×
Browse Products About Us Login / Sign Up Contact Us አማርኛ
African Law Archive
Logo
የፍርድ ቤት ውሳኔ 17361

      Sorry, pritning is not allowed

15 በኣለ ጊዜ አወሳሰንና አቆጣጠር የቁት 3 ር ሥነ የፌዴራል ጠቅላይ ፍ / ቤት
ሰበር ሰሚ ችሎት
የመ / ቁ .17361
ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
አቶ ፍሥሐ ወርቅነህ
አቶ አብዱልቃድር መሐመድ
ወ / ሮ ስንዱ ዓለሙ
ወ / ት ሂሩት መለሰ
አመልካች፡- ወ / ሮ ጋዲሴ ኢርጌ
መልስ ሰጪ፡- ወ / ሮ ወርቅአንጥፋ በቀለ
በሙግት ተካፋይ ስለመሆን
ስለተከራካሪ ወገን
መሞትና ስለክሱ
ሥርዓት ህግ ቁጥር 49- ስለ ግዴታዎች መቅረት- ስለ ይርጋ - የፍትሐብሔር ህግ
ቁጥር 1856
አመልካች ከስር ከሳሽ የነበረችውን ወ / ሮ ብሪቱ ብሩን ተክታ ለመከራከር
ያቀረበችው ጥያቄ በፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 49 የተጠቀሰው የጊዜ ገደብ
ካለፈ በኋላ የቀረበ መሆኑን በመግለጽ የስር ፍርድ ቤት ጥያቄዋን ውድቅ በማድረጉ እና
የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤትም ይግባኙን ባለመቀበሉ መልስ ሰጭ ባላነሳችው ክርክር
ፍርድ ቤቶቹ ክሱን ውድቅ በማድረጋቸው የቀረበ አቤቱታ
ው ሳ ኔ፡- የስር ፍ / ቤቶች ውሳኔ ጽንቷል ፡፡
በሥራ ነገር / Substantive / ህጉች የተደነገጉ የይርጋ ደንቦች በሥነ ሥርዓት ሕጎች
ከተደነገጉት የጊዜ ገደቦች የተለዩ ናቸው
2- በስነ ስርዓት ህጎች በግልጽ የሰፈረን የጊዜ ሳይጠብቅ የሚቀርብን ጥያቄ ፍ / ቤት
በራሱ አነሳሽነትም ቢሆን ውድቅ ማድረግ አለበት ፡፡
ቁጥር 17361
ሐምሌ 25 ቀን 1997
ዳኞች መንበረፀሐይ ታደሰ
ፍሥሐ ወርቅነህ አብድልቃድር መሐመድ ስንዱ ዓለሙ ሂሩት መለሰ
አመልካች ወ / ሮ ጋዲሴ ኢርጌ መልስ ሰጪ-- ወ / ሮ ወርቅአንጥፉ በቀለ
የቀረበው ጉዳይ በፍትሀብሄር ሥነ ሥርዓት ሕግ የተመለከቱ የሥነሥርዓት ደንቦች አፈጻጸምን የሚመለከት ነው ፡፡ ጉዳዩ ሊቀርብ የበቃው አመልካች ከስር ከሣሽ የነበረችውን ወ / ሮ ብሪቱ ብሩን ተክታ ለመከራከር ያቀረበችው ጥያቄ የሥር ፍርድ ቤት በፍትሀብሄር ሥነሥርዓት ሕግ ቁጥር 49 የተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ካለፈ በኋላ የቀረበ መሆኑን በመግለጽ ጥያቄዋን ውድቅ በማድረጉ ነው :: ጉዳዩን በይግባኝ ያየው የከፍተኛ ፍ / ቤት ይግባኙን ሳይቀበለው ቀርቷል :: የአሁን አመልካች የሰበር አቤቱታ ዋነኛ የቅሬታ ነጥብም ፍርድ ቤቱ በፍትሐብሔር ሥነሥርዓት ሕግ ቁጥር 49/2 የተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ማንም ተከራካሪ ወገን ሳያነሳው ፍርድ ቤቱ በራሱ አነሣሽነት ተፈጻሚ ማድረጉ ሕጉ ይርጋን በማስመልከት ያስቀመጠውን ሥርዓት የሚጥስ በመሆኑ መሠረታዊ የሕግ ስህተት አለበት ተብሎ ይሻርልኝ የሚል ነው ::
የሰበር ችሎቱ ጉዳዩ በሰበር እንዲታይ በመወሰኑ መልስ ሰጪ በጉዳዩ ላይ መልስ እንዲያቀርብ ተደርጓል ፡፡ የመልሱ መሠረታዊ ይዘት የሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ ምንም የሕግ ስህተት ስለሌለበት ሊፀና ይገባዋል የሚል ነው :: አመልካቿ የመልስ መልስ አቅርባለች :: ይዘቱ ከሰበር ማመልከቻው የተለየ አይደለም ::
በዚህ መዝገብ የቀረበው አቤቱታ በሥረ ነገር ሕጎች ( substantive Laws ) የተደነገጉ የይርጋ ደንቦች በሥነሥርዓት ሕጎች ከተደነገጉት የጊዜ ገደቦች ጋር ተመሳሳይ ናቸው ወይስ አይደሉም ? በሥነ ሥርዓት ሕግ ውስጥ የሚገኙ የጊዜ ገደቦች ፍርድ ቤቶች
ይሆናል ” በማለት ይደነግ ' .ግ የሙግትን ሂደት ለመከታተል የሚያስችሉ የተለያዩ በራሳቸው አነሳሽነት ተፈጻሚነታቸውን ሊከታተሉ ይችላሉ ወይስ እንደሥረነገር የይርጋ ህግ በተከራካሪ ወገን ካልተነሱ እንደተተው ይቆጠራል የሚሉትን የሕግ ነጥቦች የሚያስነሳ ሆኖ አግኝተነዋል :: ከሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ መረዳት እንደቻልነው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአሁን አመልካች ቀደም ብላ ክስ መስርታ የነበረችውን ወ / ሮ ብሪቱ ብሩን ተክታ የፍትሐብሄር ክሱን በወራሽነቷ እንድትቀጥል ያቀረበችውን ጥያቄ ውድቅ ያደረገው ጥያቄው የቀረበው የፍትሀብሄር ሥነሥርዓት ሕግ ቁጥር 49 እንደሚያዘው በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ አልቀረበም በማለት ነው :: የፍትሐብሄር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 49 ( 1 ) ከሣሽ ሲሞት የክሱ መብት ለሌላ የሚተላለፍ የሆነ እንደሆነ የሟቹ ንብረት አስተዳዳሪ ተተክቶ ክሱን ሊቀጥል እንደሚችል የሚፈቅድ ሲሆን የዚሁ ቁጥር ንዑስ ቁጥር ሁለት « ክሱን ለመቀጠል መብት አለን የሚሉት ወገኖች ዋናው ከሣሽ ወይም ከሣሾች በሞቱ በአንድ ዓመት ውስጥ ክሱን ለመቀጠል እንዲፈቀድላቸው ሳያመለክቱ የቀሩ እንደሆነ የተጀመረው ክርክር ወድቅ የፍትሀብሄር ሥነሥርዓት የጊዜ ገደቦችን ያስቀምጣል ፡፡ ይኸው ሕግ የሚያስቀምጣቸውን የጊዜ ገደቦች አፈጻጸም በሚመለከትም በሥነ ሥርዓት ሕጉ ምዕራፍ ሰባት በርካታ ድንጋጌዎች አስፍሮአል :: የሕጉ ቁጥር 192 “ በአንድ ክርክር ላይ መፈፀም ወይም መደረግ የሚገባው ነገር ሲኖርና ይህም የሚፈፀምበት ጊዜ በሕግ ያልተወሰነ ሲሆን የነገሩን አካባቢ ሁኔታ በመመልከት ፍርድ ቤቱ ተገቢ መስሎ የሚታየውን ጊዜ ይወስናል ” በማለት ይደነግጋል :: ይህ ድንጋጌ በሙግት ሂደት የሚከናወኑ ተግባራት በሕግ በተቀመጠው አሊያም ፍርድ ቤቱ በሚወስነው የጊዜ ገደብ ውስጥ መከናወን የሚጠበቅበት መሆኑን የሚያመለክት ነው :: የዚሁ ሕግ ቁጥር 195 “ በዚህ ሕግ በቁጥር 196 የተመለከተው ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ አንድ ነገር እንዲፈፀም ከተወሰነው ጊዜ በኋላ ቢፈፀምም እንዳልተፈፀመ ሆኖ ይቆጠራል » በማለት በተወሰነ የጊዜ ገደብ መፈፀም ያለባቸው ተግባራት ሕጉ ወይም ፍ / ቤቱ ባስቀመጠው ጊዜ ውስጥ ከተከናወኑ ብቻ ሕጋዊ ውጤት ሊያስከትሉ እንደሚችሉ ይደነግጋል :: የሥነ ሥርዓት ሕጎች ዋነኛ ዓላማ ለፍ /
ቤት የሚቀርቡ ክርክሮች ባነሰ ወጪ በተቀላጠፈና ፍትሃዊ በሆነ ሥርዓት እልባት እንዲያገኙ ማድረግ ነው :: በመሆኑም በሥነሥርዓት ህጎች የሰፈሩ የጊዜ ገደቦች አፈጻጸም በአንድ ጉዳይ ካሉት ተከራካሪዎች ባሻገር የሌሎች ተከራካሪዎች ጥቅም ፣ በፍርድ ቤት መኖር ያለበትን የሙግት አመራርና አጠቃላይ የሀብትና የጊዜ አጠቃቀምን የሚመለከቱ ናቸው :: የጊዜ
ገደቦች አለመከበር ለመዘግየት ፣ ለጉዳዮች መከማቸትና መጨናነቅ ምክንያትም ስለሚሆን የሚጎዳው በአንድ ሙግት የሚሳተፉት ብቻ ሳይሆን የሌሎች የፍርድ ቤት ተጠቃሚዎች መብትና ጥቅምም ይነካል ፡፡ ይህ ሁኔታ እንዳይፈጠር የሙግት ሂደት ሥርዓት እንዲይዝ ማድረግ ደግሞ ከተከራካሪዎችም የሚጠበቅ ቢሆንም በዋናነት ግን የፍርድ ቤቱ ሃላፊነት ነው : ይህን ሃላፊነት እንዲወጣ ከሚያደርጉ መንገዶች አንዱ ደግሞ በሥነ ሥርዓት ሕጉ የሰፈሩት የጊዜ ገደቦች በአግባቡ መፈፀማቸውን መከታተልና ያልተፈፀሙ ሆነው ሲገኙ ደግሞ ህጉ እንደሚያዘው ተመጣጣኝ የሆነ እርምጃ መውሰድ ነው ::
በሥነሥርዓት ሕግ የሰፈሩ ጊዜን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች ይዘትና ዓላማ ይርጋን አስመልክቶ በፍትሀብሄር ሕግ ቁጥር 1856 ( 2 ) ከሰፈረውና የይርጋ ጉዳይ በተከራካሪዎች ካልተነሣ በፍርድ ቤት አይነሳም ከሚለው ሕግ የተለየ ነው :: በፍትሀብሄር ሕግ የሰፈረው የይርጋ ሕግ ዋነኛ ዓላማ የተዋዋዮችን ጥቅም መጠበቅ ነው :: የዚሁ መብት ተጠቃሚ የሆነ ተከሣሽ ይርጋውን ካላነሣም የሚጎዳው እሱ ብቻ ነው :: ስለሆነም ወገን የተወውን መብት ፍርድ ቤት በራሱ አነሣሽነት እንዲያነሣው አይፈቀድም ፡፡ በሥነሥርዓት ሕጉ የተቀመጡ የጊዜ ገደቦች መከበር አለመከበራቸውን ግን ፍርድ ቤቱ የመከታተል ሃላፊነት አለበት :: በተከራካሪ ወገን ባይነሣ እንኳን በሥነ ሥርዓት ሕጉ ቁጥር 195 እንደተደነገገው ጊዜው ካለፈ በኋላ የተከናወነው ነገር ሁሉ እንዳልተፈፀመ ሆኖ ስለሚቆጠር የሥነሥርዓት የጊዜ ገደቦች ለተሟጋቾች ብቻ ሳይሆን ፍርድ ቤቱንም ጭምር የሚመለከቱ ናቸው :: በመሆኑም በሥነሥርዓት ሕጉ በግልጽ የሰፈረ የጊዜ ገደብ ካለፈ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም ጉዳይ ፍርድ ቤቱ በራሱ አነሳሽነትም ቢሆን ውድቅ ማድረጉ ትክክለኛው አካሄድ ነው ::
አሁን በቀረበልን ጉዳይ የአሁኗ አመልካች ጥያቄዋን ለፍርድ ቤቱ ያቀረበችው የቀድሞዋ ተከራካሪ የወ / ሮ ብሪቱ ብሩ ወራሽ መሆንዋን ካረጋገጠች ከ 3 ዓመት በኋላ ነው :: ከመዝገቡ ለመረዳት እንደተቻለው የወራሽነት ውሣኔ ያገኘችው ሐምሌ 15/91 ሲሆን ለፍርድ ቤቱ ጥያቄዋን ያቀረበችው ደግሞ ጥር 2 ዐ / 1994 ነው :: ይህም የሥነ
ሥርዓት ሕጉ ቁጥር 49 ያስቀመጠው የአንድ አመት የጊዜ ገደብ ማለፉን የሚያረጋግጥ ነው :: በሕግ የሰፈረውን ጊዜ ገደብ ያልጠበቀ ነገር የተሟጋችን ተቃውሞ ሳይጠብቅ ፍርድ ቤቱ ራሱ ውድቅ ማድረጉ ደግሞ ትክክለኛ የጉዳይ አመራር እንጂ ስህተት መፈፀሙን የሚያመለክት አይደለም ::
1. የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት በመዝገብ ቁጥር 2 ዐ 576 ግንቦት 1 ቀን
1975 የሰጠው ውሣኔ እና ከፍተኛ ፍ / ቤት በመቁ .22451 ሐምሌ 21 ቀን 1996
የሰጠው ውሣኔ ፀንተዋል :: 2. ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻሉ ፡፡

You must login to view the entire document.

Enter your email address and password to login.
Please enter a valid email address
Please enter your email address
Please enter your password
Password must be at least 8 characters long
Forgot your password?