×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
ደንብ ቁጥር ፲፭/፲፱፻፶፮ ዓ.ም የንግድ ምዝገባና ፈቃድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ማሻሻያ ደንብ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አስረኛ ዓመት ቁጥር ፲ አዲስ አበባ ኅዳር ፲፩ ቀን ፲፱፻፲፮ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ ደንብ ቁጥር ፲፭ ፲፱፻፲፮ ዓም የንግድ ምዝገባና ፈቃድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ማሻሻያ ደንብ . ገጽ ፪ሺ፬፻፵፪ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፲፭ ፲፱፻፵፮ የፌዴራል መንግሥት የንግድ ምዝገባና ፈቃድ ደንብን ለማሻሻል የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራ ሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻ዥ፯ አንቀጽ ፭ እና በንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር ፳፯ ፲፱፻፷፬ ኣንቀጽ ፵፯ መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ማሻሻያ ደንብ ቁጥር ፲፭ / ፲፱፻፲፮ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ማሻሻያ የፌዴራል መንግሥት የንግድ ምዝገባና ፈቃድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፲፫ / ፲፱፻፳፱ ከዚህ እንደሚከተለው ተሻሽሏል ። ፩ በደንቡ አንቀጽ ፫ ላይ የሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ ( ፭ ) ተጨምሯል ። ፭ አግባብ ያለው ባለሥልጣን በአዋጁና በዚህ ደንብ መሠረት ከሚቀርቡ ማመልከቻዎች ጋር የሚያያዙ የፎቶግራፎችንና የሰነዶችን ቅጂ ብዛት መወሰን ይችላል ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖ.ሣቁ ፫ሺ፩ ገጽ ፪ሺ፱የሣ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲ ኅዳር ፲፩ ቀን ፲፱፻፲፮ ዓ.ም የደንቡ አንቀጽ ፬ ተሰርዞ በሚከተለው አዲስ አንቀጽ ፬ ተተክቷል ። ፬ . የግለሰብ የንግድ ዋና ምዝገባ አመልካቹ ግለሰብ ከሆነ የሚከተሉትን ሰነዶች ከማመልከቻ ቅጹ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለበት ። ፩ . ማመልከቻው የተፈረመው በወኪል ከሆነ የውክልና ሥልጣን ማረጋገጫ ሰነድ ፎቶ ኮፒ ፣ ፪ የአመልካቹ የቅርብ ጊዜ ጉርድ ፎቶግራፎች ፣ ፫ . የአመልካቹ የመታወቂያ ካርድ ወይም የፀና ፓስፖርት ገጾች ፎቶ ኮፒ ። የደንቡ አንቀጽ ፭ ተሰርዞ በሚከተለው አዲስ አንቀጽ ፭ ተተክቷል ። ፭ አክሲዮን ማህበር ያልሆነ የንግድ ማኅበር የንግድ ዋና ምዝገባ አመልካቹ በመቋቋም ላይ ያለ አክሲዮን ማህበር ያልሆነ የንግድ ማኅበር ከሆነ የማመልከቻ ቅጹን ከሚከተሉት ሰነዶች ጋር በማያያዝ ባለአክሲዮኖቹ የባለአክሲዮኖቹ ኣለባቸው ። ፩ . ማመልከቻው የተፈረመው በወኪል ከሆነ የውክልና ሥልጣን ማረጋገጫ ሰነድ ፎቶ ኮፒ ፣ ፪ . የማኅበሩ የመመስረቻ ጽሑፍ እና የመተዳ ደሪያ ደንብ ፣ ፫ . በማኅበሩ ውስጥ የኢትዮጵያ ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች የእያንዳንዳቸው የመታወቂያ ካርድ ፎቶኮፒ ወይም እንደሀገር ውስጥ ባለሀብት የተቆጠሩ የውጭ አገር ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች ካሉ እንደ አገር ውስጥ ባለሀብት የተቆጠሩበት ሠነድ ፎቶ ኮፒ ወይም ማህበሩ ውስጥ የውጭ አገር ዜግነትያላቸው ግለሰቦች ካሉ የእያንዳንዳቸው የፀና ፓስፖርት ገጾች ፎቶኮፒ ፣ እና ፬ . በሚቋቋመው ማኅበር ውስጥ ባለአክሲዮን የሆነ የሕግ ሰውነት ያለው አካል ካለ የዚሁ አካል የመቋቋሚያ ምስክር ወረቀት ወይም ተመሳሳይ ሰነድ ፎቶ ኮፒ እና አዲስ በሚቋ ቋመው ማኅበር ውስጥ ለመግባት መወሰኑን የሚያሳይ በአገሩ ውልና ማስረጃ ጽሕፈት ቤት የተረጋገጠ ቃለጉባዔ ወይም ደብዳቤ ፎቶኮፒ ። የደንቡ አንቀጽ ፮ ተሰርዞ በሚከተለው አዲስ አንቀጽ ፮ ተተክቷል ። ፮ . የአክሲዮን ማህበር የንግድ ዋና ምዝገባ አመልካቹ በመቋቋም ላይ ያለ የአክሲዮን ማኅበር ከሆነ መሥራቾቹ ወይም ወኪላቸው የማመልከቻ ቅጹን ከሚከተሉት ሰነዶች ጋር በማያያዝ ማቅረብ ኣለባቸው ። ፩ . ማመልከቻው የተፈረመው በወኪል ከሆነ የውክልና ማረጋገጫ ሰነድ ፎቶኮፒ ፣ ፪ • በገንዘብ ከሚሸጡት አክሲዮኖች ቢያንስ አራተኛው በባንክ መቀመጡን የሚያሳይ የባንክ ማረጋገጫ ፣ ፫ አክሲዮን ለመግዛት ቃል የገቡ ሰዎች ስብሰባ ቃለ ጉባኤ እና ከጉባኤው ጋር የተያያዙ ሰነዶች ፎቶኮፒ ፣ ፬ . የአክሲዮን ማኅበሩ የመመስረቻ ጽሑፍና የመ ተዳደሪያ ደንብ ቅጂዎች ። ፭ . በዚህ ደንብ አንቀጽ ፭ ንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) የተጠቀሱት ሰነዶች እንደአስፈላጊነታቸው ። ግጽ ፪ሺ፬፻፵፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲ ኅዳር ፲፩ ቀን ፲፱፻፲፮ ዓ • ም • የደንቡ አንቀጽ ፯ ተሰርዟል ። የደንቡ አንቀጽ ፰ ተሰርዞ የሚከተለው አዲስ አንቀጽ ፰ ተተክቷል ። ፰ . የውጭ አገር የንግድ ማኅበር የንግድ ዋና ምዝገባ አመልካቹ በውጭ አገር የተቋቋመ የንግድ ማኅበር የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ከሆነ ወኪሉ የማመልከቻ ቅጹን ከሚከተሉት ሰነዶች ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለበት ። ፩ ሥልጣን ያለው የማኅበሩ አካል ውስጥ ቅርንጫፍ ለመክፈት መወሰኑን የሚያሳይ በአገሩ በሚገኝ የውልና ማስረጃ ጽሕፈት ቤት የተረጋገጠ ቃለ ጉባዔ ወይም ደብዳቤ ፣ ፪ . የማኅበሩ መቋቋሚያ የምስክር ወረቀት ፎቶ ፫ በኢትዮጵያ የማኅበሩ ቋሚ ወኪል የውክልና ሥልጣን ማረጋገጫ ሰነድ ፎቶ ኮፒ ፣ ፬ . የወኪሉ የመታወቂያ ካርድ ወይም የፓስ ፖርት ገጾች ፎቶኮፒ ፣ እና ፭ የማኅበሩ መመስረቻ ጽሑፍ እና የመተዳደሪያ ደንብ ወይም ተመሳሳይ ሰነድ ፎቶ ኮፒ ፣ የደንቡ አንቀጽ ፲ንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) ተሰርዞ በሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) ተተክቷል ። ፫ . በየበጀት ዓመቱ በኢትዮጵያ ውስጥ ለጽሕፈት ቤቱ ወጪ ቢያንስ ፵ ሺ የአሜሪካን ዶላር ወደ ሀገር ውስጥ የሚያስገባ ለመሆኑ የተፈረመ የግዴታ የደንቡ አንቀጽ ፲፪ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) ተሰርዞ በአዲስ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) የተተካ ሲሆን የሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ ( ፭ ) ተጨምሯል ፪ • ለዚህ ኣንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) አፈጻጸም አመልካቹ የሚከተሉትን ሰነዶች ከማመልከቻው ጋር ማቅረብ ኣለበት ። ሀ ) ማሻሻያው የሚደረገው ለንግድማሕበር ከሆነ የማሕበሩ ኣባላት ማሻሻያውን ለማድረግ ያስ ተላለፉት ውሳኔ ቃለ ጉባዔ ፣ ለ ) ማሻሻያው አዲስ አባል በንግድ ማሕበር ውስጥ እንዲገባ የሚያደርግ ከሆነ በዚህ ደንብ አንቀጽ ፭ ንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) የተጠቀሱትን ሰነዶች ፣ ሐ ) አዲሱ አባል የሕግ ሰውነት ያለው አካል ከሆነ በዚህ ደንብ በአንቀጽ ( ፭ ) ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተጠቀሱት ሰነዶች ። በግለሰብ ነጋዴ በተደረገ የንግድ ምዝገባ ላይ ለውጥ ወይም ተጨማሪ ምዝገባ ሲኖር አመልካቹ የቅርብ ጊዜ ፎቶግራፍ እንዲያቀርብ ተደርጎ ወረቀትና ይለጠፋል ። ፱ በደንቡ አንቀጽ ፲፯ ላይየሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) እና ( ፱ ) ተጨምሯል ፫ : ለሚከተሉት የንግድ ሥራዎች አዲስ የንግድ ሥራ ፈቃድ ሲወጣ የሙያ ብቃት ወይም የባለቤትነት ማረጋገጫ ከሚከተሉት የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች መቅረብ አለበት ። ሀ ) የሰው ፣ የእንስሳት ፣ የፀረተባይ መድኃኒቶችና የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች ለማስመ ጣትና ለማሠራጨት ከመድኃኒት አስተዳ ደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን የተሰጠ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፣ ገጽ ፪ሺ፱የ፴፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ´ ቁጥር ፲ ኅዳር ፲፩ ቀን ፲፱፻፲፮ ዓ.ም. ለ ) ለጉምሩክ አስተላላፊነት ንግድ ሥራ ከጉምሩክ ባለሥልጣን የተሰጠ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ፡ ለዕቃ አስተላላፊነት የመርከብ ውክልና ንግድ ሥራ ከመሠረተ ልማት ሚኒስቴር የተሰጠ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፣ መ ) ለደረጃ አንድ የሥራ ተቋራጭነት ንግድ ሥራ ከመሠረተ ልማት ሚኒስቴር የተሰጠ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፣ ሠ ) ለክልል ዘለል ትራንስፖርት አገልግሎት ንግድ ሥራ እንደ አስፈላጊነቱ ከክልል የሚመለከተው ቢሮ ወይም ከፌዴራል የመንገድ ትራንስፖርት ባለሥልጣን የተሰጠ የተሽከርካሪ ባለቤትነት ደብተር ፣ ለአደን ወይም የሣፋሪ አገልግሎት ንግድ ሥራ ከዱር አራዊት ልማትና ጥበቃ ድርጅት የተሰጠ የአሳዳኝነት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፣ ሰ ) ለፕሬስ ንግድ ሥራ | ጋዜጣ ወይም መጽሔት ማሳተም ከማስታወቂያ ሚኒስቴር የተሰጠ የብቃት ማረጋገጫ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) ሥር ከተጠቀሱት የንግድ ሥራዎች በተጨማሪ ሌሎች የሙያ ብቃት ወይም የባለቤትነት ማረጋገጫ የሚያስፈልጋቸው የንግድ ሥራዎች በሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚወጣ ደንብ ይወሰናሉ ። የደንቡ አንቀጽ ፲፰ ላይ የሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ ( ፮ ) ተጨምሯል በንግድ ፈቃድ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ሲደረግ ባለፈቃዱ የቅርብ ጊዜ ፎቶግራፍ እንዲያቀርብ ተደርጎ በዋናውና በቀሪው የንግድ ፈቃድ ቅጂዎች ላይ ይለጠፋል ። ፲፩ . የደንቡ አንቀጽ ፳፮ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ተሰርዞ በሚከ ተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ( ሐ ) ተተክቷል ሐ ) ለበጀት ዓመቱ ለደመወዝና ለሥራ ማስኬጃ የሚሆን ቢያንስ ፵ ሺ የአሜሪካን ዶላር ወደ ሀገር ውስጥ ያስገባ ለመሆኑ የባንክ ማረጋገጫ ፲፪ . የደንቡ አንቀጽ ፳፰ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) ተሰርዞ በሚከ ተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) የተተካ ሲሆን የሚከ ተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ተጨምሯል ። ፪ የንግድ እንደራሴው በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) በተወሰነው ጊዜ ውስጥ የንግድ እንደራሴነት የምስክር ወረቀቱን ካላሳደሰ በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ውስጥማለትም ከጥር ፩ ቀን እስከ ሰኔ ፴ ቀን ከምስክር ወረቀቱ ማሳደሻ በተጨማሪ ለዘገየበት ለጥር ወር ብር ፪ ሺህ ፭፻ ( ሁለት ሺ አምስት መቶ ) እና ለሚቀጥለው እያንዳንዱ ወር ብር ፩ ሺ ፭፻ ( አንድ ሺህ አምስት መቶ ) ቅጣት በመክፈል የንግድ እንደራሴነት የምስክር ወረቀቱን ያሳድሳል ። ፮ . የንግድ እንደራሴነት የምስክር ወረቀቱን ለማሳደስ የሚቀርብ የንግድ እንደራሴ በበጀት ዓመቱ ውስጥ እራሱንና ሌሎች ቀጥሮ የሚያሰራቸው ሠራተኞች ከደመወዝ ላይ የሚከፈል የገቢ ግብር ለመክፈሉ ከሚመለከተው የግብር ሰብሳቢ አካል የግብር ክሊራንስ ማምጣት አለበት ። ገጽ ፪ሺ፬፻፵፮ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲ ኅዳር ፲፩ ቀን ፲፱፻፲፮ ዓ.ም ፲፫ በደንቡ ኣንቀጽ ፳፬ ላይ የሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ተጨምሯል ። የንግድ እንደራሴው በዚህ ደንብ በአንቀጽ ፳፰ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እና ( ፪ ) በተወሰነው ጊዜ ውስጥ የንግድ እንደራሴነት የምስክር ወረቀቱን ሳያሳድስ በመቅረቱ ወይም በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) በተዘረዘሩት ሌሎች ምክንያቶች የምስክር ወረቀቱ ከተሰረዘማንኛውንም ግለሰብ ነጋዴ ወይም የንግድ ድርጅት በመወከል ያንኑ የምስክር ወረቀት እንደ አዲስ የሚያወጣው ከምስክር ወረቀቱ ማውጫ ክፍያ በተጨማሪ ብር ፲ ሺ ( አሥር ሺህ ) ቅጣት በመክፈል ነው ። ፲፬ • ከደንቡ ጋር ተያይዞ የነበረው ሰንጠረዥ “ ሀ ” ከዚህ ማሻሻያ ጋር በተያያዘው አዲስ የክፍያ ሰንጠረዥ የተተካ ሲሆን ሰንጠረዥ “ ለ ” እና “ ሐ ” ተሰርዘዋል ። ፲፭ በደንቡ ከአንቀጽ ፰ እስከ ፴፬ ያሉት ድንጋጌዎች እንደ ቅደም ተከተላቸው ከአንቀጽ ፯ እስከ ፴፫ ሆነው ተስተካ ክለዋል ። ደንቡ የሚፀናበት ጊዜ ይህ ደንብ ከ ኅዳር ፲፩ ቀን ፲፱፻፲፮ ዓም ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ኅዳር ፲፩ ቀን ፲፱፻፲፮ ዓም መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ ገጽ ፪ሺ፬፻፵፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲ ኅዳር ፲፩ ቀን ፲፱፻፲፮ ዓ.ም በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የንግድ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የንግድ ምዝገባና ፈቃድ ልዩ ልዩ የክፍያ ተመኖች የክፍያ ምክንያቶች የክፍያ ተመን ለመመዝገቢያ ለንግድ ዋና መዝገባ ለአጭር ምዝገባ ብር 80 ለንግድ ስም ምዝገባ ፣ ብር 80:00 ለንግድ እንደራሴ ምዝገባ ፣ ብር 5000 ለምዝገባ ግልባጭ ለእያንዳንዱ ፣ ብር 2:00 ብር 50.00 ለንግድ ምገዝገባ ለውጥ ፣ ተጨማሪ ምዝገባ ፣ ስረዛ ፡ የተውጣጣ ቅጅ ወይም የተጠየቀው ጉዳይ ያልተመ ስለመሆኑ ለሚሰጥማረጋገጫ ብር 50:00 ለንግድ ስም የምዝገባ ለውጥ ፣ ማሻሻያ ለንግድ ሥራ ፈቃድማውጫ ወይም ብር 80:00 ብር 200 : 00 ለንግድ እንደራሴነት የምሥክር ወረቀት ማውጫ ወይም ማደሻ ፣ ብር 200 : 00 ለጊያዊ ፣ ለማስፋፋት ወይም ለማሻሻያ የንግድ ሥራ ፈቃድ ፣ ብር 50:00 ለምትክ የንግድ ሥራ ፈቃድ ወይም ለምትክ የንግድ እንደራሴነት የምስክር ወረቀት ወይም ለምትክ የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፣ ብር 80:00 ድርጅት ሲተላለፍ ለሚደረግ ምዝገባና ለሚሰጥ የንግድ ሥራ ፈቃድ ፣ የንግድ ሥራ ፈቃድ ለማውጣት ሊሟሉ የሚገባቸው የልዩ ልዩ መስፈርቶች ቅጂ ለእያንዳንዱ ቅጂ ፡

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?