ሀያ ስምንተኛ ዓመት ቍጥር ፳፯ =
ነ ገ ሥ ት መ ን ግ ሥ ት s
ነ ነ ጋ ሪ ት: ጋ ዜ ጣ
የጋዜጣው ዋጋ
ባገር ውስጥ ባመት
በ፯ ወር
» ያንዱ ለውጭ አገር እጥፍ ይሆናል ▪
፲፱፻፷፩ ዓ. ም.
በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት በጽሕፈት ሚኒስቴር ተጠባባቂነት የቆመ
የሕግ ክፍል ማስታወቂያ ቍጥር ፫፻፸፪፷፩ ዓ. ም. የወለጋ ጠቅላይ ግዛት ማዘጋጃ ቤቶች የግብር ፤ የቀረጥና የታክስ ደንብ
የሕግ ክፍል ማስታወቂያ ቁጥር ፫፻፸፪ ፲፱፻፷፩ ዓ / ም በ፲፱፻፴፯ ዓ ም / ስለማዘጋጃ ቤቶች በወጣው ዐዋጅ መሠረት
የወጣ ደንብ ።
፩ ይህ ደንብ በ፲፱፻፴፯ ዓም ስለማዘጋጃ ቤቶች በወጣው ዐዋጅ (ዐዋጅ ቍጥር ፸፬ ፲፱፻፴፯ ዓ ም) በአንቀጽ ፱ እና ፲፩ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የአገር ግዛት ሚኒ ስትር ያወጣው ደንብ ነው ።
ገጽ ፪፻፲፯
፪ ይህ ደንብ « የ፲፱፻፷፩ ዓ ም የወለጋ
ማዘጋጃ ቤቶች የግብር ፤ የቀረጥና የታክስ ተብሎ ሊጠቀስ ይቻላል ።
፫ በሰንጠረዡ የተመለከቱት ማዘጋጃ ቤቶች በመማክርቶ ቻቸው አማካይነት ግብር ፤ ቀረጥና ታክስ የሚከፈልባ ቸውን ጉዳዮች በሕግ መሠረት እያስወሰኑ በዝ ርዝሩ መሠረት ግብር ፤ ቀረጥና ታክስ እንዲሰበስቡ ተፈቅዶ ላቸዋል "
፬ ይህ ደንብ ከሐምሌ ፩ ቀን ፲፱፻፷ ዓ ም / ጀምሮ የጸና ይሆናል ።
አዲስ አበባ ሐምሌ ፳፮ ቀን ፲፱፻፷፩ ዓ | ም /
ቢትወደድ ዘውዴ ገብረ ሕይወት
የአገር ግዛት ሚኒስትር
አዲስ አበባ ሐምሌ ፳፮ ቀን ፲፱፻፷፩ ዓ. ም.
ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ ይታተማል •
የፖስታ ሣጥን ቍጥር ፩ሺ፫፻፷፬ (1364)