የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አምስተኛ ዓመት ቁጥር ፴፫ አዲስ አበባ የካቲት ፳፭ ቀን ፲፱፻፲፩ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፩፻፲፪ / ፲፱፻፵፩ ዓ.ም ከማሌዥያ መንግሥት ጋር ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋትና ዋስትና ለመስጠት የተደረገው ስምምነት ማጽደቂያ ገጽ ፩ሺህ፰ አዋጅ ቁጥር ፩፻፲፪ / ፲፱፻፲፩ ከማሌዥያ መንግሥት ጋር ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋትና ዋስትና ለመስጠት የተደረገውን ስምምነት ለማጽደቅ የወጣ አዋጅ በማሌዥያ መንግሥትና በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት መካከል ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት እና ዋስትና ለመስጠት ጥቅምት ፲፪ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓም ኩዋላ ላምፑር ላይ ስምምነት የተፈረመ ስለሆነ ፡ ስምምነቱ በሚገባ ሥራ ላይ የሚውለው በተዋዋዮቹ ሀገሮች ሕጐችመሠረት ስምምነቱ መጽደቁን የሚያረጋግጡ ሰነዶችልውውጥ ከተደረገበት ከመጨረሻው ቀን ጀምሮ ከሚቆጠር የ፴ ቀናት ጊዜ በኋላ እንደሚሆን በስምምነቱ ውስጥ ስለተገለጸ ፤ ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የካቲት ፳፭ ቀን ፲፱፻፶፩ ዓም : ባደረገው ስብሰባ ያጸደቀው ስለሆነ ፣ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፲፭ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እና ( ፲፪ ) መሠረት ከዚህ እንደሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ ከማሌዥያ መንግሥት ጋር ኢንቨስትመንትን ለማስ ፋፋትና ዋስትና ለመስጠት የተደረገው ስምምነት ማጽደቂያ አዋጅ ቁጥር ፩፻፲፪ / ፲፱፻፲፩ ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ያንዱ ዋጋ ብር 2:30 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ • ፰ሺ፩ ገጽ ፩ሺህ፱ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር፵፫ -- የካቲት ፳፭ ቀን ፲፱፻፶፩ ዓም ፪ ስምምነቱ ስለመጽደቁ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በማሌዥያ መንግሥት መካከል ኢንቨስትመንትን ለማስፋ ፋትና ዋስትና ለመስጠት ጥቅምት ፲፪ ቀን ፲፱፻፵፩ ዓም ኩዋላ ላምፑር ላይ የተፈረመው ስምምነት ጸድቋል ። ፫ • የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ባለሥልጣን ኃላፊነት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ባለሥልጣን ስምምነቱ በሥራ ላይ እንዲውል ለማድረግ በዚህ አዋጅ ሥልጣን ተሰጥቶታል ። አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከየካቲት ፳፭ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓ.ም. ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ የካቲት ፳፭ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓ.ም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ