የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ሰባተኛ ዓመት ቁጥር ፰ አዲስ አበባ ታህሣሥ ፲፯ ቀን ፲፱የ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፪፻፳፮ / ፲፱፻፫ ዓ.ም የነዳጅ ሥራዎች ገቢ ግብር ( ማሻሻያ ) ገጽ ፩ሺ፬፻፴፱ አዋጅ ቁጥር ፪፻፳፮ / ፲፱፻፫ የነዳጅ ሥራዎች ቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል የወጣ አዋጅ የነዳጅ ሥራዎች ገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር ፪፻፲፮ / ፲፱፻ሮቿን ማሻሻል በማስፈለጉ፡ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ « የነዳጅ ሥራዎች ገቢ ግብር ( ማሻሻያ ) አዋጅ ቁጥር ፪፻፳፮ በህየን ' » ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ማ ሻ ሻ ያ የነዳጅ ሥራዎች ገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር ፪የን፮ ፲፱፻ሮቿ እንደሚከ ተለው ተሻሽሏል፡ ፩ የአዋጁ አንቀጽ ፪ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ተሠርዞ በሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ተተክቷል፡ “ ፩ . በነዳጅ ስምምነት መሠረትየነዳጅሥራዎች የሚያካሂድ ማንኛውም ሰው ግብር ከሚከፍልበት ገቢው ላይ ፴ በመቶ ( ሠላሳ ፐርሰንት ) የገቢ ግብር ይከፍላል ። » ፪ . የአዋጁ አንቀጽ ፬ ንዑስ አንቀጽ ፮ ( ሀ ) ተሠርዞ በሚከተለው ኣዲስ ንዑስ አንቀጽ ፮ ( ሀ ) ተተክቷል፡ « ሀ ) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እና ( ፪ ) መሠረት ከሚሰላው የሰብ ኮንትራክተሩ ግብር የሚከፈልበት ገቢ ላይ ሰብኮንትራክተሩ ፴ በመቶ ( ሠላሳ ፐርሰንት ) ተመን መክፈል ያለበትን የግብር ክፍያ ይቀንሳል፡ » ፫ . የአዋጁ አንቀጽ ፲፭ ተሠርቧል ። የአዋጁ አንቀጽ ፲፮፡ ፲፯፡ ፲፫ እና ፲ህ እንደቅደም ተከተላቸው አንቀጽ ፲፭፡ ፲፮፡ ፲ጊ እና ፲፰ ሆነዋል ። ፫ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከታህሣሥ ፲፯ ቀን ፲፱፻ ዓም ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ታህሣሥ ፲፯ ቀን ፲፱፻፫ ዓ.ም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፰ሺ፩