የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ሦስተኛ ዓመት ቁጥር ሃ፬ አዲስ አበባ - - ሰኔ ፴ቀን ፲፱፻፳፱ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፳፱ / ፲፱፻፳፱ ዓም• የፌዴራል መንግሥት የገጠር መሬት አስተዳደር አዋጅ . . . ገጽ ፮፻፳፰ አዋጅ ቁጥር ፳፱ / ፲፱፻፷፱ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግሥት የገጠር መሬት አስተዳደር አዋጅ የኢትዮጵያ ብሔሮች ፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ባደረጉት መራራ ትግል የመሬት ባለቤትነት መብት የመንግሥትና የሕዝብ ብቻ መሆኑ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመንግሥት በመረጋገጡ ፤ መሬትና የተፈጥሮ ሀብትን ለማስተዳደር ለክልሎች የተሰጠው ሥልጣን በሥራ ላይ የሚውለው የፌዴራሉ መንግሥት በሚያወጣው ሕግ መሠረት መሆኑን የሕገመንግሥቱ አንቀጽ ፲፪ ( ፪ ) ( መ ) ስለሚደነ የድንጋጌው ተግባራዊነት አጠቃላይ ይዘት ያለው ሆኖ በሁሉም ክልሎች ዘንድ ተፈጻሚነት የሚኖረው የገጠር መሬት አስተዳደር ሕግ ማውጣትን ስለሚጠይቅ ፤ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ክፍል አንድ ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የፌዴራል መንግሥት የገጠር መሬት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር ፳፱ / ፲፱፻፳፱ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ ፤ ያንዱ ዋጋ ያንዱ ዋጋ 60 | ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ . ፰ሺ፩ ገጽ ፮፻፳፱ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፬ ሰኔ ፴ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓ ም . Federal Negarit Gazeta – No . 54 7 July 1997 – Page 629 ፩ . “ ክልል ” ማለት በሕገመንግሥቱ አንቀጽ ፯ ( ፩ ) የተመለ ከተ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አባል የሆነ ክልል ሲሆን ፡ የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ መስተዳድሮ ችንም ይጨምራል ፡ ፪ . “ የገጠር መሬት ” ማለት ማዘጋጃ ቤት ከተቋቋመበት ወይም የክልሉ ምክር ቤት አግባብ ካለው አካል ጋር በመመካከር ከተማ ብሎ ከሚሰይመው አካባቢ ውጭ ያለ መሬት ነው ፡ ፫ . “ የይዞታ መብት ” ማለት ማንኛውም ኣርሶ አደር የገጠር መሬት ለግብርና ተግባር ለማዋል ፡ ለማከራየትና ይዞታው ጸንቶ ባለበት ጊዜ ውስጥ ለቤተሰቡ አባል ለማውረስ የሚኖ ረው መብት ሲሆን ፡ በመሬቱ ላይ በጉልበቱ ወይም በገንዘቡ ንብረትማፍራትንና ይኸንኑም መሸጥ ፡ መለወጥናማውረስን ይጨምራል ፡ “ የይዞታ ሽግሽግ ” ማለት የይዞታ መብት ፍትሐዊ በሆነና በተመጣጠነ መንገድ እንዲዳረስና አርሶ አደሮች በጋራ የሚጠቀሙበት መሬት ተለይቶ እንዲከለል ለማድረግ በነዋ ሪው ሕዝብ ውሳኔ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚከናወን የገጠር መሬት ያልደላ ተግባር ነው ፡ ፭ . “ የቤተሰብ አባል ” ማለት የይዞታ ባለመብቱን መተዳደሪያ ገቢ በመጋራት በቋሚነት አብሮ የሚኖር ማንኛውም ሰው ፮ . “ የመሬት አስተዳደር ” ማለት የይዞታ መብት አወሳሰንና የይዞታ ሽግሽግ አፈጸጸም ነው ። ፫• የፆታ አገላለጽ ከዚህ አዋጅ ውስጥ በወንድ ጾታ የተደነገገው የሴትንም ጾታ | ያካትታል ። ክፍል ሁለት የመሬት አስተዳደርን የሚመለከቱ አጠቃላይ ድንጋጌዎች Land is a common property of the Nations , ፩ - መሠረተ ሃሳብ መሬት የማይሸጥ የማይለወጥ የኢትዮጵያ ብሔሮች ፣ ብሔረሰቦችና | ሕዝቦች የጋራ ንብረት ነው ። ፭ የመሬት አስተዳደር ስለሚመራበት ሁኔታ ፩ . ማንኛውም ክልል የገጠር መሬት የሚያስተዳድረው በዚህ አዋጅ ውስጥ በተመለከቱት አጠቃላይ ድንጋጌዎች መሠ ረት ይሆናል ። ፪ . ለዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ድንጋጌ አፈጻጸም እያንዳ ንዱ የክልል ምክር ቤት የመሬት አስተዳደር ሕግ ያወጣል ። ፫ የክልል የመሬት አስተዳደር ሕግ የአካባቢ ጥበቃን አስመል ክቶ ከወጡ ሕጐች ድንጋጌዎች ጋር የተጣጣመ እና የፈደ ራል መንግሥት የመሬት አጠቃቀም ፖሊሲን ያገናዘበ መሆን አለበት ። የክልል የመሬት አስተዳደር ሕግ መሬትን በመጠቀም ፡ በማስተዳደርና በመቆጣጠር እንዲሁም የይዞታ መብትን በማስተላለፍና በማውረስ ረገድ የሴቶችን የእኩልነት መብት የሚያረጋግጥ መሆን ኣለበት ። የመሬት አስተዳደር ሕግ ይዘት የየክልሉ ምክር ቤት የሚያወጣው የመሬት አስተዳደር ሕግ ፩ . ከፆታ አድልዎ የጸዳ የይዞታ መብት ለአርሶ አደሩና ለዘላ ኖች በነፃ ማስገኘትን የሚያረጋግጥ እንዲሁም በክልሉ ምክር ቤት ውሳኔ መሠረት በክልሉ አጠቃላይ ወይም በከፊል በሚደረግ የመሬት ሽግሽግ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር በሌላ በማንኛውም ምክንያት ከይዞታ መብት አለመነቀልና አለመፈናቀልን የሚያስከብር ፡ ጽ ፮፻፴ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፬ ሰኔ ፴ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓም : _ Federal Negarit Gazeta - - No . 54 7 July , 1997 – Page 630 ፪ እንደየክልሉ ተጨባጭ ሁኔታ ለአርሶ አደሮችና ለዘላኖች በግብርና ሥራ ለመተዳደሪያ በቂ የሆነ የይዞታ መብት የሚያስገኝ ፡ ፫ ሴቶች በይዞታ መብታቸው ላይ ሌሎችን ቀጥረው ወይም በሌላ አኳኋን ተስማምተው ሊያሠሩእንደሚችሉ የሚፈቅድ ፣ ፬ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) የተጠቀሰውን መብት ለአካለ መጠን ላልደረሱ ዕጓለ ማውታን ' ለአቅመ ደካሞች እና ለመሳሰሉትም የሚፈቅድ ፣ ለይዞታ ባለመብትነት ብቁ የሚያደርጉ እንደቤተሰብ ኃላፊ ነት ፡ ኣዲስ ጐጆ ወጪነት ያሉ መስፈርቶችን እንዲሁም እንደቤተሰብ : : ኣላት ብዛት ያሉ የመሬት ፍላጉት መጠን ተጨጨባጭ መዘኛዎችን በመከተል የይዞታ መብቱ የሚሰጥ በትን ስፋትና ጥበት በክብደት ደረጃ ቅደም ተከተል የሚወ ለመኖሪያ ቤት መሥሪያ ፣ ለግጦሽ ፣ ለደን ፣ ለማኅበራዊ አገልግ ሎትና ለመሳሰለው የጋራ መጠቀሚያ የሚውል መሬት አከላለል እንደየአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ እና በሕዝብ ተሳትፎ እንደሚወሰን የሚደነግግ ፣ ፯• የይዞታ ሽግሽግ ሲከናወን ሕጋዊ የሆኑ ነባር ባለይዞታዎች በጉልበታቸው ወይም በገንዘባቸው ሲያለሙ ከቆዩት መሬት ውስጥ በተቻለ መጠን ሽግሽጉ የሚፈቀድላቸውን ያህል መሬት በእጃቸው እንዲቆይ ዕድል የሚሰጥ ፣ በይዞታ ሽግሽግ አፈጸጸም የይዞታ መብት በሚለዋወጥበት ጊዜ የቀድሞው ሕጋዊ ባለይዞታ በጉልበቱ ወይም በገንዘቡ ላከናወነው መሬቱን ራሱን የማልማት ሥራ ተገቢውን ካሳ ከአዲሱ ባለይዞታ እንዲያገኝየሚያስችል ፣ ፀ በይዞታ ሽግሽግ ኣፈጻጸም የይዞታ መብት ሲለዋወጥ ወይም በተለያዩ ምክንያቶች ሲቋረጥ በመሬቱ ላይ የተፈራውን ከመሬቱ ሊነጠል የማይችል ቋሚ ንብረት ወይም ሀብት የማንሳት ወይም ለዚሁ የካሳ ክፍያ ወይም አላባ የመጠየቅን መብት የሚያስጠብቅ ፣ ፲ . የይዞታ መብት የሚሰጥበትንና የይዞታ ሽግሽግ የሚከናወንበ ትን ግልጽና ፍትሐዊ የሆነ እንዲሁም አርሶ አደሩን በተለ ይም ሴቶችን የሚያሳትፍ የአፈጸጸም ሥርዓት የሚዘረጋ ፣ ፲፩ . በይዞታ መብት እና በይዞታ ሽግሽግ ጉዳይ ለሚነሱ ቅሬታ ዎች የአፈታት ሥርዓት የሚያበጅ ፡ ፲፪ ከዚህ አዋጅ ጋር የማይቃረኑ ሌሎች አጠቃላይ ወይም እንደየአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ አስፈላጊ ሆነው የሚገኙ የተለዩ ጉዳዮችን የሚደነግግ ይዘት ያለው መሆን አለበት ። ፮ ክልፍ ሦስት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ስለገጠር መሬት ይዞታ ክፍያዎች ፩ . በሕገመንግሥቱ አንቀጽ ፵፯ ንዑስ አንቀጽ ( g እና ( ፬ በተደነገገው መሠረት ፡ የመሬት መጠቀሚያ ክፍያ እና ከደን የሚገኝ የሮያሊቲ ክፍያ መጠን በክልል መስተዳድ ሮች የሚወሰንና የሚሰበሰብ ይሆናል ። ፪ የክልል ምክር ቤቶች በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) . መሠረት የክፍያ መጠን ሲወስኑ ተመጣጣኝነቱን ማረጋገጥ አለባቸው ። ገጽ ፮፻፴፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፬ ሰኔ ፴ቀን ፲፱፻፳፱ ዓም ፰ ስለክልል የመሬት አስተዳደር ሕጎች ተፈጻሚነት የመሬት ኣስተዳደርን በተመለከተ በማንኛውም የክልል ምክር ቤት የወጣ ሕግ ከዚህ አዋጅ ጋር የማይቃረን እስከሆነ ድረስ ተፈጻሚነት ይኖረዋል ። | ከሌሎች ሕጎች ጋር ስላለው ግንኙነት ከዚህ አዋጅ ጋር የሚቃረኑማናቸውንም ነባር ሕጎች በዚህ አዋጅ የተሸፈኑ ጉዳዮችን በተመለከተ ተፈጻሚነት አይኖራቸውም ፡ ፡ ፲ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ ኣዋጅ ካሰኔ ፴ ቀን ፲፱፻ዥ፱ ዓ . ም ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ሰኔ ፴ ቀን ፲፱፻፳፬ ዓ•ም• ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ