አርባ ስምንተኛ
ዓመት ቊጥር ï
ነ ጋ ሪ ት ጋ ዜ ጣ
የአንዱ ዋጋ ብር 0.60
♥ ኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዲሞክራያዊ
& ፑብሊካ
ማ ው ጫ
የመንግሥት ምክር ቤት ልዩ ድንጋጌ ቁጥር ፯ ፲፱፻፹፩ ለምሥራቃዊና ደቡባዊ አፍሪካ አገሮች
ልዩ የንግድ ቀጣና ተፈጻሚ የሚሆን የትራንዛ ክሽን ታክስና የጉምሩክ ቀረጥ ለመወሰን የወጣ የመንግሥት ምክር ቤት ልዩ ድንጋጌ.
« ኢትዮጵያ ትቅደም »
በኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የመንግሥት ምክር ቤት
ተጠባባቂነት የወጣ
ገጽ ፹፩
የመንግሥት ምክር ቤት ልዩ ድንጋጌ ቁጥር ፯ ፲፱፻፹፩ ለምሥራቃዊና ደቡባዊ አፍሪካ አገሮች ልዩ የንግድ ቀጣና ተፈጻሚ የሚሆን የትራንዛክሽን ታክስና የጉምሩክ ቀረጥ ለመወሰን የወጣ የመንግሥት ምክር ቤት ልዩ ድንጋጌ
የምሥራቃዊና ደቡባዊ አፍሪካ አገሮች ልዩ የንግድ ቀጣና ለማቋቋም ታኅሣሥ ፲፪ ቀን ፲፱፻፸፬ በሉሳካ የተፈረ መውን ስምምነት ኢትዮጵያም ተቀብላ ያጸደቀችው በመሆኑ ፤
አባል ሀገሮች በጋራ ሊስቱ ውስጥ ለተመዘገቡት ዕቃ ዎች በሦስት ደረጃ የተመደበ የታሪፍ ቅነሳ እንዲያደርጉ የልዩ የንግድ ቀጣናው የሚኒስትሮች ምክር ቤት መጋቢት ፳፪ ቀን ፲፱፻፸፱ የወሰነ በመሆኑ !
የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የመንግ ሥት ምክር ቤትም ኅዳር ፲፮ ቀን ፲፱፻፹፩ ባደረገው ስብሰባ ይህንኑ የታሪፍ ቅነሳ የተቀበለው በመሆኑ ፤
በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፹፫ ፩ መሠረት የሚከተለው ተደንግጓል ።
፩. አጭር ርዕስ ፤
ይህ ልዩ ድንጋጌ « ለምሥራቃዊና ደቡባዊ አፍሪካ አገ ሮች ልዩ የንግድ ቀጣና ተፈጻሚ የሚሆን የትራንዛክ ሽን ታክስና የጉምሩክ ቀረጥ የመንግሥት ምክር ቤት ልዩ ድንጋጌ ቁጥር ፯፲፱፻፹፩ » ተብሎ ሊጠቀስ ይቻ
አዲስ አበባ ጥር ፲፭ ቀን ፲፱፻፹፩ዓ.ም.
የፖስታ ሣጥን ቁጥር ፩ሺ፲፫ (1013)