አምሳ ሦስተኛ ዓመት ቍጥር ፸፰
የአንዱ ዋጋ
ጋ ዜ ጣ
ነ ጋ ሪ ት
የ ኢ ት ዮ ጵ ያ የ ሽ ግ ግ ር
አዋጅ ቁጥር ፺፪ ፲፱፻፹፮ ዓ. ም.
የውሃ ሀብት አጠቃቀም አዋጅ
ገጽ ፫፻፷፬
አዋጅ ቁጥር ፺፪ ፲፱፻፹፮
ስለውሃ ሀብት አጠቃቀም የወጣ አዋጅ ሀገሪቱ ለተለያዩ ግልጋሎቶች ሊውል የሚችል ከፍተኛ የውሃ ሀብት ያላት በመሆኑ
በ ኢ ት ዮ ጵ ያ የ ሽ ግ ግ ር መ ን ግ ሥ ት የተወካዮች ምክር ቤት ተጠባባቂነት የወጣ
ይህም የውሃ ሀብት በተለያዩ ግልጋሎቶችና ተጠቃሚ ዎች መካከል ሚዛናዊ በሆነ መንገድ መከፋፈሉንና በአግባቡ በጥቅም ላይ መዋሉን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሕግ ማውጣት
በማስፈለጉ ፤
በሽግግሩ ወቅት ቻርተር አንቀጽ ፱መ / መሠረት የሚ ከተለው ታውጅዋል ። ፩. አጭር ርዕስ
ይህ አዋጅ « የውሃ ሀብት አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር ፺፪ ፲፱፻፹፮ » ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ።
፪. ትርጓሜ
የቃሉ አግባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስ ተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ !
፩. « የውሃ ሀብት » ማለት በገጸ ምድርና በከርሰ ምድር የሚገኝ ማንኛውም ውሃ ሲሆን በማዕድን አዋጅ ቁጥር ፶፪ ፲፱፻፹፭ በተተረጐመው መሠረት የማዕ ድን ውሃንና የጂኦተርማል ምችቶችን አይጨ
ምርም ፥
፪. « የክልል የውሃ ሀብት » ማለት በአንድ ክልል ውስጥ ተወስኖ የሚገኝ የውሃ ሀብት ማለት ሲሆን ከአንድ በላይ የሆኑ ብሔራዊ ክልላዊ መስተዳድሮችን አቋ ርጦ ለሚፈስ ወይም ለሚያዋስን ውሃ ገባር የሆኑ ወንዞችን ይጨምራል ፤
አዲስ አበባ መጋቢት ፲፪ ቀን ፲፱፻፹፮ ዓ.ም.
የፖስታ ሣጥን ቍ ፹ሺ፩ (80,001)