×
Browse Products About Us Login / Sign Up Contact Us አማርኛ
African Law Archive
Logo
የፍርድ ቤት ውሳኔ 14554

      Sorry, pritning is not allowed

የሰበር መዝገብ ቁ . 14554 ታህሣስ 20 ቀን 1998 ዓ.ም
ዳኞች፡- 1- አቶ ከማል በድሪ
2- አቶ ፍስህ ወርቅነህ 3- አቶ አብዱልቃድር መሃመድ 4- አቶ ስንዱ አለሙ
5 አቶ መስፍን ዕቁበዮናስ አመልካች፡- ወ / ሮ ፅጌ አጥናፌ መልስ ሰጭ፡- ባላምባራስ ውቤ ሺበሺ
ተዋዋይ ወገን ሳይሆን ውል እንዲሠረዝ ሰለመጠየቅ . በአስተዳደር አካል የተሰጠ የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር ፍ / ቤት የመሠረ ሥልጣን የሌለው- ስለመሆኑ የፍትሀብሔር ህግ ቁጥር 1808 / 2 / ፣
ካስ አመልካች ፈቃድ የጋራቸው የሆነውን ቤት ስም ለማዛወር አመልካች ባለቤት ከተጠሪ ጋር የፈፀመው ውል ፈራሽ ነው በማለት የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት መወሰኑና የከፍተኛው ፍ / ቤት ውሉ እንዲፈርስ አመልካች የጠየቁት ያለአግባብ ነው በማለት የስር ፍ / ቤትን ውሳኔ በመሻሩ ፧ በመጨረሻም የጠቅላይ ፍ / ቤት ውሳኔውን ሰማፅናቱ የቀረበ እቤቱታ፡ ውሳኔ፡- የፌዴራል ጠቅላይ ፍ / ቤት የሠጠው ትዕዛዝ ተሽራል ፡፡
1- ተዋዋይ ወገን ሳይሆን በተፈፀመ ውል ምክንያት መብቴ
ተነክቷል በማለት ውሉ እንዲሠረዝ ክስ ለማቅረብ የሚቻለው ውሉ የተደረገበት ጉዳይ ወይም ምክንያት ከህግ ውጭ ከሆነ ፣ ለህሊና ተቃራኒ ወይም ለውል አፃፃፍ የተደነገገው ፎርም አልጠበቀም በሚል ምክንያት ብቻ ነው ፡፡ ከዚህ ውጭ የሚቀርብ
ጥያቄ የክስ ምክንያት የለውም ፡፡ 2- የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር የመሠረዝ ሥልጣን ደብተሩን
የሰጠው የአሥተዳደር አካል እንጅ የፍ / ቤት አይደለም ፡፡
የቤቱ ባለንብረት እንደሆነ ይቆጠራል ፡፡
የሰበር ችሎት መ / ቁ 1 4554
ቀን ታህሣሥ 20 ቀን 1998 ዓም
ዳኞች፡- 1. ኣቶ ከማል በድሪ
2. አቶ ፍስሐ ወርቅነህ
3. አቶ አብዱልቃድር መሐመድ
4. ወ / ሮ ስንዱ ዓለሙ
5. አቶ መስፍን እቁበዮናስ
አመልካች፡ ወ / ሮ ጽጌ አጥናፌ - ቀረበች መልስ ሰጭ፡- ባላምባራስ ውቤ ሺበሺ - አልቀረም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ውሣኔ ተሰጥቷል ፡፡
ፍ ር ድ
አመልካች የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት የሰጠውን ውሣኔ
በመሻር የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት የሰጠውና የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያፀናው ውሣኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በማለት እንዲሻር
ጠይቀዋል ፡፡
ጉዳዩ የተጀመረው አመልካች በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት
ባቀረቡት ክስ ሲሆን ይዘቱም ሲጠቃለል በዚህ መዝገብ የሌሉበት የሰር 2 ኛ
ተከሣሽ በሆነው ባለቤቴ በአቶ ተስፋዬ
ውቤ የተመዘገበውን እና የጋራ
ንብረታችን የሆነውን በወረዳ 20 ፣ “ ቀበሌ 44
የቤቁ 399 የሆነውን
መኖሪያ ቤት የስር 2 ኛ ተከሣሽ ባለቤቴ ከአሁን መ / ሰጭ ጋር በመመሳጠር
ለአሁን መ / ሰጭ ( የስር 1 ኛ
1 ኛ ተከሣሽ ) ለማስተላለፍ
ለማስተላለፍ የስምምነት
አድርገዋል ፤ ስምምነቱ መብቴን የሚነካ በመሆኑ ውሉ እንዲፈርስ የሚል ነው ።
የስር 2 ኛ ተከሣሽ ለክሱ ተቃውሞ እንደሌለው የገለፀ ሲሆን የአሁን መ / ሰጭ
በበኩላቸው ክሱ በፍ / ብ / ሕ / ቁ 1810 መሠረት በይርጋ ይታጎዳል ፤
በሕይወት ያለሁ በመሆኑ ቤቱ ለስር 2 ኛ ተከሣሽ በውርስ ተላልፎአል ሊባል
አይችልም ፤
የቤቱ የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር በስር 2 ኛ ተከሣሽ ስም
ይገኛል ለተባለው ደብተሩ የተገኘው በሀሰተኛ መንገድ መሆኑን ደብተሩ በስሜ
እንዲዛወር የእርቅ ስምምነት ፈርሟል ፤ በመሆኑም ቤቱ፡ የራሴ ስለሆነ ክሱ ውድቅ ይደረግ በማለት ጠይቀዋል :: ፍ / ቤቱም ጉዳዩን መርምሮ ቤቱን የአሁን
እመልካች እና የስር 2 ኛ ተከሣሽ የጋራ ንብረት ነው ፤ የስር 2 ኛ ተከሣሽም
የጋራ ንብረቱን ያለአሁን እመልካች ፈቃድ የማስተላለፍ አይችሉም በማለት
የእርቅ ስምምነቱን ውል ፍ / ቤቱ ኣፍርሶታል በማለት ወሰነ ፡፡ ጉዳዩ በይግባኝ
የቀረበለት የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት በበኩሉ የአሁን አመልካች ባቀረቡት ክስ
የአሁን መ / ሰጭ ከስር 2 ኛ ተከሣሽ ጋር ያደረጉት ስምምነት መብቴን ስለሚነካ
ስምምነቱ ይፍረስልኝ ያሉት ያለአግባብ ነው በማለት የስር ፍ / ቤት ውሣኔን
ሽሮታል ፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትም የከፍተኛው ፍ / ቤት በሰጠው
ውሣኔ ምክንያቱ ባይስማማም በውጤቱ በመስማማት አጽንቶታል ፡፡
አመልካች የሰበር አቤቱታ ለዚህ ችሉት ያቀረቡት የፌዴራል ከፍተኛ
ፍ / ቤት በሰጠውና የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባፀናው ውሣኔ ቅር በመሰኘ
ት ሲሆን ይዘቱም ሲጠቃለል በስር ፍ / ቤት ያቀረብኩት የእርቅ ስምምነት
ይፍረስልኝ የሚል ጥያቄ ሲሆን የእርቅ ስምምነቱም
አይደለም ፤ ከፍተኛ ፍ / ቤቱ በውሣው የጠቀሣቸው ድንጋጌዎች ከጉዳዩ ጋር
የሚገናኝ አይደለም ፤ በመሆኑም አቤቱታ የቀረበበት ውሣ እንዲሻር የሚል
ነው :: መ 7 ሰጭ በበኩላቸው አመልካች ያቀረቡት ክርክር የፍሬ ነገር በመሆኑ
በዚህ ሰበር ችሉት የሚታይ አይደለም ፤ በተደረገው የእርቅ ስምምነት አመልካች
የሌለችበት መሆኑ
ክስ መመሥረት ኣትችልም በማለት አቤቱታው ውድቅ
እንዲደረግ ጠይቀዋል ፡፡
በግራ ቀኙ የቀረበው ክርክር ከፍ ብሉ የተመለከተው ሲሆን ችሉቱም
ከርክሩን እና ኣቤቱታ ይቃረበበትን ትእዛዝ አግባብነት ኳላው c ሕገር አገናዝቦ
መርምሮታል ።
በዚህም መሠረት ኣመልካች የእርቅ ስምምነቱን መሠረት በማድረግ ክስ
ለማቅረብ የሚያስችላት የክስ ምክንያት አለ ? ወይስ የለም ? እና ፍ / ቤት ስልጣን
ባለው አካል የተሰጠን የባለቤትነት ማስረጃ ደብተርን ሓሰተኛ በሆነ መንገድ
የተገኘ ነው በሚል የመሠረዝ ስልጣን አለው ? ወይስ የለውም ? የሚሉትን ነጥቦች በጉዳዩ መመለስ ያለባቸው ሆኖ አግኝቷቸዋል ።
የስር ፍ / ቤት አቤቱታ ለቀረበበት ውሣኔ መሠረት የሆነውነ ውሣ
የሰጠው አመልካች ባቀረቡት ክስ መነሻነት ነው ። አመልካች ባቀረቡት ክስ የጠየቁት ዳኝነት በአሁን መ / ሰጭና በስር 2 ኛ ተከሣሽ መካከል የተደረገው
የእርቅ ስምምነት ውል መብቴን የሚነካ በመሆኑ እንዲሻር የሚል ነው :: ይሄም
ለክሣቸው መሠረት ያደረጉት እሣቸው የሌሉበትንና , አሁን መ / ሰጭ እና በስር 2 ኛ ተከሣሽ መካከል የተደረገውን የእርቅ ስምምነት ውል መሆኑን
ያሣያል ፡፡ በፍ / ብ / ሕ / ቁ .1676 ( 1 ) መሠረት ስለ ውሉች በጠቅላላ የተደነገጉት ድንጋጌዎች በዚህ ጉዳይ አግባብነት ያላቸው ናቸው ። ከእነዚህ
ድንጋጌዎች በፍ / ብ / ሕ / ቁ 1808 ( 2 ) መሠረት ከተዋዋይ ወገኖች ውጭ የሆነ ማነኛውም ጥቅም አለኝ የሚል ሰው ውሉ እንዲሠረዝ የሚጠይቀው ውሉ
የተደረገበት ጉዳይ ወይም ምክንያት ከሕግ ውጭ ከሆነ
ወይም ለሕሊና
ተቃራኒ ወይም ለውል አፃፃፍ የተደነገገው
ፎርም አልተጠበቀም በሚል ምክንያት ብቻ ነው :: በዚህ ጉዳይ የእርቅ ስምምነት ውል ተብሉ የተገለፀው
የተደረገበት ምክንያት የማይንቀሣቀስ ንብረት ሳለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር
የወጣበትን ስም ማዛወር ሲሆን ይህም ከሕግ ውጭ ወይም ለህሊና ተቃራኒ
የሚባል አይደለም ። የእርቅ ስምምነት
ውል ነው የተባለው ለውሉ
የተደነገገው ፎርም አልተጠበቀም የሚል ክርክር ደግሞ አመልካች እላቀረቡም ፡፡
እነዚህ ባልተሟሉበት ሁኔታ አመልካች የሌሉበት ( ያልገቡት ) ውል ይሰረዝ የሚል ክስ የሚያቀርቡበት ሕጋዊ ምከንያት የሌለ በመሆኑ የስር ፍ / ቤት
መጀመሪያውኑ የክስ ምክንያት የሌለ በመሆኑ አመልካች በፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕ /
ቁ 33 መሠረት አመልካች ክስ ለማቅረብ የማይችሉ ናቸው በማለት ክሱን
መዝጋት ነበረበት ። የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤትም ይሄንን ስህተት ሣያስተካክል ያለፈው በአግባቡ አይደለም ፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤቱም ይሄን ስህተት በተመሣሣይ ሁኔታ ማስተካከል ሲገባው አመልካች ባቀረበችው ክስ እንዲሰረዝ የጠየቀችው የእርቅ ስምምነት የእርቅ ስምምነት ውል ሣይሆን ውሣኔ ነው
ውሣኔ ነው በሚል ይግባኙን ማድረጉን ከትእዛዙ ይቻላል ። በመሠረቱ እንዲሰርዝ የተጠየቀው ጠቅላይ ፍ / ቤቱ እንዳለውኑ ውሣኔ ነው ቢባል እንኳን በቤቱ ላይ መብት አለኝ የሚል ወገን በአፈፃፀም ሆነ በሌላ በማናቸውም ሁኔታ ቤቱን በሚመለከት ክስ ሲያቀርብ አመልካች ቀርበው ከሚከላከሉበት ሁኔታ በቀር ክስ ሣይቀርብባቸው በራሣቸው ክስ በማቅረብ ውሣኔው ይሰረዝልኝ የሚል ጥያቄ የሚያቀርቡበት የሕግ አግባብ የለም ። ይሄም አመልካች የእርቅ ስምምነት ውል ነው ያሉት አንዱ ጠቅላይ ፍ / ቤት ድምዳሜ ውሣኔ ነው ቢባል እንኳን አመልካች ይሰረዝልኝ የሚል ክስ ሊያቀርቡ እንደማይችሉ የሚያመለክት ነው ።
በሌላ በኩል ደግሞ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት ከፍ ብሉ በተብራራው ምክንያት የስር ፍ / ቤትን ውሣኔ መሻር ሲገባው ጉዳዩን መርምሮ የስር 2 ኛ ተከሣሽ ያገኘው የባለቤትነት ማሰረጃ ደብተር በሐሰተኛ መንገድ የተገኘ ነው ፤ በዚህም ምክንያት በፍ / ብ / ሕ / ቁ 1195 ( 1 ) የተደነገገው የባለቤትነት ማስረጃ ደብተር የያዘ ሰው የቤቱ ባለሀብት እንደሆነ ይቆጠራል የሚለው የህሊና ግምት በፍ / ብ / ሕ / ቁ 1196 ( ለ ) መሠረት ፈራሽ ሆኗል ፤ በመሆኑም የስር 2 ኛ ተከሣሽ የቤቱ ሳለንብረት ያልሆነ በመሆኑ የእርቅ ስምምነቱ ” የአመልካችን መብት አይነካም በማለት ነው የስር ፍ / ቤት ውሣኔን የሻረው :: ይሄም ፍ / ቤቱ ያሣያል ፡፡ በመሆኑም ፍ / ቤቱ በፍ / ብ / ሕ / ቁ . 196 መሠረት የአስተዳደር ክፍል የሰጠውን የባለቤትነት ማስረጃ ደብተር የመሠረዝ ስልጣን እንዳለውና እንደሌለው መመርመሩ አስፈላጊ ሰመሠረቱ የፍ / ብ / ሕ / ቁ .1196 ያሚመላካቲው ኣንድ ያአስተዳደር ክፍል ( አካል ) - የሰጠው የባለቤትነት , ማስረጃ ደብተር በድንጋጌው በተመለከቱት ሁኔታዎች መሆኑን ባረጋገጠ ጊዜ የሰጠውን
የባለቤትነት ማስረጃ ደብተር የሚሰርዝበትን ኣግባብ ነው :: በመሆኑም የሰጠውን
የባለቤትነት ደብተር የመሠረዝ ስልጣን ደብተሩን የሰጠው የአስተዳደር አካል
እንጅ የፍ / ቤት አለመሆኑን ከፍ / ብ / ሕ / ቁ .1198 ( 2 ) አግባብ ጭምር መረዳት የሚቻል ነው :: ይህ ከሆነ ደግሞ የአስተዳደር ክፍሉ የሰጠውን የባለቤትነት
ማስረጃ ደብተር በአስተዳደር ክፍሉ እስካልተሠረዘ ድረስ የባለቤትነት ደብተር
ያለው ሰው በፍ / ብ / ሕ / ቁ .1195 ( 1 ) በተደነገገው መሠረት የቤቱ ባለንብረት
እንደሆነ መቆጠሩ የሚቀርበት የሕግ አግባብ አይታይም ፡፡ በዚህ ረገድ የፌዴራል
ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፌዴራል
ከፍተኛ ፍ / ቤትን ውሣኔ የተቸው ክርክሩ
ሣይቀርብለት ትንታኔ የሰጠው
በአግባቡ
አይደለም
እንጅ ፍ / ቤቱ
የአስተዳደር አካል የሰጠውን የባለቤትነት ማስረጃ ደብተር የመሠረዝ ስልጣን
የለውም በሚል አይደለም ። በመሆኑም የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይህንንም
በከፍተኛ ፍ / ቤት ውሣኔ የሚታየውን ስህተት ሣያስተባብል የቀረበለትን ይግባኝ
በፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕ / ቁ 337 መሠረት የሰረዘው በአግባቡ ሆኖ አልተገኘም ፡፡
ው ሣ ኔ
1 ኛ / አመልካች በስር ፍ / ቤት ያቀረቡት ክስ የክስ ምክንያት የለውም
በማለት ተወስኗል ፡፡
2 ኛ / እንዲሁም በፍ / ብ / ሕ / ቁ .1196 መሠረት ለአከራካሪው ቤት
ከአስተዳደር አካል , የሰጠውን የቤት ባለቤትነት ማስረጃ - ደብተር የመሠረዝ
ሥልጣን ያለው ደብተሩን የሰጠው የአስተዳደር አካል እንጂ ፍ / ቤት እይደለም
በማለት ተወስኗል ።
3 ኛ / ስለሆነም የፌዴራል ጠቅላይ ፍ / ቤት በመ.ቁ 13999 ጥር
14/1996 ዓ.ም በሰጠው ትእዛዝ አመልካች በስር ፍ / ቤት ያቀረቡት ክስ
የሥነ ሥርዓት ሕጉን ተከትሉ የቀረበ እንዳልሆነ ጠቅሶ
የሰጠውን
የሚቀበለው ቢሆንም በመጨረሻ በደረሰበት መደብደሚያ ግን ባለመስማማት
ትእዛዝ በፍ / ብ / ሥ / ሥ ሕግ / ቁ 348 ( 1 ) መሠረት ሽሮታል ።
የማይብብ የእምስት ዳኛች ፊርማ አለበት ።

You must login to view the entire document.

Enter your email address and password to login.
Please enter a valid email address
Please enter your email address
Please enter your password
Password must be at least 8 characters long
Forgot your password?