የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ስምንተኛ ዓመት ቁጥር አዲስ አበባ ጥር ፳፫ ቀን ፲፱፻፲፬ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፪፻፷፰ ፲፱፻፶፬ ዓ.ም የውሃ ልማት ፈንድን ለማቋቋምና አስተዳደሩን ለመወሰን የወጣ ገጽ ፩ሺ፯፻፪ አዋጅ ቁጥር ፪፻፳፰ ፲፱፻፲፬ የውሃ ልማት ፈንድ ለማቋቋምና አስተዳደሩን ለመወሰን የወጣ አዋጅ ሕብረተሰቡ አስተማማኝና ዘለቄታዊነት ያለው የውሃ አቅር ቦትና ሳኒቴሽን አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል የውሃ አቅርቦትንና የሳኒቴሽን አገልግሎትን ማጎልበትና ማጠናከር | beneficiary of reliable and sustainable water supply and አስፈላጊ በመሆኑ ፣ በምግብ ራስን ለመቻል በሚደረገው የልማት እንቅስቃሴ የመስኖ እርሻ ልማት ከፍተኛ ትኩረት ከሚሰጣቸው ተግባራት አንዱ በመሆኑ ለልማቱ መስፋፋት ምቹ ሁኔታ መፍጠር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፣ እነዚህንም ዓላማዎች ተግባራዊ ለማድረግ አስፈላጊ | sary to create the conducive conditions for its development : የሆነውን ገንዘብ ከተለያዩ ምንጮች በማእከል በማሰባሰብ ሁሉም ፍትሐዊና ርትአዊ በሆነ መንገድ ተጠቃሚ የሚሆንበትን አሠራር መቀየስ ተገቢና ለዚሁም የውሃ ልማት ፈንድ ማቋቋም አስፈላጊ | collected from various sources to implement the above ሆኖ በመገኘቱ ፣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ክፍል አንድ ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የውሃ ልማት ፈንድን ለማቋቋምና አስተዳደሩን ለመወሰን የወጣ አዋጅ ቁጥር ፪፻፳፰ ፲፱፻፲፬ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ፡ ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖ.ሣቁ. ፱ሺ፩ ጽ ፩ሺ፯፻፫ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፭ ጥር ፳፫ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓ ም • ፩ « የውሃ ልማት » ማለት ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም የመጠጥ ውሃ አቅርቦት፡ የመስኖ ልማት እና የሳኒቴሽን አገል ግሎት ነው፡ ፪ « ክልል » ማለት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፵፯ ( ፩ ) የተጠቀሰው ማንኛውም ክልል ሲሆን ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም ሲባል የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደርንም ይጨምራል ፤ ፫ « ሳኒቴሽን » ማለት ከመኖሪያ ቤት : ከኢንዱስትሪ ፡ ከንግድና ከመሳሰሉት ተቋማትሚወጣን ፍሳሽ አሰባስቦ በማጣራት ተገቢውን የጥራት ደረጃ የጠበቀ ውሃ ማስገኘት ነው፡ ፬ . « የመስኖ ልማት » ማለት ማንኛውም ለእርሻና ለግጦሽ የሚውል መሬት ለማልማት የሚያስችል የመስኖ ልማት ፭ « የውሃ አቅርቦት ” ማለት ለመጠጥና ለሌሎች ግልጋ ሎቶች የሚውል ደረጃውን የጠበቀ የተጣራ ውሃ ነው ፤ ፮ « ቦርድ » ማለት የውሃ ልማት ፈንድ ቦርድ ነው፡ ፯ « ተቋም » ማለት የመንግሥት የከተማ መጠጥ ውሃ አገልግሎት እንዲሁም በተደራጁ ገበሬዎች የሚለማ መስኖ ነው፡ ፰ « ሚኒስትር » እና « ሚኒስቴር » ማለት እንደቅደም ተከተሉ የውሃ ሀብት ሚኒስትር እና ሚኒስቴር ነው ። ክፍት ሁለት ስለፈንዱ መቋቋም ፫ መቋቋም ፩ የውሃ ልማት ፈንድ ከዚህ በኋላ « ፈንዱ » እየተባለ የሚጠራ በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ። ፪ • ፈንዱ ቋሚ የፋይናንስ ምንጭ ሆኖ ለዚህ አዋጅ ዓላማ ማስፈጸሚያ ይውላል ። የፈንዱ ዓላማ ፈንዱ የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል፡ ፩ . በውሃ አቅርቦት እና ሳኒቴሽን አገልግሎት ሥራ ላይ የተሰማሩ ተቋማት ሙሉ በሙሉ ራሳቸውን ችለው ለሕብረተሰቡ አስተማማኝና ዘላቂነት ያለው የውሃ አቅርቦት አገልግሎት እንዲሰጡ ማስቻል፡ ፪ • የመስኖ ልማትን በማስፋፋትና ዘለቄታዊነቱን በማረ ጋገጥ በምግብ ራስን ለመቻል ለሚደረገው የልማት እንቅስቃሴ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ማስቻል ፣ ፫ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እና ( ፪ ) የተጠቀሱትን ዓላማዎች እውን ለማድረግ ወጪን በማስመለስ መርሆ ላይ የተመሠረተ የረዥም ጊዜ ብድር ለመስጠት ሁኔታ ዎችን ማመቻቸት ። ፭ የፈንዱ ምንጮች ፩ : ፈንዱ ከሚከተሉት ምንጮች የተውጣጣ ይሆናል፡ ሀ ) ከፈንዱ ዓላማ ጋር በተያያዘ ከውጭ መንግሥታት እና ከዓለም አቀፍ ለጋሽ ድርጅቶች የሚገኝ የገንዘብ እርዳታና ብድር፡ ለ ) ከፌዴራል መንግሥት ከሚመደብለት በጀት ፣ ሐ ) ከልዩ ልዩ ምንጮች ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተጠቀሰው ገንዘብ ለፈንዱ ሲባል በጽሕፈት ቤቱ ስም በተከፈተ የባንክ ሂሣብ በገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ተቀማጭ ይደረጋል ። ጽሕፈት ቤቱ የውጭ ምንዛሪ የባንክ ሂሣብ ሊኖረው ይችላል ። ፫ : መንግሥት በብድር በሚያገኘው ገንዘብ ላይ ከአበዳሪው ወገን ጋር በሚያደርገው ስምምነት መሠረት ከሚጣል ወለደ በስተቀር ተጨማሪ ወለድ ኣይጥልም ። ፮ ስለሚለቀቀው ገንዘብ በፀደቀው ዓመታዊ የሥራ ፕሮግራም መሠረት ለሚከናወኑ ሥራዎች ከፈንዱ ሂሣብ ገንዘብ ወጭ ሆኖ የሚለቀቀው የገንዘብ ብድር መጠን ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ይሆናል ። ገጽ ፩ሺ፯፻፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፭ ጥር ፳፫ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓ ም በፈንዱ ተጠቃሚ ለመሆን የሚያበቁ መመዘኛዎች በፈንዱ ተጠቃሚ የሚሆን ተቋም ሕጋዊ ሰውነት ያለው | 7 . Criteria for being Eligible to be beneficiary of the Fund መሆን አለበት ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ከተደነገገው በተጨ ማሪም በአንቀጽ ፲፬ ( ፬ ) መሠረት በቦርዱ የሚወጡ መመዘኛዎች ተፈጻሚ ይሆናሉ ። ፰ : ስለፈንዱ ሂሣብ ፩ : ጽሕፈት ቤቱ የፈንዱን ሂሣብ በሚመለከት ትክክለኛና | 8. Account of the Fund የተሟሉ የሂሣብ መዛግብት በተለይ ይይዛል ። ፪ • የፈንዱ የሂሣብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ በዋናው ኦዲተር ወይም እርሱ በሚወክለው ሰው ይመረመራሉ ። የኦዲተሩ የምርመራ ውጤት የበጀት ዓመቱ ባለቅ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ለቦርዱ ይቀርባል ። ክፍል ሦስት ስለፈንዱ አስተዳደር ፀ • የውሃ ልማት ፈንድ ጽሕፈት ቤት መቋቋም ፩ የውሃ ልማት ፈንድ ጽሕፈት ቤት ከዚህ በኋላ “ ጽሕፈት | 9. Establishment of the Office of the Fund ቤቱ ” እየተባለ የሚጠራ ራሱን የቻለ ሕጋዊ ሰውነት ያለው ኣካል ሆኖ በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ። ፪ ጽሕፈት ቤቱ ተጠሪነቱ ለሚኒስትሩ ይሆናል ። ፲ ዋና መሥሪያ ቤት የጽሕፈት ቤቱ ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ ሆኖ ፡ እንደአስፈላጊነቱ በሃገሪቱ በማናቸውም ስፍራ ቅርንጫፎች ሊኖሩት ይችላል ። ፲፩ የጽሕፈት ቤቱ ሥልጣንና ተግባር ጽሕፈት ቤቱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፣ ፩ . የቦርዱን ውሣኔዎችንና መመሪያዎችን በትክክል በሥራ ላይ መዋላቸውን ይከታተላል፡ ያረጋግጣል፡ ፪ . የፈንዱን ሂሣብና ሪኮርድ ይይዛል፡ ፫ የቦርዱን ሥራ አመራር የስብሰባ ሪኮርዶችን ይይዛል፡ በየዓመቱ የሚቀርቡ የብድር ጥያቄዎችን በመገምገምና ቦርዱ በሚያወጣው የብድር አሰጣጥ አወሳሰን መመዘኛ መሠረት ቅደም ተከተል በማውጣት ከፈንዱ በብድር ይሰጣል፡ ለፈንዱ መግባት የሚገባውን የብድር ተመላሽ እና በአንቀጽ ፭ ከተጠቀሱት ምንጮች የሚገኘውን ተሰብሳቢ ገንዘብ ሁሉ በወቅቱ ይሰበስባል፡ በፈንዱ ሂሣብ ገቢ መደረጉን ይከታተላል፡ ያረጋግጣል፡ ፮ ፈንዱን የሚመለከቱ የፖሊሲ ሃሣቦችን ለቦርዱ ያቀርባል፡ ፯ የንብረት ባለቤት ይሆናል፡ ውል ይዋዋላል ፣ በስሙ ይከሳል ፣ ይከሰሳል ። ፲፪ : የጽሕፈት ቤቱ አቋም ጽሕፈት ቤቱ ፡፡ የውሃ ልማት ፈንድ ቦርድ፡ ፪ . በቦርዱ አቅራቢነት በመንግሥት የሚሾም አንድ ዋና ሥራ አስኪያጅ፡ እና ፫ አስፈላጊው ሠራተኞች ይኖሩታል ። ፲፫ . ስለቦርድ አባላት ቦርዱ ሰብሳቢውን ጨምሮ በመንግሥት የሚሰየሙ አባላት ይኖሩታል ። ቁጥራቸውም እንደአስፈላጊነቱ ይወሰናል ። ፲፬ • የቦርዱ ሥልጣንና ተግባር ቦርዱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል፡ ፈንዱን በበላይነት ያስተዳድራል፡ ፪ . ስለፈንዱ አሰባሰብና ከፈንዱ ገንዘብ ወጪና ተከፋይ ስለሚሆንበት ሥርዓት መመሪያ ያወጣል ፤ ፫ ለፈንዱ መግባት ያለባቸው ገቢዎች በወቅቱ መሰብሰባ ቸውን እና በፈንዱ ሂሣብ መግባታቸውን ያረጋግጣል፡ ፬ . የዚህ አዋጅ አንቀጽ ፯ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው፡ የብድር አሰጣጥ አወሳሰን መመዘኛዎችን ያወጣል ፤ ፭ . የፈንዱን ኦዲት በኦዲት ሪፖርቶች ይገመግማል ፤ በሪፖ ርቶቹ መሠረት ተገቢ እርምጃዎች መወሰዳቸውን ያረጋ ግጣል፡ በኦዲተር የተመረመረው ዓመታዊው የፈንዱ ሂሣብ እንዲጠናቀርና ይፋ እንዲሆን ያስደርጋል ፤ ገጽ ፩ሺ፮፻፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፭ ጥር ፳፫ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓም : ፈንዱ ሊያድግ የሚችልበትን መንገድ ይፈልጋል ፤ ቪ ከፈንዱ ጋር በተያያዘ ዓመታዊ የፖሊሲ ጉዳዮች ላይ መንግሥትን ያማክራል፡ የጽሕፈት ቤቱን ዓመታዊ የሥራ ፕሮግራምና በጀት ይመረምራል፡ ለመንግሥት አቅርቦ ያስፀድቃል ፤ ሀ . የጽሕፈት ቤቱን ዋና ሥራ አስኪያጅ ለመንግሥት በማቅረብ ያሾማል ። ፲፭ የቦር ስብሰባዎች የቦርዱ መደበኛ ስብሰባ በየሦስት ወሩ አንድ ጊዜ ይደረጋል፡ ሆኖም በሰብሳቢው ሲጠራ ቦርዱ በማን ኛውም ጊዜ አስቸኳይ ስብሰባ ሊያደርግ ይችላል ። በቦርዱ ስብሰባ ላይ ከግማሽ በላይ አባላት ከተገኙ ምልአተ ጉባኤ ይሆናል ። ፫ . የቦርዱ ውሣኔ የሚተላለፈው በስብሰባው ከተገኙ አባላት በአብላጫው ድምጽ ሲደገፍ ነው ። ሆኖም ድምፅ እኩል በእኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው ወሳኝ ድምጽ ይኖረዋል ። የዚህ ኣንቀጽ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው ቦርዱ የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ሊያወጣ ይችላል ። ፲፮ የጽሕፈት ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሥልጣንና ተግባር ፩ . የጽሕፈት ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ከቦርዱ በሚሰጠው አጠቃላይ መመሪያ መሠረት የጽሕፈት ቤቱን ሥራዎች ያቅዳል፡ ይመራል ፣ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) አጠቃላይ አነጋገር ሳይወሰን ፣ ዋና ሥራ አስኪያጁ ፤ ሀ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፩ የተመለከቱትን የጽሕፈት ቤቱን ሥልጣንና ተግባሮች ሥራ ላይ ያውላል ፤ ለ ) የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግን መሠረታዊ ዓላማዎች በመከተል በሚያፀድቀው መመሪያ መሠረት የጽሕፈት ቤቱን ሠራተኞች ይቀጥራል፡ ያስተዳድራል ፤ ሐ ) የጽሕፈት ቤቱን ዓመታዊ በጀትና የሥራ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ያቀርባል፡ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል ፣ ለጽሕፈቱ ቤቱ በተፈቀደው በጀትና የሥራ ፕሮግራም መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል፡ ሠ ) በጽሕፈት ቤቱ ደረጄ ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች ሁሉ ጽሕፈት ቤቱን ይወክላል፡ ረ ) ከቦርዱ የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከና ሥራ አስኪያጁ ለጽሕፈት ቤቱ ሥራ ቅልጥፍና በሚያስ ፈልግ መጠን ሥልጣንና ተግባሩን በከፊል ለጽሕፈት ቤቱ ሠራተኞች በውክልና ሊያስተላልፍ ይችላል ። ፲፯ በጀት ፩ የጽሕፈት ቤቱ በጀት በመንግሥት ይመደባል፡ ፪ . የጽሕፈት ቤቱ የበጀት ዓመት ከሐምሌ ፩ ቀን ጀምሮ ሰኔ ፴ ቀን ያበቃል ። ፲፰ . ስለሂሣብ መዛግብት አያያዝ ፩ ጽሕፈት ቤቱ ትክክለኛና የተሟሉ የሂሣብ መዛግብትን ከደጋፊ ሰነዶች ጋር ይይዛል ። ፪ • የጽሕፈት ቤቱ የሂሣብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ በዋናው ኦዲተር ወይም እርሱ በሚወክለው ሰው ይመረመራሉ ። የኦዲተሩ የምርመራ ውጤት የበጀት ዓመት ባለቀ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ለቦርዱ ይቀርባል ። ገጽ ፩ሺ፯፻፮ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፩ ጥር ፳፫ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓ.ም ክፍል አራት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ፲፱ ተፈጻሚነት ስለማይኖራቸው ሕጎች ከዚህ አዋጅ ጋር የሚቃረን ማናቸውም ሕግ በዚህ አዋጅ በተደነገገባቸው ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት አይኖረውም ። ፳ አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከጥር ፳፫ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓም ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ጥር ፳፫ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓ.ም ግርማ ወልደጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ