የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ሁለተኛ ዓመት ቁጥር፳፱ አዲስ አበባ ሰኔ ፳፯ ቀን ፲፱፻፳፰ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ ደንብ ቁጥር ፯ / ፲፱፻ዥ፰ ዓ.ም. የኢንቨስትመንት ማበረታቻ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ............ ገጽ ፪፻፳፭ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፯ / ፲፱፻፷፰ ስለኢንቨስትመንት ማበረታቻዎች የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፐብሊክ ኣስፈጸሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፷፯ አንቀጽ ፭ እና በኢንቨስትመንት | Ethiopia Proclamation No.4 / 1995 and Article 9 of the አዋጅ ቁጥር ፵፯ / ፲፱፻፰፰ አንቀጽ ፱ መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ። ክፍል አንድ ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የኢንቨስትመንት ማበረታቻ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፯ / ፲፱፻፰፰ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ ደንብ ውስጥ ፤ ፩ “ አዋጅ ” ማለት የኢንቨስትመንት አዋጅ ቁጥር ፴፯ ፲፱፻፳፰ ነው ፤ ፪ “ የጉምሩክ ቀረጥ ” ማለት በገቢ ዕቃዎች ላይ የሚጣሉ ታክሶችንም ይጨምራል ፤ ፫ . “ የገቢ ግብር ” ማለት የፌዴራሉ መንግሥት ወይም የክልል መስተዳድሮች ወይም የሁለቱ የጋራ ገቢ የሆነ በትርፍ ላይ የሚጣል ታክስ ነው ፣ ፩ . “ ቦርድ ” ማለት የፌዴራሉ መንግሥት ኢንቨስትመንት ቦርድ ነው ፤ ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖ.ሣቁ ተሺ፩ ገጽ ፪፻፳፮ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፱ ሰኔ ፳፯ ቀን ፲፱፻፲፰ ዓ • ም • ፭ . “ ባለሥልጣን ” ማለት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ባለሥ ልጣን ነው ፣ ፮- በአዋጁ አንቀጽ ፪ ለተመለከቱት ቃላት የተሰጡ ትርጓ ሜዎች ለዚህም ደንብ ተፈጻሚ ይሆናሉ ። ክፍል ሁለት ከገቢ ግብር ነፃ ስለመሆን ፫ • ልዩ ትኩረት ስለሚሰጣቸው የኢንቨስትመንት መስኮች ፩- ልዩ ትኩረት የሚሰጣቸው የኢንቨስትመንት መስኮች ከዚህ ደንብ ጋር በተያያዘው ሠንጠረዥ አንድ የተዘረዘሩት ይሆናሉ ። ፪ • ልዩ ትኩረት በሚሰጣቸው የኢንቨስትመንት መስኮች አዲስ ድርጅት ለማቋቋም ኢንቨስት የሚያደርግ ባለሀብት ከገቢ ግብር ነፃ የመሆን መብት በሚከተለው አኳኋን ይሰጠዋል ፣ ሀ ) በአዲስ አበባ ወይም በናዝሬት ወይም ሁለቱን ከተሞች በሚያገናኘው አውራ ጎዳና ግራና ቀኝ በ፲፭ ኪሎ ሜትር ክልል ውስጥ ኢንቨስት ካደረገ ለ፫ ዓመት፡ ለ ) በአንጻራዊ ደረጃ በኢኮኖሚ ልማት ወደኋላ በቀሩ አካባ ቢዎች ማለትም በጋምቤላ ፡ በቤኒሻንጉልና ጉሙዝ ፡ በደቡብ ኦሞ ፡ በአፋር የተወሰኑ ዞኖች ፡ በሶማሌ ክልል እና ቦርዱ ወደፊት እንደሁኔታው እየተመለከተ በሚወስናቸው አካባቢዎች ኢንቨስት ካደረገ ለ፭ ዓመት ፣ ሐ ) በዚህ ንዑስ አንቀጽ በፊደል ተራ ( ሀ ) እና ( ለ ) ከተመለ ከቱት ውጭ በሌሎች አካባቢዎች ኢንቨስት ካደረገ ለሽ ፫ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) ድንጋጌ ቢኖርም በአዋጁ ኣንቀጽ ፲፩ ( ፫ ) መሠረት ኢንቨስት ያደረገ የውጭ ባለሀብት ኢንቨስት ያደረገው ካፒታል ከ፭፻ሺህ የአሜሪካን ዶላር ወይም ከዚሁ ተመጣጣኝ ብር በታች ከሆነ የሚሰጠው ከገቢ ግብር ነፃ የመሆን መብት ለ፪ ዓመት ይሆናል ። ፬ • ትኩረት ስለሚሰጣቸው የኢንቨስትመንት መስኮች ፩ . ትኩረት የሚሰጣቸው የኢንቨስትመንት መስኮች ከዚህ ደንብ ጋር ተያይዞ በሚገኘው ሠንጠረዥ ሁለት የተዘረዘሩት ይሆናሉ ። ፪ • ትኩረት በሚሰጣቸው የኢንቨስትመንት መስኮች አዲስ ድርጅት ለማቋቋም ኢንቨስት የሚያደርግ ባለሀብት ከገቢ ግብር ነፃ የመሆን መብት በሚከተለው አኳኋን ይሰጠዋል፡ ሀ ) በአዲስ አበባ ወይም በናዝሬት ወይም ሁለቱን ከተሞች በሚያገናኘው አውራ ጎዳና ግራና ቀኝ በ፲፭ ኪሎ ሜትር ክልል ውስጥ ኢንቨስት ካደረገ ለ፩ ዓመት፡ ለ ) በአንፃራዊ ደረጃ በኢኮኖሚ ልማት ወደኋላ በቀሩ አካባ ቢዎች ማለትም በጋምቤላ ፡ በቤኒሻንጉልና ጉሙዝ ፡ በደቡብ ኦሞ ፡ በአፋር የተወሰኑ ዞኖች ፡ በሶማሌ ክልል እና ቦርዱ ወደፊት እንደሁኔታው እየተመለከተ በሚወስናቸው አካባቢዎች ኢንቨስት ካደረገ ለ፫ ዓመት ፣ ሐ ) በዚህ ንዑስ አንቀጸ በፊደል ተራ ( ሀ ) እና ( ለ ) ከተመለ ከቱት ውጭ በሌሎች አካባቢዎች ኢንቨስት ካደረገ ለ፪ ዓመት ። * አፍ ፫ እና ፬ መሠረት | ገጽ ፪፻፳፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፱ ሰኔ ፳፯ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓ.ም ፫ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) ድንጋጌ ቢኖርም በአዋጁ አንቀጽ ፲፩ ( ፪ ) መሠረት ኢንቨስት ያደረገ የውጭ ባለሀብት ኢንቨስት ያደረገው ካፒታል ከ፭፻ሺህ የአሜሪካን ዶላር ወይም ከዚሁ ተመጣጣኝ ብር በታች ከሆነ የሚሰጠው ከገቢ ግብር ነፃ የመሆን መብት ለ፩ ዓመት ይሆናል ። ፬ . የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) እና ( ፫ ) ድንጋጌ ቢኖርም በሠንጠረዥ ሁለት ውስጥ በፊደል ተራ ( ሐ ) ተራ ቁጥር ፰፡ ፱፡ ፲፩፡ ፵፪፡ እና በፊደል ተራመ ( ፪ ) እና በፊደል ተራ ( ሰ ) በተመለከቱት የኢንቨስትመንት መስኮች በአዲስ አበባ ውስጥ ኢንቨስት ያደረገ ባለሀብት ከገቢ ግብር ነፃ የመሆን መብት አይሰጠውም ። ፭ ነባር ድርጅትን ስለማስፋፋትና ስለማሻሻል ፩ . ልዩ ትኩረት ወይም ትኩረት በሚሰጠው የሥራ መስክ የተሠማራ ነባር ድርጅትን ለማስፋፋት ወይም ለማሻሻል ኢንቨስት የሚያደርግ ባለሀብት ያደረገውን ማስፋፋት ወይም ማሻሻል በሚመለከት ብቻ ከገቢ ግብር ነፃ የመሆን መብት በሚከተለው አኳኋን ይሰጠዋል ፤ ሀ ) ልዩ ትኩረት በሚሰጠው የኢንቨስትመንት መስክ ከሆነ ለ፪ ዓመት ፣ ለ ) ትኩረት በሚሰጠው የኢንቨስትመንት መስክ ከሆነ ለ፩ ዓመት ። ፪ • በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት የሚሰጠው ከገቢ ግብር ነፃ የመሆን መብት ተፈፃሚ የሚሆነው ማስፋፊያው ወይም ማሻሻያው ያስገኘው ተጨማሪ ገቢ ተለይቶ ሂሣብ የተያዘለት እንደሆነ ነው ። ፫ በዚህ ደንብ አንቀጽ ፬ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተደረገው ገደብ ነባር ድርጅትን በማስፋፋትና በማሻሻል ረገድም ተፈጻሚ ይሆናል ። ፮ የካፒታል ገደብ ፩ . ማንኛውም ባለሀብት በዚህ ደንብ ለሚሰጠው ማበረታቻ ብቁ የሚሆነው አዲስ ድርጅት ለማቋቋም የመደበው የኢንቨስትመንት ካፒታል ፣ ሀ ) የአገር ውስጥ ባለሀብት ሲሆን ከብር ፪፻፶ሺህ ፣ ለ ) የውጭ ባለሀብት ሲሆን ከ፭፻ሺህ የአሜሪካን ዶላር ፤ ሐ ) በቅንጅት የተደረገ ኢንቨስትመንት ሲሆን የውጭ ባለሀብቱ ድርሻ ከ፫የሺህ የአሜሪካን ዶላር፡ መ ) ትርፉን ወይም የትርፍ ድርሻውን መልሶ ሀገር ውስጥ ኢንቨስት ያደረገ የውጭ ባለሀብት ሲሆን ከ፩፻ሺህ የአሜሪካን ዶላር ወይም የዚሁ ተመጣጣኝ ከሆነ ብር ፤ ያላነሰ ከሆነ ብቻ ነው ። ፪ . ማንኛውም ባለሀብት በዚህ ደንብ አንቀጽ ፭ መሠረት ለሚሰጠው ማበረታቻ ብቁ የሚሆነው ለማስፋፊያ ወይም ለማሻሻያ ፕሮጀክቱ የመደበው የኢንቨስትመንት ካፒታል መጠን ከነባር ድርጅቱ ካፒታል ጋር ሲነጻጸር ከሚከተለው መቶኛ ያላነሰ ከሆነ ብቻ ነው፡ ሀ ) ካፒታሉ ከብር ፻፶ሺህ እስከ ብር ፪ሚሊዮን ሲሆን ፴፭ ለ ) ካፒታሉ ከብር ፪ሚሊዮን በላይ እስከ ብር ፭ሚሊዮን ሲሆን ፵በመቶ ፡ ሆኖም ከብር ፱፻ሺህ ያላነሰ ፤ ገጽ ፪፻፳፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፬ ሰኔ ፳፯ ቀን ፲፱፻፲፰ ዓም : ሐ ) ካፒታሉ ከብር ፭ሚሊዮን በላይ እስከ ብር ፳ሚሊዮን ሲሆን ፴፭በመቶ፡ ሆኖም ከብር ፪ ሚሊዮን ያላነሰ ፤ መ ) ካፒታሉ ከብር ፳ሚሊዮን በላይ እስከ ብር ፶ሚሊዮን ሲሆን ጨበመቶ ፣ ሆኖም ከብር ፲ ሚሊዮን ያላነሰ ፤ ሠ ) ካፒታሉ ከብር ፶ሚሊዮን በላይ እስከ ብር ፩፻ሚሊዮን ሲሆን ፳፭በመቶ ፣ ሆኖም ከብር ፲፭ ሚሊዮን ያላነሰ ፤ ረ ) ካፒታሉ ከብር ፩የሚሊዮን በላይ ሲሆን ፳በመቶ ፤ ሆኖም ከብር ፳፭ ሚሊዮን ያላነሰ ። ፫ : ሀ ) የነባር ድርጅት ካፒታል ትክክለኛ መጠን በኦዲተር በተመረመረ የሂሣብ ሪፖርት መረጋገጥ ወይምበኦዲተር የተመረመረ የሂሣብ ሪፖርት ከሌለ አግባብ ያለው የኢንቨስትመንት ባለሥልጣን የቀረቡለትን መረጃዎች መርምሮ ያመነበት መሆን አለበት ። ለ ) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፫ ( ሀ ) የተመለከተው፡ ማስፋፊያ ወይም ማሻሻያ ለተደረገለት ኢንቨስትመንት ካፒታል ላይ ተፈጻሚ ይሆናል ። • ከገቢ ግብር ነፃ የመሆኛ ዘመን ስለሚጀምርበት ጊዜ ከገቢ ግብር ነፃ የመሆኛ ዘመን መቆጠር የሚጀምረው ባለሀብቱ እንደአግባቡ የምርት ውጤት ካገኘበት ወይም | 7 . Commencement of Period of Exemption from Income Tax የማምረት ወይም አገልግሎት የመስጠት ሥራ ከጀመረበት ቀን ጀምሮ ይሆናል ። ፰ ኪሣራን ስለማስተላለፍ ከገቢ ግብር ነፃ የመሆን መብት በተሰጠበት ዘመን ውስጥ ኪሣራ | 8. Carry Forward of Losses ያጋጠመውማንኛውም ባለሀብት የደረሰበት ኪሣራ የነፃ መብቱ ዘመን እንዳለቀ ለሚከተሉት ዓመታት ይተላለፍለታል፡ ፩ . ኢንቨስትመንቱ በአዲስ አበባ ወይም በናዝሬት ወይም ሁለቱን ከተሞች በሚያገናኘው አውራጎዳና ግራና ቀኝ በ፲፭ ኪሎ ሜትር ክልል ውስጥ የተደረገ ከሆነና ልዩ ትኩረት ወይም ትኩረት የሚሰጠው ከሆነ ለ፫ ዓመት ፣ ፪ • ኢንቨስትመንቱ በአንጻራዊ ደረጃ በኢኮኖሚ ልማት ወደኋላ በቀሩ ማለትም በጋምቤላ፡ በቤኒሻንጉልና ጉሙዝ፡ በደቡብ ኦሞ፡ በአፋር የተወሰኑ ዞኖች፡ በሶማሌ ክልል እና ቦርዱ ወደፊት እንደሁኔታው እየተመለከተ በሚወስናቸው አካባ ቢዎች የተደረገ ከሆነ፡ ሀ ) ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ከሆነ ለ፭ዓመት ፣ ለ ) ትኩረት የሚሰጠው ከሆነ ለ፬ ዓመት ። 1 ) ኢንቨስትመንቱ ከዚህ በላይ በንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እና ( ፪ ) ከተመለከቱት ውጭ በሌሎች አካባቢዎች የተደረገ ከሆነ ፣ ሀ ) ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ከሆነ ለ፭ ዓመት ፣ ለ ) ትኩረት የሚሰጠው ከሆነ ለ፫ ዓመት ። ፱ : ስለ ጥናትና ሥልጠና ወጪዎች ማንኛውም ባለሀብት ድርጅቱን በተመለከተ ለሚያካሂደው የማሻሻያ ጥናትና ምርምር እንዲሁም የሥልጠና ፕሮግራም ያደረገው ወጪ ግብር የሚከፈልበት ገቢ ሲታሰብ ተቀናሽ ይደረግለታል ። ፤ ስለ እርጅና ቅናሽ የስሌት ዘዴ ፩ . የእርጅና ቅናሽ የሚሰላው እንደባለሀብቱ ምርጫ በየዓመቱ በአንድ ዓይነት ወይም እየቀነሰ በሚሄድ መጠን ይሆናል ። ገጽ ፪፻፳፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፱ ሰኔ ፳፯ ቀን ፲፱፻፷፰ ዓም ፪ ባለሀብቱ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት የሚያደርገው ምርጫ ከሁለት አንዱን ብቻ የያዘ ሆኖ ከኢንቨስትመንት ፈቃድ ማመልከቻው ጋር መቅረብ አለበት ። ፫ ባለሀብቱ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) መሠረት የመረጠው የእርጅና ቅናሽ የስሌት ዘዴ ድርጅቱ ለዘለ ቄታው የሚጠቀምበት ይሆናል ። ክፍል ሦስት ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ስለመሆን ፲፩ ጠቅላላ ፩- ከዚህ ደንብ ጋር ተያይዘው በሚገኙት ሠንጠረዥ አንድ ፡ 1. General ሁለትና ሦስት በተዘረዘሩት ልዩ ትኩረት ወይም ትኩረት በሚሰጣቸው የሥራ መስኮች በዚህ ደንብ አንቀጽ ፮ ከተደነ ገገው ዝቅተኛ የካፒታል ገደብ ያላነሰ ኢንቨስት የሚያደርግ ባለሀብት ለሚያቋቁመው አዲስ ድርጅት ወይም ነባር ድርጅትን ለማስፋፋት ወይም ለማሻሻል የሚያስፈልጉትን መሣሪያዎችና ዕቃዎች ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ሆነውለት ሊያስገባ ይችላል ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተጠቀሰው የካፒታል ገደብ ቢኖርም ፡ ከነባር ድርጅት ያገኘውን ከጫሺህ የአሜሪካን ዶላር ወይም የዚሁ ተመጣጣኝ ከሆነ ብር ያላነሰ ትርፍ መልሶ ለድርጅቱማስፋፊያ ወይምማሻሻያ ኢንቨስት ያደረገ የውጭ ባለሀብት ለማስፋፊያው ወይም ለማሻሻያው የሚያስፈል ጉትን መሣሪያዎችና ዕቃዎች ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ሆነውለት ሊያስገባ ይችላል ። ፫ ከዚህ ደንብ ጋር ተያይዞ በሚገኘው ሠንጠረዥ አራት በተዘረዘሩት ከብር ፪የፃሺህ የኢንቨስትመንት ካፒታል በታች በሚካሄዱ የሥራ መስኮች ኢንቨስት የሚያደርግ ባለሀብት ለሚያቋቁመው አዲስ ድርጅት የሚያስፈልጉትን መሣሪያዎችና ዕቃዎች ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ሆነውለት ሊያስገባ ይችላል ። ፩ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እና ( ፫ ) ድንጋጌ ቢኖርም በሠንጠረዥ ሁለት ውስጥ በፊደል ተራ ( ሐ ) ተራ ቁጥር ፰ ፡ ፱፡ ፲፩ ፡ ፵፪ እና ፵፫ ፥ በሠንጠረዥ ሦስት ውስጥ በፊደል ተራ ( ረ ) እንዲሁም በሠንጠረዥ አራት ውስጥ በፊደል ተራ ( ለ ) ተራ ቁጥር ፭፡ ፩፡ ፳ እና ፳፮ በተመለከቱት የኢንቨስትመንት መስኮች በአዲስ አበባ ውስጥ ኢንቨስት ያደረገ ባለሀብት ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ የመሆን መብት አይሰጠውም ። ፭ ማናቸውም የካፒታል ዕቃዎች ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ሆነው እንዲገቡ ይፈቀዳል ። ሆኖም ከውጭ ሀገር ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ የሚጠየቁ የካፒታል ዕቃዎችና መሣሪያዎች በሀገር ውስጥ የሚመረቱ ከሆኑ ከውጭ የሚገቡትን ሊተኩ የሚችሉ የካፒታል ዕቃዎችና መሣሪያዎች ዝርዝር ቦርዱ በየጊዜው በሚያወጣው መመሪያ እንዲታወቁ ያደርጋል ። ፮ ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ሆኖ የገባ ማናቸውም ዕቃ ሊከፈልበት ይገባ የነበረው የጉምሩክ ቀረጥ አስቀድሞ ሳይከፈልበት የቀረጥ ነፃ መብት ለሌለው ሰው ሊተላለፍ አይችልም ። ፲፪ . ለግብርና ኢንቨስትመንት የሚፈቀዱ መሣሪያዎችና ዕቃዎች [ 12. Machinery and Equipment to be Imported Duty Free for ለግብርና ኢንቨስትመንት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ዕቃዎች ወይም ክፍሎቻቸው በዋጋ ከ፲፭ በመቶ ከማይበልጥ የመለ ዋወጫ ዕቃዎች ጋር ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ሆነው እንዲገቡ ይፈቀዳል ገጽ ፪፻፴ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፱ ሰኔ ፳፯ ቀን ፲፱፻፷፰ ዓ.ም. Federal Negarit Gazeta ፩- አዲስ መሬትን ለእርሻ ተግባር ለማዘጋጀትና የእርሻ ውስጥ መንገዶችን ለመዘርጋት የሚያስፈልጉ ከባድ የመሬት ማዘጋጃ መሣሪያዎች ፣ ፪ መሬት ከማሰናዳት ወይም ከማለስለስ እስከ አዝመራ መሰብሰብ አስፈላጊ የሆኑ ወይም ከመሬት የሚገኘውን ውጤት ለመለየት ወይም ለማጣራት የሚያገለግሉ መሣሪ ያዎች ፣ ፫ እንስሶችን ለማራባት ወይም ከዚሁ የሚገኘውን ውጤት ለመለየት ፡ ለማዘጋጀት ወይም ለማጣራት እንዲሁም የዓሣ ልማትን ለማካሄድ የሚያገለግሉ መሣሪያዎች ፤ ፬ ለአግሮ ኢንዱስትሪ አስፈላጊ የሆኑ የማምረቻ መሣሪያ ዎችና ዕቃዎች ። ፲፫ : ለኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት የሚፈቀዱ መሣሪያዎች በቀጥታ ዕቃዎችን ለማምረት የሚያስፈልጉ የማምረቻ መሣሪ ያዎች ፡ ዕቃዎችና የእነዚሁ ክፍሎች በዋጋ ከ፲፩በመቶ ከማይበልጥ የመለዋወጫ ዕቃዎቻቸው ጋር ፡ እንዲሁም ለፋብ ሪካው ሕንፃ ግንባታ የሚያገለግሉ የስቲል ስትራክቸር አካላት ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ሆነው እንዲገቡ ይፈቀዳል ። ፲፬ • ለኮንስትራክሽን ኢንቨስትመንት የሚፈቀዱ መሣሪያዎች ለኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ እና ሌሎች የውሃ ነክ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ፥ ለኮንስትራክሽን መሣሪያዎች ኪራይ አገልግሎት ኢንቨስትመንት የሚያስ ፈልጉ የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች በዋጋ ከ፲፩በመቶ ከማይ በልጥ የመለዋወጫ ዕቃዎቻቸው ጋር ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ሆነው እንዲገቡ ይፈቀዳል ። ፲፭ ለሆቴልና ቱሪዝም አገልግሎት ኢንቨስትመንት የሚፈቀዱ 5. Equipment to be Imported Duty Free for Investments in ፩ : በኮከብ ደረጃ ለሚቋቋሙ ሆቴሎችና በፓርኮችና በታሪካዊ ቦታዎች ለሚቋቋሙ ሎጆች የሚያስፈልጉ ለምግብ ማብሰያና ማዘጋጃ ፡ እንዲሁም ለላውንድሪ አገልግሎቶች የሚውሉ ከፍተኛ ቋሚ ዕቃዎች ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ሆነው እንዲገቡ ይፈቀዳል ። ፪ • በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ሆነው እንዲገቡ የሚፈቀዱ ዕቃዎች ዓይነትና ብዛት ቦርዱ በመመሪያ በሚያወጣው ዝርዝር ይወሰናል ። ፲፮ • ለትምህርት አገልግሎት ኢንቨስትመንት የሚፈቀዱ ዕቃዎች በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት ተቋማት ሊኖራቸው ስለሚገባ የትምህርት መገልገያና የላብራቶሪ ዕቃዎች ፡ የትምህርት ሚኒስቴር በሚያወጣው መመሪያ ላይ በተገለጸው ዝርዝር መሠረት ቋሚ የትምህርት አገልግሎት መስጫ መሣሪያዎችና የላብራቶሪ ዕቃዎች ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ሆነው እንዲገቡ ይፈቀዳል ። ፲፯ • ለጤና አገልግሎት ኢንቨስትመንት የሚፈቀዱ ዕቃዎች በየደረጃው የሚገኙ የጤና አገልግሎት ተቋማት ሊኖራቸው ስለሚገባ የጤና አገልግሎት መስጫ መሣሪያዎችና የላብራቶሪ ዕቃዎች ፡ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በሚያወጣው መመሪያ ላይ በተገለጸው ዝርዝር መሠረት ቋሚ የሕክምና አገልግሎት መስጫ መሣሪያዎችና የላብራቶሪ ዕቃዎች ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ሆነው እንዲገቡ ይፈቀዳል ። ገጽ ፪፻፴፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፱ ሰኔ ፳፯ ቀን ፲፱፻፲፰ ዓም ፲፰፡ ለትራንስፖርት አገልግሎትና ለማከማቻ አገልግሎት ኢንቨስ ትመንት የሚፈቀዱ መሣሪያዎች በአገር ውስጥ የውሃ አካላት ላይ ሰዎችንና ዕቃዎችን ለማጓጓዝ የሚያገለግሉ ጀልባዎችና አነስተኛ መርከቦች ; እስከ ፳ መንገደኞች ወይም እስከ ፪ሺህ፯፻ ኪሎ ግራም የመጫን አቅም ያላቸው ኤርክራፍቶች ፡ ሌሎች የአቪየሽን አገልግሎት መስጫ መሣሪያዎችና የነዚሁ ክፍሎች ፡ በመጋዘኖች ውስጥ የሚገጠሙ የማቀዝቀዣ መሣሪያዎች ፡ የዕቃ ማንሻና የውስጥ ለውስጥማጓጓዣ መሣሪያዎችና በዋጋከ፲፩በመቶ ከማይበልጥ የመለዋወጫ ዕቃዎች ጋር ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ሆነው እንዲገቡ ይፈቀዳል ። ለኢንጂነሪንግና ቴክኒካል ምክር አገልግሎት ኢንቨስትመንት የሚፈቀዱ መሣሪያዎች የቅየሳ ፡ የዲዛይን ፡ የፎቶግራሜትሪ ፡ የካርቶግራፊክ ፡ የመለኪያ ፡ የመፈተሻና ትክክለኛነት የማረጋገጫ መሣሪያ ዎችና ሌሎች ከኮምፒዩተር ፡ ፎቶ ኮፒየርና ከመሳሰሉት የቢሮ ዕቃዎች በስተቀር ለኢንጂነሪንግና ለቴክኒካል ምክር አገል ግሎት የሚያስፈልጉ ቋሚ መሣሪያዎችና ዕቃዎች እንዲሁም የእነዚሁ ክፍሎች ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ሆነው እንዲገቡ | 20. Vehicles to be Imported Duty Free for Investment ይፈቀዳል ። ፳ ለቆሻሻ ማስወገድ አገልግሎት ኢንቨስትመንት የሚፈቀዱ ተሽከርካሪዎች ደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ ማንሻናማጓጓዣ ተሽከርካሪዎችና የነዚሁ ክፍሎች በዋጋ ከ፲፩በመቶ ከማይበልጥ መለዋወጫ ዕቃዎች ጋር ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ሆነው እንዲገቡ ይፈቀዳል ። ፳፩ ለኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትና ነዳጅ ለማጣራት ኢንቨስት መንት የሚፈቀዱ መሣሪያዎችና ዕቃዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት ፡ ለማስተላለፍና ለማከ ፋፈል የሚያስፈልጉ መሣሪያዎችና ዕቃዎች ፡ እንዲሁም ነዳጅ ለማጣራት የሚያስፈልጉ መሣሪያዎችና ዕቃዎች የነዚሁ ክፍሎች በዋጋ ከ፲፩በመቶ ከማይበልጥ መለዋወጫ ዕቃዎች ጋር ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ሆነው እንዲገቡ ይፈቀዳል ። ፳፪ • ስለድጋፍ ሰጪ መሣሪያዎችና ዕቃዎች የድጋፍ ሰጪ መሣሪያዎችና ዕቃዎችማለትም ፎርክ ሊፍቶች፡ የኤሌክትሪክ ጀኔሬተሮች ፡ ኮምፕሬሰሮች ፡ የኤሌክትሪክና የውሃ መስመሮች ለመዘርጋት የሚያስችሉ መሣሪያዎችና ዕቃዎች ፡ ኮንቨየሮች ፡ የላቦራቶሪ መሣሪያዎችና ዕቃዎች ፡ ቦይለሮችና የጥገና መሣሪያዎች : የሬዲዮ መገናኛ መሣሪ ያዎች፡ የተለየ አገልግሎት የሚሰጡማቀዝቀዣ ወይም መርጫ የተገጠመላቸው ተሽከርካሪዎች : እንስሳትን ከቦታ ቦታ ለማጓጓዝ ተብለው የተሠሩ ተሽከርካሪዎች ለኢንቨስትመንት ፕሮጀክቱ አስፈላጊነታቸው በባለሥልጣኑ ከተረጋገጠ ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ሆነው እንዲገቡ ይፈቀዳል ። ፳፫- ስለ ተሽከርካሪዎች ለአንድ ኢንቨስትመንት ፕሮጀክት ባሕሪው ፡ ስፋቱ ወይም የሚቋቋምበት ቦታ እየታየ ሥራውን ለመጀመርና ለማንቀ ሳቀስ ያስፈልጋሉ ተብለው ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ሆነው እንዲገቡ የሚፈቀዱ ተሽከርካሪዎች ዓይነትና ብዛት ቦርዱ በመመሪያ በሚያወጣው ዝርዝር ይወሰናል ። ገጽ ፪፻፴፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፱ ሰኔ ፳፯ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓ • ም • ክፍል አራት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ፳፬ . ተፈጻሚነት ስለማይኖራቸው ደንቦችና መመሪያዎች ከዚህ ደንብ ጋር የሚቃረን ማናቸውም ደንብ ወይም መመሪያ በዚህ ደንብ የተደነገገባቸውን ጉዳዮች በተመለከተ ተፈጻ ሚነት አይኖረውም ። ፳፭ ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ ይህ ደንብ ከሰኔ ፲፩ ቀን ፲፱፻፫፫ ዓ.ም. ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ሰኔ ፳፯ ቀን ፲፱፻ ፰ ዓም መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር