የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አሥረኛ ዓመት ቁጥር ፰ አዲስ አበባ - ጥቅምት ፲፯ ቀን ፲፱፻፲፮ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፫፻፸፭ ፲፱፻፲፮ ዓ.ም. የኢንቨስትመንት ( ማሻሻያ አዋጅ ገጽ ፪ ሺ፬፻፴፪ አዋጅ ቁጥር ፪፻፻፭ ፲፱፻፲፮ የኢንቨስትመንት አዋጅን እንደገና ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር ፪፻ ፲፱፻፲፬ን ለማሻሻል የወጣ ኣዋጅ ኢንቨስትመንት የሚመራበትን ሥርዓት ግልጽና ቀልጣፋ እንዲሆን ማድረግ በማስፈለጉ ፤ ለዚህም በሥራ ላይ ያለውን የኢንቨስትመንት ሕግ ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፤ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት እንደሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የኢንቨስትመንት ( ማሻሻያ ) ኣዋጅቁጥር፫፻፸፭ ] 1. Short Title ፲፱፻፲፮ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ : የስያሜ ለውጥ በአዋጅ ቁጥር ፪፻፯ / ፲፱፻፶፬ መሠረት እንደገና የተቋቋመው 1 2 Renaming የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ባለሥልጣን በዚህ አዋጅ የኢት ዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ተብሎ ተሰይሟል ። ፫ . ማሻሻያ የኢንቨስትመንት አዋጅ ቁጥር ፪፻፲ / ፲፱፻፲፬ እንደሚከተለው ተሻሽሏል ፡ ፩ ) የአዋጁ አንቀጽ ፪ ንዑስ አንቀጽ ( ፰ ) እና ( ፱ ) ተሰርዘው በሚከተሉት አዲስ ንዑስ አንቀጽ ( ፰ ) እና ( ፱ ) ተተክ ተዋል ። “ ፰ “ ማስፋፋት ወይም ማሻሻል ” ማለት የነባር ድርጅትን የሙሉ አቅም ምርት ወይም አገል ግሉት ከ፳፭ ተርሰንት በላይ በእሴት ማሳደግ ሲሆን ይህም በዓይነት ወይም ከመጠን ወይም | ` : በሁለቱም መጨመርን የሚያጠቃልል ነው ። ነጋሪትጋዜጣ ፖሣቁ ፱ሺ፩ ያንዱ ዋጋ e ሺ፬፻፴ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፰ ጥቅምት ፲፯ ቀን ፲፱፻፶፮ ዓም “ አግባብ ያለው የኢንቨስትመንት መሥሪያ ቤት ” ማለት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ( ከዚህ በኋላ “ ኮሚሽኑኝወይም የኢንቨስትመንት ፈቃድ ለመስጠት ሥልጣን የተሰጠው የክልል ኢንቨስትመንት አካል ፪ ) በአዋጁ አንቀጽ ፪ ሥር የሚከተለው አዲስ ንዑስ ኣንቀጽ ( ፲፬ ) ተጨምሯል ። “ ፲፬ . “ የቴክኖሎጂ ሽግግር ” ማለት ምርትን ለማምረት ወይም የአመራረት ሂደትን ተግባራዊ ለማድረግ ወይም ለማሻሻል ወይም አገልግሎት ለመስጠት የሚረዳ ሥርዓት ያለው ዕውቀት ማስተላለፍ ሲሆን የማኔጅመ ንትና የግብይት ሁኔታ ቴክኖሎጂንም ይጨምራል ፣ ሆኖም ዕቃዎችን ብቻ ለመሸጥ ወይም ለማከራየት የሚደረግን ግንኙነት አይሸፍንም ። ” ፫ ) በአዋጁ አንቀጽ ፭ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ሥር የሚከተለው አዲስ ፊደል ተራ ( ሐ ) ተጨምሯል ። “ ( ሓ ) ከ፳ በላይ መንገደኞችን የመጫን አቅም ባለው ኤርክራፍት የሚካሄድ የአየር ትራንስፖርት አገል ግሎት ። ” ፬ ) የአዋጁ አንቀጽ ፲፪ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) ተሠርዞ በሚከ ተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) ተተክቷል ። “ ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተደነገገው ቢኖርም ነባር ድርጅትን ገዝቶ ባለበት ሁኔታ ለማካሄድ ወይም የነባር ድርጅትን አክሲዮን ለመግዛት የሚፈልግ የውጭ ባለሀብት ጥያቄውን ለንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በማቅረብ የሚኒስቴሩን ፈቃድ ማግኘት አለበት ። ” ፭ ) በአዋጁ አንቀጽ ፲፪ ሥር የሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) ተጨምሮ የቀደሞው ንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ሆኗል ። “ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በዚህ አንቀጸ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) መሠረት ማመልከቻ ሲቀርብለት ጉዳዩን አግባብ ካለው ሕግ አንፃር በመመርመር በሁለት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ፡ ሀ ) ማመልከቻውን ከተቀበለው ተገቢውን ክፍያ በማ ስከፈል የአክሲዮን ዝውውሩን ይመዘግባል ወይም የንግድ ሥራ ፈቃዱን ይተካል ፣ ወይም ለ ) ማመልከቻውን ካልተቀበለው ያልተቀበለበትን ምክንያት ለባለሀብቱ በጽሁፍ ያሳውቃል ” ፮ ) የአዋጁ አንቀጽ ( ፲፫ ) ተሰርዞ በሚከተለው አዲስ አንቀጸ ፲፫ ፡ ፲፬ እና ፲፭ ተተክቷል ። በዚህም መሠረት ከ፲፬ - ፴፰ ያሉት የአዋጁ አንቀጾች እንደ ቅደም ተከተላቸው ከ፲፮ ፵ ሆነው ተስተካክለዋል ። “ ፲ በአገር ውስጥ ባለሀብት ስለሚቀርብ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ጥያቄ ፩ ማንኛውም የአገር ውስጥ ባለሀብት የኢንቨስትመንት ፈቃድ ለማግኘት ለዚሁ ተግባር የተዘጋጀውን የማመ ልከቻ ቅጽ በመሙላት ከሚከተሉት ሠነዶች ጋር ማቅረብ አለበት ፡ ሀ ) ማመልከቻው የተፈረመው በወኪል ከሆነ የውክልና ሥልጣን ማረጋገጫ ሠነድ ፎቶ ኮፒ ፣ ለ ) ኢንቨስትመንቱ የሚካሄደው በግለሰብ ከሆነ የባለ ሀብቱ የመታወቂያ ካርድ ፎቶ ኮፒ ፣ ወይም የሀገር ውስጥ ባለሀብትነት ሰርተፊኬት ፎቶኮፒእና ሁለት የቅርብ ጊዜ ጉርድ ፎቶግራፎች ፤ ገጽ ፪ሺ፬፻፴፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፰ ጥቅምት ፲፯ ቀን ፲፱፻፲፮ ዓ.ም. ሐ ) ኢንቨስትመንቱ የሚካሄደው በንግድ ማህበር ከሆኒየማህበሩ የመመስረቻ ጽሁፍና የመተዳደሪያ ደንብ ፎቶ ኮፒ ወይም ማኅበሩ ኣዲስ የሚቋቋም ከሆነ ከዚህ በተጨማሪ የማህበርተኞቹ የመታ ወቂያ ካርድ ፎቶ ኮፒ ወይም የሀገር ውስጥ ባለሀብትነት ሰርተፊኬት ፎቶ ኮፒ መ ) ኢንቨስትመንቱ የሚካሄደው በመንግሥት የልማት ድርጅት ከሆነ ድርጅቱ የተቋቋመበት ደንብ ፎቶ ኮፒ ወይም የመመስረቻ ጽሁፍና የመተዳደሪያ ደንብ ፎቶ ኮፒ እና ሠ ) ኢንቨስትመንቱ የሚካሄደው በኅብረት ሥራ ማኅበር ከሆነ የማህበሩ የመተዳደሪያ ደንብ ፎቶ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከቱት የማመ ልከቻ ቅጽ እና ሠነዶች ፤ ሀ ) ለኮሚሽኑ የሚቀርቡ ከሆነ በሁለት ቅጂ ፡ ወይም ለ ) ለክልል የኢንቨስትመንት አካላት የሚቀርቡ ከሆነ በአንድ ቅጂ ፡ መቅረብ አለባቸው ። ” 10 • በውጭ ባለሀብት ስለሚቀርብ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ማንኛውም የውጭ ባለሀብት ኣዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ለማግኘት ለዚሁ ተግባር የተዘጋጀውን የማመ ልከቻ ቅጽ በመሙላት ከሚከተሉት ሠነዶች ጋር በሁለት ቅጂ ለኮሚሽኑ ማቅረብ አለበት ፣ ሀ ) ማመልከቻው የተፈረመው የውክልና ሥልጣን ማረጋገጫ ሠነድ ፎቶ ኮፒ ፣ ለ ) ኢንቨስትመንቱ የሚካሄደው በግለሰብ ከሆነ የባለ ሀብቱን ማንነት የሚያሳዩ የፀና ፓስፖርት ገጾች ፎቶ ኮፒ እና ሁለት የቅርብ ጊዜ ጉርድ ፎቶግ ሐ ) ኢንቨስትመንቱ የሚካሄደው ኢትዮጵያ ውስጥ በተቋቋመ የንግድ ማህበር ከሆነ የማህበሩ የመመ ስረቻ ጽሁፍና የመተዳደሪያ ደንብ ፎቶ ኮፒ ፣ ወይም ማህበሩ አዲስ የሚቋቋም ከሆነ ከዚህ በቶጨማሪ የእያንዳንዱን የማህበሩን አባላት ማንነት የሚያሳይ የፀና ፓስፖርት ገጾች ፎቶ ኮፒ ፣ መ ) ኢንቨስትመንቱ የሚካሄደው በተቋቋመ የንግድ ማኅበር የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ከሆነ የማኅበሩ የመመስረቻ ጽሁፍ እና የመተዳ ደሪያ ደንብ ወይም የዚሁ ተመሳሳይ ሰነድ ፎቶ ኮፒ ፡ እና ሠ ) ኢንቨስትመንቱ የሚካሄደው በአገር ውስጥና በውጭ ባለሀብት ቅንጅት ከሆነ ከላይ በፊደል ተራ “ ሐ ” ከተገለጹት ሰነዶች በተጨማሪ እንደ አግባቡ የአገር ውስጥ ባለሀብቱ የመታወቂያ ካርድ ፎቶ ኮፒ ወይም የአገር ውስጥ ባለሀብትነት ሰርተፊኬት ፎቶ ኮፒ ። ” “ ፲፭ ለማስፋፋት ወይም ለማሻሻል ስለሚቀርብ የኢንቨስት መንት ፈቃድ ጥያቄ ማንኛውም ባለሀብት የማስፋፋት ወይም የማሻሻል የኢንቨስትመንት ፈቃድ ለማግኘት ለዚሁ ተግባር የተዘጋጀውን የማመልከቻ ቅጽ በመሙላት ከሚከ ተሉት ሠነዶች ጋር ማቅረብ አለበት ፤ ሀ ) የማመልከቻ ቅጹ የተፈረመው በወኪል ከሆነ የውክልና ሥልጣን ማረጋገጫ ሠነድ ፎቶ ኮፒ ፤ ለ ) ኢንቨስትመንቱ የሚካሄደው ማኅበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሁፍእና የመተ ዳደሪያ ደንብ ፎቶ ኮፒ ' እና ሐ ) የነባር ድርጅቱ የፀና የንግድ ሥራ ፈቃድ ፎቶ ኮፒ ። ገጽ ፪ሺ፱፻፴፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፰ ጥቅምት፲፯ ቀን ፲፱፻፶፮ ዓም ፪ ) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከቱት የማመ ልከቻ ቅጽ እና ሰነዶች ፤ ሀ ) ለኮሚሽኑ የሚቀርቡ ክሆነ በሁለት ቅጂ ፡ ወይም ለ ) ለክልል ኢንቨስትመንት አካላት የሚቀርቡ ከሆነ በኣንድ ቅጂ ፡ መቅረብ አለባቸው ። ” ፯ ) የአዋጁ አንቀጽ ፲፬ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ተሠርዞ በሚከ ተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ተተክቷል ። እንዲሁም በአንቀጹ ሥር የሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) ተጨምሮ ከንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) እስከ ( ፩ ) ያሉት እንደ ቅደም ተከተላቸው ከ ) እስከ ( ፮ ) ሆነው ተስተካክ “ ፩ አግባብ ያለው የኢንቨስትመንት መሥሪያ ቤት የኢንቨስትመንት ፈቃድ ማመልከቻው በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፫ ፥ ፲፫ ወይም ፲፭ መሠረት ተሟልቶ ክቀረበለት በባለሀብቱ ሊካሄድ የተቃ ደውን የኢንቨስትመንት ሥራ ክዚህ አዋጅና ኣዋጁን ለማስፈቦም ከሚወጡ ደንቦችና መመሪ ያዎች አንፃር በመመርመር በአምስት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ፤ ሀ ) ማመልከቻውን ከተቀበለው ተገቢውን ክፍያ በማስከፈል ለባለሀብቱ የኢንቨስት መንት ፈቃድ ይሰጣል ፤ ወይም ለ ) ማመልከቻውን ካልተቀበለው ያልተቀበለ ምክንያት ለባለሀብቱ ያሳውቃል ። ፪ ) አግባብ ያለው የኢንቨስትመንት መሥሪያ ቤት የኢንቨስትመንት ፈቃዱን ከሰጠ በኋላ ለአስፈ ላጊው ክትትል ለሚመለከታቸው የሴክተር መሥሪያ ቤቶች በደብዳቤ ያሳውቃል ። ” ፰ ) በአዋጁ አንቀጽ ፲፮ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) ሥር የሚከተለው አዲስ ፊደል ተራ ( ሠ ) ተጨምሯል ። “ ሠ • ባለሀብቱ የንግድ ሥራ ፈቃድ ሳያወጣ በንግድ ሥራ ላይ ተሰማርቶ የተገኘ እንደሆነ ። ” ፱ ) የአዋጁ አንቀጽ ፲፰ ተሠርዞ በሚከተለው አዲስ አንቀጽ ፳ ተተክቷል ። “ ፳ ስለ ቴክኖሎጂ ሽግግር ስምምነት ፩ ) ማንኛውም ባለሀብት ከኢንቨስትመንቱ ጋር በተያያዘ ሁኔታ የቴክኖሎጂ ገግር ስምምነት በሚዋዋልበት ስምምነቱን ለኮሚሽኑ በማቅረብ ማስፈቀድና ማስመዝገብ አለበት ። ፪ ) ኮሚሽኑ ከላይ በንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት የ ምዝገባ ማመልከቻ በቀረበለት በሁለት የሥራ ቀን ውስጥ የምዝገባ ማስረጃውን ለባለሀብቱ ይሰጣል ። ፫ ) በዚህ አንቀጽ መሠረት በኮሚሽኑ ያልተመዘገበ የቴክኖሎጂ ሽግግር ስምምነት ሕጋዊ ውጤት አይኖረውም ። ” የአዋጁ አንቀጽ ፳፪ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ፊደል ተራ ( ለ ) ተሰርዞ በሚከተለው አዲስ ፊደል ተራ ( ለ ) ተተክቷል ። “ ላ ) መደበኛ ነዋሪነቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ሆኖ እንደአገር ውስጥ ባለሀብት በተቆጠረ የውጭ አገር ዜጋ የሚደረግ ኢንቨስትመንት ” ፲፩ ) በአዋጁ አንቀጽ ፳፪ ሥር የሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) ተጨምሮ የቀድሞው ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) እና ( ፫ ) እንደቅደም ተከተላቸው ንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) እና ( ፱ ) ሆነዋል ። እንዲሁም የአንቀጹ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) ተሰርዟል ። ውናሉ ። ” ገጽ ፪ሺ፬፻፮ ፌዴራል ነጋት ጋዜጣ ቁጥርቼ ጥቅምት ፲፮ ቀን በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከተው ቢኖርም በአየር ትራንስፖርት አገልግሎትና በኤ ሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት ወይም ማስተላለፍ ወይም ማከፋፈል ሥራ ለሚሠማራ ባለህብት የኢንቨስትመንት ፈቃድ የመስጠት ፤ የማደስና የመሰረዝ ሥራን እንደቅድም ተከተላቸው የኢት ዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣንና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኤጀንሲ ኮሚሽኑን በመወከል ያከና ፲፪ ) የአዋጁ አንቀጽ ፳፬ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እና ( ፱ ) ተሰርዘው በሚከተሉት አዲስ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እና ( ፱ ) ተተክ ተዋል ። “ ፩ ኮሚሽኑ ወይም የክልል ኢንቨስትመንት አካላት የኢንቨስትመንት ፈቃድ ለሰጡኣቸው ባለሀ ብቶች አግባብ ባላቸው ህጎች መሠረት የሚከተ ሉትን ኣገልግሎቶች እንደ ኣግባቡ የሚመለከታ ቸውን የፌዴራል መንግሥት ወይም የክልል አስፈፃሚ አካላትን በመወከል ይሰጣሉ ፤ ሀ ) የመመስረቻ ጽሁፍና የመተዳደሪያ ደንብ ማዋዋል ፤ ለ ) የንግድ ምዝገባ መፈፀም ፤ ሐ ) ለውጭ ዜጋ ተቀጣሪዎች የሥራ ፈቃድ መስጠት ፤ መ ) ለኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ደረጃ መስጠት ፡ እና ሠ ) የንግድ ሥራ ፈቃድ መስጠት ። ” “ ፬ ) አግባብ ያለው የኢንቨስትመንት መሥሪያ ቤት በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ፊደል ተራ ( ሠ ) መሠረት የንግድ ሥራ ፈቃድ ማመልከቻ ሲቀር ብለት ጉዳዩን አግባብ ካለው ሕግ አንፃር በመመ ርመር በአምስት የሥራ ቀን ውስጥ ፤ ሀ ) ማመልከቻውን ከተቀበለው ተገቢውን ክፍያ በማስከፈል የንግድ ሥራ ፈቃዱን ይሰጣል ፤ ወይም ለ ) ማመልከቻውን ካልተቀበለው ያልተቀበለ በትን ምክንያት ለባለሀብቱ ያሳውቃል ። ” ፲፫ ) በአዋጁ አንቀጽ ፳፬ ሥር የሚከተሉት አዲስ ንዑስ አንቀጽ ( ፭ ) ፡ ( ፩ ) ፡ ( ፯ ) እና ( ፰ ) ተጨምረዋል ። “ ፭ ) በንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር ፳፯ ፲፱፻፳፬ አንቀጽ ፳፪ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) ፊደል ተራ ( ሀ ) የተመለከተው ቢኖርም አግባብ ያለው የኢንቨስትመንት መሥሪያ ቤት ባለሀብቱ አግባ ብነት ያላቸውን የአገሪቱን ሕጎችና መመሪያዎች ጠብቆ ለመሥራት ግዴታ እንዲገባ በማድረግ የንግድ ሥራ ፈቃድ ይሰጣል ። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተደነገገው ቢኖርም ኮሚሽኑ የንግድ ሥራ ፈቃድ የሚሰጠው የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴርን በመወከል ብቻ ይሆናል ። ፯ ) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተደነገገው ቢኖርም ከተጠቀሱት ሠነዶች ጋር በተያያዘ የሚደረጉ ማሻሻያዎችን የማዋዋል ፡ የማደስ ፡ የመተካት ወይም የመሠረዝ ሥራ የሚከናወነው አግባብ ባላቸው የፌዴራሉ መንግሥት ወይም የክልል አስፈፃሚ አካላት ነው ። ፰ ) ኣግባብ ያለው የኢንቨስትመንት መሥሪያ ቤት በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከቱትን አገልግሎቶች ከሰጠ በኋላ ለኣስፈላጊው ክትትል አግባብ ላለው የሴክተር መሥሪያ ቤት በደብዳቤ ያሳውቃል ። ” ገጽ ፪ሺ፱፻፴፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፰ ጥቅምት ፲፯ ቀን ፲፱፻፲፮ ዓ.ም. ፲፬ ) የአዋጁ አንቀጽ ፬ ተራ ቁጥር ( ፱ ) ተሰርዞ በሚከተለው ኣዲስ ተራ ቁጥር ( ፱ ) ተተክቷል ። “ ፱ ከኢንቨስትመንት ጋር የተያያዙ የቴክኖሎጂ ሽግግር ስምምነቶችን በመፍቀድ ይመዘግባል ፡ ” ፲፭ ) የአዋጁ አንቀጽ ፴፩ ተሰርዞ በሚከተለው አዲስ አንቀጽ ፬ ተተክቷል “ ፴ / የኮሚሽኑ አቋም ኮሚሽኑ ፡ ሀ ) በመንግሥት የሚሾም ኮሚሽነር ፡ እና ለ ) ኣስፈላጊ ሠራተኞች ይኖሩታል ። ” በጌ ) የአዋጁ አንቀጽ ፴፯ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) ተሰርዞ በሚከ ተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) ተተክቷል ። “ . እንደ አገር ውስጥ ባለሀብት መቆጠር የፈለገ መደበኛ ነዋሪነቱ ኢትዮጵያ ውስጥ የሆነ የውጭ አገር ዜጋ ለዚሁ ተግባር የተዘጋጀውን የማመ ልከቻ ቅጽ በመሙላት ከሚከተሉት ሰነዶች ጋር አያይዞ ለኮሚሽኑ ማቅረብ ይኖርበታል : ሀ ) ማመልከቻው የተፈረመው የውክልና ሥልጣን ማረጋገጫ ሰነድ ፎቶ ኮፒ ፣ ለ ) የፀና የንግድ ሥራ ፈቃድ ፎቶ ኮፒ ፤ ሐ ) የዋና ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ ፣ መ ) የዐና የመኖሪያ ፈቃድ ፎቶ ኮፒ ፣ ሠ ) የንግድ ሥራ ፈቃዱ የማኅበር ከሆነ የመመስረቻ ጸሁፍና የመተዳደሪያ ደንብ ፎቶ ኮፒ ፣ ረ ) አመልካቹ እንደአገር ውስጥ ባለሀብት ለሚቆጠር መደበኛ ነዋሪነቱ ኢትዮጵያ ውስጥ የሆነ የውጭ አገር ዜጋ ጥገኛ ወይም ወራሽ ከሆነ አስጠጊው ወይም አውራሹ እንደአገር ውስጥ ባለሀብት የሚቆጠር ስለመሆኑ ከላይ ከተጠቀሱት ሰነዶች በተጨማሪ የጥገኛው የፀና የመኖሪያ ፈቃድ ፎቶ ኮፒ ፡ ወይም አመልካቹ ወራሽ ለመሆኑ በፍ / ቤት የተሰጠ ውሣኔ ፎቶ ኮፒ ፣ ሰ ) የአመልካቹ ሦስት የቅርብ ጊዜ ጉርድ ፎቶግ ራፎች ። ” ፲ጊ ) በአዋጁ የሚከተለው አዲስ አንቀጽ ፩ ተጨምሮ ከ፴፬ ፴፪ ያሉት የኣዋጁ አንቀጾች እንደቅደም ተከተላቸው ከአንቀጽ ፵፪ - ፵፭ ሆነው ተስተካክለዋል ። “ ፵፩ ለኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣንና ለኢ ትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኤጀንሲ ስለተሰጠ ውክልና የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣንና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኤጀንሲ ፡ ሀ ) - በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፳፭ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) መሠረት በውክልና የተሰጣቸውን ተግባር የሚያከ ናውኑት በዚህ አዋጅና አዋጁን ለማስፈፀም በሚወጡ ደንቦችና መመሪያዎች መሠረት ይሆናል ። ለ ) በተሰጣቸው የውክልና ሥልጣን መሠረት የሰጧ ቸውን የኢንቨስትመንት ፈቃድ ኮፒ እና አግባብ ያላቸውን ሰነዶች ፎቶ ኮፒ ለኮሚሽኑ ያስተላ ልፋሉ ። ” ገጽ ፪ሺ፬፻፴፰ ዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፰ ጥቅምት ፲፯ ቀን ፲፱፻ ዓ • ም • ፬ • ደንብ የማውጣት ሥልጣን በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፫ ' ፲፬ ' ፲፭ እና ፴፯ የተጠቀሱትን ሰነዶች ዝርዝር የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ ሊያሻሽል ይችላል ። ፭ የተሻረ ሕግ የቴክኖሎጂ ሽግግር የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፻፳፩ / ፲፬፻፵፭ በዚህ አዋጅ ተሽሯል ። ፮ : ኣዋጁ የሚፀናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከጥቅምት ፲፯ ቀን ፲፱፻፲፮ ዓም ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ጥቅምት ፲፯ ቀን ፲፱፻፲፮ ዓ.ም ግርማ ወልደጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት