×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፩/፲፱፻፲፮ ዓም የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የውጭ ዜጐች በትውልድ አገራቸው የተለያዩ መብቶች ተጠቃሚ ለማድረግ የወጣ ደንብ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አሥረኛ ዓመት ቁጥር ፴፬ አዲስ አበባ -መጋቢት ፲፪ ቀን ፲፱፻፶፮ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፩ / ፲፱፻፲፮ ዓም የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የውጭ ዜጐች በትውልድ አገራቸው የተለያዩ መብቶች ተጠቃሚ ለማድረግ የወጣ ገጽ ፪ሺ፭፻፲፭ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፩ / ፲፱፻፲፮ የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የውጭ ዜጐችን በትውልድ ሀገራቸው የተለያዩ መብቶች ተጠቃሚ ለማድረግ የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፷፯ አንቀጽ ፭ እና የኢትዮጵያ | No . 4/1995 and Article 17 of Providing Foreign Nationals of ተወላጅ የሆኑ የውጭ ዜጐችን በትውልድ ሀገራቸው የተለያዩ | Ethiopian Origin with certain Rights and Privileges to be መብቶች ተጠቃሚ ለማድረግ በወጣው አዋጅ ቁጥር ፪፻፪ / ፲፱፻፶፬ | Exercised in their Country of Origin Proclamation No. 270 / አንቀጽ ፲፯ በተደነገገው መሠረት ይህንን ደንብ አውጥቷል ። ክፍል አንድ አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የውጭ ዜጐችን በትውልድ ሀገራቸው የተለያዩ መብቶች ተጠቃሚ ለማድረግ የወጣ ደንብ ቁጥር ፩፻፩ / ፲፱፻፶፮ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር | 2. Definition በዚህ ደንብ ውስጥ ፣ ፩ . “ አዋጅ ” ማለት የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የውጭ ዜጐች በትውልድ አገራቸው የተለያዩ መብቶች ተጠቃሚ ለማድረግ የወጣ አዋጅ ቁጥር ፪፻፪ / ፲፱፻፲፬ ፪ “ የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆነ የውጭ ዜጋ ” ማለት በአዋጁ አንቀጽ ፪ ( ፩ ) የተሰጠውን ትርጓሜ የሚያሟላ ሰውማለት ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ • ፳፩ ገጽ ፪ሺ፭፻፵፮ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፬ መጋቢት ፲፪ቀን ፲፱፻፰ ዓም Federal Negarit Gazeta No.34 21 March , 2004 – Page 2596 ፫ “ የኢትዮጵያ ሚስዮን ” ማለት የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፣ ቋሚ መልዕክተኛ ጽሕፈት ቤት ወይም ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ማለት ነው ። ፬ “ ሚኒስቴር ” ማለት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማለት ነው ። ፭ “ ባለሥልጣን ” ማለት የደህንነት ፣ የኢሚግሬሽንና የስደተኞች ጉዳይ ባለሥልጣን ማለት ነው ። ፮ : በዚህ ደንብ በወንድ ጾታ የተደነገገው የሴትንም ጾታ ያካትታል ። ክፍል ሁለት የኢትዮጵያ ተወላጅየሆኑ የውጭ ዜጐች የመታወቂያ ካርድ ፫ • የመታወቂያው ካርድ አሰጣጥ ሁኔታ በዚህ ደንብ መሠረት ለኢትዮጵያ ተወላጅ ለሆነ የውጭ ዜጋ የመታወቂያ ካርድ የሚሰጠው በአዋጁ የተጠቀ ሱትን ድንጋጌዎች የሚያሟላ እና ከዚህ በታች በተጠ ቀሰው ሥርዓት መሠረት ማመልከቻ ላቀረበ ሰው ይሆናል ። ፪ የመታወቂያ ካርዱን ለማውጣትማመልከቻ የሚቀርበው በሀገር ውስጥ ለባለሥልጣኑ ሲሆን ከሀገር ውጪ ደግሞ በውጭ በሚገኙ የኢትዮጵያ ሚስዮኖች አማካይነት ለሚኒስቴሩ ይሆናል ። ፫ ማመልከቻው ለዚሁ ዓላማ በሚኒስቴሩ በተዘጋጀ ቅጽ ተሞልቶና ከሚከተሉት ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖር በታል ። ሀ ) በቅርብ ጊዜ የተነሳና ሙሉ ፊትን የሚያሳይ ፎቶግራፍ ፣ ለ ማመልከቻ አቅራቢው የኢትዮጵያ ተወላጅ መሆኑን የሚያረጋግጡ የሰነድ ማስረጃዎች ፣ ሐ ) ዜግነት ካገኘበት አገር አግባብ ካለው አካል የተሰጠ የፀና ፖስፖርት ወይም ሌላ የጉዞ ሰነድ ፣ መ ) እንደአግባብነቱ የጋብቻ ማረጋገጫ ሰነድና አሥራ ስምንት ዓመት ያልሞላቸውን ልጆቹን የልደት የምስክር ወረቀት ፣ ፬ . ሚኒስቴር ወይም ባለሥልጣኑ በዚህ አንቀጽ መሠረት ማመልከቻ ከቀረበበት ጊዜ አንስቶ በ፴ ቀናት ውስጥ የመታወቂያ ካርዱ ለአመልካቹ ሊሰጠው እንደሚገባ ወይም እንደማይገባ መወሰን ይኖርበታል ። የመታወቂያ ካርዱ እንዳይሰጥ የሚወሰን ቢሆን ምክንያቱ ለአመልካቹ በጽሑፍ ሊገለጽ ይገባል ። መታወቂያ ካርዱ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ፩ . በአዋጁ አንቀጽ ፰ መሠረት የተሰጠ መታወቂያ ካርድ ከተሰጠበት ጊዜ አንስቶ በየአምስት ዓመቱ የሚታደስ ይሆናል ። ፪ የመታወቂያ ካርዱ ዕድሳት በሀገር ውስጥ ሲሆን በባለሥ ልጣኑ ፣ ከሀገር ውጭ ሲሆን በኢትዮጵያ ሚስዮኖች ሊከናወን ይችላል ። ፫ • የመታወቂያ ካርዱ ከመታደሱ በፊት በአዋጁ አንቀጽ ፲፬ መሠረት መታወቂያ ካርዱን ሊያሰርዙ የሚችሉ ምክን ያቶች አለመኖራቸው መረጋገጥ አለበት ። ስለ አገልግሎት ክፍያዎች ፩ . በአዋጁ አንቀጽ ፰ መሠረት የሚሰጠውን መታወቂያ ለማግኘት አመልካቹ ፭፻ የአሜሪካን ዶላር አምስት መቶ የአሜሪካን ዶላር ወይም የሚኖርበት አገር ተመጣጣኝ የሆነ ገንዘብ ወይም በአገር ውስጥ ሲሆን በወቅቱ የምንዛሪ ዋጋ መሠረት ተመጣጣኝ የሆነ የኢትዮጵያ ብር የአገልግሎት ክፍያ ይከፍላል ። በዚህ ደንብ አንቀጽ ፬ መሠረት መታወቂያ ለማሳደስ የሚከፈለው ፪፻ የአሜሪካን ዶላር / ሁለት መቶ የአሜ ሪካን ዶላር ወይም የሚኖርበት አገር ተመጣጣኝ የሆነ ገንዘብ ወይም በአገር ውስጥ ሲሆን በወቅቱ የምንዛሪ ዋጋ መሠረት ተመጣጣኝ የሆነ የኢትዮጵያ ብር ይሆናል ። ገጽ ፪ሺ፭፻፲፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፬ መጋቢት ፲፪ ቀን ፲፱፻፲፮ ዓም መታወቂያው የጠፋ ከሆነ መጥፋቱ በአካባቢው ፖሊስ ሲረጋገጥ ወይም የተበላሸ መታወቂያ ለመተካት ፫፻ የአሜሪካን ዶላር / ሦስት መቶ የአሜሪካን ዶላር ወይም የሚኖርበት አገር ተመጣጣኝ የሆነ ገንዘብ ወይም በአገር ውስጥ ሲሆን በወቅቱ የምንዛሪ ዋጋ መሠረት ተመጣጣኝ የሆነ የኢትዮጵያ ብር በመክፈል ሌላ መታወቂያ ካርድ ሊሰጥ ይችላል ። ፮ የመታወቂያ ካርዱ መያዝ ያለባቸው መረጃዎች ፩ የመታወቂያ ካርዱን የያዘው ሰው ሙሉ ስም ከነአያቱ ፣ የተወለደበት ቦታና ቀን ፣ ፆታ ፣ ዜግነትናልዩ ምልክቶች ፣ ፪ መታወቂያ ካርዱን የያዘው ሰው በአዋጁ የተጠቀሱት መብቶችና ግዴታዎች እንደሚመለከቱት ፤ መታወቂያ ካርዱ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ፤ ፬ . መታወቂያ ካርዱን የሰጠው ባለሥልጣን ፣ የተሰጠበት ቦታና ቀን ፤ ፭ መታወቂያ ካርዱ ከኢትዮጵያዊ ተወላጅ የውጭ ዜጋ ጋር በተፈጠረ የጋብቻ ግንኙነት የተሰጠ ከሆነ ይኸው በግልጽ መመልከት ይኖርበታል ። ክፍል ሦስት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ፯ መመሪያ የማውጣት ሥልጣን ሚኒስቴሩ ይህን ደንብ ለማስፈጸም ዝርዝር መመሪያ ለማውጣት ይችላል ። ተፈጻሚ ስለማይሆኑ ሕጐች ይህንን ደንብ የሚቃረኑ ደንቦች ፣ መመሪያዎች ፣ ውሳኔዎች ወይም አሰራሮች ይህን ደንብ በተመለከተ ተፈጻሚነት | 8. Inapplicable Laws አይኖራቸውም ። ፱ . የመተባበር ግዴታ ማንኛውም ጉዳዩ የሚመለከተው መሥሪያ ለዚህ ደንብ ተግባራዊነት የመተባበር ግዴታ አለበት ። ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ ይህ ደንብ በነጋሪት ጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ተፈጻሚ ይሆናል ። አዲስ አበባ መጋቢት ፲፪ ቀን ፲፱፻፲፮ ዓም መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?