የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ነጋሪት ጋዜጣ አራተኛ ዓመት ቁጥር ፃ ኣዲስ አበባ ሰኔ ፲፱ ቀን ፲፱፻፲ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፴፰ ፲፱፻፲ ዓ • ም • የአዲስ ሜታል ፕሬሲንግስ ድርጅት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ገጽ ፯፻፳፫ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፴፰ / ፲፱፻፲ የአዲስ ሜታል ፕሬሲንግስ ድርጅትን ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፷፯ አንቀጽ ፭ እና በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ / ፲፱፻ T ፬ አንቀጽ ፯ ( ፩ ) ( ሀ ) መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የአዲስ ሜታል ፕሬሲንግስ ድርጅት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፴፰ ፲፱፻፲ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ መቋቋም ፩ • የአዲስ ሜታል ፕሬሲንግስ ድርጅት ( ከዚህ በኋላ “ ድርጅቱ ” እየተባለ የሚጠራ ) የመንግሥት የልማት ድርጅት ሆኖ በዚህ ደንብ ተቋቁሟል ። ፪- ድርጅቱ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ ፲፱፻ዥ፬ መሠረት ይተዳደራል ። ፫ . ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን በመንግሥት የሚሰየም አካል የድርጅቱ ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ይሆናል ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፰ሺ፩ ገጽ ፯፻፷፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፱ ሰኔ ፲፱ ቀን ፲፱፻፲ ዓ.ም ፬ . ዋና መሥሪያ ቤት የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት አዲስ አበባ ይሆናል ። እንዳስፈላጊ ነቱም በማናቸውም ሥፍራ ቅርንጫፍ ሊኖረው ይችላል ። ፭ ዓላማ ድርጅቱ የተቋቋመባቸው ዓላማዎች የሚከተሉት ናቸው፡ ፩- የተለያዩ በፕሬስ የሚሠሩ የብረት ውጤቶችን ማምረት፡ ፪ • የተጓዳኝ የማምረቻ ክፍሎችን አቅም በመጠቀም ሌሎችየገበያ ምርቶችን ማምረት፡ ፫ • የሂት ትሪትመንት፡ የጥገና፡ የፕሌቲንግና የመሳሰሉትን የወር ክሾፕ አገልግሎቶች መስጠት፡ ፬ • ዓላማዎቹን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ የሆኑ ሥራዎችን ማካሄድ፡ ፮ ካፒታል ለድርጅቱ የተፈቀደ ካፒታል ብር ፩፻፲፩ ሚሊዮን ፪፻፲፮ ሺህ ( አንድ መቶ አሥራ አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ አሥራ ስድስት ሺህ ብር ) ሲሆን ከዚህ ውስጥ ብር ፻፮ሚሊዮን ፪፻፲፮ ሺህ ( ሰባ ስድስት ሚሊዮን ሁለት መቶ አሥራ ስድስት ሺህ ብር ) በጥሬ ገንዘብና በዓይነት ተከፍሏል ። ፯ ኃላፊነት ድርጅቱ ካለው ጠቅላላ ንብረት በላይ በዕዳ ተጠያቂ አይሆንም ። ፰ ድርጅቱ የሚቆይበት ጊዜ ድርጅቱ ላልተወሰነ ጊዜ ይቆያል ። ፱ ስለመብትና ግዴታ መተላለፍ የአዲስ ማሺን ቱልስ ፋብሪካን የሚመለከቱ የመሠረታዊ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኤጀንሲ መብትና ግዴታዎች በዚህ ደንብ ለድርጅቱ ተላልፈዋል ። ፲ ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ ይህ ደንብ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ሰኔ ፲፬ ቀን መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ