፲፯. ሌሎች ወንጀሎች
በሌላ ሕግ የበለጠ የሚያስቀጣ ካልሆነ በቀር ፤
፩ / ማንኛውም ሰው:
ሪፖርት የተደረገ መረጃን ፣ ከፍርድ ቤት ፣ አግባብ ካለው አካል ወይም በሕግ ከተፈቀደለት ሌላ ሰው ውጭ ለማንኛውም ሰው ያሳወቀ እንደሆነ ፤
አግባብ ካለው አካል ፣ ከፍርድ ቤት ወይም በሕግ ከተፈቀደለት ሌላ ሰው ውጭ በዚህ አዋጅ መሠረት መረጃ መጠየቁን ወይም መሰጠቱን ወይም ምርመራ በመካሄድ ላይ መሆኑን ወይም ሊካሄድ የሚችል መሆኑን በቀጥታም ማንኛውንም ሰው እንዲጠነቀቅ ወይም እንዲያውቅ ያደረገ እንደሆነ ፤
ሐ / በማዕከሉ መመሪያዎች ከተደነገገው ከማዕከሉ የተገኘ በሚስጥር መያዝ የሚገባውን መረጃ የገለፀ እንደሆነ ፤
ሳይፈቀድለት ወይም ስልጣን ሳይኖረው በማዕከሉ ቁጥጥር ሥር
የኮምፒውተር ስርአትን ወይም ማናቸውንም የኮምፒውተር ፕሮግራም ወይም መረጃ ሆነ ብሎ የተጠቀመ ወይም ሌላ ሰው እንዲጠቀም እንደሆነ ፤
ከሦስት እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ እሥራት እና ከብር ፭ሺ እስከ ብር ፲ሺ በሚደርስ መቀጮ ይቀጣል ።
፪ / ማንኛውም ሰው ፦
ሀ / በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብን ወይም ንብረትን ህጋዊ አስመስሎ _ ከማቅረብ ወይም ሽብርተኝነትን በገንዘብ ከመርዳት ድንጋጌዎች መሠረት ከተሰጠ ትዕዛዝ ጋር በተያያዘ ለሚደረግ ምርመራ ጠቃሚ የሆነ ሰነድ ወይም ማቴሪያል ወደ ሐሰት የለወጠ ፣ ያጠፋ ወይም በሌላ በማናቸውም መንገድ ያስወገደ ወይም ወደ ሐሰት ሰነድነት እንዲለወጥ ፣ እንዲጠፋ ወይም በሌላ በማናቸውም መንገድ እንዲወገድ የፈቀደ እንደሆነ ፤