ሠላሳ አራተኛ ዓመት ቊጥር ፵፫
መ ን ግ ሥ ት
ነ ጋ ሪ ት ፡ ጋ ዜ ጣ ። ጣ
የጋዜጣው ዋጋ
ባገር ውስጥ ባመት
በ፮ ወር
ለውጭ አገር እጥፍ ይሆናል "
ማ ው ጫ
፲፱፻፷፯ ዓ. ም
አዋጅ ቊጥር ፵፱ ፲፱፻፷፯ ዓ. ም.
በጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ ሊቀ መንበር ጽሕፈት ቤት ተጠባባቂነት የወጣ
የመንግሥት የሆኑ ድርጅቶች ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ
የሕግ ክፍል ማስታወቂያ ቊጥር ፳፩ ፲፱፻፷፯ ዓ. ም. የኢትዮጵያ ሆቴሎችና ቱሪዝም ድርጅት ማቋቋሚያ ደንብ
ገጽ ፪፻፳፩
አዋጅ ቁጥር ፵፱ ፲፱፻፷፯ ዓ. ም.
የመንግሥት ንብረት ለሆኑ ድርጅቶች ሠራተኞች ስለሚ ከፈል የጡረታ አበል የወጣ አዋጅ
« ኢትዮጵያ ትቅደም »
ገጽ ፪፻፳፬
የአንዳንድ ማኅበራዊ መሆኑን በመገንዘብና ፤
ወዝ አደር ሴቶችና ወንዶች ራ ላይ ለሚደርስባቸው የአካል መጉደል ፤ በእርጅናና በሞት ምክንያት ለሚደርስባ ቸው የኑሮ ችግር መድኅን መስጠት አስፈላጊ መሆኑን በመ ረዳት º
እርምጃዎች መወሰድ ተገቢ
የጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግንና የሊቀ መንበሩን ሥልጣን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቊጥር ፪ ፲፱፻፷፯ ዓ. ም. አንቀጽ ፮ መሠረት ከዚህ የሚከተለው ታውጅዋል ። ፩. አጭር ርእስ ፤
ይህ አዋጅ « የመንግሥት የሆኑ ድርጅቶች ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ ቊጥር ፵፱፲፱፻፷፯ ዓ. ም. » ተብሎ ሊጠቀስ ይቻላል ።
፪. ትርጓሜ ፤
የቃሉ አግባብ ሌላ ትርጉም ካልሰጠው በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ ፦ —
፩ « ሠራተኛ » ማለት
ሀ / ሙሉ በሙሉ ወይም አብዛኛው ድርሻ ወደ መን ግሥት በተዛወረ የእርሻ ፤ የንግድ ፤ የኢንዱስትሪ ፤ የትራንስፖርት ፤ የባንክ ወይም የመድን (ኢንሹራ ንስ) ድርጅት ውስጥ ፤ ድርጅቱ ወደ መንግሥት በተዛወረበት ቀን ቋሚሠራተኛ የነበረ ሰው ፤ ወይም ከዚህ ቀን በኋላ በነዚህ ድርጅቶች ውስጥ የቀጠረ ሰው ፤
አዲስ አበባ ጳጉሜ ፬ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓ.ም.
ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ ይታተማል "
የፖስታ ሣጥን ቍጥር ፩ሺ፴፩ (1031)