×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
አዋጅ ቁጥር ፫፻፳፯ ፲፱፻፲፭ የፌዴራል ኣገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን እንደገና ለማቋቋም የወጣ አዋጅ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ዘጠነኛ ዓመት ቁጥር ፲፪ አዲስ አበባ ጳጉሜ ፮ ቀን ፲፱፻፲፭ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፫፻፳፯ / ፲፱፻፶፭ ዓም የፌዴራል አገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣንን እንደገና ለማቋቋም የወጣ አዋጅ ገጽ ፪ሺ፫፻፳፩ አዋጅ ቁጥር ፫፻፳፯ / ፲፱፻፶፭ የፌዴራል መንግሥት አገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣንን እንደገና ለማቋቋም የወጣ አዋጅ በሕገ መንግሥቱ እና በሌሎች የታክስ ሕጐች በፌዴራሉ መንግሥት እንዲሰበሰቡ የተወሰኑ የታክስ / ገቢዎች ምንጫቸውም ሆነ ሥርጭታቸው በሁሉም የአገሪቱ ክልሎች የሚገኙ በመሆኑና | other Tax Laws , for collections by the Federal Government የነዚህ ገቢዎች አሰባሰብ በብቃት መከናወን ያለበት በመሆኑ ፣ በገቢ ባለሥልጣኑ የሚከናወነው ተግባርና የተለየ የሥራ ባህሪይ የሚጠይቀውን ከሙስና ምዝበራና ጉቦኝነት የፀዱና በከፍተኛ ዲሲፕሊንና ሥነ ምግባር የሚመሩበት የሠራተኞች | zlement and birbery and guided by high standard discipline , አስተዳደር ሥርዓት ለመዘርጋት እንዲቻል ፣ ይህን ኃላፊነት በብቃትእንዲወጣ የተሟላ ድርጅታዊ አቋም ፣ የሰለጠነ የሰው ኃይል ፣ በዘመናዊ የመረጃ ቴክኖሎጂ የሚታገዝ | responsibilities , with well equipped organizational setup ቀልጣፋ የአሰራር ሥርዓት እንዲኖረው ለማስቻል የፌዴራል አገር | trained manpower and efficient working systems supported ውስጥ ገቢ ባለሥልጣንን እንደገና ማቋቋም በማስፈለጉ ፣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፵፭ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው | of the Constitution of the Federal Democratic Republic of ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የፌዴራል አገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣንን እንደገና ለማቋቋም የወጣ አዋጅ ቁጥር ፫፻፳፯ / ፲፱፻፲፭ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ በዚህ አዋጅ ውስጥ ፣ ፩ ) “ ሰው ” ማለት ማናቸውም የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው ። ፪ ) “ የታክስ ሕግ ” ማለት በገቢና ወጪ ዕቃዎች ላይ ከሚጣለው የጉምሩክ ቀረጥ በስተቀር በፌዴራሉ መንግሥት እንዲሰበሰብ ስለተመደበው ማናቸውም ታክስ ወይም ቀረጥ የሚደነግግ ሕግ ነው ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፰ሺ፩ ገጽ ፪ሺ፫፻፳፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፪ ጳጉሜ ፮ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓም : ፫ ) “ ታክስ ግብር መወሰን ” ማለት አግባብ ባለው ሕግ መሠረት ከአንድ ታክስ / ግብር ከፋይ የሚፈለገውን የታክስ ግብር መጠን ታክስ / ግብር ከፋዩ ያቀረበውን የታክስ / የገቢ ማስታወቂያና የያዛቸውን የሂሣብ መዝገ ቦችና መግለጫዎች መሠረት በማድረግ መተመን ወይም ሕግ የሚፈቅድ ሲሆን በግምት መተመን ነው ፣ ፬ ) “ ሚኒስትር ” እና “ ሚኒስቴር ” ማለት የገቢዎች ሚኒስትር እና የገቢዎች ሚኒስቴር ናቸው፡ ፫ • መቋቋም ፩ ) የፌዴራል አገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን ( ከዚህ በኋላ ባለሥልጣን እየተባለ የሚጠራው ) የሕግ ሰውነት ያለው ራሱን የቻለ የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤት ሆኖ በዚህ አዋጅ እንደገና ተቋቁሟል ። ፪ ) የባለሥልጣኑ ተጠሪነት ለሚኒስትሩ ይሆናል ። ዋና መሥሪያ ቤት የባለሥልጣኑ ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ ሆኖ እንደ አስፈላጊነቱ በሌሎች ሥፍራዎች ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች ሊኖሩት ይችላል ። ፭ ዓላማዎች ባለሥልጣኑ የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል ፣ ፩ ) የታክስ ግብር ሕጐችን ፣ ደንቦቸንና ፣ መመሪያዎችን ማስ ከበርና ማስፈጸም ፣ ፪ ) በሕግ ተለይተው በፌዴራሉ መንግሥት እንዲሰበሰቡ የተመደቡ ታክሶች ግብሮች መወሰን ፣ መሰብሰብና ማስፈፀም ። ፮ . የባለሥልጣኑ ሥልጣንና ተግባር ባለሥልጣኑ የሚከተሉት ሥልጣኖችና ተግባሮች ይኖሩታል ፣ ፩ ) በሕግ ተለይተው በፌዴራሉ መንግሥት እንዲሰበሰቡ የተመደቡ የግብር ገቢዎችን ይወስናል ፣ ይሰበሰባል ፣ ያስፈጽማል ፤ ፪ ) ለግብር አወሳሰን የሚያስፈልጉ መረጃዎችን ይሰበስባል ፣ ያጠናክራል እንደአስፈላጊነቱም ለገቢ ሰብሳቢ አካላት ያሰራጫል ፤ ፫ ) የግብር ሕጎችን ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ በማናቸውም ሰው እጅ የሚገኙ ሰነዶችን ይመረምራል ፣ ፬ ) የግብር አወሳሰን ፣ አሰባሰብ ፣ ሂሳብ አያያዝ እና ሌሎች ተጓዳኝ ሥራዎችን ለማከናወን የሚያስችሉ የአሠራር ዘዴዎችንና ሥልቶችን ይቀይሳል ፣ ተግባራዊነታቸውንም ያረጋግጣል ፣ ፭ ) ግብር ከፋዮች መብትና ግዴታቸውን እንዲወጡ የሚያ ስችሉ ግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሞች ተግባራዊ ያደርጋል ፣ ፮ ) የግብር ሕጎችን ደንቦችንና መመሪያዎችን አፈጻጸም ለማሻሻል የሚረዱ ጥናቶችን በማካሂድ ለሚኒስትሩ ያቀርባል ፣ ፯ ) የግብር ሕጎችን በመጣስ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን በፖሊስ እንዲጣሩ ያደርጋል ፣ ዓቃቤ ሕጎች እንዲሾሙለት ወይም የአቃቤ ሕጎች ሥልጣን በውክልና እንዲሰጠው በማድረግ የወንጀል ክሶችን ይመሰርታል ፣ ይከታተላል ፣ ፰ ) አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የግብር አወሳሰን ፣ አሰባሰብና አፈጸጸም ሥልጣኑን በሙሉ ወይም በከፊል ለክልል መስተዳድሮች ገቢ ሰብሳቢ አካላት በውክልና ሊሰጥ ይችላል ፣ ለአፈጸጸሙ ተገቢውን ምክርና ድጋፍ ያደርጋል ፣ ፱ ) ለግብር አስተዳደር ብቃት ያላቸውን ባለሙያዎች ለማፍራት የሚያስችለውን ሥልጠናና የሙያ ማሻሻያ ዘዴዎችንና ሌሎች ስልቶች ይዘረጋል ፣ ፲ ) የንብረት ባለቤት የመሆን ፣ ውል የመዋዋል ፣ በስሙ የመከሰስና የመክሰስ ፣ ፲፩ ) ዓላማዎቹን ከግብ ለማድረስ አስፈላጊ የሆኑ ሌሎች ተግባሮችን ያከናውናል ። ገጽ ፪ሺ፫፻፳፫ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፪ ጳጉሜ፮ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓ.ም. ፮ . የባለሥልጣኑ አቋም ፩ ) ባለሥልጣኑ ፣ ( ሀ ) ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ ( ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጆች ፣ ( ሐ ) ለሥራው የሚያስፈልጉት ሠራተኞች ፣ ይኖሩታል ። ፪ ) ዋናው ሥራ አስኪያጅ በሚኒስትሩ አቅራቢነት በመን ግሥት ይሾማል ። ፫ ) ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጆች በዋና ሥራ አስኪያጅ አቅራቢነት በሚኒስትሩ ይሾማሉ ። ፰ የባለሥልጣኑ ድርጅታዊ መዋቅርና የሠራተኞች አስተዳደር የባለሥልጣኑ ድርጅታዊ መዋቅር እና ደሞወዝ እስኬል ተዘጋጅቶ በሚኒስትሩ አማካይነት ለመንግሥት ይቀርባል ። ሲፈቀድም ሥራ ላይ ያውላል ፣ ፪ ) የፌዴራል መንግሥት የሠራተኞች አስተዳደር አዋጅ ቁጥር ፪፲፪ / ፲፱፻፶፬ ቢኖርም የባለሥልጣኑ ሠራተኞች አስተዳደር ሚኒስትሩ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ይሆናል ። የዋናው ሥራ አስኪያጅ ስልጣንና ተግባር ፩ ) ዋናው ሥራአስኪያጅከሚኒስትሩበሚሰጠው አጠቃላይ መመሪያ መሠረት የባለሥልጣኑን ሥራዎች ያቅዳል በበላይነት ይመራል ፣ ያስተዳድራል ፣ ይቆጣጠራል ፣ ፪ ) ከዚህ በላይ በንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) በተገለጸው አጠቃላይ አነጋገር ሳይወሰን ዋናው ሥራ አስኪያጅ ( ሠ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከቱትን የባለሥል ጣኑን ሥልጣንና ተግባሮች ሥራ ላይ ላይ ያውላል ፣ ( ለ ) የባለሥልጣኑን ዓመታዊ እቅድ ፣ የሥራ ፕሮግራም እና በጀት አዘጋጅቶ ለሚኒስትሩ ያቀርባል ፣ ሰፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል ፣ ( ሐ ) ለባለሥልጣኑ በተፈቀደው በጀትና ፕሮግራም መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል ፣ ( መ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፰ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) መሠረት በሚወጣው መመሪያ የባለሥልጣኑን ሠራተኞች ይቀጥራል ፣ ያስተዳድራል ፣ ያስናብታል ፣ ( ሠ ) ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች ሁሉ ባለሥልጣኑን ይወክላል ። ፫ ) ዋናው ሥራ አስኪያጅ ለባለሥልጣኑ ሥራ ቅልጥፍና በሚያስፈልግ መጠን ሥልጣንና ተግባሩን በከፊል ለምክትል ዋና ሥራ አስኪያጆች ፣ ለሌሎች የባለሥልጣኑ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በውክልና ሊያስተላልፍይችላል ። ፬ ) ዋናው ሥራ አስኪያጅ ስለባለሥልጣኑ ሥራ እንቅስቃሴ በየዓመቱ መጨረሻ ወይም አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ሁሉ ለሚኒስትሩ ሪፖርት ያቀርባል ። ፲ • በጀት ባለሥልጣኑ በመንግሥት በሚመደብለት በጀት ይተዳደራል ። ፲፩ . የሂሣብ መዛግብት ምርመራ ፩ ) ባለሥልጣኑ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሣብ መዛግብት ይይዛል ፣ ፪ ) የባለሥልጣኑ ሂሣብ በዋናው ኦዲተር ወይም ዋናው ኦዲተር በሚወክለው የሂሣብ መርማሪ በየዓመቱ ይመረ ፲፪ • የመብትና ግዴታዎች መተላለፍ በአዋጅ ቁጥር ፳፩ / ፳፬ ተቋቁሞ የነበረው የፌዴራል አገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን መብቶችና ግዴታዎች በዚህ አዋጅ ለባለሥልጣኑ ተላልፈዋል ። ፲፫ • በታክስ ባለሥልጣኑ ሠራተኞች ስለሚፈጸሙ ጥፋቶች ፩ ) ማንኛውም የባለሥልጣኑ ሹም ወይም ሠራተኛ፡ ( ሀ ) በዝምድና ወይም በሌላ ግንኙነት የተነሳ ግብር ወይም ቀረጥእንዳይከፈል ወይምእንዲቀነስያደረገ ወይም ለማድረግ የሞከረ እንደሆነ ፣ ገጽ የሺ፫፻፳፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፶፪ ጳጉማቹቀን ፲፱፻፶፭ ዓም : ( ለ ለግብር ወይም ለቀረጥ አወሳሰን ሲባል የተሰበሰቡ መረጃዎችን ያጠፋ ፣ የሰወረ ወይም ይዞታቸውን የለወጠ እንደሆነ ፣ ጥፋተኛ መሆኑ በፍርድ ቤት ሲረጋገጥ ከብር 50,000 / ሃምሳሺ በማይበልጥየገንዘብ መቀጫእና ከ፲ ዓመት በማያንስ ከ፳ ዓመት በማይበልጥ እሥራት ይቀጣል ። ፪ ) ከሥራው ጋር በተያያዘ ሁኔታ የሚፈጽማቸው ሌሎች ጥፋቶችን በሚመለከት አግባብ ያላቸው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግሥት የፋይናንስኣስተዳደር አዋጅቁጥር ፵፯ / ፲፱፻፳፱ ድንጋጌዎች ተፈጻሚ ይሆናሉ ። ፲፬ • ደንበና መመሪያ የማውጣት ሥልጣን ፩ ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለዚህ አዋጅ አፈጸጸም ደንብ ሊያወጣ ይችላል ፣ ፪ ሚኒስትሩበዚህ አዋጅ የተሰጠውን ሥልጣን ለማስፈጸም መመሪያሊያወጣ ይችላል ። ፲፭ የተሻሩና ተፈጻሚ የማይሆኑ ሕጎች ፩ ) የፌዴራል አገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣንን ለማቋቋም ቁጥር ፳፩ / ፲፱፻፰፱ በዚህ አዋጅ ተሽሯል ፣ ፪ ) ይህን አዋጅ የሚቃረኑ ሕጎች ፣ ደንቦች ፣ መመሪያዎችና የኦሠራር ልምዶች በዚህ አዋጅ የተሸፈኑ ጉዳዮችን በሚመለከት ተፈጻሚነት አይኖራቸውም ። ፲፮ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፀደቀበት ከጳጉሜ ፮ ቀን ፲፱፻፭ ዓም ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ጳጉሜ ፮ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓም ግርማ ወልደጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት አታሚ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?