×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
አዋጅ ቁጥር 32/1989 ዓምብሔራና የመጠሮበቂያ ነዳጅዎችእስተMማቋቋሚያእጅ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ሦስተኛ ዓመት ቁጥር ፴፭ አዲስ አበባ ሰኔ ፳፬ ቀን ፲፱፻፷፬ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ዥ፪ / ፲፱፻፷፱ ዓም ብሔራዊ የመጠባበቂያ ነዳጅ ዲፖዎች አስተዳደር ማቋቋሚያ አዋጅ . . . | ገጽ ፭፻፴፩ አዋጅ ቁጥር ፳፪ / ፲፱፻፷፱ ብሔራዊ የመጠባበቂያ ነዳጅ ዲፖዎች አስተዳደርን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ የነዳጅ አቅርቦት ቢቋረጥ ወይም እጥረት ቢያጋጥም ችግሩን ለመቋቋም የሚያስችል ብሔራዊ የመጠባበቂያ ነዳጅ ማከማቸት አስፈላጊ በመሆኑ ፤ _ ይህንን ዓላማ ተግባራዊ ለማድረግ ራሱን የቻለ የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤት ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፤ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፴፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ ብሔራዊ የመጠባበቂያ ነዳጅ ዲፖዎች አስተዳደር ማቋቋሚያ አዋጅቁጥር፳፪ / ፲፱፻፷፱ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ በዚህ አዋጅ ውስጥ ፣ እ ፡ “ ነዳጅ ” ማለት ቤንዚን ፡ ነጭ ናፍታ ፥ ጥቁር ናፍታ ፡ የጄት | 2 . Definitions ነዳጅ ፡ ላምባ ፡ ቡታ ጋዝና ሌሎች የኃይድሮ ካርቦን ውጤቶችን ያጠቃልላል ፣ ፪ “ አስቸካይ የነዳጅ እጥረት ” ማለት በተፈጥሮ ወይም በሰው ሰራሽ አደጋ ወይም በሌላ ምክንያት የሚፈጠር የመደበኛ የነዳጅ አቅርቦት ማነስ ወይም መቋረጥ ነው ፤ ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖ ሣቁ• ፰ሺ፩ | ገጽ ፭፻፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፭ ሰኔ ፳፬ቀን ፲፱፻፳፱ ዓም Federal Negarit Gazeta – No . 45 1 July , 1997 - Page 542 “ ብሔራዊ የመጠባበቂያ ነዳጅ ” ማለት የነዳጅ እጥረት በሚከሰትበት ጊዜ እጥረቱን ለመሸፈን የሚያስችል የነዳጅ ክምችት ነው ፤ ፬ . “ ሚኒስቴር ” ወይም “ ሚኒስትር ” ማለት እንደቅደም ተከ ተሉ የማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስቴር ወይም ሚኒስትር ነው ። መቋቋም 1 ፫ ፩ ብሔራዊ የመጠባበቂያ ነዳጅ ዲፖዎች አስተዳደር ( ከዚህ በኋላ አስተዳደሩ እየተባለ የሚጠራ ) የሕግ ሰውነት ያለው ራሱን የቻለ የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤት ሆኖ በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ። ያ አስተዳደሩ ተጠሪነቱ ለሚኒስትሩ ይሆናል ። 3 ፬ ዋና መሥሪያ ቤት የአስተዳደሩ ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ ሆኖእንደአስፈላጊ ነቱ በማናቸውም ሥፍራ ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤት ሊኖረው ይችላል ። 3 ኛ ዓላማ የአስተዳደሩ ዓላማ ብሔራዊ የመጠባበቂያ ነዳጅ ክምችት መያ ዝናማስተዳደር ይሆናል ። ሥልጣንና ተግባር አስተዳደሩ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ፩ ሀገሪቱ የሚያስፈልጋትን የመጠባበቂያ ነዳጅ ዲፖዎች ብዛት ፡ መጠንና ስርጭት በማጥናት የዲፖዎችን ግንባታ ዕቅድና በጀት ማዘጋጀት ፡ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ማዋል ፤ ጀ የዲፖዎችን ዲዛይን መሥራት ወይም አማካሪ መሐንዲሶችን በመቅጠር እንዲሰሩ ማድረግ ፤ ፫ የዲፖዎች ግንባታ ሥራ በራሱ ወይም ተቋራፎችን በመቅ ጠርማሠራት የግንባታ ሥራው በዲዛይኑና በውሉ መሠረት መከናወኑን በራሱ ባለሙያዎች ወይም አማካሪ መሐንዲሶ ችን በመቅጠር መቆጣጠር ፤ ፩ ሊከማች የሚገባውን ብሔራዊ መጠባበቂያ ነዳጅ መጠን ማቀድ ፡ ሲፈቀድም ነዳጅ ገዝቶ ማከማቸት ክምችቱ በአግባቡ መያዙን መቆጣጠር ፤ ፭ አስቸኳይ የነዳጅ እጥረት ሲከሰት ከሚኒስትሩ በሚሰጠው መመሪያ መሠረት ከክምችት ወጥቶእንዲከፋፈል ማድረግ ፤ ፮ : በክምችት ያለው ነዳጅ ጥራቱን ጠብቆ እንዲቆይ አስፈላጊ ውን የቴክኒክ ጥበቃ ማድረግ ' ክምችቱ ብዙ ከመቆየት የተነሳየባህሪ ለውጥእንዳያመጣናእንዳይባክን አስፈላጊውን ስልት መቀየስ ፤ ፯ የዲፖ ግንባታና የነዳጅ ክምችት ሥራዎች ስለ አካባቢ ደህንነት የወጡ ሕጎችን ያገናዘበ መሆኑን ማረጋገጥ ፤ ፰ የንብረት ባለቤት መሆን ፡ ውል መዋዋል ' በስሙ መክሰስና መከሰስ ፤ ፱ ዓላማውን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ሌሎችተግባሮ ችን ማከናወን ። ገጽ ፭፻ዥ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፭ ሰኔ ፳፬ ቀን ፲፱፻፷፱ ዓም . Federal Negarit Gazeta - - No . 45 18 July , 1997 - ~ Page 543 ፯ የአስተዳደሩ አቋም አስተዳደሩ ፤ ፩ አንድ ዋና ሥራ አስኪያጅ እና ፪ አስፈላጊው ሠራተኞች ይኖሩታል ። ፰ ስለዋናው ሥራ አስኪያጅ ፩ የአስተዳደሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ በሚኒስትሩ አቅራቢነት በመንግሥት ይሾማል ። ፪ ዋናው ሥራ አስኪያጅ ከሚኒስቴሩ በሚሰጠው አጠቃላይ መመሪያ መሠረት የአስተዳደሩን ሥራዎች ይመራል ። ያስተዳድራል ። የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) ኣጠቃላይ አነጋገርእንደተጠ በቀ ሆኖ ፡ ዋናው ሥራ አስኪያጅ ፤ ሀ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፰ የተመለከቱትን የአስተዳደሩን ሥልጣንና ተግባሮች ሥራ ላይ ያውላል ፤ በአስተዳደሩ በቴክኒካዊ ሥራ ላይ የሚሰማሩ ባለሙያዎ ችን የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግ መሠረታዊ ዓላማዎ ችን በመከተል ሚኒስትሩ በሚያወጣው መመሪያ መሠ ረት ይቀጥራል ፡ ያስተዳድራል ፤ ሌሎች ሠራተኞችን በፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግ መሠረት ይቀጥራል ፡ ያስተዳድራል ፤ ሐ ) የአስተዳደሩን የሥራ ፕሮግራምና በጀት ያዘጋጃል ፡ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል ፤ ለአስተዳደሩ በተፈቀደለት በጀት መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል ፤ ሠ ) ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች ሁሉ አስተዳደሩን ይወክላል ፤ ረ ) የአስተዳደሩን ዓመታዊ ሪፖርት አዘጋጅቶ ለሚኒስትሩ ያቀርባል ፤ ፬ . ዋናውሥራአስኪያጅለአስተዳደሩየሥራቅልጥፍናበሚያስ ፈልግ መጠን ከሥልጣንና ተግባሩ በከፊል ለአስተዳደሩ ሌሎች ኃላፊዎችና ሠራተኞች በውክልና ሊያስተላልፍ ይች ' ፀ• በጀት የአስተዳደሩ በጀት በመንግሥት ይመደብለታል ። ፲ የሂሣብ መዛግብት ፩• አስተዳደሩ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሣብ መዛግብት ይይዛል ። ፪ የአስተዳደሩ የሂሣብ መዛግብት በዋናው ኦዲተር ወይም ዋናው ኦዲተር በሚሰይመው ኦዲተር በየዓመቱ ይመረመራሉ ። ፲፩ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከሰኔ ፳፬ ቀን ፲፱፻ሺ፱ ዓ ም . ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ፣ ሰኔ ፳፬ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓም : ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?