×
Browse Products About Us Login / Sign Up Contact Us አማርኛ
African Law Archive
Logo
የፍርድ ቤት ውሳኔ 18399

      Sorry, pritning is not allowed

የሰበር መ / ቁ 18399
ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
ዓብዱልቃድር መሐመድ
ጌታቸው ምህረቱ
መስፍን እቁበዮናስ
ወ / ት ሂሩት መለሰ
አመልካች የኪራይ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት
ተጠሪዎች፡- እነ ትዕግሥት ብዙህ ( 6 ሰዎች )
ፍ ር ድ
ይህ የሠበር አቤቱታ የቀረበው የአሁኑ አመልካች በስር ፍ / ቤት ለቀረበበት ክስ
መልስ ይዞ እንዲቀርብ
በተቀጠረው ቀነ ቀጠሮ ባለመቅረቡ ከክሱ
ውጪ እንዲሆን
የተሰጠውን ትእዛዝ በመቃወም ነው ፡፡
የአሁኑ ተጠሪዎች በአመልካች እና በሌሎች ሁለት ተከሣሾች ላይ ላቀረቡት ክስ
አመልካች መልስ እንዲሰጥ ታዞ በቀነ ቀጠሮው ባለመቅረቡ ከክሱ ውጪ እንዲሆን ታዟል ፡፡
ከዚህ በኋላም ቢሆን አመልካች ትእዛዙ ተነስቶ ወደ ክርክሩ እንዲገባ ያቀረበውን ጥያቄ
የፌ / መ / ደረጃ ፍ / ቤት ሣይቀበለው ቀርቷል ፡፡ በዚህ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የፌ / ከፍተኛ
ፍ / ቤትም ይግባኙን በፍ / ሥ / ሥ / ቁ 337 መሠረት ሠርዞታል ፡፡
የአሁኑ የሠበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ላይ ሲሆን ተጠሪዎች ቀርበው ፍ / ቤቱ
የግራ ቀኙን የጽሁፍ ክርክር መርምሯል ፡፡ በዚህም ጉዳይ ሊነሣ የሚገባው የሕግ ነጥብ
መልስ እንዲቀርብ በተያዘ ቀነ ቀጠሮ የተከሣሽ አለመቅረብ የሚያስከትለው ውጤት
ምድነው ? የሚለው ነው ።
ከላይ የተያዘው ጭብጥ ለመመለስም ባለጉዳዩ ወደ ፍ / ቤት ሣይቀርብ መቅረቱ
የሚያስከትለውን ውጤት የሚደነግጉትን የፍ / ሥ / ሥ / ሕጉ ድንጋጌዎች መመልከት ጠቃሚ
ፌዴራ፡ ... • ይ 55 : ሴ ?
..... 3 ግ : 1 ጅ
ፊርማ --
ቀን ሯ - / ፅ g
ያ ቀ.ቁ.
- | መ / ደረጃ ፍ / ቤት በመ / ቁ .15610 በ 4 / 02 / 97 የሰጠው ትእዛዝ እንዲሁም ነው በተለይ አንድ ባለጉዳይ ከክሱ ውጪ እንዲሆን የሚደረገው በየትኛው የሙግት ደረጃ ላይ ፍ / ቤት ባይቀርብ ነው የሚለው መታየት አለበት ፡፡
በፍ / ሥ / ሥ / ሕ / ቁ 70 ( ሀ ) መሠረት ተከሣሽ ከክሱ ውጪ ( ex- parte ) የሚሆነው ክርክሩ እንዲሰማ በተወሰነው ቀኑቀጠሮ ያልቀረበ እንደሆነ ነው እንጂ መልስ እንዲያቀርብ በተያዘው ቀነ ቀጠሮ ባለመቅረቡ አይደለም መልስ እንዲቀርብ በተያዘው ቀነ ቀጠሮ አለመቅረቡ የሚያስከትለው ውጤት ጉዳዩ ተከሣሽ ባይቀርብም በሌለበት መቀጠል ( default proceeding ) ብቻ መሆኑን ከፍ / ሥ / ሥ / ሕግ ቁጥር 233 መገንዘብ ይቻላል ። ከፍ ሲል የተጠቀሱት አንቀፆችም በመ / ቁ 15835 ትርጉም ተሰጥቶባቸዋል ።
በመሆኑም አመልካች መልስ እንዲያቀርብ በተያዘው ቀነ ቀጠሮ ባለመቅረቡ ከክሱ ውጪ እንዲሆን የተደረገው ከሥነ ሥርዓት ሕጉ ውጪ ነው ::
ው ሣ ኔ
የፌ / ከፍተኛ ፍ / ቤት
34885 በ 2 / 04 / 97 የሰጠው ትእዛዝ ተሽሯል ፡፡
2 / የአሁኑ አመልካች በፌ / መ / ደረጃ ፍ / ቤት በሚደረገው ክርክር ከክርክሩ ውጪ
ሊሆን ስለማይገባ መልሱን ባያቀርብም ወደ ክርክሩ ገብቶ ፍ / ቤቱ ክሱን ከሰማ በኋላ
የመሠለውን ይወስን ።
3 / ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ መዝገቡ ስለተዘጋ ይመለስ ።
ፈያ ኑ በ ትላ ና፡፡.፫ { ..
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
2 % - / 5 -ዋቂ

You must login to view the entire document.

Enter your email address and password to login.
Please enter a valid email address
Please enter your email address
Please enter your password
Password must be at least 8 characters long
Forgot your password?