የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አራተኛ ዓመት ቁጥር ፳፰ አዲስ አበባ የካቲት ፳፮ ቀን ፲ህየን በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፩፻፬ ፲፱፻፲ ዓ . ም የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ኣዋጅ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . ገጽ ፯፻፲፬ | Proclamation . . . . . . . . . አዋጅ ቁጥር ፩፻፬ ፲፱የኝ ስለግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ የወጣ አዋጅ ሥራና ሠራተኛን በማገናኘት ሥራ ግለሰቦችንና የግል ድርጅ ቶችን ማሳተፍ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፡ በተለይ ወደውጭ አገር ለሥራ የሚላኩ ኢትዮጵያውያን | WHEREAS , it has particularly become necessary to ሠራተኞች መብታቸው ፡ ደህንነታቸውና ክብራቸው ተጠብቆ | protect the rights , safety and dignity of Ethiopians employed ላቸው የሚሰሩበትን ሁኔታ ማመቻቸት በማስፈለጉ ፡ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመን ግሥት አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ አዋጅ | 1 . Short Title ቁጥር ፩፻0 1ህየፕ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር ፡ 1 2 Definitions በዚህ አዋጅ ውስጥ ፡ ፩ . “ የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ” ማለት መንግ ሥታዊ አካል ያልሆነና ከሚከተሉት አንዱን ወይም ሁለቱን አገልግሎት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ከሠራተኛው ገንዘብ ሳይቀበል ሥራና ሠራተኛን በማገ ናኘት ሥራ ላይ የሚሠማራ ሰው ነው ፡ ፡ ያንዱ ዋጋ 280 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣ . ቁ : ዥሺ፩ ገጽ ፯፻፲፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፭ የካቲት ፳፮ ቀን ፲፱፯ ዓም Federal Negarit Gazeta - No . 28 5 March , 1998 - ~ Page 715 ሀ ) የሥራ ውሉ ተዋዋይ ወገን ባለመሆን በአገር ውስጥ ሥራና ሠራተኛን የማገናኘት አገል ግሎት መስጠት ለ ) ከሠራተኛው ጋር የሥራ ውል ስምምነት በማድረግ ሠራተኛውን በአገር ውስጥ ወይም በውጭ አገር ለሥራ ለሦስተኛው ሰው የማቅረብ አገልግሎት መስጠት ፣ ፪ . “ ፈቃድ ” ማለት በግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝነት ሥራ ላይ ለመሠማራት የሚያስችል አግባብ ባለው ባለሥ ልጣን ለግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ የሚሰጥ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ነው ፡ “ ሠራተኛ ” ማለት በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር ፴፪ / ፲፱፻፷፭ የተሰጠው ትርጉም ይኖረዋል ፤ ፬ . “ አግባብ ያለው ባለሥልጣን ” ማለት ሚኒስቴሩ ወይም በክልል የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ሕጐችን የማስፈጸም ኃላፊነት የተሰጠው አካል ነው ፤ ፭ “ ሚኒስትር ” ወይም “ ሚኒስቴር ” ማለት እንደአግባቡ የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ወይም ሚኒስቴር ነው ፡ “ ሰው ” ማለትማንኛውም የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው ፡ ፯• በወንድ ጾታ የተደነገገው የሴትንም ጾታ ያካትታል ። ፫ የአፈጻጸም ወሰን ፩ . የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 9ፀ / iፀየትኙ | 3 . Scope of Application | አንቀጽ ፫ ( ፪ ) ( መ ) ቢኖርም ፡ ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም ፡ አዋጅ ቁጥር ፴፪ / ፲፱፻፫፭ ለትርፍ በሚካሄድ ሥራ ላይ ላልተመሠረተ የግል አገልግሎት ሥራ ተቀጥሮ በውጭ አገር በሚሰራ ኢትዮጵያዊ ላይ ተፈጻሚነት ይኖረዋል ። የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር ፴፪ / ፲፱፻ዥ፭ አንቀጽ ፩፪ኛጀ እንደተጠበቀ ሆኖ ፡ ሚኒስቴሩ አንድን እሠሪ ቀጥታ ቅጥር እንዲያከናውን ካልፈቀደ በስተቀር ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ለሥራ ወደውጭ አገር ሊሄድ የሚችለው በግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ አማካኝነት ብቻ ነው ። በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፪ ( ፩ ) ( ለ ) የተመለከተውን አገል ግሎት በሚሰጥ ኤጀንሲ እና በሠራተኛው መካከል ማንኛውም የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ እና በዚህ አዋጅ በአንቀጽ ፲፭ የተጠቀሰው መብት በመጣሱ ምክንያት የሚነሳ ክርክር በአዋጅ ቁጥር ፴፪ / ፲፱፻፳፭ መሠረት ሊታይ ይችላል ። ፬ . ይህ አዋጅ ማንኛውም የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ በሌሎች ሕጉች ያሉበትን ግዴታዎች የሚያግድ አይሆንም ። ፬ ፈቃድ ስለማስፈለጉ የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ሆኖ ለመሥራት | 4 Beuirement ofL የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ከሚከተሉት አካላት ፈቃድ ማውጣት ይኖርበታል ፡ ፩ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) እንደተጠበቀ ሆኖ ፡ የሥራና ሠራተኛ አገናኝነቱን አገልግሎት በአንድ ክልል ውስጥ የሚሰጥ ከሆነ ይህንኑ አገልግሎት በሚሰ ጥበት ክልል ውስጥ የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ሕጎችን ለማስፈጸም ኃላፊነት ከተሰጠው አካል ፣ ገጽ ፯፻፲፮ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፰ የካቲት ፳፮ ቀን ፲፱፻፲ ዓ . ም . Federal Negarit Gazeta - - No . 28 55March , 1998 – Page 716 ፪ . የሥራና ሠራተኛ አገናኝነቱን አገልግሎት በሁለትና ከሁለት በላይ በሆኑ ክልሎች ውስጥ የሚሰጥ ከሆነ ከሚኒስቴሩ ፤ ፫ የሥራና ሠራተኛ አገናኝ አገልግሎቱ ኢትዮጵያዊ ሠራተኛን ቀጥሮ ከኢትዮጵያ ውጪ ለሦስተኛ ሰው ለሥራ ለማሰማራት ከሆነ ከሚኒስቴሩ ። ፭ ፈቃድ ለማግኘት መሟላት ስላለባቸው ሁኔታዎች በዚህ አዋጅ መሠረት በግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀን ሲነት ለመሥራት የሚያመለክት ማንኛውም ሰው የሚከተ ሉትን ማሟላት ይኖርበታል ፡ ፩ በኤጀንሲነት ሥራ ላይ ለመሰማራት የሚያስችለው የንግድ ምዝገባ ያለው መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ የማቅረብ ፣ ፪ . በዚህ አዋጅ መሠረት ሠራተኛን ለሥራ ወደውጭ አገር በመላክ አገልግሎት የሚሰጥ ከሆነ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፬ መሠረት የተመለከተውን የዋስትና ግዴታ መሟላቱን የሚያሳይ ማስረጃ የማቅረብ ፡ ፫ ይህን አዋጅ መሠረት አድርጎ በሚወጣው ደንብ የተወሰ ነውን የፈቃድ ክፍያ አግባብ ላለው ባለሥልጣን የመክፈል ፡ ፬ . የአደረጃጀት መዋቅሩን የሚያሳይ ቻርትና በግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝነት ሥራውን የሚካፈሉ አባሎቹን ዝርዝር የማቅረብ ፡ ፭ የሥራውን እና የወኪሉን አድራሻ የማሳወቅ ፣ ፮ ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ አግባብ ባለው ባለሥልጣን የሚጠየቁ መረጃዎችን የማቅረብ ። ፮ ፈቃድ ስለመስጠት በዚህ አዋጅ መሠረት ፈቃድ ለማግኘት የሚያበቁ ሁኔታዎች መሟላታቸው እንደተረጋገጠ አግባብ ያለው ባለሥልጣን ለአመልካቹ ፈቃድ ይሰጣል ። ለፈቃድ ብቁ ስላለመሆን በሕገወጥ ሥራና ሠራተኛ ማገናኘት ሥራ ምክንያት በወንጀል የተቀጣ ሰው ለግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ | ኤጀንሲነት ፈቃድ ብቁ አይሆንም ። ቿ ፈቃዱ ጸንቶ ስለሚቆይበት ጊዜ በዚህ አዋጅ መሠረት የሚሰጥ ፈቃድ በየዓመቱ የሚታደስ ሆኖ ለ፪ ዓመት ጊዜ የጸና ይሆናል ። ፬ ቢሮ መክፈት አስፈላጊ ስለመሆኑ ፩ . ማንኛውም የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ለሥራው ማስኬጃ ቢሮ መክፈት ይኖርበታል ። ፪• ኢትዮጵያውያንን በሥራ ቅጥር ወደውጭ አገር የሚልክ የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ሠራተኛውን በሚልክበት አገር ቅርንጫፍ ቢሮ ወይም ተወካይ ሊኖረው ይገባል ። _ ፲ ፈቃድን በግልጽ ቦታ ስለማስቀመጥ ማንኛውም የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ በዚህ አዋጅ መሠረት የተሰጠውን ፈቃድ በከፈተው ቢሮ ለሌሎች | ሰዎች ግልጽ ሆኖ እንዲታይ ማድረግ ይኖርበታል ። ፲፩ ቢሮን ስለማዛወር ማንኛውም የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ቢሮውን ወደሌላ ሥፍራ ከማዛወሩ በፊት በቅድሚያ አግባብ ላለው ባለሥልጣን ማሳወቅ ይኖርበታል ። ፲፪ ስለግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲው ግዴታዎች ፩ . በዚህ አዋጅና በሌሎች ሕጎችከተመለከቱትግዴታዎች | በተጨማሪ ማንኛውም የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ | ኤጀንሲ ፡ ገጽ ፯፻፲፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፰ የካቲት ፳፮ ቀን ፲፱፻፲ ዓ . ም Federal Negarit Gazeta No . 28 5 March , 1998 – Page 717 ሀ ) እንደአስፈላጊነቱ የሥራ ፈላጊዎችን አመላመልና ምዝገባ ሥነ ሥርዓት አዘጋጅቶ አግባብ ላለው | ባለሥልጣን አቅርቦ የማጸደቅ ፡ ለ ) ፈቃድ ሲያወጣ ፡ ሲያሳድስና ሲተካ በዚህ አዋጅ መሠረት በሚወጣው ደንብ የሚፈለግበትን የፈቃድ ክፍያ አግባብ ላለው ባለሥልጣን ዩ ። የመክፈል ፣ : : ቢሮውን ለመዝጋት ሲፈልግ በቅድሚያ አግባብ ያለውን ባለሥልጣን የማሳወቅ ፣ መ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፪ ( ፩ ) ( ለ ) በተመለከተው መሠረት ሥራና ሠራተኛን የማገናኘትግልጋሎት የሚሰጥ ከሆነ የሥራ ውሉን አግባብ ባለው ባለሥልጣን የማጸደቅ እና የዚሁኑም ትክክለኛ ቅጂ ለዚሁ አካል አቅርቦ የማስመዝገብ ግዴታ አለበት ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ከተመለከቱት ግዴታዎች በተጨማሪ ሠራተኛን ወደውጭ ኣገር | ለሥራ የሚያሰማራ የግል ሥራና ሠራተኛ ኤጀንሲ የሚከተሉት ግዴታዎች ይኖሩታል ፡ ሀ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፱ ( ፪ ) መሠረት በውጭ አገር የሚገኘው ቅርንጫፍ ቢሮ የተቋቋመበት ወይም ወኪል የተሰየመበትን ሕጋዊ ሠነድ የማቅረብና የቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቱን ወይም የወኪሉን ሙሉ አድራሻ የማሳወቅ ፣ ለ ) ሠራተኛው የሥራ ውሉን ከመፈረሙ በፊት ስለሚ ቀጠርበት ሥራና አገር በቂ ግንዛቤ እንዲኖረው አስፈላጊ የሆነ መግለጫ የመስጠት ፡ ሐ ) ሠራተኛው ደመወዙን እንደአግባቡ በከፊል ወይም በሙሉ ወደአገሩ ለመላክ ሲፈልግ በዚያው አገር ሕግ መሠረት አስፈላጊውን ሁኔታዎች የማ መቻቸት ፡ መ ) ሠራተኛው በሄደበት አገር ስለሚገኝበት ሁኔታ በየዓመቱ ወይም እንደአስፈላጊነቱ በሚኒስትሩ ሲጠየቅ ሪፖርት የማድረግ ፡ ሠ ) ሥራውን በሚሠራበት ጊዜ የኅብረተሰቡን ሞራልና ባህል የመጠበቅ ፣ • ረ ) የሥራ ውሉን ለማራዘም ወይም ለማሻሻል ሲፈልግ በቅድሚያ ለሚኒስቴሩአቅርቦ የማጸደቅእንዲሁም የሥራ ውሉ ሲቋረጥ ሚኒስቴሩን የማሳወቅ ፣ ሰ ) የሥራ ውሉ በሚቋረጥበት ወይም ሠራተኛው በሚጠይቅበት በማንኛውም ጊዜ ሲሠራ የነበ ረውን የሥራ ዓይነት : የአገልግሎት ዘመንና ሲከፈለው የነበረውን ደመወዝ የሚያሳይ የምስክር ወረቀት በነጻ እንዲሰጠው የማድረግ ፡ ሽ ) ወደውጭ አገር ለሥራ የላካቸውን ሠራተኞች ስም ፡ ዕድሜ ፡ የትምህርት ደረጃ ፡ ሙያ ፥ የተቀጠሩበትን የሥራ ዓይነት ፡ ደረጃ ፡ የደመወዝ መጠን ውሉ . . . ጸንቶ የሚቆይበትን ጊዜና ሌሎች በሚኒስቴሩ የሚጠየቁ መረጃዎችን በመዝገብ የመያዝና ሚኒስቴሩ በጠየቀ ጊዜ የማሳወቅ ፡ ቀ ) ወደውጭ ለሥራ የላካቸውን ሠራተኞች በሚሰ ሩበት አገር አቅራቢያ ላለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አሳውቆ የማስመዝገብ ። ፲፫ ፈቃድን ስለማገድ ወይም ስለመሠረዝ የዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፯ ( ፪ ) እና ( ፫ ) እንደተጠበቀ ሆኖ ፣ | አግባብ ያለው ባለሥልጣን በሚከተሉት ሁኔታዎች ፈቃድን ሊያግድ ወይም ሊሠርዝ ይችላል ፡ ገጽ ጎበኘቷ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፰ የካቲት ፳፮ ቀን ፲፱፻፶ ዓም Federal Negarit Gazeta – No . 28 5 March , 1998 - ~ Page 718 እ ፈቃዱበተሳሳተ መረጃ ላይ ተመሥርቶለግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲው የተሰጠ ሆኖ ሲገኝ የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲው ወይም ወኪሉ ከሠራተኛ በዓይነትም ሆነ በገንዘብ ክፍያ ተቀብሎ ሲገኝ ፫ የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲው ሌሎች የአዋጁን ድንጋጌዎች ወይም አዋጁን መሠረት አድርገው የወጡ ደንቦችና መመሪያዎች እንዲሁም ሌሎች ሕጎችን ተላልፎ ፲፩ ስለዋስትና ገንዘብ አስፈላጊነት ፩ . በዚህ አዋጅ መሠረትሠራተኛን ወደ ውጭ አገር ለሥራ የሚልክ ማንኛውም የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ | 14 . Requirement of Guarantee ኤጀንሲ ለሠራተኛው መብት ዋስትና ማስከበሪያ የሚውል ከዚህ በታች የተመለከተውን የገንዘብ መጠን በጥሬ ወይም ከታወቀ የገንዘብ ድርጅት የተረጋገጠና የማይሻር ተመጣጣኝ የዋስትና ወረቀት ማስቀመጥ ይኖርበታል ። ሀ ) እስከ አምስት መቶ ለሚደርሱ ሠራተኞች 6 ሺ የአሜሪካን ዶላር ወይም ተመጣጣኙን የኢትዮጵያ ከአምስት መቶ አንድ እስከ አንድ ሺህ ለሚደርሱ ሠራተኞች ፵ ሺ የአሜሪካን ዶላር ወይም ተመጣ ጣኙን የኢትዮጵያ ብር ፡ ሐ ) ከአንድ ሺህ አንድ በላይ ሠራተኞች ፲ ሺህ የአሜሪካን ዶላር ወይም ተመጣጣኙን የኢትዮጵያ ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት ተቀማጭ የሆነው የዋስትና ገንዘብ መጠን ለሠራተኛው መብት ዋስትና ማስከበሪያ ከዋለ ወይም ተቀናሽ ከሆነ የግል ሥራና ሠራተኛአገናኝኤጀንሲው የዋስትናውን ገንዘብ በአሥር ቀን ጊዜ ውስጥ ማሟላት ይኖርበታል ። ፫• ከሠራተኛው መብትና ጥቅም ጋር የተያያዘ ጥያቄ ሥልጣን በተሰጠው አካል በመታየት ላይ ካልሆነ በስተቀር ሚኒስቴሩ ዋስትናውን የሚለቀው በግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲው አማካኝነት ለሥራ የወጡ ሠራተኞች የሥራ ውላቸው ተቋርጦ ሕጋዊ መብታቸው መከበሩ በተረጋገጠ በ፫ ወር ይሆናል ። ፲፭ የሠራተኛውን መብት ስለመጠበቅ ፩ . በዚህ አዋጅ መሠረት ሠራተኛን ወደውጭ አገር ለሥራ በሚልክ የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲና | 15 . Protection of the Worker ' s Right በሠራተኛው መካከል የሚደረግ የሥራ ውል ቢያንስ በኢትዮጵያ ሕግ የተመለከቱትን መሠረታዊ የሥራ ሁኔታዎች ለሠራተኛው የሚያስጠብቅ ሆኖ በማና ቸውም ሁኔታ ለኢትዮጵያዊው ሠራተኛ በተመሳሳይ የሥራ ዓይነትና ደረጃ ላይ ከሚገኙ አገልግሉቱ ከሚሰ ጥበት ሀገር ሠራተኞች ያነሰ መብት ወይም ጥቅም የሚሰጥ አይሆንም ። ፪• የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲው በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ከተመለከቱት መብትና ጥቅሞች በተጨማሪ የሠራተኛው መብት ደህንነትና ክብር መጠበቁን የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት ። ፲ : ስለቁጥጥር ፩ አግባብ ያለው ባለሥልጣን በማናቸውም የሥራ ሰዓት በቅድሚያ ሳያሳውቅ በማንኛውም የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ቢሮ ለመግባት ፡ አግባብነት ያላቸው ሠነዶችን ለመመርመር ወይም ጥያቄ ለማቅረብ ይችላል ። ገጽ የገሀ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፯ የካቲት ፳፮ ቀን ፲ህየን ዓም . Federal Negarit Gazeta – No . 28 5 March , 1998 - ~ Page 719 ፪ . በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፪ ( ፩ ) ( ለ ) የተመለከተውን አገል | 2 ) The competent authority shall be responsible fo ግሎት የሚሰጥ ኤጀንሲ ጊዜው ከማለቁ በፊት የተሰ | ጠውን ፈቃደ ሲመልስ ለሥራ ያሰማራው ሠራተኛ መብቱ እንዳይጓደል ኣግባብ ያለው ባለሥልጣን ቁጥጥርና ክትትል የማድረግ ኃላፊነት አለበት ። ፲፯ ስለተጠያቂነት በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፪ ( ፩ ) ( ለ ) የተመለከተውን አገልግሎት ለመስጠት ከሠራተኛው ጋር የተደረገ የሥራ ውል ቢጣስ የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲውና ሦስተኛው ሰው ለሠራተኛው መብት በጋራ እና በተናጠል ተጠያቂ ወይም ኃላፊ ይሆናሉ ። | በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ የበለጠ ቅጣት የሚያስቀጣ ካልሆነ በስተቀር ማንኛውም ሰው ፡ ፩ . በዚህ አዋጅ መሠረት ፈቃድ ሳያወጣ ፡ ሀ ) በኢትዮጵያ ውስጥ ሥራና ሠራተኛን ያገናኘ እንደሆነ ከሦስት ዓመት ባላነሰ ከአምስት ዓመት ባልበለጠ እሥራትና ብር ፲ ሺ ( አሥር ሺህ ብር ) መቀጫ ይቀጣል ። ለ ) ኢትዮጵያዊ ዜጋን ለሥራ ወደ ውጭ አገር የላከ እንደሆነ ከአም ! ዓመት ባላነሰ ከአሥር ዓመት ባልበለጠ እስራትና ብር ፳፭ ሺ ( ሃያ አምስት ሺህ ብር ) መቀጫ ይቀጣል ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ከተመለከተው ውጭ ይህን አዋጅና በዚህ አዋጅ መሠረት የወጣውን ደንብ ወይም መመሪያ ተላልፎ የተገኘ እንደሆነ ፡ በዚህ ኣዋጅ በአንቀጽ ፲፫ የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ እስከ ሁለት ዓመት በሚደርስ እስራት ወይም እስከ ብር ፲ ሺ ( አሥር ሺህ ብር ) መቀጫ ይቀጣል ። ወደውጭ አገር ለሥራ የተላከው ኢትዮጵያዊ ሰብአዊ መብ . ኣካላዊ ደህንነቱ ፡ ላይ ጉዳት የደረሰበት እንደሆነ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ( ለ ) የተመለ ከተው ቅጣት ከ፭ እስከ ፳ ዓመት ጽኑ እስራትና እስከ | ብር ፶ ሺ ( ሃምሣ ሺህ ብር ) መቀጮ ሊደርስ ይችላል ። ፲፱ : ስለፈቃድ : ክፍያ በዚህ አዋጅ መሠረት ለሚሰጥ ፈቃድ የሚጠየቅ ክፍያ በሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚወጣ ደንብ ይወሰናል ። የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር ፵፪ iሀየዝሯ አንቀጽ ፩የሮጌ ተሽሮ በሚከተለው አዲስ አንቀጽ ፩የሮጌ ተተክቷል ፡ “ ኔየሮጌ ክልከላ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ከሠራተኛ ገንዘብ በማስ ከፈል ሥራና ሠራተኛን የማገናኘት ተግባር ሊያከናውን አይችልም ። ” ፳፩ መመሪያ የማውጣት ሥልጣን ሚኒስትሩ ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም ኣስፈላጊውን መመሪያ ሊያወጣ ይችላል ። ፳፪• አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከየካቲት ፳፮ ቀን ፲፱የኝ ዓም ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ የካቲት ፳፮ ቀን ፲፱የን ዓም ዶ ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ