የመ / ቁ .16062
ህዳር 19 ቀን 1998 ዓ.ም
ዳኞች፡- 1. አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
2. ኣቶ ዓብዱልቃድር መሓመድ 3. አቶ ሐጎስ ወልዱ 4. አቶ ዳኜ መላኩ
5. አቶ መስፍን ዕቁበዮናስ አመልካች፡- የኢትዮጵያ መድን ድርጅት መልስ ሰጭዎች፡- ወ / ሮ አረጋሽ ከበደ
ከውል ውጭ ስለሚደርስ አላፊነት ካሣ ስለሚጠየቅበት ክስ- ክስ ስለሚቀርብበት ጊዜ - የፍትሐ - ብሄር ህግ ቁጥር 2143 / 1 / ፤ 2143 / 2 /
መልስ ሰጭ በኣቶ ከበደ ኃይሉ ይሽከረከር የነበረና ንብረትነቱ የአቶ አሊ መሃመድ የሆነ ተሽከርካሪ ሰኔ 5 ቀን 1984 ዓ.ም ባለቤቴን ገጭቶ ገድሏል በማለት እርሷና ሁለት ህፃናት ልጆቿ ተቋርጦብናል የምትለውን ገንዘብ በማስላት ብር 222,000 እንዲከፈላት መስከረም 4 1992 ዓ.ም ባቀረበችው ክስ አመልካች ለተሽከርካሪው በሰጠው መድን በጣልቃ ገብነት በመግባት ክሱ ስፍ / ብ / ህ / ቁ . 2143/2 ! መሰረት በይርጋ ይታገዳል በማለት ያቀረበውን ክርክር የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ / ቤት ውድቅ አድርጎ በፍሬ ነገሩ ውሳኔ በመስጠቱና ውሳኔውም በኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍ / ቤት በመጽናቱ የቀረበ ውሳኔ፡ የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ / ቤት የሰጠውና የኦሮሚያ ጠቅላይ
ፍ / ቤት ያጸናው ውሳኔ ተሽሯል ፡፡ 1. የፍ / ብህ / ቁ .2143 ከውል በሚደርስ ኣሳፊነት የቀለብ ገንዘብ በመጠየቅ
በሚቀርብ ክስ ተፈፃሚ ይሆናል ፡፡ 2. ሚስት ከውል ውጭ በባሏ ላይ በሚደርስ የሞት ጉዳት የቀለብ
ጥያቄ ለማቅረብ ስትል ሚስትነቷን ለማረጋገጥ በፍርድ ቤት
የምታቀርበው ጥያቄ በፍ / ብ / ህ / ቁ . 2143 የተደነገገው የይርጋ ጊዜ
አያቋርጥም ፡፡
ሐጉስ ወልዱ ርሃም ፀጋዬ ቀረበ
የሰ / መ / ቁ .16062
ህዳር 19 ቀን 1998 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ
አብዱልቃድር መሐመድ ዳኜ መላኩ
መስፍን ዕቁበዮናስ ተጠሪ፡- ወ / ሮ አረጋሽ ካበደ አልቀረሰችም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል ፡፡
በዚህ መዝገብ ለቀረበው የሰበር አቤቱታ መነሻ ሊሆን የቻለው የምሥራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ / ቤት የሰጠው ውሣኔ ነው ፡፡
ይኼው ክርክሩን በመጀመሪያ ደረጃ ያየው ፍ / ቤት በፍ / መ / ቁ .304 / 92 በቀረበለት ካሳ ጉዳይ ላይ የአሁኑ አመልካች በጣልቃ ገብነት የክርክሩ ተካፋይ እንዲሆን አድርጐ ጣልቃ ገቡ በፍትሐብሔር ህግ ቁ .2143 / 1 / መሠረት ያቀረበውን የይርጋ ክርክር በብይን ውድቅ ካደረገ በኋላ ግንቦት 21 ቀን 1995 ዓ.ም በዋለው ችሎት በከሣሽ በኩል የቀረበውን ክሥና በግራ ቀኙ መካከል የተደረጉትን የፍሬ ነገር ክርክሮች መርምሮ ከሣሽዋ ወ / ሮ አረጋሽ ከበደ ባለቤቷ አቶ ሀ / ሚካኤል መርጊያ ንብረትነቱ የአንደኛ ተከሣሽ በሆነው የሰሌዳ ቁጥር 3-17155 መኪና ተገጭቶ በመሞቱ ምክንያት በሚስቱና በሁለቱ ህፃናት ልጆቹ ላይ ሰቀለብ ረገድ ለደረሰው ጉዳት የመኪናው ባለቤት አንደኛው ተከሣሽ እና መኪናውን ሲያሽከረክር አደጋውን ያደረሰው ሁለተኛው ተከሣሽ በሕግ ኃላፊ ስለሚሆኑ ካሣ ብር 60,000 ሊከፍሉ ይገባል ። ጣልቃ ገብ የሆነው የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በበኩሉ ግጭቱን ላደፈሰው መኪና በገባው የመድን ዋስትና መጠን ካሣውን መክፈል አለበት የሚል ውሣኔ ሰጥቷል ፡፡
ጣልቃ ገብነት የክርክሩ ተካፋይ እንዲሆን የተደረገው የአሁኑ አመልካች የዞኑ ከፍተኛ ፍ / ቤት በሰጠው ውሣኔ ባለመስማማትና ክሱም * Th ይርጋቋራ ሆኗል ያሚል ምክንይት + በፍዷመቁ : 03564 ዉልአሮማይጠቅ 48
ፍ / ቤት ይግባኙን ሊያቀርብ የቻለ ቢሆንም የክልሉ ጠቅላይ ፍ / ቤት በበኩሉ
መጋቢት 14 ቀን 1996 ዓ.ም መርምሮ በሰጠው ትዕዛዝ ከፍተኛው ፍ / ቤት የሰጠው ውሣኔ ጉድለት የለበትም በማለት በፍ / ሥ / ሥ / ህ / ቁ .337 መሠረት ይግባኙን በመሠረዝ አሰናብቶታል ፡፡
በዚህ መዝገብ ለሰበር አቤቱታ የቀረበውም ክርክሩን በመጀመሪያ ደረጃ ያየው የምሥራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ / ቤት የሰጠው ውሣኔም ሆነ የክልሉ ጠቅላይ ፍ / ቤት በይግባኝ ደረጃ ጉዳዩን ተመልክቶ የሰጠው ትዕዛዝ መሠረታዊ የሕግ ስህተት አለበት በሚል ሲሆን አመልካች በተነሣው የይርጋ ክርክር ላይ የተሰጠው ውሣኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት አለበት የሚልበትን ምክንያት ሰኔ 11 ቀን 1996 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ አብራርቶ
አቅርቧል ።
ጉዳዩ ተመርምሮ የይርጋው ጥያቄ ከሕጉ አኳያ ተጣርቶ መወሰን የሚያስፈልገው ሆኖ በመታየቱ ለሰበር ችሎት እንዲቀርብ የተደረገ ሲሆን በአመልካች በኩል የቀረበው ማመልከቻም ለአሁኗ¨ ተጠሪ ተልኮ ቀርባ መልስ እንድትሰጥበት ታዞ በ 15 / 4 / 97 ዓ.ም የተፃፈ መለስ አቅርባለች ። በጽሑፍ ያቀረበችው መልስ ሲታይ ተጠሪ ባለቤቴ በመኪና ተገጭቶ በመሞቱ ምክንያት በክሱ የተጠየቀው የጉዳት ካሣ እንዲከፈል : ሣይሆን በቀለብና መተዳደሪያ ረገድ ታስቦ ልክፈለን የሚገባ ገንዘብ ነው ፡፡ ክሱ ያልተመሠረተ ደግሞ , አመልካች የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2143/1 ! በመጥቀስ የሚያቀርበው የይርጋ ክርክር ሊኖር አይችልም ፡፡ ስለዚህ ክሱ በይርጋ ቀሪ የሚሆንበት ምክንያት የለም ፡፡ ከዚህ ሌላ በሚስትነት ጉዳይ በተለያዩ ፍርድ ቤቶች በክርክር ላይ ቆይቼ የመጨረሻ ውሣኔ የተሰጠው በ 07 / 07 / 90 ስለሆኔ ክሥ የማቅረብ መብት ያገኘሁት ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ነው ፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ሲታሰብ ደግሞ ሰ 4 / 1 / 92 ያቀረብኩት ክሥ ከይርጋ ነፃ ነው የሚሉትን ክርክሮች ያቀፈ
የአሁኑ አመልካች ደግሞ ክሱ በይርጋ ቀሪ ሊሆን ይገባል በማለት አጥብቆ የሚከራከረው ተጠሪ ክሥ ያቀረበችው ኣደጋው ወይም ጉዳቱ ከደረሰ ከሰባት አመት ቆይታ በኋላ ነው ፡፡ የይርጋ ጊዜ በፍትሐብሄር ሕግ
ቁጥር 2143 / 2 / መሠረት ለወንጀሉ ጉዳይ የተወሰነው የይርጋ ዘመን ልክ
ክሥ ቀርቦበት በብር 1000 የተቀጣ መሆኑ በማሥረጃ ስለተረጋገጠ ለዚህ
ወንጀል የትወሰነው የይም 9
ችሎቱም በቀረበው ጉዳይ በዋናነት ሊመረመር የሚገባው ክሱ በይርጋ ቀሪ ይሆናል አይሆንም ? ጉዳቱ በወንጀል የሚያስቀጣ ሆኖ ከተገኘ የይርጋው ዘመን ልክ ምን ያህል ነው የሚለው የይርጋ ጥያቄ መሆኑን ተገንዝቧል ፡፡
ከፍተኛው ፍ / ቤት ከሰጠው ውሣኔ ለመረዳት እንደተቻለው ከሣሽ የሆነችው የአሁኗ ተጠሪ ሁለተኛ ተከሣሽ የሆነው ከበደ ኃይሉ ንብረትነቱ የአንደኛው ተከሣሽ አሊ መሐመድ የሆነ የሰሌዳ ቁጥሩ 3-17155 መኪና እያሽከረከረ ሲጓዝ ሰኔ 5 ቀን 1984 ዓ.ም ባለቤቴ አቶ ሀ / ሚካኤል መርጊያን ጥፋት ሰሆነ ቸልተኝነት ገጭቶ ገድሎታል በማለት በባለቤቷ መሞት ምክንያት እርሷ እና ሁለት ህፃናት ልጆቹ ቀርቆብናል ወይም አጥተናል የምትለውን ገንዘብ በመግለጽ አስልታ በጠቅላላው ብር 222,000 ተከሣሾች በኣንድነት በነጠላ እንዲከፍሏት በ 4 / 1 / 92 እንዲቀርብ ባደረገችው ክሥ ጠይቃለች ፡፡ የአሁኑ አመልካች የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በቀጥታ የቀረበበት ክሥ ባይኖርም አደጋውን ላደረሰው መኪና የመድን ዋስትና ሰጥቷል በመባሉ ምክንያት
በመባሉ ምክንያት በፍ / ሥ / ሥ / ህ / ቁ .43 / 1 / መሠረት የክርክሩ ተካፋይ እንዲሆን የተደረገ ሲሆን አመልካችም አደጋውን ላደረሰው መኪና የመድን ዋስትና በተገባለት መጠን ካሣ የመክፈል ኃላፊነት እንዳለበት እምኖ ክሱን በማስመልከት የበኩሉን መልስ ሲሰጥ የይርጋ ክርክር አንስቷል ፡፡ ሰኢንሹራንስ ምክንያት ካሣ እንዲከፍል የክርክሩ ተካፋይ እንዲሆን ከተደረገ ኢንሹራንስ ገቢው ጉዳት ደርሳብኛል ብሎ ሰከሰሰው ሰው ላይ ሊያቀርብ የሚችላቸውን የሕግ ክርክሮች ማቅረብ ይችላል ፡፡ አመልካች ሦስተኛ ወገን ሆኖ የክርክር ተካፋይ በሆነበት ጉዳይ ክሱን በመቃወም የይርጋ ክርክር ሊያቀርብ የቻለው በዚሁ ሁኔታ በመጠቀም ነው ፡፡
የቀረበውን የይርጋ ክርክር በተመለከተም ጉዳዩ ከውል ውጭ የሆነ ኃላፊነትን የሚመለከት ስለሆነ ክሱ በይርጋ ቀሪ መሆን አለመሆኑ ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2143 አኳያ የሚመረመር ነው ፡፡ የአሁኑ
አመልካች ለይርጋው ክርክር መነሻ ያደረገው ይኼው ከውል ከውል ውጭ
የክሱ ፍሬ ነገር ጉዳዩ ከውል ውጭ የሆነ ኃላፊነት የሚመለከት መሆኑን
እያረጋገጠ ተጠሪዋ በአመልካች በኩልጎ ለቀረበው የሰበር አቤቱታ መልስ ስትሰጥ ጉዳዩ ሟች በመኪና ተገጭቶ ከመሞቱ ጋር የተያያዘ ቢሆንም ክሱ የተመሠረተው ሰቀለብ ጥያቄ ላይ እንጅ በጉዳት ካሣ ላይ ስላልሆነ በፍትሐብሄር ሕግ ቁጥር 2143 ላይ የተመለከተው የይርጋ ድንጋጌ ተፈፃሚ ሊሆን አይችልም በሚል ያቀረችው ክርክር ተቀባይነት የለውም ፡፡ ተጐጂው በመሞቱ ምክንያት ሚስት ወይም ልጆች በፍትሐብሄር ሕግ ቁጥር 2095 መሠረት በቀለብ መተዳደሪያ ረገድ የሚያቀርቡት የካሣ ጥያቄም ሲሆን ከውል ውጭ የሆነ ኃላፊነትን የሚመለከት እንጂ በሌላ የተለየ ግንኙነት ላይ ወይም በሌላ የሕግ ምክንያት ላይ የተመሠረተ : አይደለም ፡፡ በተጠቀሰው
የፍትሐብሄር የተመለከተው የይርጋ ዘመን ሲታይ የመጀመሪያው ንዑስ ቁጥር « 1 » : ' ' ተበዳዩ ክሥ ማቅረብ የሚችለው ካሣ የሚጠየቅበት ጉዳት ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ሁለት ኣመት ድረስ መሆኑን የሚደነግግ ሲሆን ንዑስ ቁጥር 523 ደግሞ ጉዳቱ በወንጀል የሚያስቀጣ ሆኖ የይርጋ ዘመኑ ርዝመት የበለጠ እንደሆነ የካሣው ጉዳይ ክሥ የይርጋ ዘመኑ ርዝመት እንደሚሆን ይገልፃል ፡፡
የቀረበው ጉዳይ ከዚሁ የይርጋ ድንጋጌ አንፃር ሲመረመር የአሁኗ ተጠሪ ካሣ የተጠየቀበት ጉዳት ሰኔ 5 ቀን 1984 ዓ.ም ደርሶ የካሣውን ጉዳይ ክሥ ያቀረበችው መስከረም 4 ቀን 1992 ዓ.ም መሆነ ስለተረጋገጠ በሕጉ የመጀመሪያ ንዑስ ቁጥር 13 ላይ የተጠቀሰው ሁለት አመት የይርጋ ዘመን ያለፈው የመሆኑን ጉዳይ አከራካሪ ሊሆን አይችልም ፡፡ የሚቀረው ጉዳቱ በወንጀል የሚያስቀጣ ሆኖ ከተገኘ በወቅቱ በነበረው የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ የተመለከተው የይርጋ ዘመን ምን ያህል ይሆናል ? በዚህ ሕግ መሠረት ቢታይ የይርጋው ዘመን እሳለፈም ሊባል ይችላል አይችልም ? የሚለው ጥያቄ ነው ፡፡ አደጋ ያደረሰውን መኪና ሲያሽከረክር የነበረው ሾፌር ሁለተኛው ተከሣሽ በዚህ ጉዳይ ጥፋት በሆነ ቸልተኝነት በመኪና ሰው ገጭቶ ገድሏል ተብሎ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ቁጥር 526 / 1 / ተጠቅሶ ሰቀረበበት የወንጀል ክሥ ፍ / ቤት ጥፋተኛ መሆኑን አረጋግጦ በገንዘብ
መቀጫ ብር 1000 እንዲቀጣ መወሰኑ ተገልጿል ። ሾፌሩ በወንጀሉ ጉዳይ * The ቅጽ ጥፋተኛ w ተብሎ ii የተቀጣበት * የቃትግ -ኣንቀጽ a የወንጀለኛ መቅጫ ok ግ
ቁጥር 526 / 1 / መሆኑ ከታወቀ የወንጀሉ ጉዳይ የክሥ አቀራረብ የይርጋ
ዘመን ምን ያህል ጊዜ ነው የሚለውን በተመለከተ ከወንጀለኛ መቅጫ ህግ ቁጥር 226 በመመልከት ለማረጋገጥ ይቻላል ፡፡ በዚህም መሠረት በዚህ ጉዳይ ተፈፃሚ ነው ለማለት የተቻለው የይርጋ ዘመን በዚሁ በተጠቀሰው ሕግ ፊደል 53 ላይ የተመለከተው አምሥት አመት ነው ፡፡
የአሁኗ ተጠሪ ደግሞ ክሱን ያቀረበችው ጉዳቱ በደረሰ በአምሥት አመት ጊዜ ሣይሆን ከሰባት አመት ቆይታ በኋላ መሆኑ ተረጋግጧል ፡፡ ተጠሪ ሚስትነቴን እስካስወሰን ድረስ በክርክር ላይ የቆየሁት ጊዜ መታሰብ የለበትም ፣ ክሥ የማቅረብ መብት ያገኘሁት ሚስትነቴን ካስወሰንኩ በኋላ ስለሆነ የይርጋው ጊዜ መታሰብ ያለበት ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ነው በሚል ያቀረችው ክርክር በሕግ ተቀባይነት የለውም ፡፡ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር እንደተመለከተው የይርጋው የሚቆጠረው የሚጠየቅበት ጉዳት ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ ነው ። ተጠሪ ለክሱ መዘግየት የጠቀሰችው ምክንያት በሕጉ ይርጋውን የሚያቋርጥ ወይም የሚያረዝም አይደለም ፡፡
ክሱ የቀረበው በወንጀሉም ጉዳይ የተወሰነው የይርጋ ዘመን ካለፈ በኋላ ስለሆነ በይርጋ ቀሪ ሆኗል ፡፡ አንድ ተከራካሪ ወገን በሕግ ይገባኛል የሚለውን መብት በሕጉ በተወሰነ ጊዜ ውስጥ ካልጠየቀ በሕግ ከሶ የመጠየቅ መብቱ ቀሪ ይሆናል ፡፡ የአሁኗ ተጠሪም በባለቤቷ መሞት ምክንያት በሕግ ይገባኛል የምትለውን ካሣ ስሕጉ በተወሰነው ጊዜ ውስጥ ክሥ ኣቅርባ ስላልተጠየቀች ካሣ የመጠየቅ መብቷ ቀርቷል ፡፡
በዚህ ምክንያት በቀረበው ጉዳይ ክሱ በይርጋ ቀሪ አይሆንም በሚል የተሰጠው ውሣኔ መሠረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል ፡፡
ው ሣ ኔ 1. ክርክሩን በመጀመሪያ ደረጃ ያየው የምሥራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ
ፍ / ቤት ይህንን ጉዳይ በማስመልከት በ 21 / 9 / 1995 ዓ.ም የሰጠው • ውሣኔም ሆነ የኦሮሚያ ጠቅላይ በመ / ቁ .03564 ሰ j47 / 96
ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ / ሥ / ሥ / ህ / 348 / 1 / መሠረት ተሽራል ፡፡ 2. በዚህ ክርክር ምክንያት የደረሰውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ
የየራሣቸውን ይቻሉ ፡፡
በዚህ መዝገብ የተሰጠው ውሣኔ ትክክለኛ ግልባጭ ይተላለፍ ጉዳዩ
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
You must login to view the entire document.