×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፲፬/፲፱፻፵፯ ዓም የኢሚግሬሽን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አሥራ አንደኛ ዓመት ቁጥር ፬ አዲስ አበባ - ጥቅምት ፲ ቀን ፲፱፻፯ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፲፬ / ፲፱፻፲፯ ዓም • “ የኢሚግሬሽን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ .. ገጽ ፪ሺ፱፲፰ | “ Immigration Council of Ministers Regulations Page 2918 የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፲፬ / ፲፱፻፲፯ ስለኢሚግሬሽን የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፷፯ አንቀጽ ፩ እና በኢሚግሬሽን | pursuant to Article 5 of the Definition ofPowersand Duties of አዋጅ ቁጥር ፪፻፶፬ / ፲፱፻፲፭ አንቀጽ ፳፩ መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ። ክፍል አንድ ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የኢሚግሬሽን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፲፬ / ፲፱፻፲፯ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ፪ . ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ ደንብ ውስጥ ፤ ፩ “ የቤተሰብ አባል ” ማለት የአንድ ሰው የትዳር ጓደኛ ወይም በሥሩ የሚተዳደር ልጅ ወይም ጥገኛ የሆነ ሌላ ሰው ነው ፤ “ መደበኛ መኖሪያ ቦታ ” ማለት በኢትዮጵያ የፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር ፩፻፷፫ የተደነገገውን ትርጓሜ የሚያሟላ የአንድ ሰው መኖሪያ ቦታ ነው ፤ ፫ “ ባለሥልጣን ” ማለት የደህንነት ፣ የኢሚግሬሽንና የስደ ተኞች ጉዳይ ባለሥልጣን ነው ፤ ፬ . “ ሚኒስቴር ” ማለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው ፤ ፭ “ አዋጅ ” ማለት የኢሚግሬሽን አዋጅ ቁጥር ፫፻፵፬ | ፲፱፻፲፭ ነው ፡፡ ያንዱ ዋጋ 4.40 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፰ሺ፩ ገጽ ፪ሺ፱፻፳፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፩ ጥቅምት፫ ቀን ፲፱ጀ፯ ዓ • ም • ፴፱ : ስለተሻሩ ሕጎች የጉዞ ሰነዶችና ቪዛዎች ኣሰጣጥ ደንብ ቁጥር ፫፻፲፭ / ፲፱፻፳፫ እንደተሻሻለ / እና የቪዛና የመኖሪያ ፈቃድ አገልግሎት ዋጋን እንዲሁም የመውጫና የመግቢያ በሮችን የሚወስነውደንብ ቁጥር ፫፻፬ / ፲፱፻፳፫ / እንደተሻሻለ / በዚህ ደንብ ተሽረዋል ። Ø የመሸጋገሪያ ድንጋጌ ይህ ደንብ ከመጽናቱ በፊት ለረጅም ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ የኖሩና በዚህ ደንብ ከአንቀጽ ፳፮ እስከ ፳፬ በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሠረት የሚጠየቁ ሁኔታዎችን ሊያሟሉ የማይችሉ የውጭ ኮሙዩኒቲ አባላት የሚመዘገቡበትና የመኖሪያ ፈቃድ የሚያገኙበት ሁኔታ ባለሥልጣኑ በሚያ ወጣው መመሪያ ይወሰናል ። ፴፩ ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ ይህ ደንብ ከመስከረም ፩ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓም ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ጥቅምት ፲ ቀን ፲፱፻፵፯ ዓ.ም መለሰ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ገጽ ፪ሺ፱፻፳፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር 8 ጥቅምት ፲ ቀን ፲፱፻፵፯ ዓም : ሠንጠረዥ አንድ ለጉዞ ሰነዶች የሚከፈል የአገልግሎት ዋጋ የጉዞ ሰነዱ ዓይነት ዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ሰርቪስ ፓስፖርት መደበኛ ፓስፖርት ሀ / በአገር ውስጥ ሲሰጥ ፩ ተማሪዎች ላልሆኑ ፪ / ለተማሪዎች ለ በውጭ አገር ሲሰጥ ፩ / ተማሪዎች ላልሆኑ ፪ ለተማሪዎች የሐጂና ኡምራ መጓጓዣ ፓስፖርት የውጭ አገር ሰው ፓስፖርት የይለፍ ሰነድ አስቸኳይ የጉዞ ሰነድ የስደተኞች የጉዞ ሰነድ ሠንጠረዥ ሁለት ለቪዛዎች የሚከፈል የአገልግሎት ዋጋ የቪዛው ዓይነት ዲፕሎማቲክ ቪዛ ሰርቪስ ቪዛ የሥራ ቪዛ ሀ / የአንድ ጊዜ መግቢያ ለ / በሦስት ወር የብዙ ጊዜ መመላለሻ ሐ / በስድስት ወር የብዙ ጊዜ መመላለሻ መ / በአንድ ዓመት የብዙ ጊዜ መመላለሻ የመኖሪያ ቪዛ የቱሪስት ቪዛ ሀ / የአንድ ጊዜ መግቢያ ለ / በሦስት ወር የብዙ ጊዜ መመላለሻ ሐ / በስድስት ወር የብዙ ጊዜ መመላለሻ ትራንዚት ቪዛ ሀ [ ለአንድ ጊዜ ትራንዚት ለ / ለሁለት ጊዜ ትራንዚት የተማሪ ቪዛ ሠንጠረዥ ሦስት ለመኖሪያ ፈቃድና ለመታወቂያ የሚከፈል የአገልግሎት ዋጋ የአገልግሎት ዓይነት ጊዜያዊ መኖሪያ ፈቃድ ሀተማሪ ላልሆኑ ለተማሪ ለሆኑ ቋሚ መኖሪያ ፈቃድ የኢትዮጵያ ዜግነት በሕግ ለተሰጠው የውጭ አገር ሰው የሚሰጥ የምስክር ልዩ ልዩ መታወቂያዎች ገጽ ፪ሺ፱፻፲፱ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፬ ጥቅምት ፲ ቀን ፲፱፻፵፯ ዓም ክፍል ሁለት ስለጉዞ ሰነዶች አሰጣጥ ሁኔታ ፫ የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ፩ የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ለሚከተሉት ይሰጣል ፤ ሀ ) በውጭ አገር በኢትዮጵያ ኤምባሲዎች እና ቋሚ መልዕክተኛ ወይም ቆንስላ ጽሕፈት ቤቶች ለሚመደቡ አምባሳደሮች ፣ የዲፕሎማቲክ ወኪሎች ፣ አታሼዎች ፣ የቆንስላ ወኪሎች እና ለነዚሁ የትዳር ጓዶች ፤ ለ ) የኢትዮጵያ መንግሥትን በመወከል በጉባዔ ወይም በስብሰባ ለመሳተፍ ወይም ለሌላ የመንግሥት ሥራ ወደ ውጭ አገር ለሚሄዱ ደረጃቸው ሚኒስቴሩ በሚያወጣው መመሪያ ለሚወሰን መል ዕክተኞች ፣ ሐ ) በልዩ ልዩ ምክንያት ወደ ውጭ አገር ለሚሄዱ ደረጃቸው ሚኒስቴሩ በሚያወጣው መመሪያ ለሚወሰን የመንግሥት ባለሥልጣኖች መ ) በዓለም አቀፍና አህጉራዊ ድርጅቶች ለሚሠሩና የዲፕሎማቲክ ደረጃ ላላቸው ኢትዮጵያውያን እና ለነዚሁ የትዳር ጓደኞች ፣ ) ሚኒስቴሩ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ከፍተኛ ክብር ለሚሰጣቸው ሰዎች ። ፪ . የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት እንዲሰጥ ጉዳዩ የሚመለ ከተው መሥሪያ ቤት ወይም እንደ ሁኔታው ኣመልካቹ ራሱ ለሚኒስቴሩ በሚያቀርበው ማመልከቻ ላይ የዲፕሎ ማቲክ ፓስፖርት ለማሰጠት የሚያበቃው ምክንያት በግልጽ መጠቀስ አለበት ። ፬ ሰርቪስ ፓስፖርት ፩ ሰርቪስ ፓስፖርት ለሚከተሉት ይሰጣል ፤ ሀ ) በኢትዮጵያ ኤምባሲዎች እና ቋሚ መልክተኛ ወይም ቆንስላ ጽ / ቤቶች በሠራተኛነት ለሚመደቡ ኢትዮጵያውያን ፤ ለ ) በዚህ ደንብ አንቀጽ ፫ ላልተመለከቱና ለመን ግሥት ሥራ ወደ ውጭ አገር ለሚሄዱ ኢትዮጵያ ሐ ) በዚህ ደንብ አንቀጽ ፪ ንዑስ አንቀጽ ፩ / ሀ / መሠረት የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ለተሰጣቸው ሰዎች ቤተሰብ አባላት ፤ መ ) በዓለም አቀፍና አህጉራዊ ድርጅቶች ውስጥ ለሚሠሩና ኢትዮጵያዊ ለሆኑ ዓለም አቀፍ ሲቪል ሠራተኞች እና ለነዚሁ የትዳር ጓደኞች ፤ ፪ • ሰርቪስ ፓስፖርት እንዲሰጥ ጉዳዩ የሚመለከተው መሥሪያ ቤት ወይም እንደ ሁኔታው አመልካቹ ራሱ ለሚኒስቴሩ በሚያቀርበው ማመልከቻ ላይ ሰርቪስ ፓስፖርት ለማሰጠት የሚያበቃው ምክንያት በግልጽ መጠቀስ አለበት ። ፭ መደበኛ ፓስፖርት መደበኛ ፓስፖርት ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሲያመለክት ይሰጣል ። ፮ የሐጂና ኡምራ ፓስፖርት ለሐጂና ኡምራ ፀሎት ተጓዦች አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የሐጂና ኡምራ ፓስፖርት ሊሰጥ ይችላል ። ፯ የውጭ አገር ሰው ፓስፖርት የውጭ አገር ሰውፓስፖርት በኢትዮጵያ ነዋሪ ለሆነናከአገሩ መንግሥት የጉዞ ሰነድ ለመቀበል ላልቻለ የውጭ አገር ሰው ወይም ዜግነት ለሌለው ሰው ይሰጣል ። ገጽ ፪ሺ፱፻፳ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፬ ጥቅምት ፲ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓም ፰ : የይለፍ ሰነድ የይለፍ ሰነድ ፓስፖርት ለሌለውና ከውጭ ወደ አገሩ ለሚመለስ ኢትዮጵያዊ ይሰጣል ። ፱ . አስቸኳይ የጉዞ ሰነድ ፩ አስቸኳይ የጉዞ ሰነድ ከኢትዮጵያ ለሚወጣና ከአገሩ መንግሥት የጉዞ ሰነድ ለመቀበል ላልቻለ የውጭ አገር ሰው ወይም ዜግነት ለሌለው ሰው ይሰጣል ። ፪ . የአስቸኳይ የጉዞ ሰነድ የሚያገለግለው ለአንድ ጊዜ መውጫ ብቻ ነው ። የስደተኞች የጉዞ ሰነድ ፩ . የስደተኞች የጉዞ ሰነድ ኢትዮጵያ ውስጥ በስደተኛነት ለታወቁ ሰዎች ይሰጣል ። ፪ • የስደተኞች የጉዞ ሰነድ ለመውጫ ብቻ ወይም ለደርሶ መልስ ሊሰጥ ይችላል ። ፲፩ • የጉዞ ሰነዶች ፀንተው ስለሚቆዩበት ጊዜ የጉዞ ሰነዶች ፀንተው የሚቆዩበት ጊዜ እንደሚከተለው ሀ ) የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት አምስት ዓመት ለ ሰርቪስ ፓስፖርት አምስት ዓመት ሐ ) መደበኛ ፓስፖርት አምስት ዓመት የሐጂና ኡምራ ፓስፖርት ....... አንድ ዓመት የውጭ አገር ሰው ፓስፖርት አንድ ዓመት ረ ) የይለፍ ሰነድ እስከ ስድስት ወር አስቸኳይ የጉዞ ሰነድ እስከ ሦስት ወር ሸ ) የስደተኞች የጉዞ ሰነድ ........ አንድ ዓመት ፪ : የጉዞ ሰነድ ሲጠፋ ፣ ሲበላሽ ወይም ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ሲያበቃ በአዲስ የጉዞ ሰነድ እንዲተካ መጠየቅ ይቻላል ። ፲፪ : የጉዞ ሰነዶች ዝግጅት ፩ የሁሉንም ዓይነት የጉዞ ሰነዶች ቅርጽና ይዘት የመወ ሰንና የማሳተምኃላፊነት የባለሥልጣኑይሆናል ። ሆኖም የዲፕሎማቲክና ሰርቪስ ፓስፖርቶችን በሚመለከት ባለ ሥልጣኑበቅድሚያከሚኒስቴሩጋር መመካከር አለበት ። ፪ የዲፕሎማቲክና ሰርቪስ ፓስፖርቶች የሚሰጡት በሚኒ ስቴሩ ቢሆንም ለእያንዳንዱ አመልካች ለመስጠት የሚዘ ጋጁት በባለሥልጣኑ ይሆናል ። ክፍል ሦስት ስለቪዛዎች አሰጣጥ ሁኔታ ፲፫ : ጠቅላላ በዚህ ደንብ መሠረት ማንኛውም የመግቢያ ቪዛ ከመሰጠቱ በፊት ጠያቂው በአዋጁ አንቀጽ ፭ መሠረት ቪዛ የሚያስከለ ክለው ሁኔታ አለመኖሩ መረጋገጠ አለበት ። ፲፬ የዲፕሎማቲክ ቪዛ ፩ ዲፕሎማቲክ ቪዛ ለሚከተሉት የውጭ አገር ሰዎች ይሰጣል ፤ ሀ ) በኢትዮጵያ በሚገኙ የውጭ አገርኤምባሲዎችእና ቋሚ መልእክተኛ ወይም ቆንስላ ጽሕፈት ቤቶች ለሚመደቡ አምባሳደሮች ፣ የዲፕሎማቲክ ወኪሎች ፣ አታሼዎች ፣ የቆንስላ ወኪሎች እና ለእነዚሁ የትዳር ጓደኞች ፣ ለ ) የዲፕሎማቲክ ደረጃ ላላቸው ተቀማጭነታቸው በኢትዮጵያ የሆኑ የዓለም አቀፋዊና አህጉራዊ ድርጅቶች ኃላፊዎችና ለእነዚሁ የትዳር ጓደኞች ፣ ሐ ) ለመንግሥት ሥራ ጉዳይ ወደ ኢትዮጵያ ለሚገቡ ወይም ኢትዮጵያን አቋርጠው ወደ ሌላ አገር ለሚሄዱ የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ለያዙ የውጭ አገር ሰዎች ። ገጽ ፪ሺ፱፻፳፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፬ ጥቅምት ፲ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓ • ም • በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ / ፩ መሠረት ዲፕሎማቲክ ቪዛ የሚሰጠው ከጠያቂው አገር የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ፣ ኤምባሲ ፣ ቋሚ መልዕክተኛ ወይም ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ወይም ከሚመለከተው ዓለም አቀፋዊ ወይም አህጉራዊ ድርጅት የዲፕሎማቲክ ኖት ሲቀርብ ፲፭ ሰርቪስ ቪዛ ፩ ሰርቪስ ቪዛ ለሚከተሉት የውጭ አገር ሰዎች ይሰጣል ፤ ሀ ) በኢትዮጵያ በሚገኙየውጭ አገር ኤምባሲዎችእና ቋሚ መልእክተኛና ቆንስላ ጽሕፈት ቤቶች ውስጥ በቋሚነት ተመድበው ለሚሰሩና ፓስፖርት ለያዙ ሠራተኞችና ለቤተሰቦቻቸው አባላት ፣ ለ ) ተቀማጭነታቸው ኢትዮጵያ ውስጥ በሆኑ ዓለም አቀፋዊ ወይም አህጉራዊ ድርጅቶች ውስጥ ተመድበው ለሚሠሩ የዓለም አቀፍ ሲቪል ሠራተኞች እና ለቤተሰቦቻቸው አባላት ፤ ሐ ) ለመንግሥት ሥራ ጉዳይ ወደ ኢትዮጵያ ለሚገቡ ወይም ኢትዮጵያን አቋርጠው ወደ ሌላ አገር ለሚሄዱ ሰርቪስ ፓስፖርት ለያዙ የውጭ አገር መ ) በዚህ ደንብ አንቀጽ ፲፬ / ፩ / ( ሀ ) እና ( ለ ) መሠረት የዲፕሎማቲክ ቪዛ ለሚሰጣቸው ሰዎች ቤተሰብ አባላት ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ / ፩ / መሠረት ሰርቪስ ቪዛ የሚሰጠው ከጠያቂው አገርየውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ኤምባሲ ፣ ቋሚ መልዕክተኛ ወይም ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ወይም ከሚመለከተው ዓለም አቀፋዊ ወይም አህጉራዊ ድርጅት የዲፕሎማቲክ ኖት ሲቀርብ ነው ። ፲፮ የሥራ ቪዛ የሥራ ቪዛ በሚከተሉት ምክንያቶች ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ የውጭ አገር ሰዎች ይሰጣል ፤ ሀ ) በኢንቨስትመንት ሥራ ለመሰማራት ፤ ለ ) የሥራ ፈቃድን በሚመለከት አግባብ ባለው ሕግ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ፣ በማንኛውም የሥራ መስክ ተቀጥረው ለመሥራት ፤ ሐ ) ከውጭ አገር መንግሥት ፣ ከዓለም አቀፍ ወይም አህጉራዊ ድርጅት ወይም መንግሥታዊ ካልሆነ ድርጅት ጋር በተደረገ ስምምነት መሠረት የተለያዩ ሥራዎች ለመሥራት ፤ መ ) ለበጎ አድራጎት ሥራ ያለደመወዝ ለማገልገል ፤ ሠ ) ኢትዮጵያ ውስጥ በሚካሄድ ሲምፖዚየም ፣ ኢግዚ ቢሽን ፣ ዓውደ ጥናት ወይም በመሳሰሉት ዝግጅቶች ለመሳተፍ ወይም ሥልጠና ለመስጠት ፤ ረ ) ለጥናትና ምርምር ፤ ሰ ) ለመገናኛ ብዙኃን ሥራ ። ፪ . የሥራ ቪዛ ለአንድ ጊዜ መግቢያ ወይም ለብዙ ጊዜ መመላለሻ እንዲያገለግል ሊሰጥ ይችላል ። ፲፯ የመኖሪያ ቪዛ የመኖሪያ ቪዛ የሚሰጠው ለሚከተሉት ይሆናል ፤ ፩ . በኢትዮጵያ ውስጥ ለመኖር ለሚመጡ በኢትዮጵያዊያን ጉዲፈቻ ለተደረጉ ወይም ከኢትዮጵያ ዜጎች ጋር የፀና ጋብቻ ላላቸው የውጭ አገር ሰዎችና ለቤተሰቦቻቸው ኣባላት ፤ ፪ • ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲኖሩ ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ለተሰጣቸው የውጭ አገር ሰዎች ቤተሰብ አባላት ፤ ፫ ጥቅም የሚያገኙበትን ማናቸውንም ሥራ ሳይሠሩና ለአገሪቱ ሸክም ሳይሆኑ በኢትዮጵያ ውስጥ ለመኖር ለሚመጡ የውጭ አገር ሰዎችና ለቤተሰቦቻቸው ኣባላት ። በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ይወሰና ር . ገጽ ፪ሺ፱፻፳፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፬ ጥቅምት ፲ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓም ፲፰ የቱሪስት ቪዛ ፩ የቱሪስት ቪዛ የሚሰጠው ለጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ የውጭ አገር ሰዎች ይሆናል ። ፪ • የቱሪስት ቪዛ ከመሰጠቱ በፊት በአዋጁ አንቀጽ ፫ / ፪ / የተደነገጉት ሁኔታዎች መሟላታቸው መረጋገጥ አለበት ። ፫ የቱሪስት ቪዛ ለአንድ ጊዜ መግቢያ ወይም ለብዙ ጊዜ መመላለሻ እንዲያገለግል ሊሰጥ ይችላል ። ፬ • በቱሪስት ቪዛ ወደ ኢትዮጵያ የገባ ማንኛውም ቀውጭ አገር ሰው በኢትዮጵያ ውስጥ ማናቸውንም ሥራ እንዲሠራ አይፈቀድለትም ። ፲፱ • የትራንዚት ቪዛ ፩ የትራንዚት ቪዛ የሚሰጠው ኢትዮጵያን አቋርጦ ወደሌላ አገር ለሚሄድ የውጭ አገር ሰው ነው ። ፪ • የትራንዚት ቪዛ ከመሰጠቱ በፊት በአዋጁ አንቀጽ ፫ / ፪ / የተደነገጉት ሁኔታዎች መሟላታቸው መረጋገጥ አለበት ። ፫ የትራንዚት ቪዛ ለአንድ ጊዜ ወይም ለደርሶ መልስ ትራንዚት እንዲያገለግል ተደርጎ ሊሰጥ ይችላል ። ፳ የተማሪ ቪዛ ፩ . የተማሪ ቪዛ የሚሰጠው ለትምህርት ወይም ለሥልጠና ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጣ የውጭ አገር ሰው ይሆናል ። ፪ . የተማሪ ቪዛ ከመሰጠቱ በፊት ፣ ሀ ) በኢትዮጵያ ውስጥ ትምህርቱን ወይም ሥልጠ ናውን የሚሰጠው የትምህርት ተቋም የተቀበለው ስለመሆኑ ፣ እና ለ ) የትምህርትና የመኖሪያ ወጪው ስለሚሸፈንበት ሁኔታ ፣ የሚገልጽ ማረጋገጫ ጠያቂው ማቅረብ አለበት ። ፳፩ ቪዛዎች ፀንተው ስለሚቆዩበት ጊዜ ፩ የዲፕሎማቲክና ሰርቪስ ቪዛዎች ፀንተው የሚቆዩበት ጊዜ ሚኒስቴሩ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ይወሰናል ። ፪ • ሌሎች ቪዛዎች ፀንተው የሚቆዩበት ጊዜ ባለሥልጣኑ ክፍል አራት የጉዞ ሰነዶችንና ቪዛዎችን ለማግኘት ስለሚቀርብ ማመልከቻ ፳፪ • የጉዞ ሰነዶችን ለማግኘት ስለሚቀርብ ማመልከቻ ፩ . የዲፕሎማቲክና ፓስፖርት ለማግኘት ማመልከቻ የሚቀርበው ለሚኒስቴሩ ይሆናል ። ሚኒስቴሩ ማመልከቻውን መርምሮ ፓስፖርቱ እንዲ ሰጥ ሲወስን በዚህ ደንብ አንቀጽ ፲፪ መሠረት ለፓስፖርቱ ዝግጅት የሚያስፈልጉመረጃዎችን ለባለሥ ልጣኑ ያስተላልፋል ። ፪ • የይለፍ ሰነድ ለማግኘት ማመልከቻ የሚቀርበው ለኢት ዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽሕፈት ቤቶች ይሆናል ። የዚህ ደንብ አንቀጽ ፳፬ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆኖ ፣ ሌሎች የጉዞ ሰነዶችን ለማግኘት ማመልከት የሚቀ ርበው ለባለሥልጣኑ ይሆናል ። የጉዞ ሰነዶችን ለማግኘት የሚቀርብ ማመልከቻ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀ ቅጽ ተሞልቶና አግባብ ባለው አካል ከተሰጠ መታወቂያ ወረቀት ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት ። ፭ አመልካቹ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ከተመለከቱት በተጨማሪ ፎቶግራፉንና የጣት አሻራውን መስጠት አለበት ። ገጽ ፪ሺ፱፻፳፫ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፬ ጥቅምት ፲ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓም : ፳፫ ቪዛዎችን ለማግኘት ስለሚቀርብ ማመልከቻ ፩ የዲፕሎማቲክና ሰርቪስ ቪዛዎች ለማግኘት ማመልከ ቻዎች የሚቀርቡት ለሚኒስቴሩ ወይም ለኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽሕፈት ቤቶች ይሆናል ። ፪ • ሌሎች ቪዛዎችን ለማግኘት ማመልከቻዎች የሚቀ ርቡት ለባለሥልጣኑ ወይም ለኢትዮጵያ ኤምባሲዎች እና ቆንስላ ጽ / ቤቶች ይሆናል ። ፫ ቪዛን ለማግኘት የሚቀርብ ማመልከቻ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀ ቅጽ ተሞልቶና ከጸና የጉዞ ሰነድን እንደአስፈ ላጊነቱ ከጸና የጤና የምስክር ወረቀት ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት ። ፳፬ • የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽሕፈት ቤቶች የጉዞ ሰነዶችንና ቪዛዎችን ስለሚሰጡበት ሁኔታ ፩ • የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽሕፈት ቤቶች ፣ ሀ ) በዚህ ደንብ አንቀጽ ፰ መሠረት የይለፍ ሰነድ ይሰጣሉ ፤ ለ ) ከይለፍ ሰነድ እና ከዲፕሎማቲክና ሰርቪስ ፓስፖ ርቶች በስተቀር ሌሎች የጉዞ ሰነዶችን በሚመ ለከት የሚቀርቡላቸውን ማመልከቻዎች ተቀብ ለው መሟላታቸውን ሲያረጋግጡ ለባለሥልጣኑ ያስተላልፋሉ ፤ የጉዞ ሰነዶቹ በባለሥልጣኑ ተዘጋ ጅተው ሲላኩላቸውም ለአመልካቾቹ ይሰጣሉ ። ፪ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽሕፈት ቤቶች የዚህን ደንብ ድንጋጌዎችና በዚህ ደንብ አንቀጽ ፴፰ መሠረት በሚኒስቴሩና በባለሥልጣኑ የወጡ መመሪያ ዎችን በመከተል ቪዛዎችን ይሰጣሉ ። የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ / ፪ / ድንጋጌ ቢኖርም የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽሕፈት ቤቶች የመኖሪያ ቪዛ ወይም የተማሪ ቪዛ ከመስጠታቸው በፊት የባለሥልጣኑን ስምምነት ማግኘት አለባቸው ። ፳፭ በመግቢያ በሮች ላይ ቪዛ ስለሚሰጥበት ሁኔታ በመግቢያ በሮች ላይ ቪዛ ለመስጠት የሚያስችሉ ሁኔታዎች በዚህ ደንብ አንቀጽ ፴፰ መሠረት ሚኒስቴሩና ባለሥልጣኑ በሚያወጧቸው መመሪያዎች ይወሰናሉ ። ክፍል አምስት ስለውጭ አገር ሰዎች ምዝገባና መኖሪያ ፈቃድ ፳፮ : ስለምዝገባ ፩ . በአዋጁ አንቀጽ ፲፫ መሠረት ለምዝገባ የሚቀርብ ማንኛውም የውጭ አገር ሰው ማመልከቻውን ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀ ቅጽ ሞልቶ ከሚከተሉት ጋር አያይዞ የማቅረብ እና የሚቀርብለትን ጥያቄ በትክክል የመመለስ ግዴታ አለበት ፤ ሀ ) እንደአግባቡ የጸና የጉዞ ሰነድ ፤ ለ ) ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖርበትን ወይም ከዘጠና ቀናት በላይ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚቆይበትን ምክንያት የሚያረጋግጥ ማስረጃ ፤ እና ሐ ) ባለሥልጣኑ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት የሚጠየቁ ሌሎች መረጃዎችና ሰነዶች ። ፪ • አመልካቹ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ከተመለ ከቱት በተጨማሪ ፎቶግራፉን መስጠት አለበት ። ገጽ ፪ሺ፱፻፳፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፬ ጥቅምት ፲ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓም ፳፯ ስለመኖሪያ ፈቃድ በዚህ ደንብ በአንቀጽ ፳፮ መሠረት የተመዘገበ ማንኛውም የውጭ አገር ሰው በዚህ ደንብ መሠረት የሚጠየቀውን የመኖሪያ ፈቃድ አገልግሎት ክፍያ ከፈጸመ በኋላ እንደሁኔታው በዚህ ደንብ አንቀጽ ፳፰ ወይም ፳፱ መሠረት ቋሚ ወይም ጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃድ ይሰጠዋል ። ፪ የመኖሪያ ፈቃድ የተሰጠው ማንኛውም የውጭ አገር ሰው በምዝገባ ወቅት ባስመዘገባቸው መረጃዎች ላይ በተለይም የስም ፣ የዜግነት ፣ የሥራ ፣ የጋብቻ ወይም የሥራ ወይም የመኖሪያ አድራሻ ለውጥ ሲኖር ለውጡ ባጋጠመ በ፴ ቀናት ውስጥ ለባለሥልጣኑ ማስታወቅ አለበት ። ፫ አግባብ ባላቸው ባለሥልጣኖች በሚጠየቅበት ጊዜ ማንኛውም የውጭ አገር ሰው እንደአግባቡ የመኖሪያ ፈቃዱን ፣ በአዋጁ አንቀጽ ፲፬ / ፪ / የተመለከተውን የመታወቂያ ወረቀት ወይም ወደ ኢትዮጵያ የገባበትን የጉዞ ሰነድ የማቅረብ ግዴታ አለበት ። ፳፰ ስለቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ፩ . በዚህ ደንብ አንቀጽ ፲፯ ንዑስ አንቀጽ / ፩ / ወይም / ፪ / መሠረት በመኖሪያ ቪዛ ወደ ኢትዮጵያ ለገቡ የውጭ አገር ሰዎች ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ይሰጣል ። ፪ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ / ፩ / እንደተጠበቀ ሆኖ ፣ ሀ ) መደበኛ መኖሪያውን ኢትዮጵያ ውስጥ ለመሠ ረተና ማመልከቻውን እስካቀረበበት ቀን ድረስ ቢያንስ ለሦስት ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ ለ ) እራሱንና ቤተሰቡን ለማስተዳደር የሚያስችል ሕጋዊ የገቢ ምንጭ ላለው ፣ እና ሐ ) መልካም ሥነ ምግባር ላለው ፣ የውጭ አገር ሰው ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ሊሰጥ ይችላል ። የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ / ፪ ድንጋጌ ቢኖርም ከኢትዮጵያ ዜጋ ጋር የፀና ጋብቻ የፈጸመ የውጭ አገር ሰው ጋብቻው ከተፈጸመ ከአንድ ዓመት ያላነሰ ጊዜ የሞላው ከሆነ ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ሊሰጠው ይችላል ። ፬ . በኢትዮጵያ ውስጥ በኢንቨስትመንት ወይም በበጎ አድራጎት ሥራ ላይ የተሠማራ ወይም ለኢትዮጵያ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከተ ወይም ሊያበረክት ይችላል ተብሎ የሚገመት የውጭ አገር ሰው በዚህ አንቀጽንዑስ አንቀጽ ፪ / ሀ / የተመለከተውን የጊዜ ገደብ ባያሟላም ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ሊሰጠው ይችላል ። ፭ ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ የተሰጠው የውጭ አገር ሰው አግባብ ባላቸው ሕጎች መሠረት የሥራ ወይም የኢንቨስ ትመንት ፈቃድ ይሰጠዋል ። ፳፱ ጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃድ ስለሚሰጥበት ሁኔታ በዚህ ደንብ አንቀጽ ፳፮ መሠረት የተመዘገበና ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ሊሰጠው የማይችልማንኛውም የውጭ አገር ሰው ጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃድ ይሰጠዋል ። ፪ ጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሚያገለግለው ከተሰጠበት ቀን ጀምሮከአንድ ዓመትላልበለጠጊዜ ሆኖከዚያ በላይ መቆየት ካስፈለገ ፀንቶ የሚቆይበትጊዜ ሲያበቃ በአዲስ መተካት አለበት ። ገጽ ፪ሺ፱፻፳፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፬ ጥቅምት ፲ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓም ፴ የመኖሪያ ፈቃድ ስለሚሰረዝበት ሁኔታ ፩ . የመኖሪያ ፈቃዱ የተገኘው ሐሰተኛ ማስረጃ በማቅረብ መሆኑ ሲታወቅ ሊሠረዝ ይችላል ። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ / ፩ / ከተመለከቱት በተጨማሪ ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ በሚከተሉት ሌሎች ምክንያቶች ሊሰረዝ ይችላል ፤ ሀ ) ባለፈቃዱ ኢትዮጵያን ለቅቆ በውጭ አገር በተከ ታታይ ከአንድ ዓመት በላይ ከኖረ ፣ ወይም ለ ) ፈቃዱ የተገኘው የመኖሪያ ፈቃድ ማግኘትን ለማ መቻቸት ሲባል ብቻ በተፈጸመ ጋብቻ ምክንያት ሆኖ ከተገኘ ። ፴፩ የመኖሪያ ፈቃድን ስለመመለስ የመኖሪያ ፈቃድ የተሰጠው ማንኛውም የውጭ አገር ሰው ኢትዮጵያን ለዘለቄታው ለቅቆ ሲሄድ የተሰጠውን የመኖሪያ ፈቃድ ለባለሥልጣኑ መመለስ ይኖርበታል ። ክፍል ስድስት ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች ስለሚጠየቁ ክፍያዎች ፴፪ የክፍያዎች መጠን ፩ ለጉዞ ሰነዶችየሚከፈለው የአገልግሎትዋጋ ከዚህ ደንብ ጋር በተያያዘው ሠንጠረዥ አንድ የተመለከተው ይሆናል ። ፪ . ለቪዛ የሚከፈለው የአገልግሎት ዋጋ ከዚህ ደንብ ጋር በተያያዘው ሠንጠረዥ ሁለት የተመለከተው ይኖራል ። ፫ ለመኖሪያ ፈቃድናልዩልዩ መታወቂያዎች የሚከፈለው የአገልግሎት ዋጋ ከዚህ ደንብ ጋር በተያያዘው ሠንጠረዥ ሦስት የተመለከተው ይሆናል ። የጉዞ ሰነድ ፣ የመኖሪያ ፈቃድ ወይም መታወቂያ ተበላሽቶ ወይም ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ አብቅቶ በአዲስ ሲተካ የመደበኛው ሙሉ ክፍያ ይፈጸማል ፤ ሆኖም ጠፍቶ ሲተካ በመደበኛው ክፍያ ላይ ፳ ፐርሰንት ተጨምሮ ይከፈላል ። በጉዞ ሰነድ ፣ በመኖሪያ ፈቃድ ወይም በመታወቂያ ላይ የተፈጠረን ስህተት ለማረም የመደበኛው ሙሉ ክፍያ ይፈጸማል ፤ ሆኖም ስህተቱ የተፈጠረው በባለሥልጣኑ ምክንያት ከሆነ ክፍያ አይጠየቅም ። ፮ . የሚኒስትሮች ምክር ቤት የፋይናንስ ደንብ ቁጥር ፲፯ ፲፱፻፵፱ የአንቀጽ ፴፪ ድንጋጌ ቢኖርም በዚህ አንቀጽ መሠረት ለሚሰበሰብ ክፍያ በባለሥልጣኑ የተዘጋጀ ደረሰኝ ሊሰጥ ይችላል ፤ ሆኖም የተሰበሰበው ገንዘብ በተጠቀሰው ደንብ አንቀጽ ፴፭ መሠረት ገቢ መደረግ አለበት ። ፴፫፡ ከክፍያ ነፃ ስለመሆን ፩ . በዚህ ደንብ አንቀጽ ፴፪ መሠረት የሚጠየቁ ክፍያዎች በሕግ ወይም በዓለም አቀፍ ውል መሠረት ከክፍያ ነጻ እንዲሆኑ የተደረጉ ሰዎችን በሚመለከት ተፈጻሚ አይሆኑም ። በዚህ ደንብ አንቀጽ ፰ መሠረት በይለፍ ሰነድ ወደ አገሩ ለመመለስ የሚጠይቅና የመክፈል አቅም የሌለው ኢትዮ ጵያዊ ከክፍያ ነፃ ይሆናል ። ፫ • በዚህ ደንብ አንቀጽ ፱ መሠረት አስቸኳይ የጉዞ ሰነድ እንዲሰጠው የሚጠይቅና የመክፈል አቅም የሌለው ሰው ከክፍያ ነፃ ይሆናል ። ገጽ ፪ሺ፱፻፳፮ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፬ ጥቅምት ፲ ቀን ፲፱፻፲፯ ዓም : ክፍል ሰባት ስለመግቢያና መውጫ በሮች እና ስለኢምግሬሽን ቁጥጥር ፴፬ • የመግቢያና የመውጫ በሮች ፩ ወደ ኢትዮጵያ የመግቢያ ወይም ከኢትዮጵያ የመውጫ በሮች የሚከተሉት ይሆናሉ ፤ ሀ ) በአየር ሲሆን ፣ ኣዲስ ኣበባና ድሬዳዋ ፤ ለ ) በየብስ ሲሆን ፣ ሞያሌ ፣ ደወሌ ፣ ጋላፊ ፣ መተማ ፣ ሁመራ ፣ ኦሞራቴ ፣ ቶጎ ውጫሌና ዶሎ ኦዶ ። ፪ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ባለሥልጣኑ ተጨማሪ በሮችን ሊከፍት ወይም ያሉትን ሊዘጋ ይችላል ። ፴፭ በመግቢያና በመውጫ በሮች ላይ ስለሚደረግ ቁጥጥር በአዋጁ አንቀጽ ፲፮ መሠረት የተመደበ የኢምግሬሽን ኦፊሰር ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ወይም ከኢትዮጵያ የሚወጡ ሰዎች በአዋጁ አንቀጽ ፫ ወይም ፮ የተመለከቱትን ሁኔታዎች ማሟላታቸውን ወይም እነዚህ ሁኔታዎች የማይመለከቷቸው ከሆኑ ተገቢውን የመታወቂያ ወረቀት የያዙ መሆናቸውን በመግቢያና መውጫ በሮች ላይ ይቆጣጠራል ። ፴፮ • በሆቴሎችና የእንግዳ ማረፊያ አገልግሎቶች ስለሚደረግ ፩ . በኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ ማንኛውም የውጭ አገር ሰው በማናቸውም ሆቴል ወይም የእንግዳ ማረፊያ አገል ግሎት ለማደር ሲፈልግ የጸና የጉዞ ሰነድ በማቅረብ ባለሥልጣኑ በሚያዘጋጀው ፎርም መሠረት መመዝገብ አለበት ። ፪ . ማንኛውም ሆቴል ወይም የእንግዳ ማረፊያ አገልግሎት በኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ የውጭ አገር ሰው ሲያስተ ናግድ በ፳፬ ሰዓት ውስጥ ለባለሥልጣኑ ወይም ባለሥ ልጣኑ ለወከለው አካል ወይም በአቅራቢያው ለሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ሪፖርት የማቅረብ ግዴታ አለበት ። ፫ በኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ የውጭ አገር ሰውን ተቀብሎ በራሱ የእንግዳ ማረፊያ የሚያስተናግድ ተቋም የተባ ለውን ሰው የጉዞ ሰነድ በመያዝ በ፳፬ ሰዓት ውስጥ ለባለሥልጣኑ ወይም ባለሥልጣኑ ለወከለው አካል ወይም በአቅራቢያው ለሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ሪፖርት የማቅረብ ግዴታ አለበት ። ክፍል ስምንት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ፴፯ : ስለሪኮርድ አያያዝ በዚህ ደንብ መሠረት ከሚሰጡ የጉዞ ሰነዶችና ቪዛዎች እንዲሁም ከውጭ አገር ሰው ምዝገባና የመኖሪያ ፈቃድ ጋር ተያይዞ በአመልካቾች የሚቀርቡ መረጃዎች በኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች አማካይነት ሊወሰዱና ሊያዙ ይችላሉ ። ፴፰ መመሪያ ስለማውጣት ፩ . ሚኒስቴሩና ባለሥልጣኑ ይህን ደንብ ለማስፈጸም በየሥ ልጣን ክልላቸው ዝርዝር መመሪያ ለማውጣትይችላሉ ። ፪ • ይህን አዋጅ ለማስፈጸም የሚወጡ መመሪያዎች ሁሉ በሥራላይእንዲውሉከመደረጋቸው በፊት ለሕዝብ ይፋ እንዲሆኑ መደረግ አለባቸው ።

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?