ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፳፰ ፲፱፻፲፭ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ዘጠነኛ ዓመት ቁጥር ፳፩ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አዲስ አበባ ሐምሌ ፲፩ ቀን ፲፱፻፲፭ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፳፰ ፲፱፻፲፭ ዓም ያለውጭ ምንዛሪ ክፍያ ወደ አገር ውስጥ ስለሚገቡ ዕቃዎች ተሻሽሎ የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ገጽ ፪ሺ፫፻፳፪ ያለውጭ ምንዛሪ ክፍያ ወደ አገር ውስጥ ስለሚገቡ ዕቃዎች ተሻሽሎ የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፑብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፷፯ አንቀጽ ፭ መሠረት ይህን ደንብ ኣውጥቷል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ ያለውጭ ምንዛሪ ክፍያ ወደ አገር ውስጥ ስለሚገቡ ዕቃዎች ተሻሽሎ የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፰፰ ፲፱፻፲፭ ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ ያለውጭ ምንዛሪ ክፍያ ወደ ኣገር ውስጥ ሊገቡ የሚችሉ በዚህ ደንብ አንቀጽ ፫ ( ፪ ) የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ያለውጭ ምንዛሪ ክፍያ ወደ አገር ውስጥ ሊገቡ የሚችሉት የሚከተሉት ዕቃዎች ብቻ ናቸው ። ፩ ) የዲፕሎማቲክና የቆንስላ ሚሲዮኖች ፣ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና የዕርዳታ ድርጅቶች ለታወቁ አገልግ ሎቶች የሚያስገቧቸው ዕቃዎች ፣ ፪ ) የዲፕሎማቲክና የቆንስላ ሚሲዮኖች ፤ የአለም አቀፍ ድርጅቶችና የዕርዳታ ድርጅቶች ሹማምንቶችና ሠራተኞች ለግልና ለቤት ውስጥ መገልገያ የሚያስገ ቧቸው ዕቃዎች ፣ ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፰ሺ፩ ገጽ ፪ሺ፫፻፳፫ ፌዴራል ቁጥር ፳፩ ሐምሌ ፲፩ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓም • ፫ ) የኢትዮጵያ መንግሥታዊ ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች ፣ የሲቪል ማኅበራት በስጦታ ፣ በዕርዳታ ወይም በልገሳ የሚያስገቧቸው ከሥራቸው ጋር የተያያዘ ለተግባራቸው አጋዥ ዕቃዎች ፣ ፬ ) የሃይማኖት ፣ የትምህርት ፣ የሕክምና ወይም የሞያ ተቋማት ወይም ድርጅቶች ለተቋሞቹ ወይም ለድር ጅቶቹ ተግባራት ብቻ የታቀዱ በስጦታ ወይም በዕርዳታ ከውጭ አገር የሚያስገቧቸው ለንግድ የማይውሉ ዕቃዎች ፣ ፭ ) ለቤተሰብ ፣ ለዘመድና ለጓደኛ ከውጭ አገር በስጦታና በልገሳ የሚገቡ ለንግድ የማይውሉ ተሽ ከርካሪን የማይጨምር የግልና የቤት ውስጥ መገልገ ፮ ) በማንኛውም መስክ ላለ ተመራማሪ አግባብ ካለው አካል ማስረጃ የሚያቀርብ ፣ ከምርምር ሥራው ጋር የተያያዘ በስጦታና በልገሳ የሚገቡ መሣሪያዎች ፣ ፯ ) በኢትዮጵያ ውስጥ ለመኖር ለመጀመሪያ ጊዜ የሚመጡ ግለሰቦች የሚያስገቧቸው ተሽከርካሪን የማይጨምር የግልና የቤት ውስጥ መገልገያዎች ፣ ፰ ) በልዩ ልዩ ምክንያት ውጭ አገር ቆይተው ጠቅልለው የሚመለሱ ኢትዮጵያውያን እና የኢት ዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የውጭ ዜጎች የሚያስገቧቸው የግልና የቤት ውስጥ መገልገያዎች እንዲሁም ለግል ሥራቸው የሚያውሏቸውና የሚጠቀሙ ባቸው መሣሪያዎች ፣ ፱ ) አግባብ ባለው የመንግሥት መሥሪያ ቤት የኢንቨስ ትመንት ፈቃድ ያገኙ በውጭ አገር በዘላቂነት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና የውጭ ዜግነት ያላቸው የኢትዮጵያ ተወላጅ ባለሀብቶች ለኢንቨስ ትመንት ሥራቸው የሚሆን የካፒታል ዕቃ ፣ ጥሬ ዕቃ እስከ ኮሚሽኒንግ ደረጃ የሚበቃ እና ለግል መገልገያ የሚያስገቧቸው ዕቃዎች ፣ ፲ ) በስፖርት በኪነትና በመሳሰሉት ለግለሰቦችና ድርጅቶች የሚላኩ ሽልማቶች ፣ ለሽያጭ ያልመጡ ለስጦታብቻ የሚውሉ ዋንጫዎች ሜዳሊያዎች እና ሌሎች ሽልማቶች ፣ ፲፩ ) ወደ ውጭ አገር ለሚላኩ ዕቃዎች በግብአትነት የሚያገለግሉ ዕቃዎች እንደ መለያ ፣ ዘሮች እንዲሁም መጠቅለያዎችና እና መያዣዎች የመሳሰሉ ፣ ፲፪ ) ለሽያጭ ያልመጡ ስጦታዎች ፣ የንግድ ናሙናዎች እና የማስታወቂያ ዕቃዎች ፣ ፲ ) አገር ውስጥ ገብተው የማይቆዩ በተደጋጋሚ ዕቃ የሚመጣባቸው ኮንቴነሮች ፣ ሳጥኖች ፣ ጣሳዎች ፣ ጠርሙሶች ፣ ማድጋዎች እና ሌሎች መያዣዎች ፣ ፲፬ ) ለአካል ጉዳተኞች የሚመጡ ወይም የሚላኩ ለንግድ የማይውሉ ዕቃዎችና መሣሪያዎች ፣ ፲፭ ) የጐደሉ ወይም ብልሽት ያለባቸውን ዕቃዎች ለመተካት አቅራቢው ከአስመጪው ጋር ባለው የዋስትና ስምምነት መሠረት የሚገቡ ዕቃዎች ፣ ፲፮ ) ለኣንድ ተቋም መደበኛ ሥራ እና ለግሰለብ ጤና እጅግ አስፈላጊ የሆኑ በአፋጣኝ ሊገቡ ካልቻሉ ሥራው ላይ እንቅፋት የሚፈጥሩ ወይም ሕይወትን አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ዕቃዎች ፣ ፲፯ ) መንገደኞች ይዘዋቸው የሚመጡት የግል መገልገ ፲፰ ) በጊዜያዊነት ወደ አገር ገብተው ተመልሰው የሚወጡ ዕቃዎች ። ገጽ 3 ሺ፫፻፳፬ ፌዴራል ነጋሪት ቁጥር፳፩ ሐምሌ ፲፩ ቀን ፲፱፻፷፭ዓም : ፫ የገቢዎች ሚኒስቴር ሥልጣን ፩ . ሚኒስቴሩ ይህንን ደንብ ለማስፈጸም የሚረዳ መመሪያ ያወጣል ፤ ፪ . ሚኒስቴሩ በቂ ምክንያት ሲኖር በልዩ ሁኔታ ዕቃዎች ያለውጭ ምንዛሪ እንዲገቡ ለመፍቀድ ይችላል ። ፬ • የተሻረ ደንብ ያለውጭ ምንዛሪ ክፍያ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ዕቃዎች የሚኒስትሮች ደንብ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፰፰ በዚህ ደንብ ተሽሯል ። ይህንን ደንብ የጣሰ ማንኛውም ሰው ጥፋተኛ ሆኖ ሲገኝ አግባብ ባለው የወንጀል ሕግ መሠረት ይቀጣል ። ደንቡ የሚፀናበት ጊዜ ይህ ደንብ ከሐምሌ ፲፩ቀን ፲፱፻፲፭ ዓ.ምጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ሐምሌ ፲፩ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓም መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ የአዋጅ ቁጥር 359,1995 የገጽ ቁጥሩ ( 2216-2221 የተባለው በስህተት ስለሆነ የገጽ ቁጥሩ 2316 2321 ተብሎ ይነበብ ።