የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ነጋሪት ጋዜጣ አራተኛ ዓመት ቁጥር ፩ አዲስ አበባ ጥቅምት ፲ ቀን ፲፱፻፲ በኢትየጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፳ ፲፱፻፲ ዓ.ም የኢትዮጵያ የንግድ ማስተባበሪያና የመረጃ ልውውጥ ማዕከል ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ገጽ ፮፻፴፯ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፳ ፲፱፻፲ የኢትዮጵያ የንግድ ማስተባበሪያና የመረጃ ልውውጥ ማዕከልን ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ ፲፱፻፷፯ አንቀጽ ፭ መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የኢትዮጵያ የንግድ ማስተባበሪያና የመረጃ ልውውጥ ማዕከል ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፳ ፲፱፻፶ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ ደንብ ውስጥ ፣ ፩ . “ ሚኒስቴር ” ወይም “ ሚኒስትር ” ማለት እንደ ቅደም ተከተሉ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ወይም ሚኒስትር ፪ • “ የማዕከል ተሳታፊዎች ” ማለት የውጭ ንግዱን እንቅስ ቃሴ በማመቻቸት ረገድ ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱ መንግሥ ታዊና የግል ድርጅቶች ማለት ነው ። • መቋቋም ፩ . የኢትዮጵያ የንግድ ማስተባበሪያና የመረጃ ልውውጥ ማዕ ከል ( ከዚህ በኋላ “ ማዕከሉ ” እየተባለ የሚጠራ ) የሕግ ሰውነት ያለው ራሱን የቻለ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ሆኖ በዚህ ደንብ ተቋቁሟል ። ፪ • የማዕከሉ ተጠሪነት ለሚኒስትሩ ይሆናል ። ያንዱ ዋጋ 2.30 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፱ሺ፩ ገጽ ፮፻፴፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፩ ጥቅምት ፲ ቀን ፲፱፻፲ ዓ.ም ማዕከሉ የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል ፤ የሀገሪቱን የውጭ ንግድ ለማበረታታት ንግድ ነክ የሆኑ መረጃዎችን የመሰብሰብ ፣ የማጠናቀር ፣ የማዘጋጀት እና በአግባቡ የማሠራጨት ፣ ፪- የማዕከሉ ተሳታፊዎች የተቀናጀ አገልግሎት የሚሰጡበትን ሁኔታ በማመቻቸት የውጭ ንግድ ሥርዓቶች የተቀላጠፉ እንዲሆኑ የማድረግ ፣ ፫ በዓለም አቀፍ ደረጃዎች ላይ በተመሠረተ የኤሌክትሮኒክ ግንኙነት ዘዴ ንግድ የሚከናወንበትን ሁኔታ የማመቻቸት ። ፭ የማዕከሉ ሥልጣንና ተግባር ለሌሎች የመንግሥት መ / ቤቶች በሕግ ተለይተው የተሰጡት ሥልጣንና ተግባሮች እንደተጠበቁ ሆነው ማዕከሉ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፣ ፩ . የዓለም አቀፍ የንግድ መረጃ መረብ አካል በመሆንና ዘመናዊ የግንኙነት ዘዴዎችን በመጠቀም ንግድ ነክ የሆኑ መረጃዎችን የመቀበል ፣ የመሰብሰብ ፣ የማጠናቀርና ለተጠ ቃሚዎች የማሰራጨት፡ ጀ ለውጭ ንግድ ሥራ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ከውጭም ሆነ ከአገር ውስጥ ከሚገኙ ምንጮች በመግዛትና በመሰብ ሰብ መረጃዎቹን የማጠናቀር ፣ የማዘጋጀትና ለተጠቃሚዎች የማሰራጨት ፣ ፫ በውጭ ንግድ ፖሊሲና ስትራቴጂ ላይ ለሚኒስትሩ ሃሳብ የማቅረብ ፣ ፬ . በሌሎች አገሮች ከሚገኙ ተመሳሳይማዕከሎች ጋር የተጠና ከረ ትብብር እና ግንኙነት እንዲፈጠር የማድረግ ፣ የሌሎች አገሮችን የውጭ ንግድ ሕጎች ፣ ደንቦች ፣ መመሪያዎችና የቴክኒክ መስፈርቶች የመሰብሰብና ፣ የማሰራጨት ፣ የማዕከሉን መገናኛ በመጠቀም የአገር ውስጥ ምርቶችን በዓለም አቀፍ ገበያዎች የማስተዋወቅ ፣ ፮ ለውጭ ንግድ ሥራ አግባብ ያላቸው ተቋሞች የሚሰጧቸው አገልግሎቶች ቅንጅት እንዲኖራቸው ሁኔታዎችን የማመቻ ፤ ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች ዋጋ የማስከፈል ፤ ፰ በዚህ ደንብ የተሰጡትን ተግባራት ለማከናወን አግባብ ካላቸው የአገር ውስጥም ሆነ የውጭ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት የማድረግ ፣ ፬ . የንብረት ባለቤት የመሆን ፣ ውል የመዋዋል ፣ በራሱ ስም የመክሰስ እና የመከሰስ፡ ፲ ዓላማዎችን ከግብ ለማድረስ የሚያስፈልጉ ሌሎች ተግባራ ትን የማከናወን ። ፮ የማዕከሉ ጽሕፈት ቤት የማዕከሉ ጽሕፈት ቤት በአዲስ አበባ ውስጥ ይሆናል ። ፯ የማዕክሉ አቋም ማዕከሉ ፡ ፩ የሥራ አመራር ቦርድ ( ከዚህ በኋላ “ ቦርዱ ” እየተባለ የሚጠራ ) ፣ ፪ . በቦርዱ አቅራቢነት በሚኒስትሩ የሚሾም አንድ ዲሬክተር ፣ ፫ አስፈላጊው ሠራተኞች ፣ ይኖሩታል ። ገጽ ፮፻፴፱ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፩ ጥቅምት ፲ ቀን ፲፱፻፶ ዓም ፰ የቦርዱ አባላት ፩ ቦርዱ ከግሉ ዘርፍ እና ከመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የተውጣጡ በመንግሥት የሚሰየሙ ሰባት አባላት ይኖሩ ፪ • የቦርዱ ሰብሳቢ ከአባላቱ መካከል በመንግሥትይመደባል ። የቦርዱ ሥልጣንና ተግባር ቦርዱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ፩ . የማዕከሉን ሥራዎች በበላይነት የመቆጣጠር ፣ የመከታተል እና ማዕከሉ በዓላማው መሠረት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማድረጉን የማረጋገጥ ፤ ፪ • የማዕከሉን ድርጅታዊ መዋቅር የመወሰን ፣ ማዕከሉየሚሰጣ ቸውን አገልግሎቶች ለማቀላጠፍ የሚረዱ መመሪያዎችን የማውጣት ተግባራዊ መሆናቸውን የማረጋገጥ ፤ ፫ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግን መሠረታዊ መርሆዎች በመከተል የማዕከሉ ሠራተኞች የሚቀጠሩበትንና የሚተዳ ደሩበትን ረቂቅ መመሪያ አዘጋጅቶ ለሚኒስቴሩ የማቅረብና ሲፈቀድም ተግባራዊነቱን የማረጋገጥ ፤ ፬ . ለዲሬክተሩ በቀጥታ ተጠሪ የሆኑ ኃላፊዎችን ቅጥር ፣ ምደ ባና ስንብት የማፅደቅ ፤ በውጭ ንግድ ፖሊሲና ስትራቴጂ ላይ የመምከርና ለሚኒስ ቴሩ ሃሣብ የማቅረብ ፤ ፮ • ማዕከሉ ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች የሚያስከፍለውን የክ ፍያ ተመኖች የመወሰን ፣ ፯ ማዕከሉ ከአገር ውስጥ ወይም ከውጭ አገር ተቋማት ጋር የሚያደርጋቸውን ስምምነቶች ገምግሞ የማፅደቅ ፣ ፰ • የማዕከሉን የሥራ ፕሮግራምና በጀት ለሚኒስቴሩ የማቅ ረብ ሲፈቀድም ተግባራዊነቱን የመቆጣጠር ፤ ፬ ይህንን ደንብ መሠረት በማድረግ የሚዘጋጁ የማዕከሉን የውስጥ ደንቦች የማፅደቅ ፣ ተግባራዊነታቸውንም የመከታ ፲ • በማዕከሉዲሬክተር በሚቀርቡ ሌሎችየፖሊሲ ጉዳዮች ላይ የመምከር ፣ የመወሰን ፤ ፲፩ ለማዕከሉ ዲሬክተር አጠቃላይ የሥራ መመሪያ የመስጠት ፤ ፲፪ የማዕከሉን የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት በየሩብ ዓመቱ ገምግሞ ከኣስተያየት ጋር ለሚኒስቴሩ የማቅረብ ። ፲ የቦርዱ ስብሰባ ፩ . ቦርዱ በወር አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ይኖረዋል ፤ ሆኖም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በማናቸውም ጊዜ አስቸኳይ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል ። በቦርዱ ስብሰባ ላይ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት አባላት ከተገኙ ምልዓተ ጉባዔ ይሆናል ። ፫ . የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) እንደተጠበቀ ሆኖ ቦርዱ ውሳኔ የሚሰጠው በድምጽ ብልጫ ይሆናል ፤ ሆኖም ድምጹ እኩል ለእኩል የተከፈለ ከሆነ ሰብሳቢው ወሳኝ ድምጽ ይኖረዋል ። የዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው ቦርዱ የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ሊያወጣ ይችላል ። ፲፩ . የዲሬክተሩ ሥልጣንና ተግባር ፩ ዲሬክተሩ የማዕከሉ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ ከቦርዱ በሚሰጠው አጠቃላይ መመሪያ መሠረት የማዕከሉን ሥራ ዎች ይመራል ፣ ያስተዳድራል ። ሆኖ የማዕከሉን ዓላማዎች ለማስፈፀም ጦዛግብት ገጽ ፭፻፵ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፩ ጥቅምት ፲ ቀን ፲፱፻፮ ዓም ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከተው አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ፣ ዲሬክተሩ ፤ ሀ ) በዚህ ደንብ አንቀጽ ፭ የተመለከቱትን የማዕከሉን ሥልጣንና ተግባሮች ሥራ ላይ ያውላል ፤ ለ ) የማዕከሉን ሠራተኞች በዚህ ደንብ አንቀጽ ፬ ንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) በተደነገገው ሁኔታ በሚጸድቀው መመ ሪያ መሠረት ይቀጥራል ፣ ያስተዳድራል ፣ ያሰናብታል ፤ ሐ ) የማዕከሉን የሥራ ፕሮግራምና በጀት አዘጋጅቶ ለቦርዱ ያቀርባል ፣ ሲፈቀድም ሥራ ላይ ያውላል ፤ መ ) ለማዕከሉ በተፈቀደለት በጀትና የሥራ ፕሮግራም መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል ፤ ሠ ) ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች ማዕከ ሉን ይወክላል ፤ ረ ) የማዕከሉን የሥራ አፈጻፀምና የሂሣብ ሪፖርት አዘጋ ጅቶ ለቦርዱ ያቀርባል ፤ ዲሬክተሩ ለማዕከሉ የሥራ ቅልጥፍና ባስፈለገ መጠን ከሥልጣንና ተግባሩ በከፊል ለማዕከሉ ሌሎች ኃላፊዎችና ሠራተኞች በውክልና ሊሰጥ ይችላል ። ፲፪ በጀት የማዕከሉ በጀት ከሚከተሉት ምንጮች የተውጣጣ ይሆ ናል ፤ * ሀ ) በፌዴራሉ መንግሥት ከሚመደብለት በጀት ፤ ለ ) ከሚሰበሰበው የአገልግሎት ክፍያ ፤ እና ሐ ) ከዕርዳታ ፣ ከስጦታ እና ከማናቸውም ሌሎች ምን ጮች ከሚያገኘው ገቢ ። ለማዕከሉ የመንግሥት በጀት የሚመደብለት ሙሉ በሙሉ በራሱ ገቢ መተዳደር እስኪችል ድረስ ብቻ ይሆናል ። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ( ለ ) እና ( ሐ ) የተመለከተው ገንዘብ በማዕከሉ ስም በሚከፈት የባንክ ሂሣብ ተቀማጭ ይሆናል ። ፲፫ • የሂሣብ መዛግብት ማዕከሉ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሣብ ይይዛል ። የማዕከሉ የሂሣብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በዋናው ኦዲተር ወይም እርሱ በሚሰይመው የውጭ ኦዲተር በየዓ መቱ ይመረመራሉ ። ደንቡ የሚፀናበት ጊዜ ይህ ደንብ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ጥቅምት ፲ ቀን ፲፱፻፲ ዓ.ም መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤትታተመ