የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ሁለተኛ ዓመት ቁጥር ፭ አዲስ አበባ የካቲት ፭ ቀን ፲፱፻ዥ፰ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅቁጥር ፲፯ / ፲፱፻፰ ዓም ወደ ግል ይዞታ የተዛወሩ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ባለ አደራ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ . . ገጽ ፲ህ አዋጅ ቁጥር ፲፯ / ፲፱፻T፰ ወደ ግል ይዞታ የተዛወሩ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ባለ አደራ ቦርድን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ፖሊሲ መሠረት በመንግሥት ይዞታ ሥር እንዲቆዩ ከሚደረጉት በስተቀር የልማት ድርጅቶች ወደ ግል ይዞታ የሚዛወሩ በመሆኑ ፤ በዚሁ የዝውውር ሂደት ውስጥ ወደ ግል ይዞታ የሚዛወሩ የልማት ድርጅቶችን ከሽያጭናርክክብ በኋላ በእንጥልጥል የሚቀሩ ተሰብሳቢ ሂሳቦችን ፡ እዳዎችንና ግዴታዎችን እንዲሁም የሕግ ጉዳዮችን የሚከታተልና የሚያስፈጽም አንድ የሕግ ሰውነት ያለው ኣካል ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፤ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ ወደ ግል ይዞታ የተዛወሩ የመንግሥት የልማት | ድርጅቶች ባለ አደራ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ ቍጥር ፲፯ ፲፱፻ጅቷ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ “ የልማት ድርጅት ” ማለት በአዋጅ ቍጥር ፳፭ / ፲፱፻፳፬ | ወይም በተመሳሳይ ሕግ መሠረት ተቋቁሞ በፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር T፯ / ፲፱፻፴፮ መሠረት ወደ ግል ይዞታ የተዛወረ የመንግሥት የልማት ድርጅት ወይም | ቅርንጫፍ ነው ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ተሺ፩ ገጽ ፻ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፭ የካቲት ፭ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓም . Federal Negarit Gazeta – No . 5 13 February 1996 – Page 100 ፫ መቋቋም ፩ ወደ ግል ይዞታ የተዛወሩ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች | ባለአደራ ቦርድ ( ከዚህ በኋላ “ ቦርዱ ” እየተባለ የሚጠራ ) የሕግ ሰውነት ያለው ራሱን የቻለ የመንግሥት መሥሪያ | ቤት ሆኖ በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ። ፪ ቦርዱ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሆናል ። ፩ . ዋና መሥሪያ ቤት የቦርዱ ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ ሆኖ እንደአስፈላጊነቱ በማናቸውም ሥፍራ ቅርንጫፍ ሊኖረው ይችላል ። ፭ ዓላማ የቦርዱ ዓላማ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ወደ ግል ይዞታ በሚዛወሩበት ጊዜ ለአዲሱ ባለቤት የማይተላለፉ ተሰብሳቢ ሂሳቦችን መሰብሰብ እዳዎችንና ግዴታዎችን መረከብ የሕግ ጉዳዮችን መከታተልናእንዲሁምእነዚህን አላማዎችእንደነስ ፈላጊነቱ በቅልጥፍና ማስፈጸም ይሆናል ። ፮ . ሥልጣንና ተግባር ቦርዱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ፩ ከልማት ድርጅቱ አዲስ ባለቤት ጋር ርክክብ በሚጀመ ርበት ጊዜ በካዝና የሚገኘው ጥሬ ገንዘብ ተቆጥሮ በቅድሚያ ወደሚወሰን የባንክ ሂሳብ ገቢ መደረጉን ያረጋግጣል ፤ ከባንክና ከሌሎች የሂሳብ መግለጫ ሰነዶች ጋር ያገናዝባል ፤ ፪ በገንዘብ ሚኒስቴር አረካካቢነት ርክክብ በሚፈጸምበት ጊዜ የተገኘው ቋሚና አላቂ ንብረት ፡ ጥሬ እቃና ምርት በመዝገብ በሚታየው መጠንና ሁኔታ ለመሆኑ ዝርዝር የማገናዘብና የማስታረቅ ምርመራና ቁጥጥር እንዲካሄድ ያደርጋል ፤ ፫ በፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲና በልማት ድርጅቱ አዲሱ ባለቤት ወይም ሰው መካከል በተፈረመው ውል በተለየ ሁኔታ ካልተወሰነ በስተቀር ፤ ሀ ) የልማት ድርጅቱ ወደግል ይዞታ እስከተዛወረበት ቀን ድረስ ሳይሰበሰቡ የቀሩ የልማት ድርጅቱን ተሰብሳቢ ሂሳቦች ይሰበስባል ፤ ለመሰብሰብ ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል ፡ ለ ) የልማት ድርጅቱን እዳዎች ለመንግሥት እያቀረበ እንዲከፈሉ ያደርጋል ፤ ሲፈቀድም ራሱ ይከፍላል ፤ ሌሎች ግዴታዎችን ይፈጽማል ፡ ሐ ) የልማትድርጅቱን የተሰራባቸው ሰነዶችና መዝገቦች የሠራተኞችን ፋይሎች ተረክቦ ያስቀምጣል ። መ ) የልማት ድርጅቱን የሚመለከቱ የፍርድ ቤት ጉዳዮች በባለቤትነት ይረከባል ፤ ይከታተላል ፣ ከፍርድ ቤት ውጭ በስምምነት ይጨርሳል ፤ ፬ ራሱ በሚያወጣው መርሀ ግብርና እቅድ መሠረት ባለገንዘ ቦችን ይጠራል ፤ አቤቱታቸውንናማስረጃዎችን ይቀበላል ፤ እየመረመረና እያጣራ ይወስናል ፤ ፭ ወደ ግል ይዞታ የተዛወረውን የመንግሥት የልማት ድርጅት የመጨረሻ የሀብትና እዳ መግለጫ ማስታወቂያ ያወጣል ፤ የዚህን ማስታወቂያ ግልባጭ ለገንዘብ ሚኒስቴርና ለዋናው ኦዲተር መሥሪያ ቤት ያስተላልፋል ፤ ፮ : ስለተሰብሳቢና ተከፋይ ሂሳቦች እንዲሁም በፍርድ ቤት ክርክር ላይ ስለሚገኙ ጉዳዮች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ዝርዝር ሪፖርት ያቀርባል ፤ ለኢትዮጵያ ፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲም በግልባጭ ያሳውቃል ፤ ፯ . ከሕጋዊ ሰውነቱ ጋር በተያያዘ የንብረት ባለቤት ይሆናል ፤ ውል ይዋዋላል ፤ በስሙ ይከሳል ፣ ይከሰሳል ፡ ገጽ ፻፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፭ የካቲት ፭ ቀን ፲፱፻ዥ፰ ዓም ፰ ዓላማውን ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ ሌሎች ተግባሮችን ያከናውናል ። ፯ የቦርዱ አቋም ፩ . የሥራ አመራር ቦርድ ፤ ፪ አንድ ዋና ሥራ አስኪያጅ እና ፤ ፫ አስፈላጊው ሠራተኞች ይኖሩታል ። | ፰ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት የሥራ አመራር ቦርዱ የሚከተሉት አምስት አባላት ይኖሩታል ፤ ፩ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚሰየም . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . ሰብሳቢ ፪ የገንዘብ ሚኒስቴር ተወካይ ፫ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ጽሕፈት ቤት ተወካይ . . . ፬ . የኢትዮጵያ ፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ተወካይ . . . . . . . ፭ በቦርዱ አቅራቢነት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚሾም የቦርዱ ዋና ሥራ አስኪያጅ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . ኣባልና ፀሐፊ ፱ የሥራ አመራር ቦርዱ ሥልጣንና ተግባር የሥራ አመራር ቦርዱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች | 9 . Powers and Duties of the Board of Management ይኖሩታል ፤ ፩ የቦርዱን ሥራዎች በበላይነት ይመራል ፡ ይቆጣጠራል ፤ ፪ የልማት ድርጅቱ ወደ ግል ይዞታ እስከተዛወረበት ቀን ድረስ ሳይሰበሰቡ የቀሩ ተሰብሳቢ ሂሳቦች ገቢ መደረጋ ቸውን ያረጋግጣል ፤ ይቆጣጠራል ፤ ፫ የልማት ድርጅቱን እዳዎች ለመክፈል ለመንግሥት አቅርቦ ያስፈቅዳል ፤ ሲፈቀድም በአግባቡ መከፈሉን ያረጋግጣል ፤ ይቆጣጠራል ፬• የልማትድርጅቱን የሚመለከቱ የሕግ ጉዳዮች በፍርድ ቤት ወይም ከፍርድ ቤት ውጭ በሚደረግ ስምምነት እልባት እንዲያገኙ ተገቢውን ክትትልና ቁጥጥር ያደርጋል ፤ ፭ ለመንግሥት የሚቀርበውን የቦርዱን ዓመታዊ በጀትና የሥራ ፕሮግራም ያጸድቃል ፤ ፮ . የቦርዱን ዓላማ ከግብ ለማድረስ አስፈላጊ መስሎ የሚታ የውን ሁሉ ይፈጽማል ። ፲ የሥራ አመራር ቦርድ ኣባላት ተጠያቂነት ፩ . የሥራ አመራር ቦርዱ አባላት በዚህ አዋጅ መሠረት | 10 Liability of Members of the Board of Management የተሰጣቸውን ተግባር በጥንቃቄ መፈጸም አለባቸው ። [ 1 ) Members of the Board of Management shall carry out ፪• አባላቱተግባራቸውን በአግባብ ባለመፈጸማቸው ምክንያት በቦርዱ መሥሪያ ቤት ላይ ለሚደርሰው ጉዳት በአንድነትና በነጠላ ተጠያቂ ይሆናሉ ። ፲፩ የሥራ አመራር ቦርዱ ስብሰባ ፩ የሥራ አመራር ቦርዱ ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ ይሰበ ሰባል ፤ ሆኖም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በሰብሳቢው ጥሪ በማናቸውም ጊዜ ሊሰበሰብ ይችላል ። ፪ ከቦርዱ አባላት ከግማሽ በላይ የሚሆኑ በስብሰባ ላይ ከተገኙ ምልዓተ ጉባዔ ይሆናል ። ፫ ቦርዱ ውሳኔ የሚያሳልፈው በድምጽ ብልጫ ይሆናል ፤ ሆኖም ድምጽ እኩል በእኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰበሳቢው ያለበት ወገን ሀሳብ የቦርዱ ውሳኔ ሆኖ ያልፋል ። ፩ ቦርዱ የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ያወጣል ። ገጽ ፻፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፭ የካቲት ፭ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓም . Federal Negarit Gazeta - - No . 5 13 February 1996 – Page 102 ፲፪• የዋናው ሥራ አስኪያጁ ሥልጣንና ተግባር ፩ ዋና ሥራ አስኪያጁ የሥራ አመራር ቦርዱ በሚሰጠው መመሪያ መሠረት የቦርዱን ሥራዎች ይመራል ያስተዳ ፪ . በዚህ አንቀጽንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከተው አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ዋና ሥራ አስኪያጁ ፤ ሀ ) የሥራ አመራር ቦርዱ አባልና ፀሐፊ ሆኖ ይሠራል ፤ ለ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፮ ለቦርዱ በተሰጠው ሥልጣንና ተግባር መሠረት የሥራ አመራር ቦርዱ የሚሰጠውን መመሪያ ያስፈጽማል ፤ ሐ ) በፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕጐች መሠረት የቦርዱን ሠራተኞች ይቀጥራል ፡ ያስተዳድራል ፤ መ ) የቦርዱን በጀትና የሥራፕሮግራም አዘጋጅቶ ለሥራ አመራር ቦርዱ ያቀርባል ፤ ሠ ) ለቦርዱ በተፈቀደለት በጀትናየሥራፕሮግራምመሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል ፤ ረ ) ከሶስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች ሁሉ ቦርዱን ይወክላል ፤ ሰ ) የቦርዱን የሥራእንቅስቃሴና የሂሳብ ሪፖርት አዘጋጅቶ ለሥራ አመራር ቦርዱ ያቀርባል ። ፫• ዋና ሥራ አስኪያጁ ለቦርዱ የሥራ ቅልጥፍና ባስፈለገ መጠን ሥልጣንና ተግባሩን በከፊል በሥሩ ላሉ ኃላፊ | ዎችና ሌሎች ሠራተኞች በውክልና ሊያስተላልፍ ይችላል ፤ ሆኖም እርሱን ተክቶ የሚሰራውኃላፊ ከ፴ ቀናት ለሚበልጥ ጊዜ የሚሰራ ከሆነ ውክልናው አስቀድሞ ለሥራ አመራር ቦርዱ ቀርቦ መፈቀድ አለበት ። ፲፫ በጀት የቦርዱ ዓመታዊ በጀት በፌዴራሉ መንግሥት ይመደባል ። | 13 . Fuget ፲፬ የመብትና ግዴታ መተላለፍ ፩ በአዋጅ ቁጥር ፳፯ ፲፱፻፰፮ መሠረት ወደ ግል ይዞታ | 14 . Transfer of Rights and Obligations የተዛወረ የመንግሥት የልማት ድርጅት ርክክቡ ሲጠናቀቅ በመንግሥት የልማት ድርጅትነት የተሰጠው የሕግ ሰውነት ይሠረዛል ። ከዚህ ጊዜም ጀምሮ የመን ግሥት የልማት ድርጅትነት ሕልውናው ያበቃል ። ፪ ወደ ግል ይዞታ የተዛወረው የልማት ድርጅት እስከ መጨረሻው የርክክብ እለት ድረስ ያለው መብትና ግዴታ በዚህ አዋጅ ለተቋቋመው ቦርድ ይተላለፋል ። ፫ ወደ ግል ይዞታ የተዛወረው የልማት ድርጅት ርክክብ | ሲጠናቀቅ ሽያጩን ሦስተኛ ወገኖች እንዲያውቁት ለማድረግ ቦርዱ ሰፊ ሥርጭት ባለው ጋዜጣ ወይም በሌላ | የመገናኛ ዘዴ ሕዝቡ እንዲያውቀው ያደርጋል ። ፲፭ ስለ ሂሳብ ማጣራት ሥልጣንና ተግባር የመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ ፲፱፻፳፬ ኣንቀጽ ፵፩ ፵፭ እንደ አስፈላጊነቱ ለዚህ አዋጅ ዓላማም | ተፈጻሚ ይሆናሉ ። በእነዚህ አንቀጾች ስለሂሣብ ማጣራት | ለመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን | ጽሕፈት ቤት የተሰጠው ሥልጣንና ተግባር ወደ ግል ይዞታ የተዛወሩ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን በሚመለከት ለቦርዱ ተላልፋል ። ገጽ ፻፫ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፭ የካቲት ፭ ቀን ፲፱፻፰፰ ዓም . Federal Negarit Gazeta - No . 5 13 February 1996 Page 103 ፲፮ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከየካቲት ፭ ቀን ፲፱፻፰፰ ዓም ጀምሮ የጸና | ይሆናል ። አዲስ አበባ የካቲት ፭ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት 4 ፋሲዮ ፉል ኒሰት እ ን * - ኣ "