×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
አዋጅ ቁጥር ፲፫/፲፱፻፶፭ የአካባቢ ብክለት ቁጥጥር አዋጅ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ዘጠነኛ ዓመት ቁጥር ፲፪ አዲስ አበባ ኅዳር ፳፬ ቀን ፲፱፻፶፭ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፫፫ / ፲፱፻፶፭ ዓም የአካባቢ ብክለት ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር ፫፫ / ፲፱፻፲፭ የአካባቢ ብክለት ቁጥጥር አንዳንድ ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት ጥረቶች ልማቱን የሚቀለብስ ጎጂ አካባቢያዊ ተፅዕኖ ሊያስከትሉ የሚችሉ በመሆ ናቸው ፣ በአጠቃላዩ አካባቢን መጠበቅ ፡ በተለይም የሰውን ጤንነትና general , and the safeguarding of human health and well በጎ ሁኔታ እንደዚሁም የሕያዋንን ደሕንነትና የተፈጥሮን ሥነ | being , as well as the maintaining of the biota and the aesthetic ውበትማቆየት የሁሉም ተግባርና ኃላፊነት በመሆኑ ፣ የመከላከያ ወይም የማስወገጃእርምጃዎችን በመውሰድ በማሕበ ራዊና በኢኮኖሚያዊ ልማትጥረቶችሂደት የሚከሰተውንና የማይፈ ለገውን ብክለት ማስወገድ ሳይቻል መከላከል ተገቢ በመሆኑ ፣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ክፍል አንድ ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የአካባቢ ብክለት ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር | 1. Short Title ፲፪ / ፲፱፻፶፭ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ፣ ፪ . ትርጓሜ በዚህ አዋጅ ውስጥ ፣ ፩ / “ ባለሥልጣን ” ማለት የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ነው ፤ ፪ / “ ኬሚካል ” ማለት ኤለመንት ፣ ወይም ያልተቀላቀለም ይሁን የተቀላቀለ ውሁድ ፣ ወይም ተቀምሞ በሰው የተሠራ ፣ ወይም ደግሞ ከተፈጥሮ የተገኘ ፣ ቁስአካል ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ • ፰ሺ፩ ጽ ፩ሺ፪፻፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፪ ኅዳር ፳፬ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓም • ፫ “ አግባብ ያለው መሥሪያ ቤት ” ማለት ይህ ስያሜ የተጠቀሰበት ድንጋጌ በሚነካው ጉዳይ ላይ በሕግ የተሰጠ ኃላፊነት ያለው የፌዴራል ወይም የክልል የመንግሥት አካል ነው ፤ ፬ . “ ሥልጣን ያለው ፍርድ ቤት ” ማለት በፌዴራል መንግሥት ሲሆን የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፣ እንዲሁም በብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሲሆን በክልሉ ሕግ መሠረት የሚሰየም ፍርድ ቤት ነው ፤ ፭ “ ፍሳሽ ” ማለት ተጣርቶ ወይም ሳይጣራ ፣ በቀጥታ ወይም ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ ወደ አካባቢ የሚለቀቅ ቆሻሻ ውሃ ወይም ሌላ ቆሻሻ ፈሳሽ ወይም ጋዝ ነው ። ፮ . “ አካባቢ ” ማለት በመሬት ፣ በከባቢ ኣየር ፣ በአየር ሁኔታ እና በአየር ንብረት ፣ በውሀ ፣ በህያዋን ፣ በድምፅ በሽታ ፣ በጣእም ፣ በማህበራዊ ጉዳዮች እና በስነ ውበት ሳይወሰን ፣ በተፈጥሮአዊ ሁኔታቸው ወይም በሰው ኣማካኝነት ተሻሽለው ወይም ተለውጠው የሚገኙ ነገሮች በሙሉና ያሉበት ቦታ ፣ እንዲሁም መጠናቸውን ወይም ሁኔታ ቸውን ወይም ደግሞ የሰው ወይም የሌሎች ሕያዋን በጎ ሁኔታን የሚነኩ ተስተጋብሮቶቻቸው ድምር ነው ፤ ፯ . “ የአካባቢ ተቆጣጣሪ ወይም ተቆጣጣሪዎች ” ማለት በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፯ / ፩ / መሠረት የሚሰየመው አካል ፰ “ አደገኛ ነገር ” ማለት በሰው ጤና ወይም በአካባቢ ላይ ጉዳይ የሚያደርስ ጠጣር ፣ ፈሳሽ ወይም ጋዝ ወይም ተክል ፣ እንስሳ ወይም ረቂቅ ሕዋስ ነው ። ፱ . “ አደገኛ ቆሻሻ ” ማለት ተፈላጊነት የሌለው ሆኖ በአካባቢ ወይም በሰው ደህንነት ወይም ጤና ላይ ጉዳት ያደርሳል ተብሎ የሚታመን ማንኛውም ነገር ነው ። ፲ . “ ሰው ” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው ፤ ፲፩ . “ በካይ ” ማለት ፈሳሽ ፣ ጠጣር ወይም ጋዝ የሆነ ፣ በቀጥታም ሆነ ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ ፣ ሀ ) ያረፈበትን የአካባቢ ክፍል ጥራት በመለወጥ ጠቀሜታ የመስጠት አቅሙን የሚያጓድል ፣ ወይም ለ ) በሰው ጤና ወይም በሌሎች ሕያዋን ላይ ጉዳት የሚያደርስ ወይም ሊያደርስ የሚችል መርዝን ፣ በሽታን ፣ ክርፋትን ፣ ጨረርን ፣ ድምፅን ፣ ንዝረትን ፣ ሙቀትን ወይም ሌላ ክስተትን የሚያመነጭ ፣ ማንኛውም ነገር ነው ፤ ፲፪ “ ብክለት ” ማለት በዚህ አዋጅ ወይም አግባብ ባለው ሌላ ሕግ የተደነገገን ማንኛውንም ግዴታ ፣ ማዕቀብ ወይም ገደብ ጥሶ የማንኛውንም አካባቢ ክፍል ቁሳዊ ፣ ጨረራዊ ፣ ሙቀታዊ ፣ ንጥረ ነገራዊ ፣ ሥነሕይወታዊ ወይም ሌላ ባህርይን በመለወጥ የተፈጠረ ፣ በሰው ጤና ወይም በጎነት ወይም ደግሞ በሌሎች ሕያዋን ላይ አደገኛ የሆነ ወይም አደገኛ ሊሆን የሚችል ሁኔታ ነው ፤ ፲፫ . “ ክልል ” ማለት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፵፯ / ፩ / የተመለከቱት የአገሪቷ ክፍሎች ማለት ሲሆን ፣ ለዚህ አዋጅ አፈፃፀም የአዲስ አበባ እንደዚሁም የድሬዳዋ አስተዳደሮችንም ይጨምራል ። “ የክልል የአካባቢ መሥሪያ ቤት “ ማለት ለአካባቢና ለተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ወይም ቁጥጥር በክልሉ መንግሥት ኃላፊነት የተሰጠው ማንኛውም የክልል መንግሥት አካል ነው ፤ ፲፭ “ መልቀቅ ” ማለት በውል ታስቦም ይሁን ሳይታሰብ በካይን ወደ ማንኛውም የኣካባቢ ክፍል መጨመር ክፍል ሁለት የብክለት ቁጥጥር የብክለት ቁጥጥር ማንም ሰው ተገቢን የአካባቢ ደረጃ በመተላለፍ አካባቢን ሊበክል ወይም በሌላ ሰው በኩል እንዲበከል ሊያደርግ አይፈቀድለትም ። ፪ ሕግ በመተላለፍ ማንኛውንም በካይ ወደ አካባቢ በሚለቅ ሰው ላይ ባለሥልጣኑ ወይም የሚመለከተው የክልል የአካባቢ መሥሪያ ቤት አስተዳደራዊ ወይም ሕጋዊ ዕርምጃ መውሰድ ይችላል ገጽ ፩ሺ፪፻፳፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፪ ኅዳር ፳፬ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓም ፫ • ብክለትን ወይም ሌላ ኣካባቢያዊ ጉዳትን ሊያስከትል በሚችል የተግባር መስክ የተሰማራማንም ሰው ፣ የቆሻሻ መመንጨትን ለማስወገድ ወይም ወደተፈላጊው መጠን ለመቀነስ በባለሥልጣኑ ወይም በሚመለከተው የክልል የአካባቢ መሥሪያ ቤት ትዕዛዝ መሠረት በተገቢ ቴክኖ ሎጂና ሲቻልም ቆሻሻን መልሶ በጥቅም ላይ ለማዋል በሚያስችሉ ዘዴዎች መጠቀም አለበት ። ፬ ብክለትን ያደረሰ ማንኛውም ሰው ፣ ባለሥልጣኑ ወይም የሚመለከተው የክልል የአካባቢ መሥሪያ ቤት በሚወ ስነው ሁኔታና የጊዜ ገደብ መሠረት አካባቢውን ከበካይ ማፅዳት፡ ወይም ለማፅጃ የወጣውን ወጪ መሸፈን አለበት ። በጤና ወይም በአካባቢ ላይ አደጋ እንዳያስከትል ከሚያሰጋ የሥራ እንቅስቃሴ ሊመጣ የሚችል ጉዳትን ለመከላከል ባለሥልጣኑ ወይም የሚመለከተው የክልል የኣካባቢ መሥሪያ ቤት ድርጅትን እስከ መዝጋት ወይም ወደ ሌላ ቦታ እስከ ማዛወር የሚደርስ ማንኛውንም አስፈላጊ እርምጃ መውሰድ ይችላል ። ፬ . ስለአደገኛ ቆሻሻ፡ ኬሚካልና ጨረር አመንጪ ቁስ አያያዝ ፩ ከባለሥልጣኑ ወይም ከሚመለከተው የክልል የአካባቢ | 4. Management of Hazardous Waste , Chemical and መሥሪያ ቤት ፈቃድ ሳይያዝ ማንኛውንም ኣደገኛ ቆሻሻን ማመንጨት፡ ማስቀመጥ፡ ማከማቸት፡ ማጓጓዝ፡ ማምከን ወይም ማስወገደ የተከለከለ ነው ። ፪ . ማንኛውንም ኣደገኛ ቆሻሻ በመሰብሰብ፡ መልሶ በጥቅም ላይ በማዋል፡ በማጓጓዝ፡ በማምከን ወይም በማስወገድ ሥራ የተሰማራ ማንኛውም ሰው በአካባቢ ወይም በሰው ጤና ወይም በጎ ሁኔታ ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ተገቢውን የጥንቃቄ እርምጃ መውሰድ ኣለበት ። ጨረር አመንጪ ቁስን ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት፡ ከከርሰ ምድር ለማውጣት፡ ለማጣራት፡ ለማስቀመጥ እንደዚሁም በአገር ውስጥ ለማሰራጨት፡ ለማከማቸት፡ ለማጓጓዝ ፥ በጥቅም ላይ ለማዋል ወይም ለማስወገድ፡ አግባብ ካለው መሥሪያ ቤት ፈቃድ መገኘት አለበት ። ፬ አደገኛ ተብሎ የተመደበን ወይም ለተወሰነ አገልግሎት ብቻ እንዲውል የተወሰነን ኬሚካል ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት፡ ለመቀመም፡ ለማስቀመጥ፡ በአገር ውስጥ ለማሰራጨት፡ ለማከማቸት፡ ለማጓጓዝ ፥ ወይም በጥቅም ላይ ለማዋል ከባለሥልጣኑ ወይም ደግሞ ከሚመለ ከተው የክልል የአካባቢ መሥሪያ ቤት ወይም አግባብ ካለው ከሌላ መሥሪያ ቤት ፈቃድ መገኘት አለበት ። ፭ አደገኛ የሆነ ወይም ለተወሰነ አገልግሎት የሚውል ኬሚካልን በመቀመም፡ በማምረት ወይም በማጓጓዝ ወይም በኬሚካሉ በመነገድ ሥራ ላይ የተሰማራ ማንኛውም ሰው ኬሚካሉ በተገቢዎቹ ደረጃዎች መሠረት መመዝገቡን፡ መታሽጉንና ምልክት የተለጠ ፈበት መሆኑን ማረጋገጥ አለበት ። ፭ የከተማ ቆሻሻ አያያዝ ፩ የከተማ አስተዳደሮች የተቀናጀ የከተማ ቆሻሻ አያያዝ ሥርዓትን በማውጣት፡ የከተማ ቆሻሻ መሰብሰቡን፡ መጓጓዙን ፣ እንደተገቢነቱም በጥቅም ላይ መዋሉን፡ መምከኑን ወይም ጉዳት እንዳያመጣ ተደርጎ መወገዱን ማረጋገጥ አለባቸው፡ ፪ . ከሚመለከተው የክልል የአካባቢ መሥሪያ ቤት ጋር በመተባበር፡ ባለሥልጣኑ የከተሞች የቆሻሻ አያያዝ እና አጠቃቀም ሥርዓቶችን ብቃት መመዘንና የአተገባበራ ቸውንም ውጤታማነት መገምገም፡ መከታተልና ማረጋገጥ አለበት ። ለሕዝብ ክፍት የሆነ ቦታን የሚያስተዳድርማንም ሰው ፥ ምንጊዜም በቂና ተስማሚ የመፀዳጃ ቤት፡ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ዕቃዎችና አስፈላጊ የሆኑ ሌሎች መገልገ ያዎች በቦታው መዘጋጀታቸውን ማረጋገጥ አለበት ። ፭ የሕዝብ ጥቅምን ለማጎልበት ሲባል አግባብ ያለውን ገጽ ፩፱፻፳፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፪ ኅዳር ፳፬ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓ.ም ባለሥልጣኑ ከየሚመለከተው የክልል የአካባቢ መሥሪያ ቤት እንዲሁም አግባብ ካላቸው ሌሎች መሥሪያ ቤቶች ጋር በመተባበር፡ የከተሞች የቆሻሻ ማስወገጃ መገልገያ ዎችን መገምገምና በአጥጋቢ ሁኔታ መሟላታቸውን ለማረጋገጥ አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎችን መውሰድ አለበት ። ክፍል ሶስት ስለአካባቢ ደረጃዎች ፮ ስለአካባቢ ደረጃዎች አግባብ ካላቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር በመመካከር፡ ባለሥልጣኑ በሣይንሳዊና በአካባቢያዊ መርሆዎች ላይ የተመሠረቱና ተግባራዊ ለመሆን የሚችሉ የአካባቢ ደረጃዎችን ያዘጋጃል።እነዚህም ደረጃዎች ቢያንስ የሚከ ተሉትን ማካተት አለባቸው፡ ሀ ) ወደ ውሃ ኣካላትና ወደ ፍሳሽ መቀበያ መስመሮች የሚለቀቁ ፍሳሾች ደረጃዎች፡ ለ ) የአካባቢ አየር ጥራትን የሚገልፁና ለማይንቀሳ ቀሱና ለሚንቀሳቀሱ የአየር ብክለት ምንጮች የተፈ ቀዱትን የልቀት መጠኖች የሚወስኑ የአየር ጥራት ደረጃዎች፡ ሐ ) ወደ አፈር የሚጨመሩ ኬሚካሎችን ወይም በአፈር ላይ ወይም ውስጥ የሚወገዱ ቁሶችን ዓይነትና መጠን የሚወስኑ የአፈር ጥራት ደረጃዎች፡ መ ) የአሰፋፈር ሁኔታንና የአገሪቱ የሣይንስና የቴክ ኖሎጂ ኣቅምን በማገናዘብ የሚፈቀደውን ከፍተኛ የድምፅ መጠን የሚወስኑየድምፅ ልቀትደረጃዎች፡ ሠ ) ለተለያዩ የቆሻሻ ዓይነቶች አመነጫጨት፡ አያያዝ ፥ አከመቻቸት ' አመካከንህ አጓጓዝና አወጋገድ የሚያ ገለግሉ የመጠንና የአተገባበር ደረጃዎች ። ፪ . የሚያስከትለውን ጠንቅ ለመግታት በሚከረፋ ሽታ ምንጮች ላይ ቁጥጥር መካሄድ አለበት ። ፫ . ባለሥልጣኑ አካባቢን ለመጠበቅ ወይም መልሶ እንዲያ ገግም ለማድረግ እንደአስፈላጊነቱ ለተለያዩ ሥፍራዎች የተለያዩ የአካባቢ ደረጃዎችን ሊያወጣ ይችላል ። ፬ • ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥታት በየራሳቸው ልዩ ሁኔታ በመመሥረት በፌዴራሉ እርከን ከተወሰኑት የጠበቁ ደረጃዎችን አውጥተው በሥራ ላይ ሊያውሉ ይችላሉ ። በፌዴራሉ እርከን ከተወሰኑት የላሉ ደረጃዎች እንዲ ያወጡ ግን አይፈቀድላቸውም ። የአካባቢ ደረጃ እንዲያሟሉ የሚጠበቅባቸውን የተወሰኑ ተፈላጊ ሁኔታዎችን ተፈፃሚነት ባለሥልጣኑ ለተወሰነ ጊዜ እንዲታለፉ ሊፈቅድ ይችላል ። ክፍል አራት ስለአካባቢ ተቆጣጣሪዎች ፯ : ስለአካባቢ ተቆጣጣሪዎች ፩ የአካባቢ ተቆጣጣሪዎች / ከዚህ በኋላ “ ተቆጣጣሪዎች ” እየተባሉ የሚጠሩ በባለሥልጣኑ ወይም በሚመለከተው የክልል የአካባቢ መሥሪያ ቤት ይሰየማሉ ፣ ፪ ተቆጣጣሪዎች በዚህ አዋጅ መሠረት ሥልጣንና ተግባራ ቸውን ሲወጡ ሥራቸውን በትጋትና ያለአድልዎ መፈፀም አለባቸው ። ፰ የተቆጣጣሪዎች ሥልጣንና ተግባር ፩ . የአካባቢ ተቆጣጣሪዎች የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሯቸዋል ፤ ሀ ) የአካባቢ ደረጃዎችናተዛማጅግዴታዎች በሥራላይ መዋላቸውን ማረጋገጥ ፣ ለ ) የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) እና ( 6 ) ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆኖ ፤ ሳያሳውቁ ወይም ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሳይዙ በማንኛውም ተገቢ መስሎ በሚታ ያቸው ጊዜ ወደ ማንኛውም ቦታ ወይም ቅጥር ግቢ መግባት ፤ • ርምጃ ቅር የተሰኘ | ገጽ ፩ሺ፱፻፳፫ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፪ ኅዳር ፳፬ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓ • ም • ሐ ) ማንኛውንም ሰው ብቻውን ወይም በምስክር ፊት መጠየቅ ፣ መ ) ከብክለት ጋር ግንኙነት ያለውን ማንኛውንም ወረቀት ፣ ማሕደር ወይም ሌላ ሠነድ መፈተሽ ፣ መገልበጥ ወይም ለይቶ መቅዳት ፣ ሠ ) የማንኛውንም ቁስ ናሙናዎች እንደአስፈላጊነቱ ያለክፍያ መውሰድና በአካባቢ ወይም በሕይወት ላይ ጉዳት የሚያደርስ መሆን አለመሆኑን ለመወሰን መመርመር ወይም ማስመርመር ፣ ረ ) ይህ አዋጅ እና አግባብ ያለው ማንም ሌላ ሕግ መከበሩን ለማረጋገጥ ሸቀጥን ፣ የአመራረት ሂደትን ወይም መገልገያን በፎቶግራፍ ማንሣት ፣ መለካት ፣ መሳል ወይም መፈተሽ ፣ ሰ ) ይህን አዋጅ ወይም አግባብ ያለውን ሌላ ሕግ በመተላለፍ ጥፋት ተፈጽሞበታል የተባለ መሣሪያን ወይም ሌላ ነገርን መያዝ ፣ ፪ : የተመደበው ተቆጣጣሪ የዚህን አዋጅ ወይም ማንኛ ውንም አግባብ ያለውን ሕግ ድንጋጌ ለተላለፈ ሰው የመተላለፉን ምንነት ይዘረዝርለታል ፣ ይህንኑ መተላለፍ በተወሰነ ጊዜ ውስጥ ለማስቀረት መውሰድ ያለበትን እርምጃ በመግለጽም እርምጃው እንዲወሰድ ሊያዝ ይችላል ። ፫ የተመደበው ተቆጣጣሪ ማንኛውም እንቅስቃሴ በአካባቢ ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል ብሎ ሲጠረጥር እንቅስቃ ሴውን እስከማስቆም የሚደርስ የእርምት እርምጃ እንዲ ወሰድ ትዕዛዝ ይሰጣል ። ፬ • ማንኛውም የተመደበ ተቆጣጣሪ በባለሥልጣኑ ወይም በሚመለከተው የክልል የአካባቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ፤ የመሥሪያ ቤቱ ማህተም ያለበት መታወቂያ መያዝ ፣ ሲጠየቅም ማሳየት አለበት ። ፭ ናሙና ሲወሰድ ባለንብረቱ የመገኘት ወይም ወኪል የመላክ መብት ስላለው ይህንኑ መብት እንዲያውቀው መደረግ አለበት ። የሥራ አፈፃፀም ቅልጥፍናውን የሚበድልበት ካልሆነ በስተቀር ማንኛውም የተመደበ ተቆጣጣሪ ወደ ማንም ድርጅት ቅጥር ግቢ ወይም ቦታ ሲገባ ለባለንብረቱ ማስታወቅ አለበት ። ፱ : ስለይግባኝ ፩ ተቆጣጣሪው በወሰደው ማንኛውም ማንኛውም ሰው ፣ እርምጃው ከተወሰደበት ቀን አንስቶ በአሥር ቀናት ውስጥ ለባለሥልጣኑ ወይም ለሚመለ ከተው የክልል የአካባቢ መሥሪያ ቤት የበላይ ኃላፊ ይግባኝ ማለት ይችላል ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ መሠረት ውሳኔ ያልተሰጠ በመሆኑ ወይም የተሰጠው ውሣኔ ተገቢ ባለመሆኑ ቅር የተሰኘ ሰው ውሣኔው ከተሰጠበት ወይም የሚሰጥበት የጊዜ ገደብ ካለፈበት ቀን አንስቶ በሰላሣ ቀናት ውስጥ ክስ መመስረት ይችላል ፣ ስለማበረታቻ ፩ ብክለትን ለመከላከል ወይም መጠኑን ለመቀነስ በሚያ ስችል በማንኛውም ዘዴ መጠቀም ለሚጀምር ለማን ኛውም ነባር ድርጅት የሚሰጥ ማበረታቻ በዚህ አዋጅ ሥር በሚወጣ ደንብ ይወሰናል ። ፪ በባለሥልጣኑ ሲረጋገጥብክለትን ለመከላከል ሲባል ወደ አገር ውስጥ የሚገባ መሣሪያ ከገቢ ዕቃዎች የጉምሩክ ቀረጥ ክፍያ ነፃ ይሆናል ። ፲፩ : ስለመክሰስ መብት ፩ . ነገሩ የሚመለከተው መሆኑን ማስረዳት ሳይጠበቅበት ፣ ማንኛውም ሰው በአካባቢ ላይ ጉዳት አድርሷል ወይም ጉዳት ሊያስከትል የሚችል ተግባር እየፈጸመ ነው በሚለው በማንኛውም ሰው ላይ ለባለሥልጣኑ ወይም ለሚመለከተው የክልል መሥሪያ ቤት ቅሬታ የማቅረብ መብት አለው ። ገጽ ፩ሺ፱፻፳፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፪ ኅዳር ፳፬ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓ • ም • ባለሥልጣኑ ወይም የሚመለከተው የክልል የአካባቢ መሥሪያ ቤት በሰላሳ ቀናት ውስጥ ውሣኔ ካልሰጠ ወይም ቅሬታ አቅራቢው በውሳኔው ካልተስማማ ፣ ውሳኔው ከተሰጠበት ወይም የሚሰጥበት የጊዜ ገደብ ካለፈበት ቀን አንስቶ በስድሳ ቀናት ውስጥ በፍርድ ቤት ክስ መመሥረት ይችላል ። ክፍል አምስት ጥፋትና ቅጣት ፲፪ : ጠቅላላ ይህን አዋጅ ወይም አግባብ ያለውን ሌላ ሕግ የተላለፈ ፣ ነገር ግን ጥፋቱ በወንጀለኛ መቅጫ ሕግም ሆነ በዚህ አዋጅ ቅጣት ያልተመደበለት ሆኖ የተገኘ ማንም ሰው ጥፋተኛነቱ ሲረጋገጥ ፣ ሀ ) የተፈጥሮ ሰው ሲሆን ፣ ከአምስት ሺህ ብር በማያ ንስና ከአስር ሺህ ብር በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ ወይም ከአንድ ዓመት በማይበልጥ እሥራት ወይም በሁለቱም ይቀጣል ፣ ለ ) በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው ሲሆን ከአሥር ሺህ ብር በማያንስና ከሃያ ሺህ ብር በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ / ፩ መሠረት በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ጥፋተኛነቱ ሲረጋገጥ የተፈፀመውን ጥፋት ማወቅ የነበረበትና ኃላፊነቱን በብቃት ያልተወጣው የሥራ ኃላፊ ከአምስት ሺህ ብር በማያንስና ከአስር ሺህ ብር በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ ወይም ከሁለት ዓመት በማይበልጥ እሥራት ወይም በሁለቱም ይቀጣል ፣ ፫ • በወንጀኛ መቅጫ ሕግ መሠረት የከበደ ቅጣት የሚያ ስቀጣ ካልሆነ በስተቀር ፣ በዚህ አዋጅ የተደነገጉት ቅጣቶች ተፈፃሚ ይሆናሉ ። ፲፫ ከተቆጣጣሪዎች ጋር በተያያዘ ስለሚፈፀሙ ጥፋቶች ፩ የተመደበ ተቆጣጣሪን ሥራውን እንዳያከናውን ያደናቀፈ ወይም ያሰናከለ ፣ ተቆጣጣሪው በሕግ መሠረት የጠየ ቀውን ወይም ያዘዘውን ያልፈፀመ ፣ በማስመሰል ተቆጣጣሪ ነው ሊባል የሞከረ ፣ ተቆጣጣሪው ወደ ማንኛውም ቦታ ወይም ቅጥር ግቢ እንዳይገባ ወይም መዛግብት እንዳይመረምር ያደናቀፈ ማንኛውም ወረቀት ማሕደር ፣ ወይም ሌላ ሰነድ እንዳይፈትሽ ፣ እንዳይገለብጥ ፣ ወይም ለይቶ እንዳይቀዳ የከለከለ ፣ ለተቆጣጣሪ መረጃ የከለከለ ፣ ያሳሳተ ወይም የተሳሳተ መረጃ የሰጠ ማንም ሰው ጥፋት ፈጽሟል ፣ ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ / ፩ / መሠረት ጥፋት የፈፀመ የተፈጥሮ ሰው ጥፋተኛነቱ ሲረጋገጥ ከሶስት ሺህ ብር በማያንስና ከአሥር ሺህ ብር በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል ጥፋቱን የፈፀመው በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ከሆነ ደግሞ ጥፋተኛነቱ ሲረጋገጥ ከብር አሥር ሺህ በማያንስና ከብር ሃያ ሺህ በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል ፣ የሥራኃላፊውም ከአንድ ዓመት በማያንስ እና ከሁለት ዓመት በማይበልጥ እሥራት ወይም ከአምስት ሺህ ብር በማያንስና ከአስር ሻህ ብር በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ ወይም በሁለቱም ይቀጣል ። መዛግብትን በተመለከተ ስለሚፈፀሙ ጥፋቶች አንድ ሰው በዚህ አዋጅ ወይም በሥሩ በሚወጡ ደንቦች | 14. Offences Relating to Records መሠረት በመዝገብ እንዲያሰፍር የተጠየቀውን የእንቅ ስቃሴ ፣ የምርት ፣ የቆሻሻ ዓይነት ባሕርይ ወይም መጠን ወይም ሌላ ተፈላጊ መረጃ በተገቢው ሳይመዘግብ ከቀረ ወይም በመዝገብ የሰፈረውን ከለወጠ ፣ ከአስር ሺህ ብር ሰማያንስና ከሃያ ሺህ ብር በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል ። ገጽ ፩ሺ፪፻፷፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፪ ኅዳር ፳፬ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓም : ፲፭ አደገኛ የሆነ ቆሻሻንና ሌላ ቁስን በተመለከተ ስለሚፈፀም ፩ ኣንድ ሰው አደገኛ ቆሻሻን ወይም አደገኛ ነገርን አግባብ ባላቸው ሕጎች መሠረት ካልያዘ ፣ መለጠፍ ያለበት ዝርዝርን አሳስቶ ከለጠፈ ወይም ጭራሹን ካልለጠፈ ፣ ወይም ደግሞ ማንኛውንም አደገኛ ቆሻሻን ፣ ወይም ሌላ ነገርን በተመለከተ መረጃ ከነፈገ ወይም ያልተፈቀደ የአደገኛ ቆሻሻ ዝውውርን ለማካሄድ ከሞከረ ወይም ካካሄደ ወይም ደግሞ እንዲካሄድ ለመርዳት ከሞከረ ወይም ከረዳ ጥፋተኛ ነው ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ / ፩ መሠረት ጥፋት የፈፀመ የተፈጥሮ ሰው ጥፋተኛነቱ ሲረጋገጥ ከሃያ ሺህ ብር በማያንስና ከሃምሳ ሺህ ብር በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ ፣ ጥፋቱን የፈፀመው በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ከሆነ ደግሞ ከሃምሳ ሺህ ብር በማያንስና ከአንድ መቶ ሺህ ብር በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል ። የሥራ ኃላፊውም ከሦስት ዓመት በማያንስና ከስድስት ዓመት በማይበልጥ እሥራት ወይም ከሰላሳ ሺህ ብር በማያንስና ከሰባ ሺህ ብር በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ ወይም በሁለቱም ይቀጣል ። ፲፮ • ብክለትን በሚመለከት ስለሚፈፀም ጥፋት አንድ የተፈጥሮ ሰው የዚህን አዋጅ ወይም በሥሩ የሚወ ጡትን ደንቦች በመተላለፍ በካይን ወደ ኣካባቢ በመልቀቅ ጥፋተኛ ሆኖ ሲገኝ፡ ከአንድ ሺህ ብር በማያንስና ከአምስት ሺህ ብር በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ ወይም ከአንድ ዓመት በማያንስና ከአሥር ዓመት በማይበልጥ እሥራት ወይም በሁለቱም ይቀጣል ። ጥፋቱን የፈፀመው በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ከሆነ ከአምስት ሺህ ብር በማያንስና ከሃያ አምስት ሺህ ብር በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል ፣ የሥራ ኃላፊውም ከአምስት ዓመት በማያንስና ከአስር ዓመት በማይበልጥ እሥራት ወይም ከአምስት ሺህ ብር በማያንስና ከአስር ሺህ ብር በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ ወይም በሁለቱም ይቀጣል ። ፲፯ ስለመውረስ እና ወደ ነበረበት ሁኔታ ስለመመለስ ይህን አዋጅና በሥሩ የሚወጡትን ደንቦች በመጣስ ጥፋተ ኛነቱ በተረጋገጠበት ሰው ላይ ከሚወሰንበት ማንኛውም ቅጣት በተጨማሪ ፍርድ ቤቱ ፣ ሀ ) ለጥፋቱ ተግባር የዋለ ማንኛውም ነገር ተወርሶ ለመን ግሥት ገቢ እንዲሆን ወይም በሌላ መንገድ እንዲወገድ ፣ ለ ) አካባቢውን የማፅጃ ወይም መሣሪያውን ፣ ኬሚካሉን ወይም ዕቃውን የማስወገጃ ወጪ ተከሳሹ እንዲከፍል ፣ እንደዚሁም ፣ ሐ ) ጉዳት የደረሰበትን አካባቢ ተከሳሹ በራሱ ወጪ ነበረበት ሁኔታ እንዲመልስ ወይም ደግሞ ይህ የማይቻል ከሆነ ተገቢ ካሣ እንዲከፍል ማዘዝ ይችላል ። ክፍል ስድስት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ፲፰ የመሸጋገሪያ ድንጋጌ በሥራ ላይ ያሉ ተቋማት ይህን አዋጅ እንዴት ተፈፃሚ እንደሚያደርጉት በዚህ አዋጅ ሥር በሚወጣ ደንብ ይወሰናል ። ፲፱ መረጃ የመስጠት ግዴታ ፩ የዚህን አዋጅ ወይም ከዚህ አዋጅ ጋራ ግንኙነት ያለውን የሌላ ሕግ ድንጋጌ የሚመለከት ተግባርን የሚያከናውን | 19. Duty to Provide Information ማንኛውም ሰው ባለሥልጣኑ ወይም የሚመለከተው የክልል የአካባቢ መሥሪያ ቤት በሚፈልገው መሠረት የሥራ እንቅስቃሴውን መረጃ ማቅረብ አለበት ። ባለሥልጣኑ ማንኛውንም አካባቢን የሚመለከት መረጃ የማግኘት መብት አለው ። ገጽ ፩ሺ፪፻፳፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፪ ኅዳር ፳፬ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓ.ም. ደንብ የማውጣት ሥልጣን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ይህንን አዋጅ በተሟላ ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረግ አስፈላጊ የሆኑ ደንቦችን ሊያወጣ ይችላል ። ፳፩ . ተፈፃሚነት የሌላቸው ሕጎች ከዚህ አዋጅ ጋር ተቃራኒ የሆነ ሕግ ወይም አሠራር በዚህ አዋጅ በተመለከቱት ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚነት አይኖረውም ። ፳፪ • አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ ይህ አዋጅከኅዳር፳፬ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓም ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ኅዳር ፳፬ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓ.ም ግርማ ወልደጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰምተድርጅትታተመ

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?