የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አራተኛ ዓመት ቁጥር ፪ አዲስ አበባ ሰኔ ፳፫ ቀን ፲፱፻፲ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ . | የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፩፻፳፪ ፲፱፻፲ ዓ . ም የብሔራዊ ዕፅዋት ዘር ኢንዱስትሪ ኤጀንሲ ማቋቋሚያ ( ማሻሻያ ) ኣዋጅ . . . . . . . . . . . . . . . . . ገጸ ፤ የዥ፯ አዋጅ ቁጥር ፩፻፳፪ ፲፱የኝ ብሔራዊ የዕፅዋት ዘር ኢንዱስትሪ ኤጀንሲ ማቋቋሚያ አዋጅን ለማሻሻል የወጣ አዋጅ ብሔራዊ የዕፅዋት ዘር ኢንዱስትሪ ኤጀንሲ ማቋቋሚያ አዋጅን ማሻሻል በማስፈለጉ ፡ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የብሔራዊ ዕፅዋት ዘር ኢንዱስትሪ ኤጀንሲ ማቋቋሚያ ( ማሻሻያ ) አዋጅ ቁጥር ፩፻፳፪ / ፲፱፻፲ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ማሻሻያ የብሔራዊ የዕፅዋት ዘር ኢንዱስትሪ ኤጀንሲ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ሃጌ ሀየፐ፭ እንደሚከተው ተሻሽሏል ፡ ፩ . የአዋጁ አንቀጽ ፬ ተሠርዞ በሚከተለው አዲስ አንቀጽ ፱ ተተክቷል ፡ ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖ . ሣ . ቁ : ዥሺ፩ | ገጽ ፯፻፵፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፶፪ ሰኔ ፳፫ቀን ፲፱፻፲ ዓ . ም “ ፱ የቦርዱ አባላት ቦርዱ ሰብሳቢውን ጨምሮ በመንግሥት የሚሰየሙ ቁጥራቸው እንዳስፈላጊነቱ የሚወሰን አባላት ይኖሩታል ። ” | ፪ በአዋጁ ውስጥ በማናቸውም ሥፍራ “ ምክር ቤት ” የሚለው ስያሜ “ ቦርድ ” ተብሎ ይነበባል ። [ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከሰኔ ፳፫ ቀን ፲ህየ3 ዓ . ም ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ሰኔ ፳፫ ቀን ፲፱፻፲ ዓ . ም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ